Quantcast
Channel: admin – Medrek
Viewing all 3686 articles
Browse latest View live

የህወሓት ኮማንድ ፓስት ወታደራዊ ዕዝ በቋራ ህዝብ ላይ ቤታቸውን በማፍረስ የበቀል እርምጃውን ቀጥሏል!!

$
0
0

ደም መላሽ ተገኘ

በቋራ በረሃ ለነፃነት የሚዋደቁ ትጥቅ አንስተው የሞት ሽረት ትግል ላይ ያሉ አርበኞች ከዚህ ቀደም ያላቸውን ለም መሬት እንዳይታረስ በመከልከልና በኢንቨስትመንት ስም እየተቀሙ ለህወሓት ባለሀብቶችና ባለስልጣናት ቤተሰቦች ሲሰጥ የነበረ ሲሆን ከሰሞኑ ካለፍነው ግንቦት ወር ጀምሮ ደግሞ በቋራ ወረዳ ገለጉ ከተማ የሚገኝ የመኖሪያ ቤታቸውን በህገወጥነት ስም እያፈረሱባቸው ቤተሰቦቻቸው በክረምቱ ያለመጠለያ እያስቀሩ እየተበተኑ ይገኛል።በከተማው እስካሁን ከ200 ቤቶች በላይ በህገወጥነት ስም የፈረሱ ሲሆን ብዙወች ወጣቶች በዚህ የበቀል በትር ተማረው ወደ ጫካ ገብተዋል።

መቀመጫውን በ1990 ዓ.ም እንደከተማ በተመሰረተችው ገለጉ ከተማ ያደረገው የቋራ ወረዳ ወታደራዊ ዕዝ ኮማንድ ፖስት በኮነኔል ገብረ መስቀል ፀጋየ እየተመራ ከዚህ በፊት በማስመሰያ የምህረት እርቀ ሰላም በካድሬ ቄሶች አማካኝነት ትጥቅ ለማስፈታት፣ ቤተሰቦቻቸውን በማስገደድ እጂ እንዲሰጡ ለማድረግ ሲጥር የነበረው ሲሆን ይህ ሁሉ እንዳሰበው አልሳካ ሲለው እና በየጊዜው የሚደርስበት የደፈጣ ውጊያ መቋቋም ሲያቅተው በአጎራባች የሱዳን ዞን ወታደራዊ አመራሮችን በመሰብሰብ የነፃነት ታጋዩችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር በሱዳን ከዲንደር ዞን የተውጣጣ ወታደራዊ አመራሮች በኮነኔል ገብረ መስቀል ፀጋየ ከሚመራው የህወሓት የቋራ ኮማንድ ፖስት ወታደራዊ ዕዝ ጋር በሱዳን ” የዲንደር ፓርክ ” እና በአማራ ቋራ ” አላጥሽ ” ፓርክ በሰፊው ምድር የሚንቀሳቀሱ የነፃነት ሃይሎችን ለመቆጣጠር የሱዳን ባለሃብቶች ከቋራ ገበሬ ተነጥቆ በወያኔ በተሰጣቸው መሬት በዘለቄታ እንዴት ማረስ እንደሚችሉ ከነፃነት ሃይሎች የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል በመረጃ ልውውጥ ለመስራት በገለጉ ከተማ ተገናኝተው ቢመክሩም ምንም ውጤት ሲያመጣ አልታየም።ይልቁስ የነፃነት ትግሉ አድማሱን እያሰፋ እየተቀጣጠለ ያለበት ሁኔታ በጉልህ ታይቷል።

የህወሓት ኮማንድ ፖስት የነፃነት ሃይሎች የጉሬላ የተጠና ወታደራዊ ጥቃት ለመቆጣጠር ባለመቻሉ ይህንና መሰል የተለያዩ የበቀል እርምጃወችን እየወሰደ ይገኛል። የነፃነት ትግሉን ለመቀላቀል በመምሰል ከነሙሉ ትጥቃቸው ያዘመታቸው ወታደሮች የነፃነት ሃይሎችን ለማጥቃት ከሰሞኑ የጠነሰሰው እቅድ ቀድሞ መረጃው በደረሳቸው የነፃነት ሃይሎች ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፉ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ እና ሴራው መክሸፉ ከኪሳራ ላይ ኪሳራን ደርቦበታል።
የነፃነት ትግል ጉዞ በበቀል በትር አይደናቀፍም!!
ድል ለጀግኖቹ !!
@እንቅዩጳዝዩን የአርበኞቹ ልጂ

The post የህወሓት ኮማንድ ፓስት ወታደራዊ ዕዝ በቋራ ህዝብ ላይ ቤታቸውን በማፍረስ የበቀል እርምጃውን ቀጥሏል!! appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


Ethiopia: Eid Al-Fitr an Iconic Expression of Social Bond – AllAfrica.com

$
0
0

Muslims across Ethiopia marked the end of the holy month of Ramadan last Sunday, breaking a month of fasting. Known as the “Haven of the First Migration or Hijra” by Islamic history and tradition, Ethiopia marked the holiday with the Muslim community celebrating with friends and family, as well as among followers of other religions, and displaying acts of faith and brotherly love.

Ethiopia has an age-long history of accommodating people of various religions. Following the early years of great persecution of Islam in 614 CE in Mecca from the Quraysh, the Prophet Muhammad sent his followers to the land of Abyssinia in order to escape the persecution. The journey of these early Muslims ended when they settled in Abyssinia at the present place called Al-Negash, in Eastern Tigrai State. This journey, which is referred as the first Hijra, is a living monument of the religious plurality and mutual coexistence.

Since the first Hijra that was manifested by welcoming the companions of Prophet Mohammed and allowing them to practice their religion free from persecution, Islam became an integral part of the long Ethiopian history.

This made Ethiopia the first country in the world to allow Muslims to practice their religion even before Saudi Arabia. That was why Prophet Mohammed ordered his followers not to touch the Abyssinians except in self-defense. Followers of Prophet Mohammed have also a remarkable history of peaceful co-existence with their non-Muslim brothers and sisters while religious conflicts continue around the globe.

Eid al-Fitr (festival of the breaking of the fast) is among one of the major festivities celebrated by Muslims worldwide to mark the end of the fasting month of Ramadan. The faithful begin the day by traveling to a pray known as Salat al-Eid that have been always performed in congregation in big mosques, open fields or large halls.

The religion teaches the faithful to observe Eid al-Fitir by maintaining support to the needy and urging them the good deeds that have been exercised during Ramadan to be internalized into their personality and in their day to day lives.

President of Islamic Affairs Supreme Council Sheikh Mohammed-Amin Jamal Omar said the teaching to communal observance of Eid would have a big role in enhancing peoples’ interaction with different economic and religious backgrounds.

He said: “It is a customary practice in Ethiopia to observe Eid by calling families, relatives and neighbors as well as the needy, regardless of their economic status and religious affiliations. Eid ceremonies enables the participants to exchange views about their livelihood and thus bolster their understating about values each religion attaches to, and to enable them live in harmony and appreciate and respect their differences.”

According to Sheikh Mohammed, the religion orders the faithful to uphold the support and empathy they have shown for the needy during Ramadan, which also would have a role in strengthening the much cherished Ethiopian culture of sharing with the disfavored and sharing bread with all walks of life.

On Eid, Muslims are expected to solace and support people that are in various difficult situations, including in grief, in jail, orphans, the sick and those who do not have access to food, clothes and other amenities and sharing what they have with the needy to enable them celebrate the day in same manner.

Sheikh Mohammed said: “Prophet Muhammad made Zakat al-Fitr (charity given to the poor at the end of the Islamic holy month of Ramadan) on every Muslim whether young and or male or female to enable the needy to celebrate the holiday along with themselves.”

The head of the household may pay the required amount for his/ her dependencies and go into the community in order to find those who deserve such charity. In this regard, Zakat al-Fitr plays a very important role in the development of the bonds of community since the rich are obliged to come in direct contact with the poor, and the poor are put in contact with the extremely poor.

This contact between the various levels of society helps to build real bonds of brotherhood and sisterhood within the Islamic community and trains those who have, to be generous to those who do not have.

Sheikh Mohammed noted that charities such as Zakat al-Fitr are the manifestation of the faithful’s brotherhood regardless of geographic, linguistic or ethnic differences.

Following the situation in Saudi Arabia, many Ethiopians face mass deportation in which the participation of all sector of the society is essential in the repatriation process.

Sheikh Mohammed said the Muslim community need to show empathy and compassion for the returnees and play its own role in the reintegration efforts by providing them with the necessary financial and non-financial support and offering moral support.

Strong social bonds among Muslims one another and with their fellow non-Muslim brothers and sisters is so essential in a country like Ethiopia where people with different faiths live together.

The social bonds enable people, regardless of religious affiliations, stand together to work the country’s vision of bring economic development and build democracy while defend its interests.

Sheikh Mohammed said; “Muslims need to maintain their culture of observing events such as Eid al-Fitr in the way enhancing harmony and understand with their fellow non-Muslim brothers and sisters. This would in turn enable Ethiopia to achieve its vision of building peace and economy through active participation of people with different religious backgrounds.”

Furthermore, the understating among people with different religions would play an indispensable role to support the nation’s engagement to build the democratic system and ensure the constitutionally-granted citizens’ rights.

Closeness among Muslims and non-Muslims in events such as Eid al-Fitr would also have a great role to fight the destructive activities of some radicalized interest groups such as Wahhabism.

Wahhabism, an ultra-conservative brand of Islam, targets to disrupts the long cherished religious coexistence in Ethiopia and try to instigate conflicts among people with different religions.

Those groups try to instigate Ethiopia’s moderate Muslim, especially the youth to have radicalized viewpoint and wage unnecessary jihad against their brothers and sisters.

Cognizant to the groups’ interest to not only disrupt the peaceful balance that exist between religions, but also destabilize Ethiopia’s long peace and stability, due attention need to be given to the society, especially the youth, not to be hijacked by their destructive propaganda.

In this regard, various festivities such as Eid al-Fitr have indispensable role in keeping people with different faiths live in harmony and shun away hatred and stereotypical attitude towards people with particular religious’ affiliation.

By understating the closeness and unity created by events such as Eid al-Fitr and to sustain the longstanding religious tolerance that exists in Ethiopia, in contrast to the much turbulent Middle East region, due attention is needed to keep this culture remains for long time to come.

የማለዳ ወግ… ይድረስ ለሚመለከታችሁ ባለስልጣናት – ነቢዩ ሲራክ

$
0
0
* ለአንባሳደር አሚንና ለአንባሳደር ውብሸት ባላችሁበት
* ቅጅ /ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ወርቅነህ ገበየሁ
     
መረጃን ማቀበሌ ወንጀል ሆኖ ” የነቢዩ ሲራክ ልጆች ከሚማሩበት የጅዳ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት እንዲታገዱ ” የሚለው የካድሬዎች ሀሳብ ያን ሰሞን ቀርቦ እንደነበር በድጋሜ በማረጋገጤ አዝኘ ነበር ያደርኩት ።  … ስለ እውነት ለመናገር ፣ ስለ እውነት እየተገፉ መኖር ግድ ይላል ብዬ የሚሰራው ባይደንቀኝም በዘመነ ኦሪት እንኳ ባልታዬ ህግ ልጆች በአባታቸው ” ወንጀል ” ስማቸው ሲጠራ መስማት ልቤን በሀዘን ሰብሮት አድሯል  🙁 እናም ሁሉንም ለመርሳት ልጆቸን እረፍት ወደ ማይሰማ ወደ ማይናገረው ቀይ ባህር ይዣቸው ዘና ልበል ብዬ ማልጀ ስነሳ ሌላ አሳዛኝ መረጃ ደረሰኝ ። መረጃው እንዲደርሰኝ ያደረገው ደግሞ አንድ አደር ባይ ወዳጄ ነበር ፣ ወዳጄን እኔን ያመመኝ አሞት ስለማያውቅ የዜጎች ጉዳይ አግብቶኝ የተገፊውን ድምጽ ሳሰማ ” ሥራ ፈት ነህ  !” እያለ ያላግጥብኝ ነበር። ዛሬ ግን የራሱ የሆነች እህት በሪያድ አየር መንገድ ለቀናት በደረሰባት እንግልት ተደናግጦ” አገር ይያዝ” ጩኸት አሰማኝ  ። ቀጠለና ዜጎች እየተሰቃዩ ነው የታላችሁ በማለት ከጅዳ ቆንስል እስከ ሪያድ ኢንባሲ ሹም ወዳጆቹን ጨምሮ መረጃውን እኔው ጋር አድርሶታልና አዘንኩ … ደጋግሞ ሲደውልልኝና መረጃ ሲሰጠኝ ዝም ብየ ሰማሁትና ለመሆኑ እኔ ስናገር ሥራ ፈት እያልክ  አልነበር?  ዛሬ ችግሩ በዘመድህ መጥቶ መናገር መናደድ ጀመርክ?   እስከ አሁንስ የት ነበርክ ? ማለቴ አልቀርም ። እሱ ግን አፈረ ፣ እኔም  ያፈረውን አድርባይ  ወዳጄን መጎሻሸሙን አልወደድኩትም …በወዳጄ ዛሬ መቆርቆር አላዘንኩም የሰጠኝን መረጃ ተከትዬ ያሰባሰብኩት እውነት ግን በእርግጥም ያስከፋል ። ይህን መልዕክት እንድጽፍ ላችሁ ያነሳሳኝ ጉዳይም ይኸው የደረሰኝ መረጃ ነው ።
  ላለፉት ሶስት ወራት ሌት ተቀን ግሩም በሆነ ዝግጅት የከረመው የኢንባሲና የቆንስል መረጃ ቅበላ በመቋረጡ የተከተለውን ውዥንብር እንደ ዜጋ ታዝቤያለሁ ። የኢንባሲና የቆንስል መረጃ ቅበላ በማቆሙም ቦታውን ባልተካም በመረጃ እጦት ስደተኛው እንዳይንገላታ ባሳለፍናቸው ሁለት ሳምንታት የምችለው ለማድረግ ሞክሬያለሁ ። አሁንም የምቀጥለው በዚሁ መንፈስ ነው  … የኢንባሲና የቆንስል ለመረጃ የተዘጋው በር ከተከፈተ እኔ ብዙም ላይክና ሸር ፈላጌ ዝር ላልል ቃል ልግባላችሁ  ! ብቻ ለዜጋው መረጃ ያስፈልገዋልና የተዘጋውን በር ክፈቱለት ለማለት  ለመማጸንና ለመምከርም ጭምር ነው ።
   በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ችግር በጅዳና በሪያድ አየር መንገዶች እየተንገላታ ያለው ሰው ለቅሶ ዛሬም ደርሶኛል ። በምህረት አዋጁ መራዘም ዙሪያ በሚናፈሰው መረጃ ለሚዋልለው ዜጋ እያደረጋችሁ ያለውን ጥረትና እውነቱን አስረዱት ።  ”  የምህረቱ ጊዜ አብቅቷል !” ተብሎ በሳውዲ ፖስፖርት ፖሊሶች እንዳይሳፈሩ መመለስ ስለመጀመሩ ጉዳይ ግልጽ መረጃ ከእናንተ ይጠበቃል ።  ከቀናት በፊት በጀዛን ትናንት ደግሞ በጅዳ አንዳንድ ተመላሾች ” የምህረቱ ጊዜ አብቅቷል !” ተብለው በፖስፖርት ፖሊሶች እንዳይሳፈሩ ተከልክለው እንደነበር ከጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች በግል መረጃውን አረጋግጫለሁ። በዚህና በዚያ  በተለያዬ አቅጣጫ የሚሰማው መረጃ ብዙዎችን ግራ እያጋባ ይገኛል ።
     በሚሰራጩት መረጃዎች ፣ እየተደረገ ስላለው ጥረትና  ተዛማጅ የተመላሽ ዜጎች ጉዳይ በሳውዲ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች በምህረት አዋጁ ወቅት ያደርጉት እንደነበረው ሳያቋርጡ መረጃን ሊሰጡ ይገባል የሚለው የብዙ ወዳጅ ተከታዮቸ መልዕክት ነው ። በእርግጥም ወቅታዊ መረጃን ሲሰጡ ከርሞ አሁን በወሳኙ ጊዜ ማቋረጥ  በመቶ ሽዎች የሚቆጠር ዜጋ ብቻ ሳይሆን በመላ አለም ያለው ሚሊዮን ሀገር ወዳድ እንዳይረጋጋ ያደርጋል ። በውል የተጠና የመረጃ ቅበላው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል። በሪያድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ እና የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በወሳኙ ጊዜ ያቋረጣችሁትን የመረጃ ቅበላ ትቀጥሉ ዘንድ እመክራለሁ  !  በየአየር ማረፊያዎች ቀንና ማታ ቀርቶ ለሰአታት መቋቋም በሚከብደው ደረቅ ሀሩር ጸሃይ ሙቀት እየተለበለበ ያለው ወገን ያለበትን ሁኔታ መከታተልና መደገፍ ፣  መረጃ ፣ ማብራሪያ በሉት ምክር ካስፈለገ በቦታው እየተገኙ መስጠት ተገቢ ነው እላለሁ !
  ይህን ምክር እንድጽፍ ያነሳሳኝ መታበይ እንዳይመስላችሁ ። በቂ ምክንያት አለኝ  ” ላለፉት ሶስት ቀናትበሪያድ አየር መንገድ አውላላ ሜዳ ላይ ተሰቃየን ” በሚል የሚደርሱኝ መረጃዎች እጅግ  ውስጥን ይረብሻሉ  🙁  እናንተም በዚህ ዙሪያ ምንም አይነት ወቅታዊ መረጃ ስለማታቀርቡ በእንግልት ላይ ያሉ ዜጎች  የመረጃ እጦት ሌላ ፈተና እንደሆነባቸው መረዳት ችያለሁ ! እባካችሁ ዜጎች መረጃን  ከእናንተ ከህዝብና መንግስት አገልጋዮች የማግኘት መብታቸውን አለንና እሱኑ መብት አክብሩልን   !
የግርጌ ማስታወሻ
====∞===== = ለወዳጆቸና ለተካታታዮቸ ፣ ይህ መልዕክት ለኃላፊዎች እንዲደርስ Share እና Like ማደረጋችሁን አትዘንጉ ፣ ሁላችንም  ስለተገፉት ዜጎች ድምጽ መሰማትና መፍትሔ ማግኘት መትጋት ግድ ይለናል  !
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 21 ቀን 2009 ዓም

The post የማለዳ ወግ… ይድረስ ለሚመለከታችሁ ባለስልጣናት – ነቢዩ ሲራክ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የኦሮሚያን የአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀደቀ

$
0
0

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀስ 5 ላይ ‹‹የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል የምትገኝ በመሆኗ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፤›› በማለት ተደንግጎ ይገኛል፡፡

‹‹የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ልዩ ጥቅም በሕገ መንግሥቱ እንዲሰፍር ያደረጉት የኦሮሞን ሕዝብ ጨምሮ መላው የአገራችን ሕዝቦች ናቸው፡፡ የመረጡት የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የፌዴራል መንግሥትና የክልሎች መንግሥታት እንደሚኖሩ የሚደነግግ በመሆኑ፣ የፌዴራል መንግሥቱ መቀመጫ የሆነች ከተማ መመረጥ ስለነበረበትም የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ መላው የአገራችን ሕዝቦች በኦሮሚያ ክልል እንብርት ላይ ያለችውን አዲስ አበባ ከተማን የፌዴራሉ መንግሥት መቀመጫ አድርጎ መርጠዋታል፡፡ ይህም በሕገ መንግሥቱ እንዲሰፍር አድርገዋል፤›› ያለው ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. የወጣውና በኢሕአዴግ ይፋዊ የፌስቡክ ድረ ገጽ ላይ የታተመው መግለጫ፣ ይህንን ጉዳይ በዝርዝር ሕግ መመለስ የሚያስፈልግ በመሆኑ የሕገ መንግሥቱን መንፈስ ተከትሎ ዝርዝሩ እንዲሠራ መደረጉን ያመለክታል፡፡

ዝርዝሩን ለመሥራት ግብዓት እንዲሆን በክልሉ ገዥ ፓርቲ ኦሕዴድና በኦሮሚያ ክልል፣ በአዲስ አበባ አስተዳደርና በፌዴራል ደረጃ ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተው በመጨረሻ በኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ በዝርዝር ታይቶ የመንግሥት ሕጋዊ ተቋማት መክረውባቸው ሕግ ሆኖ እንዲወጣ ስምምነት ላይ መደረሱን መግለጫው አመልክቷል፡፡

በዚህም መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በረቂቅ አዋጁ ላይ በመወያየት የተወሰኑ ጉዳዮችን ተመልክቶ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክሮበት ሕግ ሆኖ እንዲወጣ ውሳኔ ማሳለፉም ተገልጿል፡፡ እነዚህም ሦስት ጉዳዮች ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 5 ያስቀመጣቸው ማለትም 1ኛ/ ከአገልግሎት አቅርቦት ልዩ ጥቅም አኳያ፣ 2ኛ/ ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና የአካባቢ ጥበቃ ጋር የተያያዙ ልዩ ጥቅሞች አኳያ፣ 3ኛ/ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል የምትገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳሰሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ማዕከል በማድረግ የኦሮሚያ ክልል ያለው ልዩ ጥቅምን ማስጠበቅ ሲሆኑ፣ ይህን ለማሳካት የሚያስችሉ አንቀጾች እንዲቀረፁና እንዲካተቱ መደረጉን አስገንዝቧል፡፡

መግለጫው ስለአዲስ አበባ ሲናገር፣ ‹‹በኦሮሚያ ክልል እምብርት ላይ የምትገኝ ከኒዮርክና ከጄኔቫ ቀጥላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሦስተኛ ማዕከል የሆነች፣ የአፍሪካውያን የፖለቲካና ዲፕሎማሲ መዲና የሆነች . . . የፌዴራል መንግሥቱ መቀመጫና ሕገ መንግሥቱ ከመፅደቁ በፊት በሽግግር ወቅትም የክልል 4 ዋና መዲና፣ እንዲሁም ሕገ መንግሥቱ ከፀደቀም በኋላ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ ሆና እየገለገለች ያለች ናት፤›› ብሏል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ልዩ ጥቅም እንዲጠበቅ የሚወጣው ሕግም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪያዎችን መብቶችና ጠቅሞች በምንም መልኩ የማይሸራርፍ፣ ይልቁንም የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለው ልዩ ጥቅም በመጠበቁ ምክንያት የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕዝብና የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ ትስስርና መስተጋብር ይበልጥ ሕጋዊ መስመር ይዞ እንዲጠናከር የሚያደርግና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት እንደሚሆን መግለጫው አትቷል፡፡

በመግለጫው በረቂቅ አዋጁ የሚካተቱ የአገልግሎት አቅርቦት ጉዳዮች ተካተዋል፡፡  ከእነዚህም መካከል ከትምህርት አኳያ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የአርሶ አደሩ ልጆችን እንዲሁም አዲስ አበባ ወይም ፊንፊኔ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ በመሆኗ ምክንያት ልጆቻቸው በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር ለሚፈልጉ ዜጎች የከተማ አስተዳደሩ በአፋን ኦሮሞ፣ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ማደራጀት እንዳለበት መቀመጡን ጠቅሷል፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ያለው የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ አብዛኛውን አገልግሎቱን በተለይም የሆስፒታል አገልግሎቶችን ከከተማዋ የሚያገኝ በመሆኑ፣ አዲስ አበባ ይህንን አገልግሎት ለመስጠት በዕቅዷ ውስጥ ማካተት እንደሚኖርባትም ይገልጻል፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ የአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን እንዲሆን መደረጉንም አስታውሷል፡፡ በዚህ አዋጅ መሠረት የአገልግሎት ተጠቃሚ ለሆኑት የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች በቋንቋቸው አገልግሎቱ እንዲቀርብ ከአማርኛ በተጓዳኝ አፋን ኦሮሞ በከተማ አስተዳደሩ የሥራ ቋንቋ ሆኖ እንደሚያገልግልም ተመልክቷል፡፡

ከተማዋ ዓለም አቀፍና አኅጉራዊ፣ እንዲሁም አገራዊና የከተማ ነዋሪዎችን ለማገልገል ከምታደርገው ጥረት ባሻገር የኦሮሞ ሕዝብ ማንነት የሚያንፀባርቁ አሻራዎች በከተማዋ ውስጥ በቋሚነት እንዲኖር ከክልሉ ሕዝብ ጋር በተያያዙ ታሪካዊ ክስተቶች ስም መታሰቢያዎች እንዲኖሩ አመቺ የሆኑ እንደ አደባባዮች፣ ጎዳናዎች፣ ሠፈሮችና የመሳሰሉት ቦታዎች እንዳስፈላጊነቱ በቀድሞ የኦሮሞ ስማቸው እንዲጠሩ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም የከተማዋ አስተዳደር የኦሮሞ ሕዝብ ባህልና ታሪክ የሚያንፀባርቁ የባህልና ታሪክ ማዕከላት፣ የቴአትር፣ የኪነ ጥበባትና የመዝናኛ ማዕከላት የሚነገቡበትንና የሚተዋወቁበትን ሁኔታዎች እንደሚመቻችም ተመልክቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የከተማዋ መጠሪያዎች ‹‹ፊንፊኔ›› እና ‹‹አዲስ አበባ›› በሕግ ፊት እኩል ዕውቅና እንደሚኖራቸውም ተገልጿል፡፡ መሠረታዊ ነገሩን የሚቀይር ባይሆንም የስሞቹን አጠቃቀም ዝርዝር በደንብ እንደሚወሰንም አስቀምጧል፡፡ አርሶ አደሩ ለልማት ተነሺ ሲሆን፣ በቂ ካሳ የማግኘትና በዘላቂነት የማቋቋም አገልግሎቶችን እንዲያገኝ እንደሚደረግም አመልክቷል፡፡ አርሶ አደሩ በልማቱ ማስፋፋት ምክንያት ተጎጂ ሊሆን በጭራሽ ስለማይገባ ለወደፊቱ በቂ ካሳና በዘላቂነት የሚቋቋምበት ሁኔታ እንዲመቻችለት፣ ከዚህ በፊት የተሠራውም ሥራ ተፈትሾ ጉድለቶች እንዲስተካከሉ፣ እነዚህን ሥራዎች የሚያስተባብር የሚመራና የሚያስፈጽም ጽሕፈት ቤት እንዲደራጅ በአዋጁ እንዲካተት መደረጉን አመልክቷል፡፡ ነገር ግን መግለጫው በአዲስ አበባ ነዋሪ ዜጎች ላይ በብሔር ልዩነት ምክንያት የተለየ ጥቅም እንደማይቀርብ ግንዛቤ ሊያዝበት እንደሚገባ ያሰምርበታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጠጥ ውኃ የሚያገኘው በአብዛኛው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር መገኛዎች በመሆኑ፣ ከዚህ አኳያ ጉድጓዱ የሚቆፈርበት፣ ግድብ የሚለማበት ወይም የውኃ መስመሩ አቋርጠው የሚያልፍባቸው የክልሉ ከተሞችኛና ቀበሌዎች በአስተዳደሩ ወጪ የመጠጥ ውኃ ተጠቃሚ  እንዲሆኑ እንደሚደረግም ተቀምጧል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከባንኮች ጋር በመተባበር የማኅበራዊ ቤቶች የሆኑትን የኮንደሚኒየም ቤቶች አስገንብቶ ከእነዚህ ውስጥ በከተማው ላሉ የመንግሥት ሠራተኞትና ሴቶች በኮታ በዕጣ ውስጥ ገብተው እንዲወዳደሩ እንደሚደረግ ያስታወሰው መግለጫው፣ በተመሳሳይ ለኦሮሚያ ክልል መንግሥት ሠራተኛ ሆነው በከተማው ውስጥ ለሚኖሩትም ተመሳሳይ ዕድል እንዲሰጥ በአዋጁ ውስጥ እንዲካተት መደረጉን ገልጿል፡፡

ከከተማው መሠረተ ልማት አቅርቦት፣ ከመጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ ከደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ጋር የተያያዘ በተፈጥሮ ሀብት ላይና በአየርና ውኃ ላይ የሚደርስ ብክለት እንዳይኖር የሚያደርግና ይህንን መብት የማስጠበቅ ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠውም ተገልጿል፡፡

በረቂቅ አዋጁ በአዋጁ ውስጥ የተጠቀሱትንና ሌሎች የጋራ ጉዳዮችን ክልሉና አስተዳደሩ የሚወያዩበትና የሚወስኑበት ተጠሪነቱ ለፌዴራል መንግሥት የሆነ ከአስተደደሩና ከክልሉ ምክር ቤት የተውጣጣ የጋራ ምክር ቤት እንደሚቋቋም ተመልክቷል፡፡ የምክር ቤቱ ዋና ዓላማውም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 49(5) መሠረት የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት፣ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ ከተማ በኦሮሚያ ከልል መሀል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በዚህ አዋጅ የተዘረዘሩትን ልዩ ጥቅሞች በተጨባጭ ተግባራዊ እንዲሆን መከታተል፣ መገምገምና ለአፈጻጸሙ ቅልጥፍና ድጋፍ ማድረግ እንደሚሆን ተቀምጧል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይሁንታን ያገኘው ይኼ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ መመራቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በ ጋዜጣዉ ሪፓርተር

The post የኦሮሚያን የአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀደቀ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ግልፅ ደብዳቤ ለልሳነ ግፉዓን ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች

$
0
0

ጉዳዩ፡ “ልሳነ ግፉዓን ከዚህ ወዴት?”

መቅድም

በቅድሚያ እራሱን “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ድርጅት” እያለ የሚጠራው ወራሪና ተስፋፊ ቡድን የተከዜን ወንዝ ተሻግሮ የጎንደርን ታሪካዊ መሬቶች በሃይል ለመያዝ ከሞከረበት ጊዜ ጀምሮ በሚቻላችሁ ሁሉ በመቃወም ውድ ህይወታችሁን ለሰዋችሁ፣ ወርቃማውን የወጣትነትና የጎልማሳነት ዘመናችሁን በእስር፣ በስቃይና፣ በስደት ለማሳለፍ የተገደዳችሁ፣ ትዳራችሁንና ህፃናት ልጆቻችሁን ያለ አባትና አሳዳጊ ለመተው የተፈረደባችሁ፣ አዛውንትና ደካማ ወላጆቻችሁን ያለጧሪ ለቀሩባችሁ፣ ይልቁንም የፈራችሁት መከራና ጥፍት በወልቃይት፣ በጠገዴና፣ በጠለምት ማህበረስብ ላይ ደርሶ፤ የቀደሙት አባቶቻችሁ እርስት የትግሬ ሰፋሪ መፈንጫና መገልሞቻ ሆኖ ባያችሁ ጊዜ ሞትን መርጣችሁ በዱር በገደሉ ለምትዋደቁ፣ በየማሰቃያው ስፍራ መራር ግፍና መከራ ለምትቀበሉ፣ በያላችሁበት ሆናችሁ ጠላትን ለማንበርከክ የአቅማችሁን ለምታደርጉ ሁሉ ምንም እንኳ ትግሉ መራር ቢሆንም መስዋዕትነታችሁና ድካማችሁ ፍሬ አፍርቶ የወልቃይት ጥያቄ የተነሳችሁለትን ግብ ሳይመታ ላይቀለበስ ትውልድ ላይ ታትሟልና በሰማይም ሆነ በምድር ደስ ይበላችሁ።      

በማስቀጠልም ከቀደሙት ጀግኖቻችን የተረከባችሁትን የህልውና ትግል ለጠላት ባደሩ ተንበርካኪዎችና ተላላኪዎች ሳይበረዝና ሳይከለስ  ጠብቃችሁ፣ ተቋማዊ ቅርፅ በማስያዝ ድርጅት መስርታችሁ፣ በብዙ እንግልትና መሰናክል ውስጥ አልፋችሁ፣ ከልሳነ ግፉዓን ጋር በይፋ መስራት እስከ ጀመርኩብት ጊዜ ድረስ የድርጅቱን ህልውና፣ ጥራትና፣ ብቃት በአስተማማኝ ሁኔታ ጠብቃችሁ ላቆያችሁኝ የልሳነ ግፉዓን አመራሮችና መስራች አባላት የአክብሮት ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ።

እኔ ወደ ሰሜን አሜሪካን በስደት ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ያመንኩትና በይፋ አብሬው የሰራሁት ድርጀት ቢኖር ልሳነ ግፉዓን ብቻ ነው። ምክንያቱም ልሳነ ግፉዓን የቆመለት አላማና የሚከተለው የትግል ስልት/strategy/፣ የመሪዎቹና የአባላቱ ታማኝነትና፣ ጨዋነት፣ ፋሽስቱንና ተስፋፊውን የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ድርጅት አምርሮ ለመታገል ያላቸው ብቃትና ቁርጠኝነት፣ ይልቁንም ለህወሃት የስለላ መዋቅርና ለተመሳሳይ ሰርጎ ገቦች በፍፁም የማይከፈትና ለዘለዓለሙ የተዘጋ የምስጢር አጠባብቅ ዘዴ ባለቤት መሆናቸው ሁሌም ያረካኛል።

በአለፉት 7 አመታት (2010 መጨረሻ ጀምሮ) ከልሳነ ግፉዓን ጋር ያደረኩትን የትግል ጉዞና በሂደቱም ያሳለፍኳቸውን ውጣ ውረዶች፣ እንቅልፋ አልባ ሌሊቶችና እረፍት አልባ ቀናት፣ በብዙ ጭንቀትና ሰቀቀን ያገኘናቸውን መረጃዎች፣ በአሜኬላ በተሞላው የህወሃት መንደር ለተልዕኮ የተሰማሩ ወገኖች ያስመዘገቧቸው ድሎች፣ በዚህ ሁሉ ሂደት ያጣጣምናቸውን መራር ሽንፈቶችና ጣፋጭ ድሎች … ወዘተ ሳስብ ልቤ በሃሴትና በቁጭት እኩል ትነድብኛለች። ይህን ስሜት ለእኔ ፍፁም ልዩ ነው! ለዚህም ነው ለልሳነ ግፉዓንና አብሪያቸው ለታገልኩት ጓዶቼ ሁሉ ልዩና እስከመጨረሻው የታመነ ፍቅርና አክብሮት እንዲኖረኝ ያስገደደኝ።

ወደ ልሳነ ግፉዓን ስቀላቀል በእድሜም ሆነ በትግል ልምድ ጎረምሳ ነበርኩ። ዛሬ ከ 7 አምታት በኋላ እራሴን ስገመግምና የመጣሁበትን የህይወት ጎዳና ወደኋላ ስቃኝ ከትላንቱ በብዙ የተለወጥኩ ይመስለኛል። ብዙ ተምሪያለሁ፣ ብዙም አውቂያለሁ። በእግዚአብሄር መልካም ፈቃድ ወደፊት ገና ብዙ እማራለሁ! ብዙ አውቃለሁ! ብዙም እሰራለሁ! ምስጋና በራቸውን ከፍተው በፍቅርና በአክብሮት ተቀብለው ወገኔን ከጥፋት ለመታደግ በሚደረገው የምር ትግል ውስጥ የአቅሜን እንዳበረክትና የድርሻዬን እንድወጣ እድሉን ለሰጡኝ ሁሉ ይሁን።

ዛሬ ላይ ሆነን ወደ ራሳችን ስንመለከት

እኔም ወደ ልሳነ ግፉዓን ከተቀላቀልኩና ትግሉም እዚህ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ብዙዎችን ከጎናችን ማሰለፍ እንደቻልን አውቃለሁ። ብዙዎችም ልሳነ ግፉዓን ባነገባቸው አጀንዳዎች ዙሪያ ተሰልፈው እየተጋደሉ እንደሚገኙ አውቃለሁ። ነገ እልፎች ከጎናችን እንደሚሰልፉ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ይልቁንም በዚህ ሰአት ሌት ከቀን ጎትጉተንና የእኛን ድርጅታዊ አመራር አምኖ ወደ ትግሉ ሜዳ ያስገባነው ወገናችን ከፊትና ከኋላ በመሆን እንደ ከያኒው “… ወደ ኋላ የለም! ወደ ኋላ!” እያለ በፅናትና በቁርጠኝነት ወደ ታላቁ ድል እንድንገሰግስ እየገፋን ያለ ይመስለኛል።

በእኔ እምነት ዛሬ በአለፉት የትግል አመታት የመጣንበትን መንገድ ቆም ብለን የምንገመግምበትና ቀጣዩንም የትግል አቅጣጫ የምንተልምበት ምቹና ትክክለኛ ወቅት ነው ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም ነገ ወደ ድርጅታችን የሚመጣውን የታጋይ ህዝብ ብዛት መሸከም የሚችል ድርጅታዊ መዋቅር መዘርጋትና ከዚሁም ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የህዝብ ፍላጎትና ጥያቄ ማስተናገድና በብቃት መምራት የሚችል ብቁ አመራር መፍጠር የዛሬና በሚቀጥሉት ጥቂት ጊዜያት ውስጥ ከስር ከስር የሚሰራ ተቀዳሚ ስራ እንጂ ነገ በህዝብ ጥያቄ፣ በአባላት ብዛትና፣ በስራ መደራረብ ምክንያት እራሱን በእራሱ አፍኖ የሚገድል ባለተራው ኢትዮጵያዊ ድርጅት እስክንሆን ድረስ መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም። እዚህ ላይ “ሰርገኛ መጣ፣ በርበሬ ቀንጥሱ” የምትለውን የማንቂያ ደወል መጠቀም አይከፍም ።

ዛሬ ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን አንግቦ የተነሳቸውንና የወልቃይት የጠገዴና የጠለምት ህዝብ ሰቆቃና የድረሱለኝ ጥሪ ልሳን መሆን፣ በግፍ ለተነጠቃቸው ሰብአዊ መብቶቹ መከበር ግንባር ቀደም ተሟጋች የመሆን፣ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ አጀንዳዎችና አላማዎቹን በሚያኮራና ታሪካዊ በሆነ ደረጃ አተሳክቷል ብዬ አምናለሁ። በዚህ አጋጣሚ ለመላው አባላቱ እና አመራሮቹ እንኳን ደስ ያላችሁ ማለትን እወዳለሁ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ህዝባዊ ትግሉ ከየአቅጣጫው የቀሰቀሰውና በዙሪያው ያሰለፈው የህዝብ ብዛትና እነዚህ ትግሉን የተቀላቀሉ ወገኖቻችን  ይዘዋቸው የተነሷቸው የግልና የጋራ ብሶቶቻቸውና ጥያቄዎቻቸው ፍትሃዊ ምላሽ እንዲያገኙ አብሮ የመታገልና የማታገል የሞራልም ሆነ የዜግነት ወገናዊና ታሪካዊ ግዴታ አለብን ብዬ አምናለሁ። ስለሆነም ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን ከላይ ያነሳኋቸውንና በመጣጥፌ ውስጥ በዝርዝር የምመለስባቸውን ግዴታዎች ከቆመለት አላማና ራዕይ ጋር በማገናዘብ ዘመኑን የዋጀ ድርጅታዊ የማሻሻያ እርምጃዎች ሊወስድ የሚገባ ይመስለኛል። ዛሬ አሁን በደረስንበት የእድገት እና የአሸናፊነት ልዕልና ላይ ሆነን ስንነጋገር በዋናነት መነሳት ይኖርባቸዋል ከምላቸው አበይት ቁምነገሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ

  1. ልሳነ ግፉዓን ዋና ዋና አላማዎቹ ምን ምን ነበሩ? የትኞቹን አሳክቷል?
  2. የድርጅታችን የስኬት ምስጢሮቹ ምን ምን ናቸው?
  3. ድርጅታችን ከተመሰረተበት ከ2009 ጀምሮ በጉዞው የገጠሙት ፈተናዎች ምን ምን ነበሩ? እንዴትስ አለፋቸው?
  4. የልሳነ ግፉዓን ወደ ፊት የሚጠብቁት ተግዳሮቶች ምን ምን ናቸው?
  5. ልሳነ ግፉዓን ከዚህ ወዴት? ቀጣዩ የትግል ጉዞና አካሄድ ምን መሆን ይኖርበታል? የሚሉት ናቸው።

የልሳነ ግፉዓን ከቆመላቸው አላማዎችና ግቦች አንፃር ለህዝባችን ምን አይነት ስኬቶችና ድሎች አበርክቷል?

1ኛ. ልሳነ ግፉዓን ዋና ዋና አላማዎቹ ምን ምን ነበሩ? የትኞቹን አሳክቷል?

በዋናነት ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን በግንባር ቀደምትነት አንግቧቸው ከተሳው አበይት አላማዎች በላቀ ሁኔታ የጠላትን ትክክለኛ አላማ፣ ባህሪና፣ አካሄድ በቅጡ ከመረዳትና ጠላትን ድል ለመንሳት የሚያስችል ተመጣጣኝ የትግል ስልትና ዘዴ ቀርፆ መንቀሳቀስ ለስኬታማነታችን እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ እንደ ነበር አፅንኦት ሰጥቶ የሰራበት ጉዳይ ነበር። ስለሆነም የሚከተሉትን ግዙፍ ተግባራት ለመከወንና አላማዎቹንም በሚያስደስት ሁኔታ ለማሳካት ችሏል።

ሀ. የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ በህወሃት የተከፈተበትን ወረራና ከፊቱ የተደቀነበትን የዘር ማፅዳት ጥፋት በትክክል እንዲረዳና  እራሱንና መጭውን ትውልድ ከጥፋት ለመታደግ በቁርጠኝነት ለትግል እንዲነሳ ማስቻል፤

የወልቃይት ህዝብ በትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ድርጅት በኩል የታወጀበትን ታሪክ ነጋሪ አዛውንቱን በማጥፋት፣ ጎልማሳውን በማሰር፣ በመሰወር፣ በማሳደድ፣ በመግደል ዕርስትና ትውልድ ጠባቂ በማሳጣት፣ ታሪክ ተረካቢ የሆነውን ወጣቱን ትውልድ ህወሃት በፈበረካቸው ሃሰተኛና ልብወልድ ትግሪያዊ ተረታ-ተረቶች በመበረዝ፣ ከደም-መላሽ ወንድሙና አለኝታው ከሆነው የጎንደር ህዝብ በመነጠል፣ አማራዊ ማንነቱንና ኢትዮጵያዊ ኩራቱን በማጠልሸትና በማጥፋት፣ ለም መሬቱን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ በሚሆኑ ከትግራይ በመጡ የትግሬ ሰፋሪዎች በማስወረር፣ በአጠቃላይ ዘሩን የማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካቱን ሴራና ሂደት በቅጡ ተረድቶ ወቅቱ የሚጠይቀውን ግንዛቤ እንዲኖረውና በጉዳዩ ላይ ግልፅ አቋም እንዲይዝ በማስቻል ለትግል እንዲነሳ ማድረግ እጅግ አስቸጋሪና ፈታኝ ነበር። ምክንያቱም፦

  1. ችግሩን አስመልክቶ በልሳነ ግፉዓን በኩል ይቀርብ የነበረው ትክክለኛ ትንታኔ እና መረዳት ከህዝባችንም ሆነ በጉዳዩ ላይ እውቀትና ልምድ ካላቸው ምሁራንና ፖለቲከኞች በእጅጉ የላቀ በመሆኑ የልሳነ ግፉዓን አቀራረብ መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር በእጅጉ የማይመጣጠን እና በጣም የራቀ ነው የሚል የተዛባ ግንዛቤና አቋም በብዙዎች ዘንድ በመያዙ፤
  2. የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችና ሃገር ቤት ውስጥ በሚያካሂዷቸው የእርሻና የንግድ እንቅስቃሴዎች ምክንያት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለህወሃት የተንበረከኩ ኣንዳንድ ግለሰቦች በማህበረሰቡ ውስጥ የፈጠሩት የጥቅመኝነት ባህልና የመከፋፈል ሴራ፤
  3. ከወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ ከአቶ ፀጋዬ አስማማውና፣ ከአቶ ፈረደ የሽወንድም ከመሳሰሉ የህወሃት ተላልኪዎችና አገልጋዮች ጋር የጠበቀ ግንኙነት በነበራቸው ግለሰቦች አማካኝነት ወደ ህዝባችን የሚሰራጨው የመከፋፈልና የማበጣበጥ ሴራ ቤተሰባዊ ባህሪ የተላበሰ በመሆኑ ተፅዕኖው ከባድና ውስብስብ ስለነበር፤
  4. ቁጥራቸው አነስተኛም ቢሆንም እንኳ ከትግሬ ዘር የተወለዱና ከትግሬ ጋር የተጋቡ የወልቃይት ተወላጆች በማህበረሰባችን ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው የግለሰቦችን ትግሪያዊ ማንነት ከህዝብ ማንነት ጋር በመቀላቀልና በማምታታት የህወሃትን የመስፋፋትና አማራን የማጥፋት ሴራ ለማክሸፍ የሚደረገውን ትግል ህዝባችን በሙሉ ሃይሉና ልቡ እንዳይታገል እንቅፋት በመሆን ሊያደነቃቅፉት ይውተረተሩ ስለነበር ነው።

ስለሆነም ህዝባችን በጠራ የትግል አቋምና የፀና አንድነት ውስጥ በመሆን ሊያጠፋው የመጣውን ጠላት በሙሉ ሃይሉ አምርሮ እንዳይታገል ማነቆ የሆኑትን ሳንካዎች በማጋለጥ ከትግሉ ሜዳ ጠራርጎ ማስወገድና ህዝባችን “እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ አንደበት ተናጋሪ” በመሆን በቁርጥኝነት ወደ ትግሉ ሜዳ እንዲገባ ማስቻል የድርጅታችን ዋነኛ ተቀዳሚ አጀንዳ ነበር።

በመሆኑም ድርጅታችን በህዝባችን ውስጥ ባደረገው የውስጥ ለውስጥ መራራ ትግልና ያላሰለሰ ጥረት እንክርዳዶቹን ከንፁሁና ከታጋዩ ህዝብ መካከል ለይቶ በማውጣት ጠላት ወደ ድርጅታችን ሰርጎ ሊገባበት የሚችለውን ቀዳዳ ሁሉ በመድፈን በማይቀረው ፍትሃዊ ትግል ውስጥ የበኩላቸውንና አቅማቸው የሚፈቅደውን አስተዋፅዕ ለማበርከት ወደ ድርጅታችን የተቀላቀለውን ታጋይ ህዝብ ደህንነቱና ምስጢሩ በአስተማማኝነት በተጠበቀ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እንዲታገል ማስቻል ሙሉ ለሙሉ ተችሏል። ለዚህም የድርጅታችን አመራሮችና አባላት ላቅ ያለ ምስጋና ይጋባቸዋል።

ለ. ለወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ እውነተኛ ድምፅ መሆን

ተስፋፊውና ፋሽስቱ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ድርጅት የጎንደርን ለምና ታሪካዊ መሬቶች ወደ ትግራይ በማካለል አካባቢውን ትግሪያዊ ለማድረግ በያዘው እኩይ አላማ ምክንያት የወልቃይት የጠገዴና የጠለምትን ህዝብን ከአካባቢው በማፅዳት ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጥ ቁጥር ያለው የትግራይ ሰፋሪ በአካባቢው በማስፈር ነባሩን የአማራ ህዝብና ዘር እንዲጠፋና በትግሪያዊነት እንዲተካ በማድረግ በህባችን ላይ ከፍተኛ ግፍና በደል ሲፈፅን ኖሯል።

ምንም እንኳ ህዝባችን ይህን እኩይ የዘር ማፅዳት ወንጀል ለመቀልበስ የሚችለውን ሁሉ ቢያደርግም “ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” እንዲሉ ጊዜ የሰጠው ፍሽስቱ ህወሃት ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ ህልቆ መሳፍርት የሌላቸው ወገኖቻችን የሰቆቃ ድምፃቸው ለኢትዮጵያም ህዝብ ሆነ ለዓለም ማህበረሰብ እንዳይሰማ በማድረግ ለጀምላ እስር፣ ለመራር ስቃይ፣ ለግፋዊ ግድያና፣ ለመጠነ ሰፊ ስደት ዳርጓቸዋል።

ህወሃት የሃገሪቱን መንግስታዊ ስልጣንና ሃብት ከተቆጣጠረ ጀምሮ “ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት” የሚለው ስምና በእነዚህ አካባቢዎች የምንኖር የጎንደር ተወላጆችን አማራዊ ዘር ጨርሶ ከምድረ-ገፅ የማጥፋቱን ስራ በረቀቀና በተጠና ሁኔታ ማከናወኑ ያሳሰባቸው በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ወንድሞቻችን የወሰዱት ታሪካዊ እርምጃ ቢኖር “ልሳነ ግፉዓን” የሚል የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ማቋቋም ነበር። በመቀጠልም ተቀዳሚ ተግባራቸው ያደረጉት በዚህ ድርጅት ዙሪያ በመሰባሰብ ህዝባችን ጨርሶ ከመጥፋቱ በፊት የህዝባችንን የሰቆቃ ድምፅ ለኢትዮጵያና ለዓለም ሰላምና ፍትህ ወዳድ ህዝቦች፣ የፍትህና የሰብአዊ መብት አስከባሪ አካላትና፣ እውነተኛ ጋዜጠኞች ዘንድ በማድረስ የህወሃት የዘር ማፅዳት ሴራና ወንጀል በተጨባጭ መረጃ ማጋለጥ ነበር።

በዚህም መሰረት የልሳነ ግፉዓን አመራሮችና አባላት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና የውይይት መድረኮች በመቅረብ የወልቃይትን ህዝብ የድረሱልኝ ጥሪ ላልሰማው ወገናችን ሁሉ በማሰማት፤ በተለይም በኢሳት ቴሌቪዥንና ሬድዮ፣ በግንቦት 7 ሬዲዮ፣ በጀርመን ድምፅ ሬዲዮ፣ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ፣ እንዲሁም በተለያዩ የአውሮፓና የአሜሪካ ከተሞች በሚገኙ ሬዲዮና የቴሌቪዥ ስርጭቶች ቀርቦ በማስረዳትና ከህዝብ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት የህዝባችን ጩሃት በሁሉም ዘንድ ያለ አንዳች ገደብ እንዲደመጥ አስችሏል።

በተመሳሳይ መልኩ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ድረ-ገፆችና ብሎጎችን በመጠቀም የወልቃይት ጩሃት እውነተኛ የንፁሃን የሰቆቃ ድምፅ መሆኑንና ጉዳዩ ከወሬ በዘለለ ሁኔታ በተጨባጭ ሰነዶችና በትክክለኛ መረጃዎች የተደገፈ እንደሆነ የሚያስገነዝቡና የሚያሳስቡ የተለያዩና ተከታታይነት ያላቸውን ፅሁፎችና መግለጫዎችን በማቅረብ ግንዛቤ እንዲፈጠር ያደረገ ሲሆን፣ በህወሃትና በተላላኪዎቹ በኩል የሚቀርቡትን ሃሰተኛ መግለጫዎችና ሰነዶችን ታሪካዊነታቸው በተረጋገጠላቸው እውነተኛ ማስረጃዎች ማጋለጥና በዚህም የህዝባችን የደረሱልኝ ጩሃትና የሚያካሂደው ፍትሃዊ ትግል በሁሉም ዘንድ ተቀባይነትና ድጋፍ እንዲያገኝ ማድረግ ተችሏል።

ከሁሉም በላይ የወልቃይት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘትና የልሳነ ግፉዓን እውነተኛ የህዝብ ድምፅ መሆን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈጠርው ግንዛቤና ይህንንም ተከትሎ ከየአቅጣጫው የቀሰቀሰው ህዝባዊ ጥያቄና ጫና ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ፋሽስቱና ተስፋፊው የህወሃት ወራሪ ቡድን  በሃይል ወደ ትግራይ የከለላቸውን የወልቃይት የጠገዴና የጠለምት ለምና ታሪካዊ የጎንደር መሬቶች ላይ በተዛባና በሃሰተኛ መረጃዎች ላይ የተመሰረተ ቅስቅሳ ላይ እንዲጠመድና በታሪክ “ወልቃይት የትግራይ አካል ነበረች” ወደሚል የአደባባይ ቅስቀሳና ሙግት ውስጥ ተገዶ እንዲገባ ማድረግ ተችሏል። በዚህም  ምክንያት ህዝባችን ከሁሉም በላይ የሆነውን ድል እንዲጎናፀፍ አስችሎታል።  ይሃውም፦

  1. ኢትዮጵያዊ ምሁራን፣ የሃገር ሽማግሌዎችና፣ ታሪክ አዋቂዎች በህዝባችን ትግል ውስጥ ቀጥተኛ ተሳታፊና ባለቤት የመሆን እድልን ፈጥሮላቸዋል። ስለሆነም የህወሃትን የሃሰት ቅስቀሳና አስተምህሮት በእውነተኛና በታሪክ በተደገፉ ማስረጃዎችና ትክክለኛ አስተምህሮት በአደባባይ እንዲጋለጥና የህወሃት አይን ያወጣ ወረራና ዝርፊያ ህገወጥ መሆኑ በሁሉም ዘንድ እንዲታዎቅ አስችሏል።
  2. ወጣት ምሁራንና ፖለቲከኞች በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ ጥያቄ ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙና ትክክለኛ እወቀት ኖሯቸው ከህዝባችን ትግል ጎን እንዲሰለፉ አስችሏል።
  3. እነ ክቡር ልዑል እራስ መንገሻ ስዩምንና አቶ ገብረመድህን አርአያን የመሳሰሉ ታዋቂ የትግራይ ተወላጆችና ፖለቲከኞች በአደባባይ የወልቃይትን ህዝብ ትግል እንዲደግፉና በህወሃት በኩል የሚቀርበውን የሃሰት አስተምህሮ በአደባባይ በፅናት እንዲቃወሙና እውነታውን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያጋልጡ አስችሏቸዋል። በዚህ አጋጣሚ ጋዜጠኛ ተክሌ የኋላን ለመጀመሪያ ጊዜ ለዑል ራስ መንገሻ በጀርመን ድምፅ ላይ በማቅረብ እውነታውን እንዲናገሩ በማድረጉ በግሌ ላመስገነው እወዳለሁ።
  4. ጋዜጠኞችና የታሪክ ምሁራን በወልቃይት ዙሪያ አበክረው ትምህርት እንዲሰጡና የተለያዩ ፕሮግራሞችን እንዲያዘጋጁ መነቃቃትን ፈጥሯል።
  5. ታላላቅ ሚዲያዎች፣ በብዛት ተነባቢ የሆኑ ድረ-ገፆችና፣ ታዋቂ ብሎጎች ላለፉት 5 አመታት ቢያንስ በሳምንት አንዴ በወልቃይት ጉዳይ ዙሪያ የሚዘግቡ ሲሆን፤ ከአለፉት 2 አመታት ወዲህ ግንባር ቀደም ሃገራዊ አጀንዳ ለመሆን ችሏል።

በአጠቃላይ ምንም እንኳ ህወሃት የወልቃይትን ጉዳይ ከኢትዮጵያ ህዝብና ከዓለም ማህበረሰብ እይታ ሰውሮ በፀጥታ ማጥፋትን አቅዶ ለአለፉት 35 ዓመታት ቢሰራም የልሳነ ግፉዓን መነሳት ይህን እኩይ ሴራ ወደ አደባባይ እንዲወጣና ህወሃት ፍፁም በሚሸነፍበት የትግል ሜዳ ውስጥ ተገዶ እንዲገባ አስችሏል። ለዚህም ታላቅ ጥበብና ተጋድሎ የድርጅታችን አመራሮችና አባላት ይልቁንም ከላይ የዘረዘርኳቸው ባለድርሻ አካላት ሊመሰገኑ ይገባል። (ከ2010 ጀምሮ ለህዝብ የቀረቡ ልሳኖች መካከል ለናሙና የመረጥኳቸው እባሪ ላይ ተያይዘዋል)

መ. መረጃዎችን ማሰባሰብና ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ

ፀረ-ህዝብና ፀረ-ሰላም የሆነው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ቡድን ከታሪካዊ ጠላቶቻችን የተቀበለውን ኢትዮጵያንና ህዝቧን የማዳከምና ብሎም የማጥፋት እኩይ አጀንዳ በተግባር ላይ ማዋል የጀመረው የወልቃይትን ህዝብ በማጥፋት መሬቱ በትግሬ ሰፋሪዎች በማጥለቅለቅ፣ በተቀነባበረ ዘዴ የወልቃይት ሴቶች ለትግሬ ወንዶች እንዲወልዱ በማድረግ፣ የወልቃይትን ታሪካዊ የመንገድና የአካባቢ ስሞች በትግሪያዊ ስም እንዲለወጡ በማድረግ፣ በአጠቃላይ በአካባቢው ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ ወልቃይት የትግሪዎች ብቸኛ መኖሪያ፣ መበልፀጊያና፣ መፈንጫ እንድትሆን በማድረግ ነበር።

ይህን ዘርፈ ብዙ፣ በፍፁም ጥንቃቄና፣ በዝግ የሚደረግ የዘር ማፅዳት ወንጀል በንቃት ተከታትሎ በተጨባጭ ማስረጃዎች አስደግፎ ለህዝብ ማጋለጥና ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ አላማው አድርጎ የተንሳው ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን በዚህ ረገድ የሄደበት መንገድ እጅግ የሚያስመሰግንና የሚያበረታታ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

በተለይም ዛሬ ዛሬ በተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች በኩል በሚወጡ ሰነዶች ላይ በህወሃት የግፍ አገዛዝ ተደብድበው አካላቸው የጎደሉ፣በጨለማ ውስጥ የታሰሩ፣ በድብቅና በአደባባይ የተገደሉና፣ ታፍነው ተወስደው የገቡበት ያለታወቁ ህልቆ መሳፍርት የወልቃይት የጠገዴና የጠለምት ተወላጆች ስም ዝርዝሮች ሁሉም ማለት ይቻላል በልሳነ ግፉዓን በኩል የተሰበሰቡና በተለያዩ ጊዜያት ለህዝብ ይፋ በተደረጉ የድርጅታችን መግለጭዎች አማካኝነት የትሰራጩ መሆናቸውን ስናይ ድርጀታችን ልሳነ ግፉዓን ህወሃት በህዝባችን ላይ ያደረሰውን የዘር ማፅዳት ወንጀል ለማጋለጥና ለወገናችን ሰብአዊ መብቶች መከበር እያደረገ ያለውን ታላቅ ተጋድሎና የወሰደውን የመሪነት ሚና በተጨባጭ የሚያሳይ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

ሰ. የወልቃይትን ጉዳይ በሃገራችን ግንባር ቀደም የመታገያ አጀንዳ እንዲሆን ማስቻል

እነሆ ዛሬ የህዝባችን ትግል ፍሬ አፍርቶ ትላንት ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የት እንዳሉ ጨርሶ የማያውቀውና በተለይም “ወልቃይት” የሚለውን ስም አስተካክሎ እንኳ መጥራት የማይችለው የሃገራችን ህዝብና ፖለቲከኛ ዛሬ ከጎንደር ተራሮች እስከ ሶማሌ በረሃ፣ ከአፋር እስከ ጋምቤላ በሁሉም አቅጣጫ ያለው ወገናችን “ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!” በማለት የሚታገልለትና የሚሞትለት አገር አቀፍ አብይ አጀንዳ ለመሆነ በቅቷል።

ዛሬ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ በስደት ከኢትዮጵያ ውጭ ለሚገኘው ህዝባችን ከሰሜን አሜሪካ አውራ ጎዳናዎች እስከ አውሮፓ የባቡር ጣቢያዎች በግግር በረዶ ማሃል ሌት ከቀን የሚሰለፍለት፣ ከኒውዚላንድ/አውስትራሊያ ደሴት እስከ እስራኤል የጦር ካምፕ፣ ከሰሜን ሱዳን እስከ ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ወገኖቻችን ተቀዳሚ ጉዳያቸው ለመሆነ የቻለ ሲሆን፤ ይልቁንም ስለ ወልቃይት ሲባል በቁጣና በምሬት ህወሃት ላይ መነሳት የህዝባችን የአንድነትና የወገንተኝነት መለኪያና መገለጫ፣ የኢትዮጵያዊ ጀግንነት አብይ ምግባር ከሆነ ውሎ አድሯል።

የወልቃይት ህዝብ ጩሃትና ሰቆቃ ዛሬ የአለማችን ሃያላን መንግስታትና ድርጅቶቻቸው ሳይቀሩ ጆሯቸውን የሰጡትና በራቸውን የከፈቱለት ታላቅ የህዝብ ጥያቄ ሆኗል። ከአሜሪካው ሴኔት አስከ እስራኤሉ ከንሴት/Knesset/፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአውሮፓው ፓርላማ፣ የአፍሪካው አንድነት ድርጅት፣ እንዲሁም ሁሉም አለም አቀፍና ሃገር በቀል የሰብአዊ ተሟጋች ድርጅቶች በአንድነት ጥብቅና የቆሙለትና በንቃት የሚከታተሉት ቁልፍ አጀንዳ ነው።

ይልቁንም ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን ካሳካቸው አበይት ተግባራት አንዱና ዋነኛው ሰሚ ላልነበረው ለወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ የሰቆቃ ድምፅ እውነተኛ ድምፅ በመሆን የሰው ዘር በሙሉ እንዲሰማውና አጋር እንዲያገኝ ማድረግ ቢሆንም የሚበልጠው ስኬት ግን ዛሬ በዚህ ትግል ዙሪያ በንቃት የሚሳተፉና የህዝባችንን ጉዳይ ቀዳሚ አጀንዳቸው አድርገው ለሚነሱ ህዝባዊ ቁጣዎችና ንቅናቄዎች ሁሉ እርሾ ሆኖ ማገልገል የቻለ ግልፅ፣ ቀጥተኛና፣ መዳረሻው የታወቀ አጀንዳ ቀርፆ ትግሉን በፅኑ መሰረትና ባቡሩንም በትክክለኛ ሃዲዱ ላይ እንዲሸከረከር በማስቻሉ ጭምር ነው።

2ኛ. የድርጅታችን የስኬት ምስጢሮች

ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን ተመጣጣኝ በሆነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ስኬታማ እንዲሆን ካስቻሉት ዋነኛ ምክንያቶች መካከል ይበልጥ ትርጉምና ተፅዕኖ ፈጥረዋል የምላቸውን ለመጥቀስ እሞክራለሁ።

  1. የጠላትን ሴራና አካሄድ ጠንቅቆ በመረዳት ላይ የተመሰረተ ትክክለኛ የትግል ስትራቴጂ ማውጣትና ያወጣውንም የትግል ስልትና አካሄድ በትክክል ወደ ተግባር መተርጎም በመቻሉ፤
  2. አመራሩ ከአባላቱ ጋር ለቆሙለት አላማ እንደ አንድ ቤተሰብ በፅናትና በቁርጠኝነት በመቆም ትግሉን መምራት በመቻላቸው፤
  3. አባላቱ እና አመራሩ ቀጥተኛ የችግሩ ሰለባዎች በመሆናቸው ከማንኛውም ውጫዊና ውስጣዊ ሴራና ተፅዕኖ የፀዳ አመራር መፍጠር በመቻሉ፤
  4. በአመራሩ በኩል ቅድሚያ የተሰጣቸው ምስጢርን የመጠበቅና ለትግሉ ቅድሚያ ሰጥቶ የመስራት ባህርያት ሙሉ ለሙሉ ተግባር ላይ መዋላቸው፤
  5. የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅትና ተላላኪዎቹን በትክክል የተረዳና የእነሱንም የማያባራ የስለላ ሴራና ፈርጀ ብዙ ጥቃት ለመመከት በድርጅቱ ውስጥ ሙሉ ቁረጠኝነት መኖሩና በቂ ትግል በመደረጉ ናቸው ብዬ አምናለሁ።

3ኛ. ድርጅታችን ከተመሰረተበት ጀምሮ በጉዞው የገጠሙት ፈተናዎች ምን ምን ነበሩ? እንዴትስ አለፋቸው?

ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን እንደ ማንኛውም ድርጅት በጉዞው መካከል መሰናክሎችና ፈተናዎች ሳይገጥሙት አላለፈም። በተለይም የህዝባችንና የሃገራችን ግንባር ቀደም ጠላት ከሆነው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ቡድን በኩል የሚሰነዘረው ተደጋጋሚ ጥቃትና ፈተና እጀግ ከባድ ነበር። ከነዚህም መካከል ዋና ዋና ያለኳቸውን አራቱን ብቻ በአጭሩ ለማንሳት እሞክራለሁ።

  1. በተለይም ህወሃት በወ/ሮ አዜብ መስፍን ዙሪያ በማሸመቅ ከወልቃይት ህዝብ ጋር ያላትን የስጋ ዝምድና ተጠቅሞ ቀላል የማይባሉ ተላላኪዎችን ማሰማራት ችሎ ነበር። በእነዚህ የህወሃት ፍርፋሪ ለቃሚዎች አማካኝነት የህዝባችንን ህብረትና የመታገል ቁርጠኝነትን የተለያዩ የማማለያ ዘዴዎችና ስጦታዎች በማቅርብ ሲቦረቡር ኖሯል። ይህ ሴራ ወደ ልሳነ ግፉዓን የሚመጡትንና በውስጥም ያሉትን በከፍተኛ ሁኔታ ለማጥመድ ለረዥም ጊዜ የተሰራበት በመሆኑ ይህንንም ሴራ ለማክሸፍ በጥንቃቄና በቀስታ መስራት የግድ ነበር። ይልቁንም በሃገር ቤት ያለውን ወገናችን ደህንነት ከመጠበቅ አንፃር ቅድሚያ በመስጠት ቀድሞ የተዘጋጁትን እቅዶችና ግንኙነቶች ሙሉ በሙሉ መቀየር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ በጉዟችን ላይ እንቅፋት መፍጠሩ አለቀረም ነበር።

 

  1. በሁለተኝነት ሊጠቀስ የሚችለው ተግዳሮት የአመራሩ የአቅም ውስኑነት ከትግሉ ስፋትና ጥልቀት በዚህም ምክንያት ከሚጠይቀው የሰው ሃይል ብዛትና ጥራት ጋር በፍፁም የሚመጣጠን አልነበረም። በአመራርነት የተቀመጠው ቡድን በቁጥር እጀግ አነስተኛ ሲሆን የሚሰራው ስራ ግን እጅግ የበዛ ነበር። ለምሳሌ ያህል ለመጥቀስ በአንድ በኩል የወልቃይትን ማህበረሰብ በህልውናው ላይ የተጋረጠውን አደጋ በወቅቱ ተረድቶ አቋምና እርምጃ እንዲዎስድ ማስቻል በአንድ በኩል ሲሰራ፤ በተመሳሳይ ወቅት በወልቃይት “የዘር ማፅዳት” ወንጀል እየተፈፀመ ነውና ድረሱልን ብሎ ወደ ኢትዮጵያ ህዝብ በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ መጮህና ሰሚና አጋር ለማግኘት መታገል እጅግ ፈታኝ ነበር። ምንም እንኳ አምርሮ በሚታገልና በሚያታግል አመራር የማያቋርጥ ጥረትና ብርቱ ትግል አማካኝነት በሁለቱም ዘርፎች አኩሪ ውጤት ቢገኝም የትግሉን በተጠበቀው ፍጥነት እንዳይጓዝ ማድረጉና የአመራሩንም ህልውና የተፈታተነ ሂደት ነበር።

 

  1. በሶስተኛነት የሚጠቀሰው አብይ ፈተና የገንዘብ እጥረት ነበር። እንደሚታወቀው እያንዳንዷ እንቅስቃሴ የገንዘብ ወጪ አለባት። በተለይም የሃገሪቱን ሃብት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ገንዘቡን ለስለላና ለመደለያ ከሚያውል ህወሃትን መሰል ድርጃት ጋር መታገል እጅግ ፈታኝ ነበር። ይልቁንም ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን አንድም ጊዜ ከህዝብ የሰበሰበው ወይም ከድርጅት የተደጎመው ምንም አይነት ገንዘብ ሳይኖር ከአባላት ብቻ በሚሰበሰብ ገንዘብ ትግሉን መምራት ተአምር የሚታይ ነበር (የጎንደር አመፅ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በሁለት ድርጅቶች የታቀፉ ወገኖቻችን በራሳቸው ተነሳሽነት ለልሳነ ግፉዓን ገንዘብ እንደለገሱ ማስታወስ እወዳለሁ። በዚህ አጋጥሚ ለወገኖቼ ምስጋናዬ ይድረሳቸው። ስማቸውን ድርጅቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ይገልፃል ብየ አምናለሁ) ። አንዳንዴም አመራሩ አባላትን ገንዘብ ለመጠየቅ በመሳቀቅ ለአንዳንድ አስቸኳይ ጉዳዮች ከኪሱ የሚያወጣው ገንዘብ ትግሉን በእጅጉ ይፈታተነው እንደነበር ህያው ምስክር ነኝ። ይህን መሰል የገንዘብ ችግር ባይኖርና አመራሩ በአቀደው መሰረት ቢጓዝ ኖሮ ድላችን ዛሬ ካስመዘገብነው አንፀባራቂ ድል እጅግ የላቀ ሊሆን ይችል እንደነበር በፍፁም አልጠራጠርም። በዚህ አጋጣሚ በልሳነ ግፉዓንና በአመራሩ ተማምነው ገንዘባቸውን በተጠየቁ ቁጥር ያለስስት በልግስና በመስጠት ከጎናችን ለተሰለፉ አባሎቻችን ሁሉ ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ። ያለ እናንተ እርዳት ህወሃትን ድል ማድረግ የማይታሰብ ነበርና ነው።

 

  1. በአራተኛነት ደረጃ የሚቀመጠው ወደ ህዝባችን የምንደርስበትና ሃሳባችንን የምናስተላልፍበት የብዙሃን የመገናኛ ዘዴ ማገኘት አለመቻል ነበር። በተለይም ኢሳት እስኪቋቋምና ሙሉ ለሙሉ ከእኛ ጋር መስራት እስኪጀምር ድረስ ወደ ሃገር ቤት የሚገቡት የሬድዮ ስርጭቶች የጀርመንና የአሜሪካ ድምፅ ብቻ በመሆናቸውና የእነሱንም ልብ አሸንፎ መድረኩን ማገኘት እጅግ ፈታኝ ነበር። ወልቃይት ጠግዴና ጠለምትን አስመልክቶ በጀርመን ድምፅ በኩል አልፎ አልፎ ጋዜጠኛ ተክሌ የኋላ ይሰራቸው ከነበሩት ፕሮግራሞች በቀር ጉዳዩ የሚነሳበት ይህ ነው የሚባል እድል አልነበረም። ምንም እንኳ ልሳነ ዓፉዓንም እንደ ድርጅት መድረኩን ለማገኘት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም እድሉን ያገኘበት ወቅት አልነበረም። በዚህም ምክንያት ኢሳት እስከተቋቋመና አብረን መስራት እስከጀመርን ያለው ጊዜ በእጅጉ የሚያስቆጭ እና የብዙ ንፁሃንን ህይወት ማዳን የምንችለበት ወርቃማ ጊዜ ነበር። ይህ ደግሞ ሁሌም ሲያመን ይኖራል።

 

  1. የመጨራሻው እና ሁሌም አደጋው ገዝፎ የሚታየን የመገናኛ ዘዴ ችግር ነው። እንደሚታወቀው የሃገሪቱን የቴሌ አገልግሎት በብቸኝነት ተቆጣጥሩ በዓለም ላይ ውድ በሆኑና በተመሰከረላቸው የስልክ መጥለፊያ ዘዴዎች በመጠቀም ሌት ከቀን የኢትዮጵያን ህዝብ የሚሰልለው ህወሃት ጎንደርን በተለይም በወልቃይት ዙሪያ ከፍተኛ ሃይል አሰማርቶ እንደሚሰራ እንገምት ነበር። በዚህም ምክንያት ወደ ሃገር ቤት የሚደረገው ግንኙነት እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት በመሆኑ ግንኙነቱን ጠባብ፣ የትግሉንም ሂደት አዝጋሚ ሊያደርግው የግድ ነበር። ምንም እንኳ ድርጃታችን በወሰደው ከፍተኛ ጥንቃቄ ምክንያት አንድም መረጃና ተልዕኮ በህወሃት እጅ መግባትና መደናቀፍ ያላጋጠመው ቢሆንም ሂደቱ ግን በተወሰነም ደረጃ ቢሆን መጓተቱ አልቀረም ነበር። የመገናኛው ዘዴ የተሳለጠ ቢሆን ኖሮ ህወሃት አሁን የደረስበትን ሃገር አቀፍ ሽንፈትና ኪሳራ ከ5 ዓመታት በፊት ማስተናገድ በተገደደ ነበር። ይህ ደግሞ የህዝባችንን የስቃይ ጊዜ በእጅጉ ያራዘመ በመሆኑ ያበሳጫል።

4ኛ. የልሳነ ግፉዓን ወደ ፊት የሚጠብቁት ተግዳሮቶች ምን ምን ናቸው?

ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን በዋናነት ከፊት ለፊቱ የሚጠብቁትን ተግዳሮቶች ሙሉ ለሙሉ ለመገመትና ጠንቅቆ ለማወቅና የብዙ አዋቂዎችና ባለሙያዎች ጥረት የሚጠይቅ ይመስለኛል። ለዚህም ሰነድ መዘጋጀት ዋነኛው ገፊ ምክንያት በዚህ ንኡስ ርዕስ ስር በአባላትና በደጋፊዎቻችን በኩል ሊዳሰሱ የሚችሉ ጭብጦችን ታሳቢ በማድረግ ነው። ነገር ግን ከቀደሙት ልምዶቻችን፣ ከሃገራችን ቀደምት ታሪኮችና፣ ካለንበት ሃጋራዊም ሆነ አለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት የሚከተሉትን ተግዳሮቶች በታሳቢነት ማንሳት እወዳለሁ። የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ቡድንና በዙሪያው ያሰለፋቸው ቀደምት ጠላቶቻችንን የሞት ሽረት ትግል እንደተጠበቀ ሆኖ፦

 

ሀ. የትግሉን የእድገት ደረጃ ያገናዘበና የጠላትን አሰላለፍ በተረዳ ሁኔታ ድርጅታዊ መፍትሄ የመስጠት አቅምና ክህሎት ጥያቄ፣

 

ለ. ከሁሉም አቅጣጫ እየጨመረ የሄደውን የአባልነት ጥያቄና የእንተባበር ፍላጎት ሊሸከምና በወቅቱ ትክክለኛ ምላሽ ሊሰጥ   የሚችል አመራር፣ ድርጅታዊ መዋቅርና፣ መሪ ሃይል ማስፈለግ፣

 

ሐ. የወልቃይት፣ የጠገዴና፣ የጠለምት ህዝብ ታሪካዊ ትግልና፣ የተገኘውን ህዝባዊ ድል ነጣቂዎችና የአማራነትና፣ የኢትዮጵያዊነትን ለምድ ለብሰው የሚመጡ የህወሃት ተላላኪዎች ጠለፋ (በትንሹም ቢሆን በተግባር የታዬ)፣

 

መ. ህወሃት ለወልቃይትና አካባቢውን በራስ ገዝ ስም ወይም በፌደራል ስር ወይም አዲስ አከላለል በመጠቀም ታጋዩን ህዝብ በመከፋፈላና ከጎንደር ህዝብ በመነጠል ማዳከምና ትግሉን ይበልጡኑ ማደቀቅ (በእንቅስቃሴ ላይ ያለ) … ወዘተ

5ኛ. ልሳነ ግፉዓን ከዚህ ወደ ዬት? ቀጣዩ የትግል ጉዞና አካሄድ ምን መሆን ይኖርበታል?

ማንኛውም ድርጀት ጊዜውን ጠብቆ እንደተወለደ ሁሉ ጊዜውንም ጠብቆ የማደጉ ጉዳይ አይቀሬ ነው። በዚህ የተፈጥሮ መርህ መሰረት ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን ከተቋቋመበት ግዜ ጀምሮ የቆመላቸውን አላማና ግቦች ከማስካት አንፃር ያሳየው ጉዞና እድገት ከላይ በዝርዝር ለማየት ሞክሪያለሁ።

ልሳነ ግፉዓን እንደስሙ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ማህበረሰብ እውነተኛ ልሳን በመሆን የህዝባችን የሰቆቃና የፍትህ ድምፅ  ከኢትዮጵያ ገጠራማ ቀበሌዎች አስከ አሜሪካው መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት ድረስ እንዲደመጥ ለማደረግ ችሏል። ይልቁንም ይህ ህዝባዊ የፍትህ ጥያቄና የሰቆቃ ድምፅ ከመደመጥ አልፎ የብዙዎችን ቁጣ የቀሰቀሰና ለመራር ትግል ያነሳሳ በመሆን የፋሽስቱን የህወሃት ስርዓት ከስር መሰርቱ ለማናጋትና ወደ ማይቀርለት ዘላለማዊና ታሪካዊ ሞት ባልተጠበቀ ፍጥነት እያንደረደረው መሆኑ ስረዳና ስመለከት  ታላቅ ኩራትና ደስታ ይሰማኛል።

የአንድን የህዝብ ክፍል የመብትና የህልውና ጥያቄ በፋና ወጊነት አንግቦ በመነሳት የቀሪውን ህዝብ ሙሉ ድጋፍ ካገኙና ከትግሉ ጎን ካሰለፉ በኋላ ቀጣዩ ሂደት ምን መሆን አለበት ብሎ ቆም ብሎ ማሰብና ማንሰላሰል፣ ብሎም ትግሉን ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ በማስተዋል መምራት የግድ አስፈላጊ ይመስለኛል። ከዚህም አንፃር በግሌ ከልሳነ ግፉዓን ጋር ያደረግነውን የትግል ጉዞ ቆምብዬ የማሰቢያ ጊዜ ያገኘሁ ይመስለኛል። በተመሳሳይ መልኩ እንዲህ አይነት ቆም ብሎ የማሰቢያና የማንሰላሰያ እድል ልሳነ ግፉዓን እንደ ድርጀት እንዲሁም አመራሩ እንደ መሪ በእጅጉ ያስፈልጋቸዋል ብዬ በጥብቅ አምናለሁ። ስለዚህ እኔም ባገኘሁት የጥሞና ጊዜ ስለ ትግላችን የወደፊት አቅጣጫ የተረዳኝን ነገሮች ማቅረብ እወዳለሁ።

ዝምታው ወደ ድንዘዛ እንዳያድግ ያሰጋኛል

ልሳነ ግፉዓን ካለው ድርጅታዊ አቅምና የአመራር ክህሎት አንፃር ያስመዘገበው ህዝባዊ ድል እጀግ የሚያኮራና የሚደነቅ ነው። በቀዳሚነት ይዞት የተነሳው ህዝባዊ ጥያቄ ዙርያ ማሰባሰብ የቻለውን የህዝብ ብዛትና አይነት ምን አልባትም በሃገራችን ታሪክ ከተከሰቱት ታላላቅ ህዝባዊ ቁጣዎችና ተቃውሞዎች መካከል አንዱ ለመሆን ያቻለ ይመስለኛል።

ይህን የህዝብ ቁጣና ተቃውሞ በትክክለኛው አቅጣጫና በቁርጠኝነት የሚመራው አካል ካለተገኘ እንደ ቀደሙት ታላላቅ ህዝባዊ ቁጣዎች ሁሉ እንዳይቀለበስ ያሰጋኛል። እንዲሁም ይህ ህዝባዊ ቁጣ እንደ ቀደሙት የኢትዮጵያ አብዮቶች ሁሉ ብዙ እበላ-ባይና ቀልባሾች  በዙሪያው ያሰፈሰፉበት ሆኖ ይሰማኛል። ይህም በተግባር እንደታየው ከወልቃይትን ህዝብ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተከሰተውን ህዝባዊ ቁጣ ተከትሎ ከ10 ያላነሱ “አማራ” ተኮር የብሄር ድርጀቶች እንደ እንጉዳይ መፍላታቸው ለተፈጠረው ውዥንብርና ጠለፋ ጥሩ ማሳያ ይመስለኛል።

በአንፃሩ ደግሞ ከላይ በቀላሉና ህዝብ በሚያውቃቸውና ምስጢራዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ በማተኮር ለማሳየት እንደሞከርኩት የወልቃይትን ህዝብ የማዳን ትግል ጠፍጥፎ የሰራው ልሳነ ግፉዓን ሆኖ እያለና በምን መንገድና እንዴት ባለ ዘዴ እዚህ እንዳደረሰው ባውቅም፤ ይልቁንም ነገሮችን በስክነት የማየት፣ ከጭብጨባውና፣ ከእዩኝ ባይነት እርቆ ትግሉ ላይ ብቻ አድፍጦ መስራቱን እጅግ የማደንቀውና የማከብረው እርምጃ ቢሆንም እንኳ የተወሰደው የበዛ ዝምታ ግን ሳያሳስበኝ አልቀረም።

የጎንደር የ“ጦርነት አውድማነት” እስከመቼ?

በግልፅ እንደሚታወቀው የየካቲት አብዮት ተብሎ በሚታወሰው ዘመን ነፍጥ ያነሱ ሃይሎች ባደረጓቸው የትጥቅ ትግሎች ውስጥ ዋነኛው ምሽጋቸው፣ የመታገያ ሜዳቸው፣ የቀለብ መሰፈሪያቸውና፣ የታጋይ መመልመያቸው ጎንደር ነበር። በአንፃሩ ደግሞ ህወሃት ኢህአፓንና ለጊዜው ስሙን የረሳሁትን አንድ የትግራይ ድርጅት አስገድዶ ከትግራይ ማስወጣቱና ወደ ጎንደር ማሳደዱ በታሪክ ተዘግቦ ይገኛል። የትግራይን ህዝብ ከተለያዩ ፖለቲካ ድርጅቶች ብዝበዛና የእርስ በርስ ክፍፍል አላቆ ለብቻው የተቆጣጠረው ህወሃት በኋላ ላይ እንደ ኢህአፓ፣ ኢዲዩ፣ ከፍኝና፣ ደርግ ሁሉ ምሽጉን ከትግራይ ወደ ጎንደር በማዛወር በተለይም ማዘዣ ጣቢያውን ከደደቢት ነቅሎ ደጀና (ወልቃይት) ውስጥ ማደረጉ ይታወቃል።

እነዚህ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጎንደር ውስጥ መመሸጋቸው ባልከፍም ነበር። ለህዝቡም በማሰብ አንድ አይነት ስምምነት አድርገው ህዝቡ ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ መቀነስ በቻሉ ነበር። ነገር ግን እነዚህ እርስ በእርሳቸው የሚጠፋፉ ሃይሎች አባላት የሚመለምሉት በቅርብ ከሚያገኙት የጎንደር ገበሬና ወጣት በመሆኑ ይህንን እንደ ወላጅ እናት መሸሸጊያ የሆናቸውን ህዝብ በተለያየ ድርጅት ውስጥ ሆኖ እርስ በእርሱ እንዲዋጋና እንዲተላለቅ አደረጉት። በተለይም አራቱ ሃይሎች ማለትም ደርግ፣ ኢዲዩ፣ ኢህአፓና፣ ህወሃት/ኢህዴን ዋነኞቹ የነበሩ ሲሆን ጎንደርም ከልጆቿ ደም ጋር የሃገሪቱ ዋነኛ የጦርነት አውድማ እንድትሆን ተፈርዶባት ነበር።

ታሪክ እራሱን ይደግማል እንዲሉ ዛሬ በእኛ ዘመን ይህ ዘግናኝ ትዕይንት ዳግም ጎንደር ላይ ዳዴ እያለ መሆኑን የማይረዳ ጎንደሬ ያለ አይመስለኝም። እውነት ለጎንደር ህዝብ የሚቆረቆር ወገን ካለ ዛሬ ጎንደር ላይ ለመመሸግና የጎንደርን ህዝብ ለተልካሻ ተልኳቸው ጭዳ ለማድረግ ያሰፈሰፉ ሃይሎችን ከወዲሁ በቃችሁ! ማለት አስፈላጊ ይመስለኛል። መቸም ቢሆን በቀደመው ታሪካዊ ፍጅት ገፈት ቀማሾችና በቁስሉም ዛሬ ድረስ የምንሰቃይ ተከታታይ ትውልዶች በህይወት እያለን ዳግም ጎንደርን የጦር አውድማ እንድትሆን መፈቀድ የለበትም። ከዚህ ታሪካዊ ጠባሳ እና ከፊት ለፊታችን ከሚጠብቀን የመድቀቅ አዙሪት በመነሳት ከድርጅታችን የሚጠበቁትን ተቀዳሚ ሚናዎችን ለመጠቆም እወዳለሁ።

ዘመኑን የዋጀ ድርጅታዊ መሪነት

በአጠቃላይ ልሳነ ግፉዓን ከዚህ ቀደም ይዟቸው ከተነሳቸው አበይት አላማዎችና ተልዕኮዎች መካከል ግንባር ቀደሞቹን በአመርቂ ሁኔታ አሳክቷል ብዬ አምናለሁ። ይህንንም በዝርዝር ለማሳየት ሞክሪያለሁ። እንደቀደመው ጊዜ ሁሉ አሁን ቀጣዩን የትግል ሂደት ከወዲሁ በአግባቡ መተለምና አባላቱንና ደጋፊውን ህዝብ በትክክለኛው አቅጣጫ የመምራት አስፈላጊነት ላይ በፅኑ አምናለሁ። ከነዚህም መካከል፦

1ኛ. ዛሬ የወልቃይትን አጀንዳ ተቀዳሚ አጀንዳው አድርጎ የተሳውና ከፋሽስቱና ከወራሪው የህወሃት ሃይል ጋር እየተጋደለ ያለው የጎንደር ህዝብ ጭብጨባና ሞቅታ በወለዳቸው ነጣቂዎችና አሻሻጮች እየተዋከበ ይገኛል። ይህን በይፋ ቀስቅሰን ወደ መረረ ትግል ያስገባነውን ህዝብ ከዘመኑ ተኩላዎች ጥቃት መከላከል የግድ ይላል። ለዚህም ድርጅታችን ዘመኑ በሚጠይቀው መጠን እራሱን በማሳደግ /Evolve/ እና ወደ መሪ ፖለትካ ድርጅትነት በማሸጋገር፣ ህዝቡን በታማኝነትና በቁርጠኝነት መምራት የጊዜው አንገብጋቢ ትልዕኮ ነው እላለሁ ፣

2ኛ. ከጎንደር ህብረትና ጎንደር ላይ አተኩረው ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር በቅርበት ተባብሮ በመስራትና በማስተባበር ህወሃት በጎንደር ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን የጀምላ ጭፍጨፋ በመመከት ስርዓቱን የማስወገድ ትግል አጠናክሮ መምራት፣

3ኛ. የጎንደርን ህዝብ ተጋድሎ ተከትሎ በአጋርነት በመቆም የህይወት ዋጋ እየከፈለ የሚገኘውን የጎጃምና የአካባቢውን ህዝብ ትግል ልዩ ትኩርት ሰጥቶ መደገፍና ማጠናከር፣

4ኛ. የጎንደርን ህዝብ ተቃውሞ በመደገፍ በህወሃት መራሹ መንግስት ላይ የተቀጣጠለውን  ኢትዮጵያዊና ዓለም ዓቀፍዊ ህዝባዊ ቁጣ በግንባር ቀደምትነት ማስተባበርና መምራት፣

5ኛ. ከኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ጋር ይፋዊ ውይይት በማድረግ የሃገራችንን አንድነት፣ ዳር ድንበርና፣ ሉዓላዊነት በሚያስጠብቅና የህዝባችንን ሰላም፣ ደህንነትና፣ መብት በሚያረጋግጥ ሁኔታዎች ላይ አተኩሮ መስራት ናቸው።

እንግዲህ እኔ እንደ አንድ ዜጋና የድርጅት አባል አቅሜ በፈቀደልኝ መጠን ለህዝቤና ለሀገሬ ሊሆን የገባል የምለውን ሃሳብ አቅረብኩ። ይህ ሰነድ በድርጅታችን ውስጥ ጤናማና ገንቢ ውይይት እንዲደረግ ይረዳል የሚል እምነት አለኝ። ከዚህም ውይይት በኋላ ልሳነ ግፉዓን ከቀደመው ይልቅ በርትቶና ገዝፎ መሪ የፖለቲካ ድርጅት ሆኖ ይወጣል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ።

በመጨረሻም እዚህ ላይ ለቀረቡት ሃሳቦችና ጉዳዮች በሙሉ ሃላፊነቱ የእኔ የአብዩ በለው ጌታሁን ቢሆንም እንደ ማንኛውም ሰው ደካማና በህፀፅ የተሞላሁ በመሆኔ ማንኛውንም ስህተት ቢገኝ በቅንነትና ባለማወቅ የተደረግ በመሆኑ ለተፈጠሩት ስህተቶች ሁሉ በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ። በፁሁፌ ውስጥ የተወላገደውን ሃስብ አቃንታችሁ፣ የጎደለውን ሞልታችሁ በሙሉና በወንድማዊ ቅንነት የድካሜን ፍሬ ታጣጥሙ ዘንድ በአክብሮት እጋብዛለሁ።

አብዩ በለው ጌታሁን

ሰኔ 2009 ዓ.ም (ኮሎምበስ/ኦሃዮ)

ልሳነግፋዓን ድርጅት በተለያዩ ወቅቶች ያወጣቸው መግለጫዎች ናሙና

  1. የልሣነ ግፉዓን ድርጅት መቋቋምን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ …………………………………. November 26 2009
  2. አቶ አባይ መንግሥቱ ወልቃይትን በሚመለከት ከግንቦት 7 ራድዮ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ……………Dec 1 2009
  3. “To the government & people of Sudan” ለሱዳን መንግሥት የቀረበ አቤቱታ …………………….. Janu 10 2010
  4. የዘር ማጽዳት (Ethnic Cleansing) ዘመቻ፡ በወልቃይትና በጠገዴ ማህበረሰብ ላይ!…………………..March 12 2012
  5. የኢትዮጵያ ገዳማትና ካህናቱ ስለሚደርስባቸው ዘርፈብዙ የመብት ረገጣና የሰበአዊ መብት ጥሰት……April 8 2012
  6. አቶ ጎሹ ገብሩና አቶ ቻላቸው አባይ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ………………………. June 15 2012
  7. የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ተቃዋሚዎችን በማፈን የኢትዮጵያን የነጻነት ትግል አያስቆምም! …….. Aug 17 2014
  8. አቶ ቻላቸው አባይና እና አቶ ፈረደ በኤስቢስ ቃለ መጠይቅ ………………………………………………………… Dec 14 2015
  9. የደም አፍሳሾች ሸንጎና የህወሃት የዘር ፍጅት አዋጅ በወልቃይት ጠገዴ ላይ ……………………………………Feb 24 2016
  10. ይድረስ ለመላው የአማራ ህዝብ ! የህወሃትን ወረራ በፋሽስት ጣሊያን ሚዛን መዝነው !…………………..May 2 2016
  11. የጎንደር ህዝብ ያከሸፈው የፋሽስቱ ህወሃት ወረራና የአጫፋሪዎቹ ጫጫታ……………………………………. July 20 2016
  12. ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ! ውድ ልጆቻችሁን ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አማራ ክልል እንዳትልኩ!…Sep 21 2016
  13. የህዝባችን ጥያቄ ምላሽ የሚያገኘው በህዝባዊ መንግስት ምስረታ ብቻ ነው!!!……………………………….. Oct 07 2016
  14. ለፋሽስቱ ህወሃትና ግብረ በላዎቹ “አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” “አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል” እንዳይሆን !…..Oct 19 2016
  15. ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ ትግል፡ በታላቅ ድል ያሸበረቀና ማይቀለበስ የትውልድ ተቀዳሚ አጀንዳ – Dec 27 2016
  16. የህወሃት ድራማ ተዋናኞች ሆይ!  እጃችሁን ከወልቃይት ላይ አንሱ!………………………………………………Janu 24 2017

ወልቃይትን አስመልክቶ በአባላቱ የቀረቡ ጽሁፎች ናሙና

  1. «ደግሞስ ወደ መንግስት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደሆን ማን ያውቃል? » (ከአብዩ በለው)……Oct 2010
  2. ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር ! የወልቃይትና የጠገዴ ማህበረሰብስ? (ከአብዩ በለው) ………………….. Dec 16 2011
  3. ወልቃይት ጠገዴ ማነው? (አባይ፣ ጎሹ፣ ቻላቸው፣ አብዩ) ……………………………………………………………….Janu 28 16

The post ግልፅ ደብዳቤ ለልሳነ ግፉዓን ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የሀይል አሰላለፉ ጎራው ሲፈተሽ – “የኦሮሞ ብሔረተኝነት ፖለቲካ ከሌለ የትግራይ ህዝብ አደጋ ላይ ይወድቃል” ገብሩ አስራት

$
0
0

(ቬሮኒካ መላኩ)

የኦሮሞ ብሔረተኝነት ፖለቲካ ከሌለ የትግራይ ህዝብ አደጋ ላይ ይወድቃል” ገብሩ አስራት

ይሄን ከዚህ በላይ የተፃፈውን የተናገረው የቀድሞው ታጋይ እና የህውሃት ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበረው ገብሩ አስራት ነው።

በሌላ በኩል የቀድሞው የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ ከሁለት ወር በፊት ከOMN ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ላይ የ OMN ጋዜጠኛ:-

“ኦነግና አንተም በግልህ ረጅም አመታት ታግላችሁ ለኦሮሞ ህዝብ ያመጣችሁት ለውጥ አለ ብላችሁ ታስባላችሁ ወይ?” በማለት ሲጠየቀው አቶ ሌንጮ ቃል በቃል እንደዚህ በማለት መልሶ ነበር።

“ሀሌ ሉያ! የኦሮሞ ህዝብ እኛ ካሰብነው ከገመትነው በላይ ግዛት ያለው ክልል አግኝተናል። ይሄ ትልቅ ስኬት ነው።” በማለት መልሷል።

ዛሬ ይችን እጅግ አጨር ማስታወሻ ለመፃፍ የፈለኩት በተለይ ለአማራ ብሄርተኞች አሁን ያለውን የፖለቲካ ቡድኖች ያለውን የሀይል አሰላለፍ በመገንዘብ ትግላችንን መረር አድርገን እንድንየዘው ለማስታወስ ነው።

ወያኔ የአናሳ ( Minority) ቡድን ነው ።ማንኛውም አናሳ ቡድን ስልጣን ላይ ለመቆየት ዜዴ ያስፈልገዋል። አንዱ ዜዴ ጠመንጃ ነው ጠመንጃው አልሆን ሲል ከብዙሃን ጋር በመጣበቅ ነው።

ህውሃትና የኦሮሞ ብሄርተኞች በፖለቲካ የሀይል አሰላለፍ ብዙ ጊዜ ተመጋጋቢ ናቸው። ህውሃት የኦሮሞ ብሄርተኞችን እንደ ስትራቴጅካል አጋር ሲወስደው በአንፃሩ የኦሮሞ ብሄርተኞች በህውሃት እየተገደሉም ወደ እስር ቤት እየታጎሩም ቢሆን ከህውሃት በሚወረወርላቸው የፖለቲካ ቅንጥብጣቢ በመርካት ህውሃትን እንደ ስልታዊ አጋር ይመለከቱታል።

በዚህ የሃይል አሰላለፍ ውስጥ ሁለቱን ቡድኖች በዚህ ያልተቀሰ ጋብቻ ያቆራኛቸው እንደ አደጋ የሚቆጥሩት የአማራ ህዝብ ነው። እነዚህ ቡድኖች በአይነ ቁራኛ እና በጠላትነት የሚመለከቱት የአማራን የፖለቲካ ሀይል ነው። በህውሃት በኩል የኦሮሞ ብሄርተኞችን የሚጠቀምባቸው እንደ ስልጣን እድሜ ማራዘሚያ የፖለቲካ ኪኒን ሲሆን በኦሮሞ በኩል ከህውሃት የሚወረወረው ቅንጥብጣቢ እስካልቆመ ድረስ ህዝባቸውን የሚመጥን የአገርን መሪነት ቦታ የሚፈልጉ አይመስልም። የኦሮሞ ብሄርተኞች በኢትዮጵያ ለሚደረግ ስር ነቀል ለውጥ አጋር ሊሆኑ አይችሉም። የእነሱ ፍላጎት ስርአቱን በጥገናዊ ለውጥ እንድያደርግ በመርዳት በሂደቱ የፖለቲካ ትርፍራፊ መለቃቀም ነው።

በፖለቲካ አለም አንድ የተለመደ አባባል አለ “በፖለቲካ ውስጥ ዘላቂ ጥቅም እንጅ ዘላቂ ወዳጅም ሆነ ዘላቂ ጠላት የለም ።” ይባላል ። ይሄ አጠቃላይ የሆነ መርህ (General Principle) አሁን ባለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለአማራ ህዝብ የሚሰራ አይመስለኝም። ወያኔ ለአማራ ህዝብ ዘላቂ ጠላት እንጅ ጊዚያዊ ወዳጅ መቼም ሊሆን አይችልም።

በዚህ የሃይል አሰላለፍ ለጊዜው አማራው ብቻውን ነው።

አማራው ምን ማድረግ አለበት?

አማራ አሁን ካለው የፖለቲካ ንቃት በተጨማሪ እንደ እሳት የሚንቀለቀልና አስፈላጊ ሲሆን እንደ ቮልካኖ የሚፈነዳ ብሄርተኝነት ማዳበር አለበት።

ጀርመናዊው የማህበረሰብ ፈላስፋ Max Weber “The future will be an Iron Cage” እንዳለው ወደ ፊት ከጠላቶቹ ጋር በዚህ ተመሳሳይ የጉስቁልና እና የጨቋኝ ተጨቋኝ ድራማ የሚያበቃበትና ለውጥ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፤ ከለውጡ ቅኝት ጋር ተስማሚ የሚሆን አቋም በመያዝ፤ ለለውጥ ፈላጊው የአማራ ህብረተሰብ ጥያቄ ምላሽ በሚሰጥ አኳኋን ራሳችንን አስተካክለን በመሄድ፤ በፖለቲካዊ ግጭት ምክንያት ሊፈጠር የሚችልን አደጋ በመቀነስ ብሎም በአሸናፊነት ለመወጣት ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ ነው።

The post የሀይል አሰላለፉ ጎራው ሲፈተሽ – “የኦሮሞ ብሔረተኝነት ፖለቲካ ከሌለ የትግራይ ህዝብ አደጋ ላይ ይወድቃል” ገብሩ አስራት appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

በአማራ ሕዝብ ትግል ውስጥ የብሔርተኝነትና የጽንፈኝነት አቋም እጅግ አስፈላጊነት! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው 

$
0
0

ከዓመታት በፊት ጀምሬ ባቀረብኳቸው ጽሑፎች ሊያከራክር በማይችል መልኩ የምዕራቡን ዓለም ሐሳብ ላይ እንጅ የዘር ልዩነት ወይም ብሔረሰብና ጎሳ ላይ ያልተመሠረተን የሠለጠነ የፖለቲካ (የእምነተ አሥተዳደር) ተሞክሮ እንዲሁም የ26 ዓመታቱን የወያኔን አገዛዝ ተሞክሮዎችን በማነጻጸር ግልጥልጥ አድርጌ በማሳየት የዘር ልዩነት ላይ ወይም የጎሳና ብሔረሰብ ላይ የተመሠረተ አደረጃጀትን ተፈጥሯዊ ኢዲሞክራሲያዊነት (ኢመስፍነ ሕዝባዊነት) ፣ ኢሰብአዊነት፣ ኃላ ቀርና ጠባብነት፣ ፀረ የሀገርና የሕዝብ አንድነት መሆንን ሳስረዳ መቆየቴ፤ ከጊዜ በኋላም አማራ በማንነቱ የተደራጀው አማራነቱ እንደወንጀል ተቆጥሮበት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ስለተዘመተበት ህልውናውን ለመታደግ እንጅ እንደሌሎቹ ጎሳና ብሔረሰብ ተኮር ጅርጅቶች ጠባብ ለመሆንና የሀገርን አንድነትና ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል አለመሆኑን በሚገባ አስረድቻለሁና እዚህ ላይ ደግሜ ማብራራት አይጠበቅብኝም፡፡

አማራ በማንነቱ ስለመደራጀቱ፣ ስለ አማራ ብሔርተኝነት፣ ዛሬ ስለአስፈላጊነቱ ስለምገልጽላቹህ ስለ አማራ ጽንፈኝነት ቃላቶች (Terms) ስናሰማ በርካታ ሰዎች እነኝህን ቃላቶች ወይም ፅንሰ ሐሳቦች የሚረዱት የቃላቶችን ፅንሰ ሐሳብ ሌሎቹ የጎሳና ብሔረሰብ ድርጅቶች በሚያራምዱት አስተሳሰብና መረዳት እየታየብን የአማራ ሕዝብ ህልውናን የመታደግ ትግል ችግር ገጥሞታል፡፡ ይህ ችግርም እኛ የአማራን ህልውናውን ከፈጽሞ ጥፋት የመታደግ ትግልን ከማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር እንደሚጠበቀው ሁሉ ከአማራ ውጭ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም እንዲደግፉት ስንጠብቅ ጭራሽ አማራ የሆኑትም ትግሉን እንዳይቀላቀሉ እያደረገብን ይገኛል፡፡

ይህ በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ላይ የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲያዝና ትግሉ የሚጠበቀውን ያህል እንዳይጋጋል በማድረጉ እረገድ ሦስት አራት የሚሆኑ በአማራ ስም የተደራጁ የወያኔ ቅጥረኛ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል፡፡ እነኝህ ሐሰተኛ የአማራ ድርጅቶች የአማራ ብሔርተኝነትንና ጽንፈኝነትን ፅንሰ ሐሳቦች ሌሎች የጎሳተኮር ድርጅቶች በሚያራምዱት አስተሳሰብ ዓይነት እንዲታይበት አድርገዋል፡፡ እርግጥ ነው እነኝህ ቅጥረኛ ድርጅቶች የአማራ ሕዝብ በጥፋት ኃይሎች እየተወሰደበት ያለው እርምጃ አንሶት እራሱን በራሱ ሊያጠፋ በሚችልበት የተወሳሰበ ችግር ውስጥ ለማስመጥ የቅጥረኝነት ዓላማቸውን ለማስፈጸም አሳቢ ተቆርቋሪ መስለው እየሠሩት ያሉትን ዕኩይ የባንዳ ሥራ፣ ከአማራ ሥነልቡናና ማንነት ጋር ተቃርኖ ያለው አስተሳሰብ በአማራ ሕዝብ ዘንድ በመታወቁ የሕዝብ ተቀባይነትን ሊያገኙ ባለመቻላቸው ከእንግዲህ ማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛ ላይ ሲወራጩ እናያቸው ካልሆነ በስተቀር በሕዝብ ልብ ላይ ቦታ የላቸውምና የሚያንፀባርቁት አስተሳሰብ ፈጽሞ ከአማራ ሕዝብ የፈለቀ ተደርጎ ሊቆጠር አይገባም፡፡

በዚህ ጽሑፍ ላይ የአማራ ሕዝብ ትግል እንዴትና ለምን በብሔርተኝነትና በጽንፈኝነት መመራት እንዳለበት፣ የአማራ ብሔርተኝነትና ጽንፈኝነት እንዴትና በምን ከሌሎቹ የጎሳ ብሔረሰብ ተኮር ድርጅቶች እንደሚለይ እናያለን፡፡ እያወራን ያለው አማራ በአማራነቱ ብቻ በጥፋት ኃይሎች እንዲጠፋ ታውጆበት ተፈጻሚ እየተደረገበት ካለው ኢሰብአዊ ጥቃት እራሱን መታደግ ስለሚችልበት ጉዳይ ነው፡፡ ልብ በሉ ለአማራ መጠቃት መንስኤ የሆነው ማንነቱ ወይም አማራነቱ ነው፡፡ ለአማራ መጠቃት መንስኤ የሆነው አማራነቱ ከሆነ እራሱን ለማዳን ከአጥቂዎቹ ሲከላከል የሚከላከለው አማራነቱን ማለትም ባሕሉን፣ ወጉን፣ ሥርዓቱን፣ ሃይማኖቱን፣ አስተሳሰቡን፣ ፍልስፍናውን፣ ሥልጣኔውን፣ ቅርሱን፣ ማንነቱን አጠቃላይ እሴቶቹን ነው ማለት ነው፡፡ ብሔርተኝነት ማለት ይሄ ነው ሌላ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው ጤነኛ ያልሆነ ብሔርተኝነትም አለ፡፡ የአማራ ብሔርተኝነት እንደዚያ አይደለም፡፡ አማራ ብሔርተኛ ሳይሆን ለእነኝህ እሴቶቹ ሊቆጭ ሊቆረቆር ሊታገል አይችልም፡፡ የአማራ ብሔርተኝነት ማለት ለእነኝህ እሴቶች ተጠብቆ መኖር አስፈላጊውን ዋጋ ለመክፈል መነሣሣት ማለት ነው፡፡ አማራ ለመጠቃቱ ምክንያት ስለሆነው ስለአማራነቱ ሳይቆጭ ሳይንገበገብ (ብሔርተኝነት ሳይሰማው) ሊታገልና እራሱን ከጥፋት ሊታደግ አይችልም፡፡ የአማራን ብሔርተኝነት ከሌሎቹ የሚለዩት አምስት ዋና ዋና ነጥቦች አሉ፦

1ኛ. የአማራ ብሔርተኝነት እራሱን እየተፈጸመበት ባለው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ጥቃት ፈጽሞ ከመጥፋት ለመታደግ የግድ መደረግ ያለበት በመሆኑ፡፡

2ኛ. የሀገርንና የሕዝቧን አንድነትና ህልውናን አደጋ ላይ የሚጥል፣ ለድርድር የሚያቀርብ ባለመሆኑ፡፡

3ኛ. እንደሌሎች ብሔርተኛ ኃይሎች ለሌሎች ብሔረሰቦችና ጎሳዎች ይሄንን ወይም ያንን ብሔረሰብ ወይም ጎሳ በመሆናቸው ብቻ ምንም ዓይነት ጥላቻ የሌለው በመሆኑ (የጥፋት ኃይሎች የጥፋት ዓላማቸውን ለማሳካትና ለማስፈጸም አማራን በተመለከተ ብዙ እየፈጠሩ የሚያወሩት ነገር አለ፡፡ እውነታው ግን በእጅጉ ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ የአሥተዳደር ሥርዓት በነበረባቸው በአውሮፓ፣ በእስያ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ያሉ የተለያዩ ብሔረሰቦችና ጎሳዎች ቋንቋቸው፣ ባሕላቸው፣ እምነታቸው፣ ማንነታቸው በገዥዎቻቸው በኃይል እንዲጠፋ ተደርጎ የገዥዎቻቸውን ቋንቋ፣ ባሕል፣ እምነት፣ ማንነት እንዲይዙ እንዲወርሱ ሲደረጉ ማንም ማየት እንደሚችለው ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የትኛውም ብሔረሰብም ሆነ ጎሳ በኃይል እንዲጠፋ ሳይደረግበት ቋንቋውን፣ ባሕሉን፣ እምነቱን፣ ማንነቱን እንደያዘ ይገኛል፡፡ ይሄ ማለት ግን ብሔራዊ ቋንቋና ሃይማኖት ኢትዮጵያ ውስጥ አልነበረም፣ የመናቅ ችግርም አልነበረም ማለት አይደለም፡፡ መናቅ ወይም መናናቅ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባሕርይ ነውና የትም ሀገር ቢሆን እንኳን ጥንት ወደፊትም ይጠፋል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ምክንያቱ ይለይ ይሆናል እንጅ ይህ ችግር ሌላው ቀርቶ በአንድ ቤተሰብ አባላት መሀከል እንኳ ያለ ችግር ነውና፡፡ ብቸኛው የትግሬ ንጉሥ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ለሚከተሉት ሃይማኖት ቀንተው ሳይሆን መጨረሻ ላይ የሚያጠፏቸው ወይም ለሕልፈት የሚዳርጓቸው እስላሞች እንደሆኑ የተነገረ ንግርት ወይም ትንቢት ስለነበረባቸው ይሄንን ንግርት ያስቀሩ መስሏቸው ወሎ ወርደው ግራኝ አሕመድ ያሰለማቸውን የወሎ እስላሞችን በኃይል ክርስቲያን ለማድረግ ከሞከሩት ድርጊት በስተቀር አንድም ንጉሥ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔረሰቦችንና ጎሳዎችን በኃይል እምነታቸውን ብቻም ሳይሆን ቋንቋቸውንም፣ ባሕላቸውንም፣ ማንነታቸውንም እንዲቀይሩ አድርጎ አያውቅም፡፡ ስላልተደረገ ነው አሁን ድረስ ማንነታቸውን እንደያዙ ሊገኙ የቻሉት፡፡ ብሔረሰቦችና ጎሳዎች ቋንቋቸው፣ ባሕላቸው፣ እምነታቸው፣ ማንነታቸው በቅኝ ገዥ እንዳይጠፋና ያልተነካካ ማንነታቸውን እንደያዙ እንዲገኙ አማራ ተነግሮ የማያልቅ መራር መሥዋዕትነትን ነው ሲከፍል የኖረው፡፡ ከዚህም በላይ ጥንታዊ ርስቱን በተለያዩ ምክንያቶች ወደሀገር ለገቡ ብሔረሰቦችና ጎሳዎች አስረክቦ ተራራማ ሥፍራ የሰፈረ ቅን ሕዝብ ነው፡፡ ነገር ግን “የግፍ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ!” እንዲሉ ለዚህና ለሌላው ተነግሮ ለማያልቀው ውለታው ሁሉ አማራ የተከፈለው ዋጋ በገዛ ሀገሩ ተሳዳጅ ተባራሪ ከመሆን አልፎ ዘሩ እንዲጠፋ ማድረግ ነው፡፡)

4ኛ. ጠባብነትንና ጭፍን ወገናዊነትን ለራሱ እሴቶች ሳያሳይ እሴቶቹን የሀገር እሴት አድርጎ በማስመረጡ ሒደት ዳኝነትን ለልኅቀትና ለምሑራዊ ተዋስኦ በመስጠቱ፡፡

5ኛ. የቅጣት እርምጃውን ተጠያቂ በሆኑ አካላት ላይ ብቻ ያነጣጠረ በመሆኑ ወይም ጅምላ ጨፍጫፊ ባለመሆኑ ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የጽንፈኝነትን መንገድ መከተሉን የግድ አስፈላጊ የሚያደርጉ አምስት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦

ሀ.) ጠላቶቻችን እኛን ለማጥፋት የተነሡበት ቁርጠኝነት ጽንፈኛ በመሆኑና እሾህን በእሾህ እንዲሉ ጽንፈኛ ጥቃትን በጽንፈኛ የመከላከል እርምጃ ካልሆነ በስተቀር በልማዳዊ ወይም ለዘብተኛ አካሔድ መመከትና መከላከል ብሎም መቀልበስ ፈጽሞ የሚቻል ባለመሆኑ፡፡ ለዘብተኛው አኪያሔድ በጥይት አረር የሚፈጅን ጠላት በብትር ወይም በቆመጥ ለመመከት የመሞከርን ያህል ጅልነት ስለሆነ፡፡

ለ.) በአማራ ላይ ጽንፈኛ አቋም የያዙ የጥፋት ኃይሎች ካልጠፉ ካልተደመሰሱ በስተቀር ይሄንን ዕኩይና ጽንፈኛ አቋም ዓላማቸውን የሚተው ባለመሆናቸው፡፡ አቅም አንሷቸው ወይም ሁኔታው ሳይመቻቸው ቀርቶ የሆነ ወቅት ላይ የተዉ ቢመስሉ ምቹ ሁኔታ ባገኙ ጊዜ ይሄንን የጥፋት ጽንፈኛ ዓላማ አቋማቸውን መልሰው የሚያነሡ በመሆናቸው፡፡

ሐ.) አማራ በመሆናቸው ብቻ ከሕፃናት እስከ አረጋውያን በጥፋት ኃይሎች የተፈጁ ወይም እንዲጠፉ የተደረጉ ወገኖቻችን ደም መመለስ ስላለበት ወይም ደመከልብ ሆኖ መቅረት ስለሌለበት፡፡

መ.) አማራ በተለያየ ጊዜ በሆደሰፊነት ያጣውን የተነጠቀውን ጥቅሙን እውነትን ታሪክን መሠረት ባደረገ ፍትሐዊ አሠራር መልሶ ማግኘት እንዲችል የጥፋት ኃይሎቹና ደጋፊዎቻቸው ፈጽሞ የማይፈቅዱ በመሆናቸው፡፡

ሠ.) ጽንፈኛ አቋምና ፍጹም ግፈኛ የጥቅም ፍላጎት ያላቸውን የጥፋት ኃይሎች ከስር ነቅሎ በማጥፋት ሀገራችንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከነዚህ የጥፋት ኃይሎችና ጠንቀኛ አስተሳሰባቸው ነጻ ማድረግ መገላገል አስፈላጊ በመሆኑ የሚሉት ናቸው፡፡

ወገን ሆይ! ወያኔንና ሌሎች የጥፋት ኃይሎችን መቃወምና አለመደገፍ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ለውጥ ለማምጣት ከተፈለገ ተደራጅቶ መታገል የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህም በዚያም በየቦታው ብንንጫጫ ከመንጫጫት ባለፈ ምንም ጠብ የምናደርገው ነገር የለም፡፡ በዚህም በዚያም በየቦታው መንጫጫታችንን እንደትልቅ ግብ ቆጥረን እሱላይ ብቻ ማተኮራችን ለውጥ ሊመጣ የሚችልበትን መላ እንዳናይ አድርጎናል፡፡ ሲጀመር ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔና በሌሎች የጥፋት ኃይሎች ማንነት ላይ ለአንድም ቀን ቢሆን ብዥታ ኖሮበት አያውቅም፡፡ ከማንም በላይ አሳምሮ ያውቃቸዋል፡፡ ሲጀመር የማናስተውል ሆነን ካልሆነ በስተቀር ግፉ የሚፈጸሙ በራሱ በሕዝቡ ላይ ሆኖ እያለ ሕዝቡ እንዴት አያውቅም ተብሎ ይታሰባል? የማያውቅ የመሰለው ማወቁን ማሳወቁ የሚያስበላው ስለሆነ ነው እንጅ ሕዝብ ወያኔንም ሆነ ሌሎችንም የጥፋት ኃይሎች አብጠርጥሮ ነው የሚያውቃቸው፡፡ በየቦታው እንደመንጫጫታችን ቢሆን ኖሮ ወያኔ እስከአሁን ድራሹ ጠፍቶ በነበረ፡፡ አሁን ባለንበት ሁኔታ ለውጥ፣ ስኬት፣ ድል ልናገኝ የምንችለው በየቦታው በመንጫጫት ወይም ሕዝቡ የሚያውቀውን እውነት መልሰን ለራሱ በመንገር፣ በማስተጋባት ሳይሆን በኅቡዕ ወይም በስውርም በግልጽም እንደሁኔታው አመችነት ተደራጅተን የታገልን እንደሆነ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ወያኔ ባይደራጅ፣ ሕዝቤ የሚለውን አደራጅቶ ባይታገልና ደርግን እያማረረ፣ እያወገዘ በመንጫጫት ብቻ ቢቀመጥ ኖሮ ዛሬ እዚህ የደረሰበት ደረጃ ላይ ባልደረሰ ነበር፡፡

ነባራዊ ሁኔታው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ባካተተ መልኩ ውጤታማ ትግልን መታገል ባለመፍቀዱ ፈዘንና ደንዝዘን እጅግ ብንዘገይም ዛሬ ላይ ቢያንስ እንዴት መደራጀት እንዳለብን አውቀን የተደራጀንበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ከተደራጀን በኋላ ግን ወያኔ ለስኬት በምንበቃበት መንገድ ላይ እንደቆምን ተረድቶ ትግላችንን ለማክሸፍ እንደ ቤተአማራ ያሉ ቅጥረኛ ድርጅቶቹን በአማራ ሕዝብ ስም አደራጅቶ ማሠማራቱ ይታወቃል፡፡ እነኝህ ቅጥረኛ ድርጅቶች ዛሬ ላይ ባወቅናቸው ደረጃ ቀደም ሲል ስላልታወቁና “የያዙትን አማራን ከኢትዮጵያ የመገንጠል የጥፋት የድንቁርናና የቅጥረኝነት አቋም የያዙት ከየዋህነትና ካለመብሰል ከሆነ እስኪ ቀርበን እንለውጣቸው!” በሚል ቅንና ኃላፊነት የተሞላበት ሐሳብ የአማራ ሕዝብ መድኅን ንቅናቄ (አሕመን) ይሄንን ውዳቂና ከአማራ ማንነት ጋር ተቃርኖ ያለውን አቋም አስተሳሰባቸውን እንደሚተው ቃል ካስገባ በኋላ ከቤተ አማራ እና ከአዴሀን ጋር ውሕደት ፈጽሞ “ቤተ አማራ መድኅን” የሚል ውሕድ ድርጅት ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም የወያኔ ቅጥረኞች ናቸውና “ትተናል!” ያሉትን የደነቆረ አስተሳሰብ እንደገና በማንሣታቸውና ለወያኔ በሰላይነት ላይ ተሠማርተው በመገኘታቸው
አደጋዎችን በመጋረጣቸው ምክንያት ዓመት እንኳ ሳይሞላ ውሕደቱ ሊፈርስ ችሏል፡፡ አሕመን ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ዝርዝር መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ የተጠበቀም ያልተጠበቀም ችግርና ፈተና ቢያጋጥምም ፈተና ትግል ውስጥ ከሚያጋጥሙ እንቅፋቶች አንዱና ዋናው በመሆኑ እንዲህና እንዲያ ያሉ የተለያዩ ዓይነት ፈተናዎች ቢያጋጥማቸውም የያዙት ትግል መሆኑን ጠንቅቀው ያውቃሉና፣ ከመጋፈጥ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ጠንቅቀው ያውቃሉና ይሄና ያ ችግር ተከሰተ ወይም አለና ብለው አሕመኖች አልበረገጉም አልተፍረከረኩም፡፡ አሕመን አንድ የተጠናከረ የአማራ ኃይል እንዲፈጠር ይፈልጋል፡፡ የግድ አስፈላጊ ነውና፡፡ በመሆኑም በሒደት ላይ ያሉ የኢትዮጵያን አንድነትና ህልውና ለድርድር ከማያቀርቡ በአማራ ሕዝብ ስም ከተቋቋሙ የአማራ ድርጅቶች ጋር የመዋሐድ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ስለ አሕመን ጥቂት መረጃ ለመስጠት ያህል ለአራት ዓመታት ያህል ጥልቅ ጥናት ከተደረገ በኋላ ከሁለት ዓመታት በፊት የተሟላ ሰብእና ያላቸው፣ በተቃውሞ ፖለቲካ ያለፉና ልምድ ያዳበሩ፣ ራሳቸውን ለትግሉ የሰጡና ዋጋ ለመክፈል የቆረጡ፣ በወገን ፍቅር የተቃጠሉ፣ የጠራና የበሰለ አቋም አስተሳሰብ የያዙ የተማሩና የጠነቀቁ ወጣቶች አሕመንን (የአማራ ሕዝብ መድኅን ንቅናቄን) መሥርተዋል፡፡ አሕመን ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ አባላትን በኅቡዕ ሲያደራጅ ቆይቷል፡፡ ይሁንና እነኝህ የወያኔ ቅጥረኞች የያዙትን የቅጥረኝነት አቋም እንዴት የአማራን ሕዝብ ሊጠቅም እንደሚችል አብራርተው ሊያስረዱ ሊገልጹ የማይችሉትን የማይሆን፣ የማይበጅ፣ የደነቆረ የመገንጠልን ሐሳብ እየነዙ ሕዝባችን ላይ በፈጠሩት ብዥታ ምክንያት ሕዝባችንን በማንነቱ ወይም በአማራነቱ ለማደራጀት አሕመን በሚያደርገው ጥረት የሚፈለገውን ያህል የሕዝባችንን ንቁ ተሳትፎ ማግኘት ችሏል ማለት አይቻልም፡፡ በውጭ ያለውም እንቅስቃሴ ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ወገን ሆይ! አሕመንን ተቀላቀሉ? ከምሁር እስካልተማረ፣ ከሴት እስከ ወንድ፣ ከሃይማኖት አባቶች እስከ ሕዝባዊ፣ ከተማሪ እስከ ሠራተኛ፣ ከነጋዴ እስከ ከያኔ ያላቹህ ሁላቹህም አማራና ኢትዮጵያዊነት ይበልጥብናል የምትሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መቀላቀላቹህ ግድ ነውና ጊዜ ሳታጠፉ አሕመንን (የአማራ ሕዝብ መድኅን ንቅናቄን) ትቀላቀሉ ዘንድ በፈጣሪ ስም በአክብሮት ትጠየቃላቹህ???

አማራን በአማራነቱ እንዲደራጅ በመደረጉም የአንድነት ኃይል ነን ከሚሉ አካላትም የሚመጣ ተቃውሞ አለ፡፡ አንድ ነገር ግን ግልጽ መሆን ይኖርበታል፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ፖለቲካ ሰፍኖ ብሔረሰቦችና ጎሳዎች ኢትዮጵያዊነትን ከመጣል አልፈው ኢትዮጵያዊነትን እየተዋጉ ባሉበት፣ የሀገሪቱን አንድነትና ህልውና አደጋ ላይ በጣሉበት ወቅት፣ የሀገሪቱ አንድነትና ህልውና መሠረትና ዋልታ የሆነው የአማራ ሕዝብ እንዲጠፋ ተፈርዶበት በአራቱም አቅጣጫ ሰፊ ዘመቻ እየተወሰደበት ባለበት ወቅት የአማራ ሕዝብ ዘግይቶም ቢሆን ኢትዮጵያን ከጥፋት ለመታደግ አስቀድሞ እራሱን መታደግ ቁልፉና አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ተረድቶ ህልውናውን ከፈጽሞ ጥፋት ለመታደግ በአማራነቱ ተደራጅቶ የሚያደርገውን ትግል መቃወም ወይም አለመደገፍ ማለት በእርግጠኝነት እነግራቹሀለሁ አማራ የሌለባት ወይም የጠፋባት ኢትዮጵያ እንድትኖር መስማማት ነው፡፡ አማራ በመጥፋቱ ውስጣቸው ደስተኛ ስለሆነ ካልሆነ በስተቀር ፖለቲከኞች (እምነተ አሥተዳደራውያን) ነን ካሉ በኋላ ይሄንን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ግፍ ሊያጋልጡ፣ ሊናገሩ፣ ሊያስተናግዱ የማይችሉበት ምን ምክንያት አለ?

አማራ በአማራነቱ ተደራጅቶ እያደረገው ያለውን የአማራን የህልውና ትግል እየተቃወማቹህ ያላቹህ ወገኖች አውቃቹህም ይሁን ሳታውቁ እያደረጋቹህ ያላቹህት ይሄንን እንደሆነ ጠንቅቃቹህ ልታውቁት ይገባል፡፡ አማራ ያልሆነው በዚህ ጉዳይ ላይ ቢስማማ ላያስደንቅ ይችላል፡፡ “አማራ ነኝ!” የሚሉ ሆነው እያለ ግን አማራ የጠፋባት፣ የተወገደባት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር መስማማት ወይም መፍቀድ ግን እጅግ አሳፋሪ፣ አስገራሚና የሚያቅለሸልሽ ጉድ አይደለም???

ሲጀመር በአማራ ላይ በሰፊው እየተወሰደ ያለውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ የሚቃወም፣ የሚያወግዝና የሚያንገበግበው የአንድነት ኃይል ቢኖር እኮ አማራ በአማራነቱ ተደራጅቶ እራሱን ከመጥፋት ለማዳን መታገሉ አስፈላጊ ባልሆነ ነበር፡፡ የሆነውና እየሆነ ያለው ግን የዚህን ተቃራኒ በመሆኑ ነው በአማራነቱ ለመደራጀት የተገደደው፡፡ “የአንድነት ኃይል ነን!” የሚሉ ኃይሎች ከፊሎቹ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ከፈጸሙ እንደ ኦነግና ትሕዴን ካሉ የጥፋት ኃይሎች ጋር ጥምረትና አንድነት ሲፈጥሩ፤ ከፊሎቹ ደግሞ ይሄንን በአማራ ሕዝብ ላይ እየተወሰደ ያለውን በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት የመጨረሻ ወንጀል እንኳንና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሊያጋልጡ ሊያስታውቁ ይቅርና ለገዛ ራሳቸው እንኳ ቢሆን ለአንድም ጊዜ ነግረውት የሚያውቁ አይደሉም፡፡ አፍነው ይዘው ነው ያስፈጁን፡፡ እጅግ የሚገርመው ነገር ደግሞ ጉዳዩ አሁንም እንደተዳፈነ ተፈጅተን እንድናልቅ ይፈልጋሉ፡፡

ያለው ሸፍጥ እንዲህ በሆነበት ሁኔታ የአማራ ሕዝብ እንዴት ሆኖ ነው ይሄንን ሸፍጥና ግፍ በጸጋ ተቀብሎ በዝምታ ሊመለከትና ድምፅ ሳይሰማ እንዲያልቅ የሚፈቅደው??? ወይ አጀንዳውን (ርእሰ ጉዳዩን) እናንተው በአግባቡ አልያዛቹህት! ይሄንን ማድረግ ካልቻላቹህ ደግሞ የአማራ ሕዝብ ተደራጅቶ የራሱን ጉዳይ እራሱ ይዞ መንቀሳቀሱን በምን ሞራላቹህ (ቅስማቹህ) ነው ልትነቅፉ፣ ልትቃወሙ፣ ልታወግዙ የምትችሉት??? ትንሽ እንኳን አታፍሩም??? ይሄ በደላቹህ ጠላት ካደረሰብን ግፍ የማይተናነስ እንደሆነ አታስተውሉም??? ኧረ ተው ተው ግፋቹህን በልክ አድርጉት??? ትንሽም ቢሆን እፍረት ይኑራቹህ???

እርግጠኛ ነኝ ዛሬ ላይ የአማራን አስገዳጅ ህልውናን የመታደግ ትግል እየተቃወሙ ካሉ አማሮች ሁሉም እንዲሁም ደግሞ ሰብአዊነትና ኢትዮጵያዊነት የሚሰማው ሌላው ዜጋ ዘግይታቹህም ቢሆን ነገሩ ይገባቹህና የኋላ ኋላ በሁኔታዎች አስገዳጅነት ይሄንን የአማራን ህልውናውን በመታደግ ኢትዮጵያን የመታደግ ትግል መቀላቀላቹህ ወይም መደገፋቹህ አይቀርም፡፡ ይሁንና ይሄንን መረዳት በምታገኙበት፣ በምትገነዘቡበት ወቅት ግን ወቅቱ በጣም የረፈደ ወይም የዘገየ ስለሚሆን ልትፈይዱ የምትችሉት ነገር ስለማይኖር እባካቹህ ነገ ነገሩ ሲገባቹህ መንቃታቹህና ለመቀላቀል መወሰናቹህ ላይቀር ነገር ለአዋቂ አንዲት ነገር ትበቃዋለችና በግልጽ ፈጠው የሚታዩ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ነገ ሳይሆን ዛሬ እንንቃና በመዘግየታችን ሊደርስብን የሚችለውን አላስፈላጊ የሆነ ከፍተኛ ጉዳትና ኪሳራ በማስቀረት እንታገልና በንጹሐን ደም የሚታጠቡትን የጥፋት ኃይሎችን፣ የኢትዮጵያ ጠላቶችን ጠራርገን እናጥፋ! ህልውናችንንም እንታደግ፡፡

ግድ የላቹህም በኔ ይሁንባቹህ ሀገራችን ኢትዮጵያን ልንታደጋት የምንችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቢሆን ደስ የሚል ነገር ግን የማይጨበጥ ሕልምና ምኞት ብቻ ነው፡፡ ይሄንን አትጠራጠሩ! ሞኞችም አትሁኑ፡፡ ትሰሙኛላቹህ? እንክርዳድ ተዘርቶ እያለ ስንዴን ለማፈስ ከመጠበቅ በላይ ምን ሞኝነትና ጅልነት አለ? ብዙ የማታውቁት ነገር አለ እንዴት ብየ ልግለጽላቹህ? ሁሉም እኮ አይነገርም፡፡ ዓይናቹህ የሚያየውን ጆሯቹህ የሚሰማውን ልብ ብትሉት እኮ ይሄ ሁሉ ጉድ ለመንቃት ከበቂ በላይ አንቂ ነገር ነበረ እኮ!

ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ በአራቱም አቅጣጫ ከገጠር እስከ ከተማ ተዘዋውራቹህ ብትመለከቱ በአማራ ላይ በኢሰብአዊ ርምጃዎች ታጅቦ እየተፈጸመ ያለው ጥላቻ እጅግ አስደንጋጭ ሆኗል፡፡ ይህ ግፍ ከአማራም ተሻግሮ አልፎ አልፎ በሚታዩ ኢትዮጵያዊነትን በሚያቀነቅኑ የሌላ ብሔረሰብ ወይም ጎሳ አባላት ላይም እየተፈጸመ ነው ያለው፡፡ ከሀገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያን ወዳጅ ኢትዮጵያውያንና ወያኔ የአማራ ክልል ብሎ ከሚጠራው የሀገራችን ክፍል ወጥተው የማያውቁ አማሮች ምን እየተካሔደ እንዳለ ቢያውቁም በሆነ ተአምር ነገሮች ድሮ በነበሩበት እንዲገኙ ካላቸው የዋህ ምኞት የትግላችንን አቅጣጫ ለመቀበል እየተቸገሩብን ተቸግረናል፡፡ ነገሮች አሁን ያሉበትን ሁኔታ ለመረዳት ራሳቸውን ንቁ በሆነ የግንዛቤ ዐውድ ላይ ባለማስቀመጣቸውና ከነባራዊ ሁኔታዎች አንጻር እራስን በጊዜው ካለው ሁኔታ ጋር ማጣጣም (making self update) አለመቻል ካልሆነ በስተቀር በተለያየ መንገድ ከሚሰሙትና ከሚያዩት ነገር ዛሬ ያለው እውነታ እነሱ ከሚያስቡትና ከሚመኙት በእጅጉ የተለየ መሆኑን ለመረዳት ሳይችሉ ባልቀሩም ነበረ፡፡ ሁኔታው የዚህን ያህል እጅግ አሳሳቢ በሆነበት ሁኔታ ይሄንን ያህል መዘናጋትንና መጃጃልን ምን ይሉታል??? ነገሩ “ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰምባትም አትሰማ!” ሆኖብህ ይሆን ወገኔ??? ኧረ ከዚህ ያውጣን በሉ! በቃ እመኑንና አብረን እንታገል??? ተዉ በኋላ ይቆጫቹሀል ተዉ ተዉ ተዉ???
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

The post በአማራ ሕዝብ ትግል ውስጥ የብሔርተኝነትና የጽንፈኝነት አቋም እጅግ አስፈላጊነት! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው  appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

“በአፋን ኦሮሞ” አማካኝቶ ማስተር ፕላኑን በጓሮ በር – (ከኤርሚያስ ለገሠ)

$
0
0

ህውሃት ለሁለት የተሰነጠቀ ሰሞን ጐልተው ከታዩ ባህሪያት አንዱ የኦህዴድ ካድሬዎች “የኦሮሞ ብሔርተኝነት ” ካርድ የመዘዙበት ነበር። እነ ኩማ ደመቅሳ እና ግርማ ብሩን ጨምሮ በመዘዙት ካርድ “የትግራይ የበላይነት ሊውጠን ነው” በማለት ወደ ስልጣን ጫፍ ( ጠቅላይ ሚኒስትርነት ጨምሮ) ለመቆጣጠር የተጉበት ነበር።

እናም በእነ ግርማ ብሩ የተመራው ቡድን የኦሮሞ ብሔርተኝነት ይቀሰቅሳል ብሎ ያሰበውን እቅዶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፋ አደረገ። ከእነዚህ ተግባራት አንዱ በአዲሳአባ የሚሰሩ ሥራዎች ተለይተው የቀረቡበት ነበር። ከስራዎቹም ውስጥ አንዱ ” በአዲሳአባ አምስት ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 28 ወረዳዎች በአፋን ኦሮሞ የሚያስተምሩ 28 አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች መክፈት” የሚል ነበር። በነገራችን ላይ በወቅቱ አዲሳአባ በአምስት ዞኖች እና 28 ወረዳዎች የተከፈለችበት ነበር።
እነዚህ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው እስኪያልቁ አምስቱም ዞኖች በአጣዳፊነት ነባር ትምህርት ቤቶችን በመለየት ለጐልማሶች የማታ፣ ለህጻናት እና ታዳጊዎች የቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በክረምት ኢ_መደበኛ ትምህርት እንዲጀመር ጥብቅ ኦህዴዳዊ ትእዛዝ ተላለፈ። በድርጅት ቋንቋ መደብ ወረደ። መደቡን ለማስፈፀም ደግሞ የአዲሳአባ ካቢኔ የነበሩት ሊቀመንበር አሊ አብዶ ፣ ሀይሉ ደቻሳ ፣ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ( የአፈ ጉባኤ ደግፌ ቡላ ባለቤት እና በኋላ ላይ በአዜብ መስፍን ከም/ል ሚኒስትርነት የተባረረች የምንወዳት እህታችን) እና አምባሳደር ሰለሞን ተመደቡ። ተግባሩ በቁልፍ ደረጃ በመቀመጡ ስራውን ያንጠባጠበ ካድሬ በኦህዴድነት መቀጠል እንደማይችል ተገለፀ።

በየቀበሌው የሚገኝ ካድሬ ቤት ለቤት እያሰሰ የኦሮሞ ዘር አለው የሚለውን አዲስአበቤ እንዲመዘግብ አደረገ። እንደ መሰረተ ትምህርት ዘመቻ ፍቃደኛ ያልሆነውን ማስገደድ ተጀመረ። በደርግ ጊዜ ዝነኛው ቆምጬ አምባው ” አስኳላ የማይሄድ ቡዳ ነው!” ያለውን በተሞክሮ በመውሰድ የአዲሳአባ ኦህዴድ ካድሬዎች ” አፋን ኦሮሞ የማይማር የነፍጠኛ ተላላኪ ነው!” የሚል ማዕከላዊ መልእክት ቀርፀው በጥቅም ላይ አዋሉ።

ስራው በተጀመረ የመጀመሪያው ወር የተመረጡት አምስት ትምህርት ቤቶች በምሽቱ ክፍለ ጊዜ ከጠቅላላው አዲሳአባ በአማካይ 500 ተማሪ ተገኘ። ቅዳሜ እና እሁድ በተዘጋጀው የህጻናት፣ ታዳጊዎች እና ወጣቶች ክፍለጊዜ በአማካይ አንድ ሺህ የሚጠጋ ተገኙ። የኦህዴድ አብዮታዊ ካድሬዎች አጀማመሩ ጥሩ እንደሆነ ገመገሙ።

ስራው በተጀመረ ሶስተኛው ወር የምሽቱ 60 ፣ የሰንበቱ ወደ 90 ተማሪ ብቻ ቀረ። አምስቱ ትምህርት ቤት ታጥፈው በዞን ሁለት ውስጥ ወደ ሚገኘው ተግባረ እድ ትምህርት ቤት እንዲጠቃለል ተደረገ። በአራተኛው ወር እንደ ኮንደሚኒየም ወደ 40/60 ተቀየረ። አካሄዱ አስደንጋጭ የሆነበት ኦህዴድ ” ሁሉም ዜሮ ዜሮ” መመዝገቡ በፊት ትምህርቱ ባልተገለፀ መመሪያ እንዲቀር ተወሰነ።

ከሁሉም የሚገርመው ነገር አዲሳባ የሚኖር አንድም የኦህዴድ ባለሥልጣን ልጆቹን አፋን ኦሮሞ እንዲማሩለት አልሰደደም። በክረምቱ ክፍለጊዜም ሆነ በሰንበት ባለሥልጣናት ልጆቻቸውን የሚልኩት የእንግሊዘኛ እውቀታቸውን የሚሳድጉበት ከ3ሺህ ብር በላይ የሚከፈልባቸው ውድ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ቤቶች ነበር። አንዳንዶቹ ከቋንቋው በተጨማሪ ልጆቻቸው እንዲዝናኑ የሚልኩት ወደ ትውልድ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ሳይሆን ወደ ሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ ነበር ። አሁንም የተቀየረ ነገር ያለ አይመስለኝም። እንደውም እየሰማን ያለነው በሌብነት እና መሬት ችብቸባ ኪሳቸው ያበጠ የኦሮሚያ ዞን እና ወረዳ ካድሬዎች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት አዲሳባ ቤት ተከራይተው እጅግ በጣም ውድ በሆነ ” ከእንግሊዘኛ ውጭ መናገር ክልክል ነው!” የሚል ማስታወቂያ የተለጠፈበት ትምህርት ቤት እንደሆነ ነው። ተወደደም ተጠላ መሬት ላይ ያለው እውነታ ይሄ ነው።

ከአዲስአባ አወቃቀር አኳያም የተቀየረ ነገር የለም። አዲስአበቤ እንኳን በሕውኃት ድርጅታዊ መመሪያ የተላከለትን ቀርቶ ሌላውንም ቢሆን በጥሞና የሚመለከት አስተዋይ ህዝብ ነው። (” ወርቅ ህዝብ ነው!” ብዬ ልገልፅ ነበር፣ ኩረጃ ይመስልብኛል ብዬ ተውለኩት።) ያለማጋነን አዲስአበቤ የህውሓትን አካሄድ እና አላማ ከመገንዘብና ከመታገል አኳያ የቀደመው የለም።

እናም ዛሬ ” የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ” በሚለው አባይ ፀሐዬና በረከት ስምኦን የፃፈው አዋጅ ላይ ” አስተዳደሩ በአፋን ኦሮሞ ልጆቻቸውን ማስተማር ለሚፈልጉ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ማደራጀት አለበት” የሚል ተፅፎ ስመለከት የተሰማኝ ከላይ የተገለጠው ነው። እነ አባይ በዚህ አዋጅ አማኸኝተው ማስተር ፕላኑን በጓሮ በር ማስገባታቸው እንዳይታወቅ “የዶሮን ሲያታልሏት” ማታለያ ይዘው ብቅ ማለታቸው እርስ በራስ ለማጋጨት ነው። ሌሎች የህጉ እሳቤዎች መሰረታዊ ምንጫቸው ይሄ እና ይሄ ብቻ ነው።

The post “በአፋን ኦሮሞ” አማካኝቶ ማስተር ፕላኑን በጓሮ በር – (ከኤርሚያስ ለገሠ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


“የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማስከበር” እያሉ በነፃ አሳልፎ መስጠት አለ እንዴ? – ስዩም ተሾመ

$
0
0

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ አራት ግዜ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል “እምብርት ላይ የምትገኝ በመሆኗ” ይላል። የሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 49 (5) ግን አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል “መሃል” የሚገኝ መሆኑን የሚጠቅሰው “ሁለቱን በሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮች” ሊኖሩ እንደሚችሉና በዚህም የክልሉ ልዩ ጥቅም ሊጠበቅለት ስለሚገባ ነው። የሕገ-መንግስቱ ድንጋጌ ታሳቢ ያደረገው አዲስ አበባ የክልሉ “እምብርት” በመሆኗ ላይ አይደለም።

በ54ሺህ ሄክታር መሬት ላይ፤ ከ3 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች፣ የክልልና የፌደራል መንግስት ተቋማት፣ እንዲሁም የአህጉራዊና ዓለም-አቀፋዊ ድርጅቶችና ሰራተኞች በውስጧ ይዛ አስፈላጊውን አገልግሎት እና የተፈጥሮ ሃብት (Natural Resource) አቅርቦት ሊኖራት እንደማይችል ሳይታለም የተፈታ ነው። ይህቺ ከተማ በኦሮሚያ ክልል ሸዋ፥ ባሌ ወይም ወለጋ፣ በአማራ ክልል ጎጃም፥ ጎንደር ወይም ሰሜን ወሎ፣ በደቡብ ወላይታ፥ ሲዳማ ወይም ሃድያ፥… ወዘተ፣ በየትኛውም የሀገራችን አከባቢ ብትገኝ በዙሪያዌ ካለው ክልል ጋር በአገልግሎት አቅርቦትና የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ረገድ የጥቅም ትስስር ይኖራታል።

አንቀፅ 49(5) በዋናነት ታሳቢ ያደረገው ነገር የፌደራሉ ዋና ከተማ በኦሮሚያ ክልል መሃል የምትገኝ ስለሆነ በመካከላቸው የጥቅም ትስስር ሊኖር እንደሚችል ነው። በተለይ በ54ሺህ ሄክታር ይዞታ ያላት አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ የሚያስፈልጋትን አገልግሎት እና የተፈጥሮ ሃብት በራሷ አሟልታ ማቅረብ አትችልም። ስለዚህ፣ የአዲስ አበባ ከተማ በራሷ በቂ የሆነ የተፈጥሮ ሃብት ስለሌላት እና በኦሮሚያ መሃል የምትገኝ እንደመሆኗ መጠን እነዚህን አገልግሎቶች እና የተፈጥሮ ሃብቶች ከክልሉ ታገኛለች። በመሆኑም፣ በሁለቱ መካከል በአገልግሎት አቅርቦት እና በተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ረገድ የጥቅም ትስስር ይኖራል። ይህን ታሳቢ በማድረግ “የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና በመሳሰሉት ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል” በማለት ይደነግጋል።

በመሰረቱ፣ ከአገለግሎት አቅርቦትና የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ መካከል ያለው ግንኙነት በዋናነት በስነ-ምጣኔ (Economics) መርህ ላይ የተመሰረተ ነው። ከተማዋ እያደገ የሚሄድ የአገልግሎትና የተፈጥሮ ሃብት ፍላጎት (demand) አላት፣ የኦሮሚያ ክልል ደግሞ አቅርቦት (Supply) አለው። ከተቆረቆረችበት ግዜ አንስቶ ለአንድ ክፍለ ዘመን ያህል አዲስ አበባ የሚያስፈልጋትን ለመጠጥ ውሃ፣ ለመኖሪያ ቤት፥ ለአገልግሎት መስጫ ተቋማት እና ለመሰረተ-ልማት ግንባታዎች የሚያስፈልጋትን የተፈጥሮ ሃብቶች ያለ በቂ ክፍያና ካሣ ስታገኝ ኖራለች። የሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 49(5) ይህን የተዛባ ግንኙነት መቀየር አለበት በሚል እሳቤ የተደነገገ ነው። ስለዚህ፣ ከተማዋ የተጠቀሱትን አገልግሎቶችና ጥሬ ሃብቶች ያለ በቂ ክፍያ ወይም በነፃ እያገኘች መቀጠል የለባትም።

ከላይ በተጠቀሰው የስነ-ምጣኔ ትስስር ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ የአገልግሎትና የተፈጥሮ ሃብት ተጠቃሚ (service and natural resource consumer) ስትሆን የኦሮሚያ ክልል ደግሞ አቅራቢ (supplier) ነው። ስለዚህ፣ የኦሮሚያ ክልል ከአገልግሎት አቅርቦትና የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ሊከበርለት የሚገባው ልዩ ጥቅም “ለከተማዋ ለሚያቀርበው አገልግሎትና የተፈጥሮ ሃብት ተገቢ ዋጋ (reasonable price) ሊከፈለው ይገባል” የሚለው ነው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ስለሚኖረው ኢኮኖሚያዊ አገለግሎት ልዩ ጥቅምን በተመለከተ የመሬት አቅርቦት፣ የውሃ አገልግሎት አቅርቦት፣ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻዎች የማስወገድ አገለግሎት፣ እንዲሁም የገበያ ማእከላት አቅርቦትና አርሶ አደሩ ለልማት ተነሺ ሲሆን በቂ ካሣ የማግኘትና በዘላቂነት የማቋቋም አገልግሎት፣…ወዘተ” በማለት ይዘረዝራል።

በእርግጥ እያንዳንዱ የአዲስ አበባ ነዋሪ ለንፁህ ውሃ አገልግሎት በፍጆታው ልክ ይከፍላል። ይህ ውሃ ከአዲስ አበባ ከርሰ-ምድር የወጣ ወይም ከሰማይ የዘነበ ሳይሆን ከኦሮሚያ ክልል የተገኘ የተፈጥሮ ሀብት ነው። ከላይ በተገለፀው የስነ-ምጣኔ መርህ መሰረት፣ አዲስ አበባ ከተማ ከኦሮሚያ ከርሰ-ምድር ለምታገኘው ለእያንዳንዷ ሊትር ውሃ ተገቢውን ክፍያ መክፈል አለባት። የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሻ አገልግሎት ድርጅት ንፁህ የመጠጥ ውሃን ከኦሮሚያ ከርሰ-ምድር በነፃ እየቀዳ ለአዲስ አበባ ነዋሪ እየሸጠ ገቢውን ለብቻው ይሰበስባል። ለምሳሌ የዛሬ አራት አመት የመስተዳደሩ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት አቅርቦቱን ለማሻሻል በየአመቱ ከ2ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ይመድባል።

የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማስከበር በሚል በወጣው አዋጅ መሰረት የክልሉ ጥቅም “የውሃ ጉድጓዱ በሚቆፈርበት እና የውሃ መስመሩ አቋርጠው በሚያልፍባቸው ከተሞችኛ አና ቀበሌዎች የመጠጥ ዉሃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ” ብቻ እንደሆነ ተጠቅሷል። ለሁለትና ሶስት ቀበሌ ነዋሪዎች የውሃ ቧንቧ በመዘርጋት ብዙ ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በነፃ እየቀዳህ ለሦስት ሚሊዮን ተጠቃሚ መሸጥና በቢሊዮን የሚቆጠር ብር መሰብሰብ የሚቻለው በየትኛው ዓለም ነው? ድንቄም ልዩ ጥቅም ማስከበር!

ሌላው የኦሮሚያ ክልል በከተማው ስለሚኖረው የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀምና የአካባቢ ጥበቃ ልዩ ጥቅም፤ “ከከተማው መሠረተ-ልማት አቅርቦት፣ ከመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ከደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ጋር የተያያዘ በተፈጥሮ ሃብት ላይና በአየርና ውሃ ላይ የሚደርስ ብክለት እንዳይኖር የሚያደርግና ይህንን መብት የማስጠበቅ” እንደሆነ ይጠቅሳል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የክልሉ ልዩ ጥቅም እንደሆነ ከተጠቀሱት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

“ለአዲስ አበባ ከተማ ልማት የግንባታ ማእድናት ማግኛ ሥፈራዎች የአየር ብክለት እንዳያስከትሉ እና ለደን ልማት ወይም ለሌሎች ልማቶች መዋል እንዲችሉ እንዲያገግሙ አንደሚደረጉ፣ ለአዲስ አበባ ከተማ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ማከሚያና ማስወገጃ ቦታዎች እንዲሁም መልሶ መጠቀሚያ ስፈራዎች አስተዳደሩና ክልሉ በጋራ ባጠኗቸው ቦታዎችና ሳይንሳዊ መስፈርቶችን ባሟሉ ሁኔታዎች እንዲተዳደሩ አንደሚደረጉ፣…”

ለአዲስ አበባ ልማት የግንባታ ማዕድናት ማግኛ ስፍራዎች ከሚወጣ የአየር ብክለት ሆነ የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች ከሚደርሱ የአካባቢ ብክለትና ጉዳት የመጠበቅ መብት በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 92 ላይ “የአከባቢ ደህንነት ጥበቃ አላማዎች” በሚል በግልፅ ተቀምጧል።የሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 49(5) የሚደነግገው የኦሮሚያ ክልል “ልዩ ጥቅም” እንዲጠበቅለት ነው። የኦሮሚያ ክልል ለአዲስ አበባ ከተማ ልማት የሚያስፈልጉ የግንባታ ማዕድናት እያቀረበ ትርፉ የአየር ብክለትና የደን ውድመት የሚሆንበት ምክንያት ምንድነው? ብክለትና ጉዳቱን መከላከል በሕገ-መንግስቱ መሰረት የተጣለ ግዴታ ነው። “ልዩ ጥቅም” ማለት ደግሞ “የክልሉ መንግስት ከእነዚህ ማዕድናት አቅርቦት ተገቢ የሆነ ዋጋ ሊከፈለው ይገባል” የሚል ነው።

በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ እንደ አዲስ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎች “አስተዳደሩና ክልሉ በጋራ ባጠኗቸው ቦታዎችና ሳይንሳዊ መስፈርቶችን ባሟሉ ሁኔታዎች እንዲተዳደሩ ይደረጋል” መባሉ በጣም ያስቃል። ምክንያቱም፣ የሰንዳፋ ዘመናዊ ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃም ቢሆን በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ምሁራን እና በሌሎች ተቋማት ተጠንቶና የቦታ መረጣ ተደርጎለት….ለወደፊት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ እኮ ነበር። የአዲስ አበባ ደረቅ ቆሻሻ በማስወገድ በየአመቱ ከ3 ሚሊዮን ብር በለይ የአገልግሎት ክፍያ ይሰበስባል። ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ወስዶ ከጣለው ደረቅ ቆሻሻ ደግሞ የኤሌክትሪካ ኃይል በማመንጨት ተጠቃሚ ይሆናል። በእርግጥ፣ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለመወሰን በወጣው አዋጅ መሰረት፣ “ቆሻሻ ለአዲስ አበባ ሃብት፣ ለኦሮሚያ ግማት ሆኖ ይቀጥላል። ይህ ረቂቅ አዋጅ በአዲስ አበባ ዙሪያ ላለው የኦሮሞ ሕዝብ ምን የተለየ ነገር ይዞ መጣ?

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ አመፅና ተቃውሞ የተነሳበት ምክንያት ምንድነው? “በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሞ አርሶ-አዶሮች በኢንቨስትመንት እና በመሰረተ-ልማት ግንባታ ሰበብ ያለ በቂ ካሣ እና የመልሶ-ማቋቋሚያ ድጋፍ ተፈናቀሉ። በዚህ ምክንያት በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ-አዶሮች ከነቤተሰቦቻቸው በድህነት አረንቋ ውስጥ እየተዘፈቁ ነው። እንደ ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ ከመሬታቸው ያለ መፈናቀል መብታቸው ይከበር…” የሚል ነበር። በአመፅና ተቃውሞ ግንባር ቀድም ከነበሩት አከባቢዎች ውስጥ የተውሰኑት ለመጥቀስ ያህል አምቦ፥ ወሊሶ፥ አለምገና፥ ቡራዩ፥ …. ተቃውሞው የነበረው በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነበር። በረቂቅ አዋጁ ቅድሚያ የተሰጣቸው ግን በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮሞ አርሶ አዶሮች ሳይሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ “ውስጥ” ለሚገኙ አርሶ አደሮች ነው፡-

“በከተማው ውስጥ ለበርካታ ጊዜያት የኖረው የኦሮሞ አርሶአደር ቁጥሩ ቀላለ ባልሆነ ሁኔታ በልማት ምክንያት ተነሺ ነበር፡፡ አሁንም ለልማቱ ተፈላጊ እስከሆነ ድረስ በማሳመን ይህንኑ መፈፀም የሚገባን ይሆናል፡፡ ዋናው ቁም ነገር ይህ ተነሺ አርሶ-አደር ቢያንስ ቢያንስ ከቀድሞ ኑሮ የተሻለ ሁኔታ ሊፈጠርለት ይገባል፡፡ በልማቱ ማስፋፋት ምክንያት ተጎጂ ሊሆን በጭራሽ አይገባም፡፡ በዚህ መሠረት ለወደፊቱ በቂ ካሣና በዘላቂነት የሚቋቋምበት ሁኔታ እንዲመቻችለት፣ ከዚህ በፊት የተሠራውም ሥራ ተፈትሾ ጉድለቶች እንዲስተካከሉ፣ እነዚህን ሥራዎች የሚያስተባብር የሚመራና የሚያስፈጽም ጽ/ቤት እንዲደራጅ በአዋጁ እንዲካተት ተደርጓል፡፡”

በመሰረተ-ልማት ግንባታና በኢንቨስትመንት ምክንያት በብዛት ከመሬቱ እየተፈናቀ ያለው በአለምገና፣ ቡራዩ፣ ገላን፥ ሰንዳፋ፥ …ወዘተ ያለ አርሶ-አደር ወይስ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለ አርሶ-አደር? ብሶትና ምሬት ፈንቅሎት ለሞት፥ ለእስርና አካል ጉዳት የተዳረገው የቱ ነው? ላለፉት ሶስት አመታት ለታየው አመፅ አለመረጋጋት ዋና ምክንያት የነበረው በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች መፈናቀልን አስመልክቶ በረቂቅ አዋጁ የቀረበው የመፍትሄ ሃሳብ “የከተማ አስተዳደሩ ምርቶቻቸውን የሚሸጡባቸውን የገበያ ቦታ በማዘጋጀት በራሱ ወጭ የግብይት ማዕከላትን እንዲያቋቁምላቸው የሚል ነው።

በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኘው አርሶ አደር በልማት ስም ከእርሻ መሬቱ ያለ በቂ ክፍያ እየተፈናቀለ ባለበት ወቅት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት “ለክልሉ ለተለያዩ መንግሥታዊ ሥራዎች እና ሕዝባዊ አገልግሎቶች የሚውሉ ሕንጻዎች የሚሠሩበትን መሬት ከሊዝ ነጻ” ይፈቀድልኝ ብሎ ይጠይቃል። በሺህዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ልጆች በከፈሉት መስዕዋት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኖሩ የክልሉ መንግሥት ሠራተኛ የኮንደሚኒዬም ቤት ሲጠይቁበት ማየት ያሳፍራል። ኧረ ለመሆኑ፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ አይደለችም እንዴ? ዋና ከተማ ከሆነች ደግሞ የከተማ መስተዳደሩ የፌደራል መንግስትን በሚያስተናግድበት አግባብ የኦሮሚያ መንግስት የማስተናገድ አለበት። የኦሮሚያ ክልል በራሱ ዋና ከተማ ውስጥ ከሊዝ ነፃ መሬት ይሰጠኝ ብሎ የሚጠይቅበት ምክንያት ምንድነው? በአዲስ አበባ ላይ የፌደራሉ መንግስት ከኦሮሚያ መንግስት ምን የተለየ መብት ሊኖረው ይችላል?

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣  googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥይቻላል።

The post “የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማስከበር” እያሉ በነፃ አሳልፎ መስጠት አለ እንዴ? – ስዩም ተሾመ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Ethiopia asks for extension of Saudi amnesty deadline

$
0
0
Thousands of Ethiopians have been attracted to Saudi Arabia by the job opportunities

Thousands of Ethiopians have been attracted to Saudi Arabia by the job opportunities

BBC

Thousands of Ethiopians are still stuck in Saudi Arabia after a 90-day amnesty for undocumented migrants expired on Tuesday without all of them leaving , the Ethiopian government has said.

Communications Minister Negeri Lencho told the BBC that the government has asked for the amnesty to be extended.

He said more than 45,000 citizens had so far returned but there were many more waiting to go back home.

Ethiopians have been employed in Saudi Arabia in building and domestic work.

Mr Negeri said that the government was expecting “a positive response” from the Saudi authorities for its request to extend the amnesty.

In March 2017 the Saudi interior minister, Crown Prince Mohammed bin Naif bin Abdulaziz, announced the amnesty under a campaign called “A nation with no legal violator”.

During this period any one in breach of the country’s residency and labour rules or regulations would be free to leave without facing any penalties.

In 2013 a similar amnesty was announced, however any illegal migrant who did not leave Saudi Arabia had to face punishment by way of fines, prison or being deported.

During that time a number of Ethiopians were killed in clashes with the Saudi police as they were being rounded up for deportation.

Illegal migrants sit on the roof of a police bus with their belongings on November 13, 2013 before being transferred to a center in the capital Riyadh ahead of their deportatioImage copyrightAFP
Image captionIllegal migrants were deported from Saudi Arabia in 2013

Mr Negeri says that there was a slow uptake during the amnesty period because some people were sceptical the Saudi authorities would take action during the just ended period of Ramadan.

Minister Negeri added that a taskforce and money has been set aside to receive and resettle the Ethiopian returnees.

The post Ethiopia asks for extension of Saudi amnesty deadline appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.

በክፉ ደዌ የተያዘው ጣና ሀይቅ  [ቬሮኒካ መላኩ]

$
0
0

ከሚኗሩባት ደመ ነፍስ ፍጡራን ሁሉ ሰው የተባለው ፍጡር አለምን እንደነጀሳት ነው። የሚባላውን ከሚጥልባት የሚጠጣውን ከሚሸናባት አልፎ በሰራው መርዙ እየመረዛት ነው። የተነሰነሰባት መርዝም ሲመዘምዛት እና ሲጠዘጥዛት ኖሯል ።
ይሄ የምታዩት እየጠፋ ያለው የጣና ሀይቅ ነው። በዚህ ሀይቅ ውስጥ አንገቱን ብቅ ያደረገ ጉማሬ ይታያል ። የእንስሳትን የፊት ገፅታ አይቼ የውስጡን ስሜቱን መረዳት ባልችልም ይሄ ጉማሬ ” የህይወቴ መሰረት የሆነው ቤቴ እየጠፋ ስለሆነ እርዱኝ! እርዱኝ! ” በማለት እየተማፀነ ይመስለኛል ።

ጣና ሀይቅ ቤቴ ብለው በውስጡ ከሚርመሰመሱት የባህር ነፍሳት ጋር ለዘመናት በጤነኛ ሂደት አልፎ አሁን ግን “እምቦጭ ” በሚባል ወያኔ አመጣሽ ደዌ ተለክፎ በጠና ታሟል ።
እንደ ወያኔ ያለው በላኤ ሰው ቡድን ከሰው ልጅ አልፎ ህገ ተፈጥሮ ለዘላለም ያቆየውን ጣና ሀይቅን እያደረቀው ይገኛል ።

አሁን በተጨባጭ በማኅበረሰባችን ፊት የተደቀነው ዋናው ፈተና የጣና ሀይቅ አደጋ ላይ መውደቁ ነው ።
ብዙዎቻችን ለጋራ ተሞክሯችን ፈጽሞ አዲስ ከሆነ ነገር ጋር ተፋጥጠን በጭንቀት እንገኛለን ። ይህ ነገር ለእኛ እስከ ዛሬ ተንከባክቦ ባቆየን ጣና ሀይቅ ላይ የደረሰ ከፍተኛ መጠን ያለው ባዮሎጂያዊና ፊዚካላዊ ለውጥ ውርጅብኝ ነው ።

ብርቅዬ የሆነውና ከኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ የሆነውና የአባይ ወንዝም አንዱ እስትንፋስ የሆነው ጣና እየተንቀሳቀሰ ያለበት አቅጣጫ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ የተወሳሰበ ሲሆን ይህ አቅጣጫ የሚያስከትለው ውጤት አብዛኞቻችንን እጅግ የሚያስፈራ ሆኗል።

ለኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም በጣና ሀይቅና በአባይ ወንዝ ዳርቻ ለሚኖሩት የአማራ ህዝብ ጣና ማለት ህይወት ማለት ነው ። ጣና ሀይቅ ለእኛ በምድራችን የሚያበራ ጮራ ነው። በፀጋዎቹ ለዘመናት ለህዝባችን ህይወት ሲለግሰን ኖሯል።
የጣና ሀይቅ ዛሬ ከፍተኛ አደጋ ላይ ወድቋል ። የሀይቁን ህይወት እንድቆይ ከተፈለገ ዛሬ ነገ ሳይሉ ጨርሶ ሳይሞት ነፍሱ እያጣጣረች ባለችበት በዚህ ሰአት መድረስ አለብን ።
ለጣና እንድረስለት !!!

ይህ የምትመለከቱት ጣና ዳር ያለው የኩሪፍቱ ሬስቶራንት ፍሳሽ ቆሻሻ ያለምንም ማጣራት/ treatment ወደ ጣና ሲለቀቅ ነው።
የጣና ጉዳይ እጅግ ያንገበግበናል። ትኩረት ለጣና!!

The post በክፉ ደዌ የተያዘው ጣና ሀይቅ  [ቬሮኒካ መላኩ] appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

The Numbers Say the Ethiopian Economy Is Doing Very Well. Reality Says Many Ethiopian Citizens Are Not. – Atlanta Black Star

$
0
0



Group of African children – Ethiopia, East Africa

For some, the emergence of Ethiopia as Africa’s third-largest economy is cause for celebration. The ancient nation skirting the continent’s horn recently surpassed its southern neighbor Kenya as the largest economy in East Africa with a projected Gross Domestic Product (GDP) of $78 billion. The first country to open an electric cross-border railway line in Africa, Ethiopia’s rapid economic expansion is due to major innovations in industry, irrigation and energy alongside its successful attraction of foreign investment. In 2015, Prime Minister Hailemariam Desalegn was named “Man of the Year” by Africa World News for sustaining the country’s substantial economic growth.

But for many Ethiopians, there is little to celebrate. The country remains desperately poor with the World Bank reporting Ethiopia’s per-capita income to be $619, well lower than the regional average. With food aid expected to run out next month, the United Nations estimates close to eight million Ethiopians are in danger of starvation. Human trafficking continues to be a major problem for the country’s poverty-stricken migrants. And human rights abuses have been rampant given ongoing land grabs by the Desalegn regime and its violent crackdown on associated protests, press and media freedoms.

Accordingly, some believe Ethiopia’s recent economic growth was not forged for its masses of struggling citizens but upon their backs.



“In the name of modernization, people have been forcibly removed from their land to clear those lands for sugarcane and cotton plantations,” says Anuradha Mittal, founder and executive director of the Oakland Institute, an independent think tank for international policy matters. The California-based institute’s recent report on Ethiopia notes its government’s plan to become one of the world’s largest sugar producers and exporters by 2023. Because of the associated displacement, explains Mittal, you had “widespread protests last year that led to more than 36,000 people being arrested. So, you have every political opposition leader behind bars, you have no freedom of press, you have people being arrested for challenging the government’s plan to take over their land with no compensation” while the country’s “newspaper editors and indigenous leaders have all been locked up” and charged as “terrorists.”

For the past eight years, the institute has shed light on how Ethiopia’s economic expansion has masked human rights abuses and how its government has displaced millions of small farmers while moving forward with plans to earmark over 15 million hectares of land for large-scale agricultural investors. It has further exposed the torture, oppression and silencing of those who have attempted to resist forced removal in indigenous and pastoralist communities within the Afar, Oromia and Amhara regions.

“Last year, we brought in a team of lawyers from very respectable law firms in Europe and the United States,” says Mittal, noting they reviewed how the Ethiopian government employed its ‘terrorism’ designation. “It was obvious that it does not meet any international standards and is a misuse of law to basically cause the complete elimination of human rights in the country.”



Some see things differently. In December 2015, upon a deadly crackdown on protests triggered by a scheme to expand administrative control in the Oromia region — and six months after the ruling party won a highly questionable 100 percent of the seats in the Ethiopian parliament — the government accused protesters of links with terror groups without any significant evidence. “Destructive forces are masterminding the violence from the front and from behind,” offered Desalegn on state television, adding the authorities “will take merciless legitimate action against any force bent on destabilizing the area.”

Such inflammatory rhetoric continues to accompany the Desalegn regime’s relentless economic agenda. Legitimate or not, part of the reason why a country like Ethiopia can ‘succeed’ economically while its citizens do not lies in the ongoing use of gross domestic product as the primary measure of a country’s economic performance. GDP is the total monetary value of all the finished goods and services produced within a country in a year. As such, it does little to account for the health and well-being of citizens since a nation’s elite class, which commonly controls major industry, can substantially increase profits and raise GDP without any significant change in the plight of the masses. Because of this, the Social Progress Index (SPI) is considered a more effective measure of national well-being as it accounts for such basic human needs and indicators as water, nutrition, sanitation, shelter, safety, access to information, personal rights, freedom, environmental quality, education, opportunity, tolerance and inclusion. When compared to countries with similar economies, Ethiopia performs poorly in a number of key SPI categories including access to water, nourishment, education, information and basic freedoms of expression and movement.

Despite these poor indicators, strategic investment allies like the U.S. can still point to GDP, positive economic growth and counterterrorism efforts as an ironic justification for its alignment with such repressive regimes. A bill promoting democracy and human rights accountability in Ethiopia has sat before the U.S. Congress for over a decade.



“The unfortunate reality is the United States has chosen to turn a blind eye to these widespread human rights abuses despite the evidence Congress has seen,” says Mittal, lamenting how America continues to “provide aid for very problematic programs which lead to the displacement of people. But also, because Ethiopia is an ally in the ‘War on Terrorism,’ the United States has not pushed for democracy.”

Still, Mittal believes change in Ethiopia can happen. “It is very important that its international allies here in the United States and the World Bank start putting pressure on the country to allow basic freedoms,” she says, citing an urgent need for independent media and fair elections.

Mittal takes it one step further. “I think we have to question the whole development paradigm.” Displacement of communities and the destruction of land, homes and families, she continues, should not be regarded as “development. It is important that international institutions such as the World Bank stop promoting very harmful development strategies which deliberately profit a few corporations” while a nation’s people are “starving.”

“So, I think we have to challenge the whole development model itself.”

The Numbers Say the Ethiopian Economy Is Doing Very Well. Reality Says Many Ethiopian Citizens Are Not – Atlanta Black Star

$
0
0



Group of African children – Ethiopia, East Africa

For some, the emergence of Ethiopia as Africa’s third-largest economy is cause for celebration. The ancient nation skirting the continent’s horn recently surpassed its southern neighbor Kenya as the largest economy in East Africa with a projected Gross Domestic Product (GDP) of $78 billion. The first country to open an electric cross-border railway line in Africa, Ethiopia’s rapid economic expansion is due to major innovations in industry, irrigation and energy alongside its successful attraction of foreign investment. In 2015, Prime Minister Hailemariam Desalegn was named “Man of the Year” by Africa World News for sustaining the country’s substantial economic growth.

But for many Ethiopians, there is little to celebrate. The country remains desperately poor with the World Bank reporting Ethiopia’s per-capita income to be $619, well lower than the regional average. With food aid expected to run out next month, the United Nations estimates close to eight million Ethiopians are in danger of starvation. Human trafficking continues to be a major problem for the country’s poverty-stricken migrants. And human rights abuses have been rampant given ongoing land grabs by the Desalegn regime and its violent crackdown on associated protests, press and media freedoms.

Accordingly, some believe Ethiopia’s recent economic growth was not forged for its masses of struggling citizens but upon their backs.



“In the name of modernization, people have been forcibly removed from their land to clear those lands for sugarcane and cotton plantations,” says Anuradha Mittal, founder and executive director of the Oakland Institute, an independent think tank for international policy matters. The California-based institute’s recent report on Ethiopia notes its government’s plan to become one of the world’s largest sugar producers and exporters by 2023. Because of the associated displacement, explains Mittal, you had “widespread protests last year that led to more than 36,000 people being arrested. So, you have every political opposition leader behind bars, you have no freedom of press, you have people being arrested for challenging the government’s plan to take over their land with no compensation” while the country’s “newspaper editors and indigenous leaders have all been locked up” and charged as “terrorists.”

For the past eight years, the institute has shed light on how Ethiopia’s economic expansion has masked human rights abuses and how its government has displaced millions of small farmers while moving forward with plans to earmark over 15 million hectares of land for large-scale agricultural investors. It has further exposed the torture, oppression and silencing of those who have attempted to resist forced removal in indigenous and pastoralist communities within the Afar, Oromia and Amhara regions.

“Last year, we brought in a team of lawyers from very respectable law firms in Europe and the United States,” says Mittal, noting they reviewed how the Ethiopian government employed its ‘terrorism’ designation. “It was obvious that it does not meet any international standards and is a misuse of law to basically cause the complete elimination of human rights in the country.”



Some see things differently. In December 2015, upon a deadly crackdown on protests triggered by a scheme to expand administrative control in the Oromia region — and six months after the ruling party won a highly questionable 100 percent of the seats in the Ethiopian parliament — the government accused protesters of links with terror groups without any significant evidence. “Destructive forces are masterminding the violence from the front and from behind,” offered Desalegn on state television, adding the authorities “will take merciless legitimate action against any force bent on destabilizing the area.”

Such inflammatory rhetoric continues to accompany the Desalegn regime’s relentless economic agenda. Legitimate or not, part of the reason why a country like Ethiopia can ‘succeed’ economically while its citizens do not lies in the ongoing use of gross domestic product as the primary measure of a country’s economic performance. GDP is the total monetary value of all the finished goods and services produced within a country in a year. As such, it does little to account for the health and well-being of citizens since a nation’s elite class, which commonly controls major industry, can substantially increase profits and raise GDP without any significant change in the plight of the masses. Because of this, the Social Progress Index (SPI) is considered a more effective measure of national well-being as it accounts for such basic human needs and indicators as water, nutrition, sanitation, shelter, safety, access to information, personal rights, freedom, environmental quality, education, opportunity, tolerance and inclusion. When compared to countries with similar economies, Ethiopia performs poorly in a number of key SPI categories including access to water, nourishment, education, information and basic freedoms of expression and movement.

Despite these poor indicators, strategic investment allies like the U.S. can still point to GDP, positive economic growth and counterterrorism efforts as an ironic justification for its alignment with such repressive regimes. A bill promoting democracy and human rights accountability in Ethiopia has sat before the U.S. Congress for over a decade.



“The unfortunate reality is the United States has chosen to turn a blind eye to these widespread human rights abuses despite the evidence Congress has seen,” says Mittal, lamenting how America continues to “provide aid for very problematic programs which lead to the displacement of people. But also, because Ethiopia is an ally in the ‘War on Terrorism,’ the United States has not pushed for democracy.”

Still, Mittal believes change in Ethiopia can happen. “It is very important that its international allies here in the United States and the World Bank start putting pressure on the country to allow basic freedoms,” she says, citing an urgent need for independent media and fair elections.

Mittal takes it one step further. “I think we have to question the whole development paradigm.” Displacement of communities and the destruction of land, homes and families, she continues, should not be regarded as “development. It is important that international institutions such as the World Bank stop promoting very harmful development strategies which deliberately profit a few corporations” while a nation’s people are “starving.”

“So, I think we have to challenge the whole development model itself.”

የሕወሓት የስንብት ዐዋጅ – ምሕረት ዘገዬ

$
0
0

 

ሰሞነኛው ሕወሓታዊ  የዕውር ድምብር እንቅስቃሴ ብዙ ነገሮችን እንዳስታውስ አድርጎኛል፡፡ እውነቱን ለመናገር ይህንን አዲስ አበባን ለኦሮሞ የመስጠት ጉዳይ በዩቲዩብ ስመለከት ከመደንገጥም አልፌ ከሦስት ቀናትም በኋላ አሁን ድረስ ላልተወኝ ራስ ምታት መጋለጤን ልደብቅ አልፈልግም፡፡ የዕብድ ሥራም አንዳንዴ ያስደነግጥና እስኪለቅ ድረስ መቸገር ይኖራል፡፡ የድንጋጤየ ዋና መነሻ የወያኔው ዕብደት የወለደው ይህ ሕዝብን የማተረማመስ ሥልት ከቁም ነገር የሚጣፍ ሆኖ ሣይሆን ከወኔያው ታሪክ በመነሣት ብዙ “አይሆኑም” የሚባሉ ነገሮች በመሆናቸው እነዚህ ውሉዳነ አጋንንት የቆይታ ዕድል ካገኙ ይህም ቅዠት እውን ሊሆን እንደሚችል በመጠራጠር ነው፤ “ጠርጥር ገንፎም አለው ስንጥር” ይባላልም እኮ፡፡ እንጂ እንዲህ ያለ ዘመኑን ያልዋጀ የዕብደት ዐዋጅ ኢትዮጵያን ያሰጋታል ብዬ ከልቤ አምኜበት አይደለም፡፡(በነገራችን ላይ ኤርምያስ ለገሠ በዚህ ነገር ዙሪያ የጻፈው ግሩም ወቅታዊ  ሀተታ አለና ያላነበበ ሰው ቢያነበው ጥሩ ነው እላለሁ፡፡)

ይህ ክስተት ከሚያስታውሱኝ በጣም በርካታ ነገሮች ውስጥ አንድ ሁለቱን ያህል ላስታውሳችሁ፡፡

ከምድራዊው ልጀምር፡፡ በትዳር ሕይወቷ ብዙ ልጆችን ያፈራች አንዲት የቤት እመቤት በጠና ትታመምና ንስሃ ለመግባት በዚያውም የኑዛዜ ቃሏን በእማኞች ፊት ለመስጠትና ይህችን “ቆሻሻ” ምድር ለመሰናበት ሁለት ሽማግሌዎችንና የነፍስ አባቷን ታስጠራለች (አሉ)፡፡ የተባሉት ሰዎች መጥተው ያችን እንደወያኔ በፅኑ ጣዕር ወህማም ላይ የነበረችን ሴትዮ በመክበብ ማዳመጥ ይጀምራሉ ፡፡ የአሥራ አንድ ልጆች እናት የሆነችው ወይዘሮ በቅድሚያ ንስሃዋን ማውረድ የፈለገች ይመስላል፡፡ እናም ቀጠለች – “መምሩ ደህና አድርገሁ ይፍቱኝ፤ በደምብ ይጸልዩልኝ፡፡ በቁርጥ ስለተያዝሁ እውነቱን ብቻ ነው የምናገረው፡፡ ለትዳሬ ታማኝ አልበርሁም፡፡ … የመጀመሪያው ልጄን የወለድሁት ከጎረቤታችን ከአቶ አውግቼው ነው፤ ሁለተኛውን ልጄን የወለድሁት ከአጥቢያ ዳኛው ከአጋፋሪ እንደሻው ነው፤ ሦስተኛውን ልጄን የወለድሁት ከባለቤቴ ነው፤ አራተኛውን ልጄንም የወለድሁት ከራሱ ከባለቤቴ ነው፤ … አምስተኛውን ልጄን የወለድሁት ከርስዎ ከራስዎ ከመምሩ ነው፡፡…” ሴትዮዋ አልጨረሰችም፤ የሕወት ድርሣኗን ከፍታ እውነትና እውነቱን ብቻ እየተናዘዘች ነበር፡፡ ሴትዮዋ በመጨረሻ የተናገረችውን ያልሰሙ በመምሰልና ለማመንም በመቸገር ጭምር ሽማግሎቹ ተደናግጠው “ምን አለች፣ ምን አለች?” ብለው እርስ በርስ ይጠያየቃሉ፡፡ ይህችን ጠባብ ዕድል ያገኙት የንስሃ አባት “ኧረ ገና ብዙ ትዘባርቃለች!” በማለት ሰዎቹ በቄሱ ላይ ያሳደሩትን ጥርጣሬን የተሻገረ የውስልትና ሥራ ለማስቀየስ ይሞክራሉ፡፡ ይህን ለማለት ያበቃቸው አለሥራቸው ታምተው ሣይሆን “ሴትዮዋ በጣር ስላለች የምትለውን አታውቅም” ለማለት ፈልገው ነው፡፡ አለቃ ገ/ሃናም ያመለጣትን እውነተኛ ፈስ እንዳልፈሳች ለማስመሰል ስትል በአፏ “ጡጥ!” ያደረገችዋን መንገደኛ “ይቺ ሌላ፣ ያቺ ሌላ” ሲሉ እንደነቁባት መግለጻቸውን እዚህ ማስታወስ ሳይገባኝ አይቀርም፡፡ የምትደበቅ እውነት እንደጭስ ናት – እንደምንም ብላ መውጣቷ አይቀርም፡፡

ለማንኛውም ወያኔ ገና ብዙ ይዘባርቃልና በጥንቃቄ መከታተል ተገቢ ነው፡፡ እነሱ ፈንጂ ባጠመዱ ቁጥር፣ እነሱ ወጥመድ በዘረጉ ቁጥር፣ እነሱ ጉድጓድ በቆፈሩልን ቁጥር እየዘለልን የምንገባ ከሆነ ስህተቱ የኛ እንጂ የነሱ አይደለምና በሚያልፍ መጥፎ ዘመን የማያልፍ ጠባሳ በታሪክ ስንክሳር ላይ ላለመተው ብዙ ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን እኛ ብዙኃኑ ነን፡፡ እመለስበታለሁ፡፡

ሰማያዊውን ልቀጥልና ወደ ቁጭቴ(ማጠቃለያየ) ላምራ፡፡ በክርስትናው እምነት እንዲህ ያለ ታሪክ አለ፡፡ መላእክት ፈጣሪን ቅዱስ እግዚአብሔርን በመንበሩ ያጡታል፡፡ ይደናገጣሉ፡፡ ያኔ የመላእክት አለቃ የነበረው ሊቀ ሣጥናኤል የመላእክቱን መደናገጥና የተፈጠረውን ክፍተት በመረዳት በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ሄዶ ይቀመጣል፡፡ ዱሮም ይቀና ነበር ማለት ነው፡፡

መላእክቱ “ማን ነው የፈጠረን?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ሊቀ ሣጥናኤልም “እኔ ፈጠርኳችሁ!” ይላቸዋል፡፡ ያመኑት አመኑ – በርሱም “ቆርበው ዳኑ”፡፡ ያላመኑት ግን “ፈጣሪያችንን እስክናገኝ በያለንበት (በጽናት) እንቁም!” ብለው ይወስናሉ፡፡ በወቅቱና አሁንም ቢሆን በኃያልነቱና በእልኸኝነቱ የማይታማው ሊቀ ሣጥናኤል እንደተነቃበት ሲረዳ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ/ጦርነት ውስጥ ይገባና በየዋህነትም ይሁን በክፉ መንፈስ ተነድተው ፈጣሪያቸውን የካዱ መሰል መላእክት ጋር በመሆን በዓላማቸው ጸንተው ለፈጣሪያቸው ከቆሙት እነቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ጋር ክንፋቸውን እየተነጫጩ በጨበጣ ይተጋተጉ ያዙ፡፡ በዚያ ታላቅ መንፈሣዊ ጦርነት እግዚአብሔር ባይደርስላቸው ኖሮ አሁን ዓለማችንን በታላቅ ግዳይነት አጋድሞ እየተጫወተባት የሚገኘው ሊቀ ሣጥናኤል ሊያሸንፋቸው ተቃርቦ እንደነበር የሃይማኖት አባቶችና መጻሕፍት ያስተምሩናል፡፡ ግን ያቺ የፈተና ጊዜ አልፋ ዳፋዋ ግን ለአዳምና ሔዋን ደርሳ በነሱም ሳቢያ ወደኛ ተላልፋ ይሄውና በሕወሓት አማካይነት ሌላ ኢትዮጵያዊ የመጨረሻ ፍልሚያ ውስጥ ገብተናል፡፡

አንደናገጥ፡፡ ብዙ ሰው የተደናገጠ ይመስላል፡፡ ብዙ ሰው ደግሞ እንደቀልድ እያዬ ይዝናናበት ጀምሯል፡፡ እንዳንደናገጥ የምመክረው ወያኔ ካርዶቹን ሁሉ አሟጦ ተጠቅሞ( አብዛኛውን በድርቅናና ሳናምንለት ነው) እዚህች የማትረባ ካርድ ላይ በመድረሱና ይህችም ካርድ እርባናቢስ በመሆኗ ነው፡፡ ወያኔና እግዚአብሔር፣ ወያኔና የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ወያኔና እውነት፣ ወያኔና ሰብኣዊነት… በቅጡ ሳይተዋወቁ እነዚህ እርጉሞች ሊሰናበቱ መቃረባቸው ግን በእውነቱ ያሳዝነኛል – “ሰው”ነትን አውቀውና ሆነውም ቢያዩት ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ከልጅነት እስከ ዕውቀት፣ ከጉርምስና እስከ ጉልምስና፣ ከወመሽነት እስከ ጅጅትና ፈጣሪንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ማወቅ አለመቻል የአለመታደል ሁሉ ጫፍ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የዐዋጅ ጋጋታም አንዱና ምናልባትም ትልቁ የድንቁርናቸው ምልክት ነው፡፡ አንድ ሰው እየሞተ እንኳን ልብ ካልገዛና ወደሰውነቱ – ወደኅሊናው ካልተመለሰ – በስም እንጂ በግብር ሰው መሆኑ ያጠራጥራል፡፡ ለምሣሌ ወያኔዎች አዲስ አበባ እንደገቡ ሰሞንና ከዚያም በኋላ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን የጥቁር አንበሣ ጄኔሬተር፣ የጎንደር ከተማ (ሆስፒታል?) ጄኔረተር፣ የአዲስ አበባ ዳቦ ቤቶች(ከኤርምያስ ሁለተኛው መጽሐፍ እንዳነበብኩት፣ በቢሊዮኖች ብር የሚገመት የመንግሥትና የግል ድርጅቶችን ሀብትና ንብረት … ቢቻል መመለስ ባይቻል መጸጸትና ለመካስ መሞከር ካልቻሉ በርግጥም እንደተወለዱ ሞቱ ሊባሉ የሚገባቸው የሰው ጭንጋፍ ናቸው፡፡ ይህን የቤት ሥራ ለትግራይ ክፍለ ሀገር ብንሰጥ የምንችል ይመስለኛል፡፡

አዲስ አበባ መተተኛ ከተማ ናት፡፡ አዲስ አበባ ልትለውጣቸው ያልቻለቻቸው ሕወሓትን የመሰሉ የጨለማው መንግሥት ወኪሎችን እንጂ ተራ ዜጋን በደቂቃዎች ውስጥ ለውጣ ክፉዎችን ገር፣ ተንኮለኞችን የዋህ የምታደርግ ግሩም ከተማ ናት፡፡ አንድ ሰው ከየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ ይምጣ፣ የትኛውንም ኢትዮጵያዊ ቋንቋ ይናገር አዲስ አበባ ሲደርስ አዲስ አበቤ እንጂ ጎጃሜ ወይም ሸዌ፣ ወሎዬ ወይም ጎንደሬ፣ ወለጌ ወይም ሐረሬ … አይሆንም፡፡ ለልጆቿ ልዩ ፍቅር ያላት፣ ገዢዎች ጣልቃ እስካልገቡባት ድረስ በተቻላት መጠን ሁሉንም ልጆቿን በእኩል ዐይን የምታይ፣ ልዩ መስተጋብር ያላት፣ ልዩ የመቻቻልና የመደጋገፍ፣ የመተሳሰብና የመተዛዘን መንፈስ ያረበበባት በውነትም ልዩ ከተማ ናት – የኔ አዲስ አበባ፡፡ ሁሉንም ሆና፣ ስለሁሉም ተጨንቃና ተጠባ የሁሉንም ስሜት ገዝታ ከክፉዎቹ ገዢዎቿ መዳፍ ምሥኪን ልጆቿን ጠብቃ የምትኖር ከተማ ከአዲስ አበባ ውጪ ብዙም አላውቅም፡፡

አንድ ወቅት እንዲህ ሆነላችሁ፡፡ አንድ ሽማግሌ ከሰሜን ሸዋ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡበት የፍርድ ቤት ሙግት ነበራቸው፡፡ ቀጠሯቸው እየተራዘመ ሲሄድ አንድ ችግር ገጠማቸውና ለችሎቱ አቤት አሉ፡፡ “ክቡር ፍርድ ቤት፣ ውኃየ አልቆብኛልና በእግዜር ይሁንባችሁ ዛሬ ፍረዱልኝ ወይም ፍረዱብኝ!” ብለው ያመለክታሉ፡፡ የመሃል ዳኛውም “የምን ውኃ ነው ያለቀብዎት?” ብሎ ይጠይቃቸዋል፡፡ እርሳቸውም “‹የአዲስ አበባ ውኃ አይለቅም‹ ሲባል ሰማሁ፤ ቤት ንብረቴን የትሚናቸውን ጥዬ እዚሁ መቅረት ስላልፈለግሁ የምጠጣውን ውኃ ታገሬ ተመንዝ ነው ይዤ የመጣሁት፡፡ የዚህን አገር ውኃ እዚሁ እንዳያስቀረኝ በመፍራት አልጠጣም፡፡…” አዎ፣ ዳኞቹ ተሳስቀው ወዲያዉኑ ወሰኑላቸው ይባላል፡፡ አዲስ አበባ ፍቅሯ እስከዚህ ነው፡፡

የአዲስ አበባን ባለቤትነት እንኳንስ ሕወሓት ዋና አዛዡ ዲያብሎስም አያገባውም፡፡ እንኳንስ ተላላኪው ሕወሓት የርሱ አለቆች ነጫጭባዎቹም አያገባቸውም፡፡ ይህች ታሪካዊት ከተማ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት እንጂ፣ የአፍሪካውያን የጋራ ንብረት እንጂ፣ የዓለማችን ሕዝብ የወል ገንዘብ እንጂ ከ90 ጎሣና ነገድ ለአንዱ ወይ ለሌላው በገጸ በረከትነት የምትሰጥ ቁስ አካል አይደለችም፡፡ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ …. የለም … የለም… ተረቱ ልክ አይደለም – ባይሆን “በሰው ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል” ቢባል ይሻላል፡፡ ለማንኛውም ወያኔዎች ስለተጨነቁ አይደለም እንዲህ ያደረጉት፡፡ ወያኔዎች ይህን ያደረጉት በተለይ ኦሮሞንና አማራን፣ በአጠቃላይ ደግሞ ኦሮሞንና ሌላውን ኢትዮጵያዊ ለማባላት ብቻ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የተበላ ዕቁብ ው፡፡ አንዳንድ ጅላጅሎችና ወያኔ-ተከል መሠሪዎች ግን እዚህና እዚያ እንደማይጠፉ መጠቆም ብቻ ሣይሆን በርግጠኝነት እንዳሉ ተረድተን ምንም ኃይልና ጉልበት ሳናባክን በጥርሳችን ብቻ እየሳቅንባቸው ቀኒቷን እንጠብቅ፡፡ እኛ ግን አደራችሁን በከፍተኛ ደረጃ እንጠንቀቅ፡፡ “እንዲህ ልጠግብ በሬየን አረድሁ” እንዳለችው ነፈዝ ሴት ላለመሆን የምንሠራውንና የምንሆነውን እያሰብን እንሥራ፣ እንሁንም፡፡ ሲያልፍ ለሚቆጭ ነገር እንዳንዳረግ እንትጋ፡፡

የኢትዮጵያ ነፃነት አንድ ቦታ እየተሠራች ነው፡፡ ያገሬ ገበሬ “ሳለ ፈጣሪ አሟጠሸ ጋግሪ!” የሚለው በፈጣሪው ዕፁብ ድንቅ ተዓምራዊ ሥራ ስለሚተማመን ነው፡፡ ስለዚህም በሰብኣዊ የውሱንነት ባሕርይ ምክንያት የመምጫዋን ጊዜና የምትመጣበትን አቅጣጫ ለይቼ ማወቅ ባልችልም ነፃነታችን እጅግ ቀርባለች፡፡ ንፋሷ አልባብ አልባብ በሚለው መለኮታዊ መዓዛው እያወደኝ ነው፡፡…

እመለስበታለሁ ወዳልኩት ነገር ልመለስ፡፡ ወገኖቼ! “ዐይጥ ወልዳ ወልዳ ጅራቷ ሲደርስ ሲጥ አለች” ይባላል፡፡ “ጦም ጧሚና ሰው ጠባቂ” ሲባልም ሳትሰሙ አትቀሩም፡፡ ያልተነካካችሁ፣ የሰው ላብ፣ የሰው ደም፣ የሰው ሃቅ… የሀገርና የወገን ዕንባ… በእጃችሁ የሌለባችሁ ወገኖች ይበልጥ ተጠንቀቁ፡፡ በነፃነት ቀን የምናፍርበት መጥፎ ሥራ ይዘን እንዳንዋረድ አሁኑንና ከአሁኑ እውነተኛ ንስሃ እንግባ፡፡ ሀገራችን ስትፀዳ የሚወጣ ዕድፍና ቆሻሻ ይታየኛል፡፡ ከቤተ መንግሥት ተጠራርጎ የሚጣል እጅግ የሚገማና የሚሰነፍጥ ቆሻሻ ይታየኛል፡፡ ዲያቆናት፣ ደባትር፣ ካህናትና ጳጳሣት ከየቤተ ክርስቲያናት እንደቁንጫና ትኋን በፍሊት ተጠራርገው ሲወገዱና ዲያብሎስ በነሱ ውስጥ ሲወገር ይታየኛል፡፡ ቤተ እግዚአብሔርን መጫወቻና መሣቂያ መሣለቂያ እንዳደረጉት ሁሉ ማጣፊያው ለሚያጥራቸው መከራና ስቃይ ይዳረጋሉ፤ ያም ቀን ቀርቧል፡፡ በቤተ ክርስቲያናት አካባቢ የሚደረጉ ወንጀሎችንና ነውሮችን በሚመለከት ዝርዝሩን ብንናገር ቤተ ክርስቲያን የሚሄድን ሰው ተስፋ ማስቆረጥ ይሆናል፡፡ በጎቹን ቀበሮና ተኩላ የሚያስበላ እረኛ ዋጋውን ከጌታው ያገኛል፡፡

አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት፡፡ ያን ማን ካደ? ከመነሻውስ አዲስ አበባን ስጡን ብሎ በሰላማዊ ሰልፍም ይሁን በወረቀት አቤቱታ ያቀረበ አለ ወይ? “ና አልመታህም!” አለው አሉ አንዱን፡፡ “ና አልመታህም”ን ምን አመጣው? አለና ሸሸው አሉ፡፡ እናስ! “አዲስ አበባን ለኦሮሞ ሰጠን፤ በኦሮምኛ የሚያስተምሩ ት/ቤቶች እንዲከፈቱ…” ቲሪሪም ቲሪሪምን ምን አመጣው? ወያኔዎች ጊዜ ካገኙ ገና ብዙ ይዘባርቃሉ፤ እንኳን ከፎከረ ከወረወረም የሚያድነው አምላከ ኢትዮጵያ ይሠውረን እንጂ ብዙና ብዙ የሚያጨራርሱን ዕቅዶች በመጋዘናቸው ውስጥ አሉ፡፡ በኦሮምኛ ይቅርና በጋፋትኛስ ቢሆን አንደኛ ትምህርት ቤት ቀርቶ ዩኒቨርስቲስ ቢሆን እንዳይከፍት የተከለከለ ወገን አለ ወይ? የምን ቅቤ አንጓችነት ነው? ማነው ሰጪ? ማንስ ነው ተቀባይ? ማን ነው መፅዋች? ማንስ ነው ተመፅዋች?

ኦሮሞዎችና አማሮች ስሙኝ፡፡ በልጅነቴ ልጆችን የምናጣለበትንና እኔም ሕጻን ሳለሁ እያጣሉኝ ትልልቆቹ የሚዝናኑብኝን አንድ ጨዋታ ላስታውሳችሁ፡፡ ጎርመስ ጎርመስ ያሉት ነፍስ ያላወቁ ትናንሽ ልጆችን ያመጡና በእጃቸው መዳፍ ላይ ምራቃቸውን እንትፍ ይላሉ፡፡ ከዚያም ወደ ሁለት ልጆች መሀል ይዘረጉና “የማን አባት ገደል ገባ፤ የማን አባት ገደል ገባ!” ይላሉ፡፡ አባቱ ገደል እንዳይገባበት በመሥጋት ቀድሞ “የጀገነው” ልጅ ያን ምራቅ በማበስ ለመቅደም ፈራ ተባ ይል የነበረውን ሌላውን ልጅ ይቀባዋል፡፡ ያ ተደፈርኩ ያለው ልጅ ምራቅ የቀባውን ልጅ በዱላ ማቅመስ ወይም  የባላንጣውን ወገብ በትግልመሰቅሰቅ ይጀምራል፡፡ ጠቡ እየከረረ ይሄዳል፡፡ ልጆቹ በእልህ ሲፋለሙ የጠቡ አነሳሾች አንድ ጥግ ጥላ ላይ ቁጭ ብለው እየተደሰቱ ይዝናናሉ – እንደወያኔ በሰው ስቃይ መደሰት፤ ዘመነ ግላዲያተር በሉት፡፡  በሰባና በሰማንያ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙት እፍኝ የማይሞሉ ወያኔ ትግሬዎች በነዚህ ኆልቁ መሣፍርት በሌላቸው አማሮችና ኦሮሞዎች መሀል በሚፈጥሩት አርቲፊሺል ጠብ ሊዝናኑና ሂትለራዊ አገዛዛቸውን ሊቀጥሉ መሆኑን የማይረዳ ዜጋ ካለ በርግጥም በትንሹ የዋህ ነው፡፡ የተደገሰለትን የዕልቂት አታሞ በራሱ ጊዜ እየደለቀ ወደ መቀመቅ ለመውረድ የተዘጋጀ የለዬለት በግ ነው፡፡ መቶና ዘጠና ሚሊዮን በግ ደግሞ ሊኖር አይገባም፡፡ የእስካሁኑ ይብቃን፡፡ ለራሳችን ስንል ነው የሚበቃን ደግሞ፡፡

ስለዚህ የትኛውም ከተማ ለማንም ተሰጠ ይባል፤ ግዴለም፡፡ ኢትዮጵያም ከነነፍሷ ለጭዳነት ቀርባ ባወጣች እየተቸበቸበች አይደለም እንዴ ? በነዚህ ማፊያዎች ያልተሸጠ ነገር፣ በወያኔ ያልተጓጓዘ ነገር፣ ሕወሓት ያላደረሰው ጥፋት ከፀሐይ በታች ምን አለ? ስለዚህ ለማይቀረው ነፃነታችን ወደፊት ከሚገለጥልን አቅጣጫ የሚመጣውን መልካም ንፋስ ከመጠበቅና የበኩላችንን አስተዋፅዖ በምንችለው ከማበርከት ባለፈ በነዚህ ያበቃላቸው የሰይጣን ሽንቶች እንዳንታለል የዜግነቴን አደራ እላለሁ፡፡

ለመሆኑ የኦሮሞው ችግር የስም ለውጥና በራስ ቋንቋ መናገር አለመቻል ነው እንዴ? አለቃ ገ/ሃና ምን አሉ? “ይቺ ሌላ፣ ያቺ ሌላ!”  አዳማና ናዝሬት፣ ቢሾፍቱና ደብረ ዘይት፣ ፊንፊኔና አዲስ አበባ፣ ጂጂጋና ጂግጂጋ፣ አለማያና ሀሮማያ፣ አዋሳና ሀዋሳ፣….  በራሳቸው ዳቦ የሚያስገኙ ቢሆን፣ ዴሞክራሲና ነፃነት የሚያመጡ ቢሆን፣ ስደትን የሚያስቀሩ ቢሆን፣ በመቶዎች በረንዳ የሚያድሩ ዜጎቻችንን ቤት ውስጥ የሚያሳድሩ ቢሆን፣ የወያኔን የመሬት ዘረፋና የሕወሓታውያንን ጋጠወጥነት የሚከላከል ቢሆን፣ የኢትዮጵያን አንጡራ ሀብት ከሕወሓት ዘረፋና ንጥቂያ የሚታደግ … ቢሆን ኖሮ የኔም ስም ከምሕረት ወደ ሥምረት ቢለወጥ ግድ ባልነበረኝ፡፡ ግን ግን ከዚያች ሴተኛ አዳሪ የምንማረውና ልብ የምንገዛው መቼ ይሆን? እንደወያኔ ያለ ሞላጫ አጭበርባሪ በ“ነገ እሰጥሻሁ” የማያልቅ ነገ  እያታለለ ቢያሰለቻት ጊዜ “አጭበርባሪ ‹አይበልጠኝም›!” አለቻ! ቋንቋ የመግባቢያ መሣሪያ ሆኖ ሳለ ወያኔ ቤተ መንግሥት ውስጥ ቁጭ ብሎ ያሻውን እያደረገ በዚህ በጣም ትንሽ ነገር ያጨራርሰናል፤ ለነገሩ እነሱ ምን አጠፉ? ገልቱዎቹ እኛ! በ“ማን አባት ገደል ገባ!” የሕጻናት ጨዋታ ተሸንፈን ሀገራችንን ከኛ ላነሱ ደናቁርት የሰጠን እኛው ነንና there is no one to blame. ዓለማችን ውስጥ ከ7106 የማያንሱ ቋንቋዎች ይነገራሉ፡፡ አንዱ አንዱን ይውጣል፤ አንዱ ከአንዱ ማሕጸን ይወጣል፡፡ በዚህ ሰው ይተላለቃል? ወይ ሞኝነት! በጀመርኩት እንግሊዝኛ ባወራ፣ በኦሮምኛ ባወራ፣ በአማርኛ ባወራ፣ በትግርኛ ባወራ፣ በጉራግኛ ባወራ፣ በሱማሌኛ ባወራ፣… ሃሳቤን ገለጥኩበት፣ ከሰው ጋር ተገናኘሁበት እንጂ ቋንቋ እኔን ፈጠረኝ እንዴ? ኢንሻኣላህ – እመለስበታለሁ፡፡ ግን ልድገመው – የቀጣፊ ሲሳይ አንሁን!! ችግራችን የሀገር ማጣት እንጂ የቋንቋና የቦታ ስም አይደለም፡፡ ወያኔዎች ዳቢትና ወርቹን፣ ፍሪምባና ጭቅናውን ይዘው እኛን በባዶ ጭራና ለዋገምትና ለዋንጫ እንኳን በማይውል ጠማማ ቀንድ ሲያጣሉን ማየት እጅግ ያማል፤ እናንተንስ አያማችሁም? mz23602@gmail.com

The post የሕወሓት የስንብት ዐዋጅ – ምሕረት ዘገዬ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አቶ መርሻ ዮሴፍ ከኑዛዜ በፊት ኢትዮጵያ፤ ዕውነት ፤ ተመክሮ እና ትምህርት ይቅደም – አቢቹ ነጋ

$
0
0

መርሻ ዮሴፍ

አቶ መርሻ በቅርቡ ለጥቁር ሕዝብ፣ ለአፍሪካውያን፣ ለራሳችን (ለኢትዮጵያውያን) መጭ፡ትውልድ፣ በማሰብ ኢትዮጵያን ጠብቀን እናቆይላቸው[1] በሚል ርዕስ ምክር አዘል ጽሑፍ በሰባት ሽህ ቃላት ታጅበው የሃያ አንደኛው ክፋለ ዘመን ኢትዮጵያዊ ወጣት ትውልድ ለሀገራዊ አንድነቱና ነፃነቱ ቀናዔ የሆነውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎትና ጥቅም ያገናዘበ ሀገራዊ ዓላማ አንግቦ፣ በሙሉ ልቡ ለኢትዮጵያ ትንሳዓኤ እና ነፃነት ቆርጦ እንዲነሳ እና እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል ። እርሳቸው እና መሰሎቻቸውም ከወጣቱ ጎን ቆመው ሃሳብ እና ምክር እንደሚለግሱ በአጽንዖት ቃል ገብተዋል። ከጽሁፋቸው መገመት እና መረዳት እንደሚቻለው ከፖለቲካው መድረክ እራሳቸውን በጥሮታ መልክ ያገለሉ አለያም ለማሸለብ (hybernate) ያሰ ይመስላል።

እንደሚገመተው አቶ መርሻ በ80ዎቹ መጀመሪያ የዕድሜ ክልል የሚገኙ አዛውንትና አክራሪ ግራ-ዘመም ፖለቲከኛ ናቸው። በዚህ ዕድሜአቸው ዘመኑ የወለደውን የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ሃሳባቸውን ማስተላለፍ መሞከራቸው ያስመሰግናቸዋል። ከ66ቱ አብዮት ጀምሮ እስካሁን ቀንደኛ የኢሃፓ አባል ብቻ ሳይሆኑ ከፍተኛ የአመራር አካል በመሆን ድርጅቱን ያገለገሉ መሆኑን ከሰዎችም ከርሳቸውም ሰምተናል።

ያ-ትውልድ የፈፀመውን አሉታዊና አውንታዊ የፖለቲካ ክስተቶች ካሠቡ፣ ከተገበሩ እና ካስተገበሩ የኢሃፓ አባላት መካከል ቀዳሚ ተዋናኝ እንደነበሩ ለማወቅ ነቢይ መሆንን አይጠይቀም። በመሆኑም ካካበቱት ልምድ ተነስተው ያሁኑን ትውልድ ለመምከርና እና ለማስተማር መከጀላቸው ተገቢ ነው። ምክንያቱም ግለሰቡ የመረጃ፤ የልምድ እና የተመክሮ ቤተመዘክር ናቸውና። በግልፅ፤ በድፍረት፤ በቆራጥነት፤ በእውነት ከተናገሩ ለዚህ ትውልድ ብዙ ትምህርት እና ምክር ሊሰጡ ይችላሉ። ይህ ሰፊ ኑዛዜ አዘል ምክር እና ተመክሯቸው (lessons learned) ዘግይቶ የመጣ ቢሆንም እንዲሁ ከሚቀር ዝግይቶ መደረጉ (better late than never) መልካም ነው።

ቁምነገሩ ተመክሯቸውን እና ልምዳቸውን ለኢትዮጵያ መፃኢ ዕድል እና ተስፍ ሲሉ (ለድርጅታቸው ሳይሆን) ያለማወላወል ሊነግሩን እና ሊአጋሩን ይችሉ ይሆን ወይ ነው። በተለይ እርሳቸውም ሆነ የሚመሩት ድርጅት በታሪክ አጋጣሚ ታሪካዊ ስህተት ሠርቶ ነበር ይሉ ይሆን የሚለው ለሁላችንም የሚሊዮን ብር ጥያቄ ይሆናል። ምንያቱም በልምዳችንም ሆነ በባህላችን እኔ ልክ ነኝ የሚል አባዜ የተጠናወተን፤ ይቅርታ ተሳስቸ ነበር ማለትን እንደውርደት እና እንደሽንፈት ስለምንቆጥር በግልጽ ይነግሩናል የሚል የሞኝ ተስፍ አንይዝም። በተለይ አክራሪ ፖለቲከኞች እና አምባገነኖች ይቅርባይነትን እና ተሳስቻለሁ ማለትን እንደክሽፈት፤ ፍርሃት፤ ውርደት ስለሚአስቡት የሚአደርጉት አይመስልም። የአክራሪ ፖለቲከኞች በሐሪ የሚአስተምረንም ይህኑ ሐቅ ነው። ምሳሌ ለመጥቀስ ካስፈለገ መኢሶን፣ ህውሃት፤ ኢሃፓ፤ ፖልፖት፤ ማኦኢዝም፤ አፓርታይድ ወዘተ በዚህ አቋማቸው የተካኑ ምስክሮች ናቸው።

ሆኖም አቶ መርሻ በቁሰ-አካል ፍልስፍና፤ በሒስ እና ግለ-ሒስ የሚአምኑ የግራ ፖለቲካ አቀንቃኝ ስለሆኑ በድፍረት ይናገራሉ ብለን ግን ተስፍ እንሰንቃለን። ስለሆነም የጥርጣሬ ስብዕናን (the benefit of the doubt) ሳልነፍግ ጽሑፋቸውን እና ሰፊ ኑዛዜአቸውን በጥሞና አንብቤአለሁ። ከዚህ በተጨማሪም ዕድሜ እየገፋ ወደ ላይኛው ቤታችን የመሄጃ ጊዜ ሲቀርብ እውነት ተናግሮ መሸኘትን ሰዎች ሁሉ ይወዳሉ። ለምሳሌ በቅርቡ አንድ MI-5 የደህንነት ሰው በሞት አልጋው ላይ ሆኖ ልዕልት ዳያናን እና ሌሎች አራት ታዋቂ ግለሰቦችን በእንግሊዝ ልዑላን ቤተሰብ ትዕዛዝ ግድያውን እንደፈጸመ ተናዟል። አበው ሲተርቱ እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ማድር ይላሉ። መርሻም እውነቱን ተናግረው እየመሸ ባለው የግዜ ቤት ሄደው ያድራሉ ብለን እየጠበቅን እረዥም ጽሑፋቸውን እንድታነቡላቸው እመክራለሁ።

በጽሑፋቸው ያ-ትውልድ ያደረገውን ስህተት የ21ኛው ክፈለ ዘመን ኢትዮጵያዊ ወጣት እና ትውልድ እናዳይደግም በማሳሰቢያ መልክ አጽኖዖት ሰጠው ምክር አዘል ማሳሰቢያ ሰጠዋል። የፀረ-ካፒታሊስትና የፀረ-ኢምፔሪያሊስት ቋንቋቸውን እና እምነታቸውን አንፀባርቀዋል። ለኢትዮጵያ ፖለቲካያዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፣ ፀጥታዊ እና ማህበራዊ ቀውስ የምዕራቡን ዓለም እና ኢምፔሪያሊዝምን ተጠያቂ አድርገዋል። ሶስተኛው ዓለም ኢትዮጵያን ጨምሮ ማለታቸው ነው የኒዎ-ሊበራሊዝም ፍልስፍና ባነሆለለው የተማረ ወይም የተመለመለ አገልጋይ (petty bourgeois) የሆነ ክፍል መሣሪያነት በምእራቡ ዓለም ተመዝብሯል ይሉናል። እርግጥ የምዕራቡ ዓለም በሶስተኛው ዓለም ላይ የማይናቅ ተጽዕኖ እንዳደረገ የማንስማማበት አመክንዮ አይኖርም።

በአንፃሩ መርሻ ጥብቅና የቆሙለት ምሥራቃዊው ዓለም (Eastern World) በርሳቸው ቋንቋ የላባደሩ ዓለም (ህብረተሰብአዊነት እና ኮሙኒስም) ከምዕራቡ ዓለም ባልተናነሰ ደረጃ ለሃገራችንና ለሶስተኛው ዓለም የፖለቲካ ችግር እና ቀውስ አስተዋጾ ማድረጉን ሳይገልጹ በለሆሳስ አልፈውታል። ሶስተኛው ዓለም በተለይም ኢትዮጵያ አክራሪ የግራ ፖለቲካ ፍልስፍና ባነሆለለው የተማረ ወይም የተመለመለ አገልጋይ (revolutionary)የሆነ ክፍል መሣሪያነት በአብዮት ስም ሕዝባችን ፍዳ እንዳየ እንዴት ሊገልጹና ሊአስተምሩን አልከጀላቸውም።  አብዮት ልጆችቿን ትበላለች ብለው እነመርሻ እንደሰበኩት ሁሉ አሁን ደግሞ የዚያ ግራ ዘመም ፖለቲካ ቅሪት አገሪቱንም ጨርሶ ሊበላት መቃረቡስ ለምን አልታያቸውም።  መርሻ አያይዘውም ጥቂት የተደራጁ አላዋቂዎች ወይንም መሃይሞች፣ የዕምነት አክራሪዎች፣ የተለያዩ አጋጣሚዎችን ተጠቅመው የአንድ ሀገርን መንግሥታዊ ሥልጣን ከጨበጡ፣ አዛዥና ናዛዥ፣ ፈላጭና ቆራጭ ሆነው የሚያዙትን ሃይል ለዚያው፣ ካላዋቂነት የያዙትን ዕምነትና መመሪያቸውን ለመተግበር በማሰማራት ከፍተኛ ጥፋት ሊያደርሱ ይችላሉ ይላሉ። እውነት ብለዋል። በኢትዮጵያ አብዮት ታሪክ እና ዘመንም የሆነው ይኸው ነው። ጥቂት የተደራጁ አላዋቂ አክራሪ የግራ ፖለቲካ አቀንቃኞች ኢሃፓ፤ መኢሶን፤ ሕውሃት፤ ሻቢያ ወዘተ በሃገራችን እና በሕዝባችን ላይ ያደረሱት ጥፋት እና እልቂት በቀላሉ የሚገመት አይደለም። ይህን ሐቅ ደፍረው ለመናገር ለምን አልቻሉም ወይም ሳይፈልጉ ቀሩ። ለዚህ ምክንያቱ አንድ እና አንድ ነው። ዓለም የወዛደሮች ትሆናለች ለሚለው መርህ አቀንቃኝ ስለሆኑ ይህን ማውገዝ አላስፈለጋቸው ይሆናል።

መርሻን የመሰሉ የወዛደሩ አምባገነን መሪዎች እና ጠበቆች ደግሞ ለዚህ አጋርነታቸውን ማሳየት ስለሚጠበቅባቸው ሳይኮንኑት፤ በተመክሮነትም ሳይገልጹልን አልፈዋል። የአይጥ ምስክሩ ድምቢጥ ሆኖባቸው ስለሆነ አንታዘባቸውም። ነገር ግን ለማስተማርና ለመምከር የከጀሉትን ያህል ግን በዚህ እረገደ ትምህርትና ተመክሮ ሳይሰጡን እናዳለፉ ግን ይወቁት።

ሆኖም ከምዕራቡና ከምስራቁ ዓለም በበለጠ በሃገራችን ፖለቲካ ትልቁን ሚና እና ተጽዕኖ ያደረገው የዛትውልድ ለመሆኑ መቀበል ከእያንዳንዳችን ይጠበቃልአሁንም እያደረገ ይገኛል። ከአቶ መርሻም በድርጅት አባልነታቸውና እንደ አንድ ፖለቲካ አዋቂነታቸው የበለጠ እንጠብቃለን። ይህን ከተቀበልን ደግሞ ያትውልድ የሰራቸውን በጎና መጥፎ ተግባሮችን ነቅሰን መነጋገር ይኖርብናል። ይህ ሲሆን ነው አዲሱን ትውልድ መምከርና ማስተማር የምንችለው። በደፈናው ያትውልድ ስህተት አድርጓል ወይም አድርገናል ብሎ በማድበስበ ማለፍ ሃላፊነት የጎደለው ኢትዮጵያዊነት ነው። ከተጠያቂነት እንደመሸሽም ይቆጠራል። በሽታውን የደበቀ ፈውስ አያገኝምና።

ሐቅ መናገር እና ስህተት አድርገናል ወይም አድርጌአለሁ ማለት ውርደት ሳይሆን አዋቂነት እና አስተዋይነት ነው። በርሳቸው የፍልስፍና አስተሳሰብ እና ክህሎትም አንፃር ቁስ አካላዊ (dialectical) ነው። በድርጅታቸው ለተደረጉ በጎ ምግባሮች ምስጋናን ከአክብሮት ጋር መለገሰ ከኢትዮጵያ ሕዝብ እና ከወጣቱ ትውልድ የሚጠበቅ ሲሆን ለተደረጉ ስህተቶች ደግሞ ሃላፊነትን ወስዶ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ ከአቶ መርሻ እና ድርጅታቸው ይጠበቃል።

ለዚህም ነው አቶ መርሻ የመሩትና እየመሩት ያለው ድርጅት ኢሃፓ ያከናወኑትን በጎ ጎኖችና የተፈጸሙ ጥፋቶችንና ቀውሶችን በነቂስ ዘርዝሮ ለዚህ ትውልድ ማስረዳት አስፈላጊ የሚሆነው። ያ-ትውልድ ያስመዘገባቸው ደግ ነገሮችና ያደረጋቸው የስትራተጅም ሆነ የፍልስፍና ስህተቶች ካሉ በማያሻማ ሁኔት ቢገለጹ ለትምህርትነት ይበጃል። አቶ መርሻ አስራ አምስት ገጽ ጽሁፍ ሲአዘጋጁ ይህንን በግልጽ ሳይመዘግቡ አልፈውታል። ምነልባት በቀጣይ ጽሑፋቸው እንደጲላጦስ ከደሙ ንፁሕ ነኝ ሳይሉ ያቀርቡት እንደሆን ወደፊት የምናየው ይሆናል።  ይህን ካላደረጉ ግን ዳዋ መቸበቸብ ወይም የጓሮ እስክስታ (bit around the bush) እንጅ ትምህርት እና ተመክሮ እንደምስጠት አይሆንም።

የአየር ንብረት መዛባት (climate change) በሰው ዘር ላይ ያስከተለውን እና ሊአስከትል የሚችልውን ቀውስ በቁንጽል ለመዘርዘር ከመሞከር እና የዓለማችን ከባቢ አየር ባለሙያ (environmental scientist) መስሎ ለመታየት ከመጣር የሚአውቁትን የነጭ ሽብር ታሪክን ስህተቶችና ተመክሮዎች ቢጠቅሱ ወጣቱ ትውልድ ከሳቸውና ከድርጅታቸው ብዙ በተማረ ነበር። ጥርሳቸው እስኪወልቅ፤ የፀጉር ቀለማቸው እስኪለቅ ከተካኑበት የነጭ ሽብር ፖለቲካ ላይ ያለውን ተመክሮ ቁልጭ አድርገው ቢአስተምሩን ምንኛ ባከበርናቸው ነበር። በዚህ ረገድ የትግል አጋራቸው የነበረችው ሕይወት ተፈራ ማማ በሰማይ (Tour In The Sky) በተሰኘው መጽሃፏ በግልጽ እንዳስቀመጠችው መርሻም በግልጽ ቢነግሩን ትልቅ ከበሬታን ያገኙ ነበር። ክብር ለሕይወት ተፈራ ይድረስ።

በቅርቡ አቶ ዓቻምየለህ የተባሉ ፀሐፊ እስኪ ዶሴው ይውጣ በሚል ርዕስ ተከታታይ ጽሑፎች የኢሃፓን ተመክሮና ስህተት ቁልጭ አድርገው በማስረጃ አስነብበውናል። ፀሐፊው የኢሃፓ ልሳን የሆነውን ዴሞክራሲያን እትሞች በማጣቀ ባቀረቡት ጽሁፍ ዓይን ያፈጠጡ ሐቆችን እና ስህተቶችን አብራርተዋል። አቶ አቻምየለህ የዚህ ትውልድ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ከእኛ ትውልድ ምን ተመክሮ እንዳገኙ ተናግረዋል። እኔ እስከማውቀው የኒህን ሰው ጽሁፍ የሚአስተባብል ከኢሃፓዎች እና ድርጅታቸው አንድም ማስተባበያ አልተሰማም። በአቶ ዓቻምየለህ አመለካከት፤ አጻጻፍ እና አነጋገር ኢሃፓ የኤርትራን የነፃነት ጥያቄ በአቅዋም ደረጃ እንደ ደገፈ፤ የሶማሊያ ወረራን በተመለከት ኢሃፓ የሁለት አምባ ገነኖች ጦርነት ስለሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ደርግን እንዳይደግፍ እንደቀሰቀሱ፤ ዓማራው ትምክህተኛ ስለሆነ ኢሃፓ ይህን ህብረተሰብ እንደሚዋጋው በልሳኑ ማወጁን ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል። በቀይ ሽብርና በነጭ ሽብር ጊዜም ኢሃፓ ከደርግ እኩል ተጠያቂ እንደሆነ አብራርቷል። የኤርትራን ነፃ መውጣት፤ የአፋር፤ ኦሮሞ እና ሌሎች ብሔሮች ከፈለጉ መገንጠል እንደሚችሉ በልሳናቻው ወስነዋል። ይህ ሁሉ ብሔር ተገንጥሎ ምን ዓይነት አገር ሊቀራቸው፤ ሥልጣን ቢይዙስ ምን ዓይነት አገር ሊአስተዳድሩ ይችሉ እንደነበር የሚአውቁት መርሻና ጟዶቹ ብቻ ናቸው። ይህ ነው ሐቁ እና ከዚያ ትውልድ የተገኘው ገሃድ ትምህርት እና ተመክሮ። አሁን ወያኔ አገር ገነጠለ አስገነጠለ እያለ ኢሃፓ በመርሻ በኩል የሚወቅሰው ለምን እንደሆነ ሊገባን አይችልም። ይህን ካላችሁ ደግሞ እስኪ ያትውልድ የያዛቸው አቋሞች ስህተት ነበሩ ብላችሁ መርሻዎች በአደባባይ አውጁ። የኢትዮጵያን ሕዝብም ይቅርታ ጠይቁ። ይህን ስታደርጉ ነው ንስሐ ገባችሁ፤ ለዚህ ትውልድም ትምህርት እና ተምክሮ ሰጣችሁ የሚባለው። አይዞዎት በድፍረት ይናገሩ፤ ምንም የሚሆኑት ነገር አይኖርም። የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርባይነት እና የሃያሉ እግዚአብሔርን መሃሪነት ለአንዴም እንኳን ቢሆን እያሰቡ ይንገሩን፤ ያጫውቱን።

ሌላ ያ-ትውልድ በዚህ ትውልድ ወቅት የሰራውን አንድ ሱህተት ለናሙና እንጥቀስ። እርስዎ እንዳሉት በ1997 ዓ.ም. ፌድራላዊ ምርጫ ህወሐት ኢሐአዴግ በቅንጅት መሸነፉን አልቀበልም እንዳለ ጠቅሰዋል። ትክከል ነው። ግን ከመጀሚሪያው ቅንጅት እንዳያሸንፍ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ ቅስቀሳ እና ተቃውሞ ያደረገ እርስዎ እና ድርጅትዎ አልነበሩምን። ከብርሃኑ ነጋ ጋር በነበራችሁ ታሪካዊ አንባጓሮ ምክንያት በጅምላ አልተቃውማችሁትምን። በዚህ እና ከዚያ በፊት በነበራችሁ ቁርሾ ምክንያት አሁንስ ቢሆን አርበኞች ግንቦት ሰባትን ዓይንህ ላፈር የምትሉት በዚህ ቂምበቀል አይደለምን። መርሻ ህብረት፤ አንድነት እያሉ በመግለጫ የሚአላዝኑትን በተግባር መተርጎም ለምን አቃተዎት። ለርስዎ ከአንድነት ይልቅ የቂም በቀል ፖለቲካ፤ ከይቅርታ በበለጠ አካኪ ዘራፍነትን አይደለም እንዴ ለዚህ ትውልድ ያስተማራችሁት።  ከብርሃኑ እና ከግንቦት ሰባት ጋር አንድነት ከመፍጠር ከሕውሃት ጋር መስራትን እንመርጣለን አላላችሁም። እናንተ ብርሃኑ እና አንዳርጋቸው አዲስ አበባ ገብተው ከወያኔ ጋር ስለሠሩ በየአደባባዩ ስታወግዙ፤ ስታጥላሉ፤ ቁምስቅላቸው ስታሳጧአቸው አልነበረም። ዛሬ በሕውሃት በኩል ምን ተቀየረና ነው አሁን አገር ቤት ገብታችሁ ከመንግሥት ጋር መሥራት የፈለጋችሁት። የተለወጠ ነገር ኖሮ ሳይሆን ብርሃኑን ለመቃወም ሲባል ብቻ የተደረገው የእርስዎ ስትራተጂካዊ ለውጥ ነው።  ሐቁ ይሄ ብቻ ነው ሌላውን ይተወት።

ስለዚህ ለአቶ መርሻ እና ቡድናቸው የምንሰጠው አንድ ተምክሮ ቢኖር ወያኔ ከርስዎ እና ከቡድንዎ ጋር ከሚሰራ ከብርሃኑ እና አንዳርጋቸው ጋር እርቀ ሰላም ፈጥሮ አብሮ መስራትን እንደሚመርጥ ነው። ለምን ቢባል እናንተ ለሥልጣን የምትቋምጡ አደገኞች፤ አንዳርጋቸዎች ደግሞ ለሃገር እድገት እና ሰላም የሚሰሩ መሆኑን ጠንቅቀው ያውቃሉና።

እውነቱን እንነጋገር ከተባል ያትውልድ አነሳሱ ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ብዙ አልሞና ሰንቆ የተነሳ ነበር። በዚህ ምክንያት የምሁሩን፤ የወታደሩን፤ የወጣቱን፤ የአርሶአደሩን ቀልብ ስቦ የነበረ ድርጅት ነው። ለዚህም ነው አብዛኛው ወጣት በጥለቀት በማያውቀው የማርክሲዝም ፍልስፍና አብዶ ሕይወቱን የገበረው። ወጣቱም ኢሃፓን የሚአሽከረክረው ኢትዮጵያዊነት እንጅ ጠባቦች ሕወሃቶችና የኤርትራ ሻቢያዎች መሆናቸውን አልተረዳም ነበር።

ሐቁ ይውጣ ከተባለ ኢሃፓን የመሩት እነመርሻ ሳይሆኑ ዘረኞች የሆኑ ሕውሃቶችና ተገንጣይ ሻቢያዎች ነበሩ። መርሻን የመሰሉ አጃቢዎች ግን አሽቃባጮች እንጅ ወሳኝ (core) መሪዎች አልነበሩም። ኤርትራዊያን እና ተጋሩ ሕዝባዊውን ዓላማ መጠቀሚያ እንዳደርጟችሁ አሁን ጉዱ ፍጥጥ ብሎ ወጧል።  የተገኘውም ትምህርትና ተመክሮ ይሀው ስለሆነ አቶ መርሻ ሊቀበሉት ይገባል። ይህን እና ይህን የመሰለውን የስህተት ሃቅ ነው ለዚህ ወጣት ፤ ለዚህ ትውልድ ማስተማር ያለብን። ሾላ በድፍኑ ወጣቱትውልድ ከእኛ ስህተት ይማር ብሎ ማላዘን ፍች የለውም።  ወጣቱን ሊአስተምረው የሚችል እና እኛ ያደረግነውን ስህተት እንዳይደግም መምከር የምንችለው ሐቁን አውጥተን መንገርና ማስተማር ስንችል ብቻ ነው።  አራት ነጥብ።

ይህች አገር እና ሕዝቧ አሁን ለደረሱበት ውድቀት መንገድ የጠረገው ያትውልድ መሆኑ ይሰመርበት። አለባብሰው ቢአርሱ ባረም ይመለሱ ነውና ሾላ በድፍኑ አዲሱ ትውልድ ከዚያ ትውልድ ስህተት ይማር ብሎ አድበስብሶ ማለፍ ማስተማር ሳይሆን ወይ ማምታታት አለያም ሐቁን ላለመናገር የተደረገ አጉል ብልጣብልጥነት መሆኑን አቶ መርሻ ሊገነዘቡት ይገባል።

በመጨረሻም መርሻ ዮሴፍ ትህትና በተላበሰ መልኩ የመጨርሻ ኑዛዜአቸውን ለግሰውናል። አስራ አምስት ገጽ፤ ሰባት ሺህ ቃላት፤ ሰላሳ ሽህ ሆህያትን ተጠቅመው ዕራያቸውን ተናግረዋል። የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ወጣት እና ኢትዮጵያዊ ትውልድ ግን ምን ትምህርት እና ተመክሮ እንዳገኘበት አቻምየለህን የመሰሉ የዛሬው ዘመን ወጣቶች ፍርዱን ይስጡበት።

ከአብዮት ጀምሮ እስካሁን የተደረጉትን የፖለቲካ እንቶ ፈንቶዎች በሚገባ የሚአውቁ ለመሆኑ ጥርጥር ስሌለለን ከኑዛዜ በፊት ኢትዮጵያ፤ ዕውነት ተመክሮ እና ትምህርት ቢቀድም ፀሐፊውን ብዙ ባስከበራቸው ነበር።  ለማንኛውም ሕይወት የማያቋርጥ ትምህርት ቤት ናትና አሁንም አልመሸም።  ወደ ማይቀረው ዓለም ከመሄድዎ በፊት ሐቁን አስተምረው በማለፍ ነፍስዎን ለንስሐ ያብቋት። ኢትዮጵያን፤ ሕዝቧን እና አዲሱን የኢትዮጵያ ትውልድም ተመክሮዎን፤ ልምድዎን እና ዕውቀትዎን ስለእውነት ብለው በማካፋል አገርዎን ይታደጟት። ያምሆኖ ግን በጥቅሉም ቢሆን ተሳስተን ነበር ማለት በመቻልዎ ምስጋናየ ከአድንቆትጋር ይድረስዎት። ለውደፊቱም እውነቱን ለመናገር እንዲችሉ እግዚአብሐር ድፍረቱን እና ተመክሮ ይስጥዎት። ቸር ይግጠመን።

አቢቹ ነጋ

ሰኔ 23 ቀን 2009 ዓ.ም.

 

 

[1] አጽኖዖት እና ህዳግ የተጨመረ

The post አቶ መርሻ ዮሴፍ ከኑዛዜ በፊት ኢትዮጵያ፤ ዕውነት ፤ ተመክሮ እና ትምህርት ይቅደም – አቢቹ ነጋ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


አዲስ አበባንና አካባቢዋን ከኦሮሞ የማጽዳት አዋጅ – ሰርጸ ደስታ      

$
0
0

እኔ ብዙ ጊዜ ብዬዋለሁ የዛሬውን ብዙ የኦሮሞ ትውልድ ወያኔ በራሱ ስለሰራችው እንደፈለገች እንደምትዘውረው ታውቃለች፡፡ ከወያኔ ጋር የኦሮሞን ሕዝብ ልጆች ለማምከን ብዙ በኦሮሞ ሥም የተንቀሳቀሱ ድርጅቶች አሉ፡፡ በዋናነት ግን ኦነግ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ቁጥሩ አነሰም በዛም ዛሬ ላይ ድምጹ ከፍ ብሎ የሚሰማው ይሄው ወያኔ የሰራችው ትውልድ ድምጽ ነው፡፡ መቼም ይህን ከሚያክል ሕዝብ የተወሰነም ቢሆን የሚያስተውል ይጠፋል ብዬ አላስብም፡፡ እነ መረራና የሱ አጋሮች ዛሬ ላይ መናገር አይችሉም፡፡ ግን ቢያንስ የእነ መረራን መርህ የሚከተል ትንሽም ቢሆን ይገባዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከመጀመሪያው ጀምሮ በዋናነት አማራ ከሚባለው ሕዝብ ጋር ልዩ ጥላቻ እንዲያድርበት በፖሊሲ ጭምር ታግዞ ሲሰራበት ነው የቆየው፡፡ ዛሬ ላለው ኦሮሞ እየገደለው ያለው ወያኔ ምኑም አደለ፡፡ ዋና ጠላት አድርጎ የሚያስበው የኦሮሞ ክብርና ልዕልና ከፍ ያለበትን የሚኒሊክ ታሪክ ነው፡፡ ይህን እውነት እስከሚገባው ድረስ ኦሮሞ ከክብር እየወረደ እንደሚሄድ አትጠራጠሩ፡፡ ኦሮሞ በኦሮሞ ሥም በሚኒሊክ ዘመን ያለው ታሪክ ሁሉ በውሸት የተቀናበረለት አኖሌ ብቻ ነው፡፡ ሲያሰኘውም ጨለንቆን ይጨምራል፡፡ ልብ በሉ አሁን እየተነገረ ያለው የአኖሌ ታሪከ ፍፁም ውሸት ሲሆን በአርሲ የነበረው ጦርነት ግን ብዙ ጥፋት እንደነበረው የራሳቸው የሚኒሊክ መዋዕለ ዜናም መዝግቦት ይነበባል፡፡ ጨለንቆን ካሰባችሁ ከእነ ጭርሱም ከኦሮሞ ጋር የተደረገ ጦርነት አልነበረም፡፡ ከሀረሪው ገዥ ጋር ነበር እንጂ፡፡ ዛሬ ዘጠና ከመቶ በላይ የሚሆነው  ኦሮሞ ጨለንቆን ከኦሮሞ ጋር የተደረገ ጦርነት እንደሆነ ነው የሚያውቀው፡፡ ዛሬ የሚነገረው የአኖሌውንም የጨለንጦውንም የውሸት ታሪክ አስተውላችሁት እንደሆን እየተቀነቀነ ያለው በሙስሊም አክራሪዎች ነው፡፡ ኦሮሞን በሙሉ በሙስሊም አክራሪ ሴራ ውስጥ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ በተቃራኒው ታላላቅ ዝናና ገድልን የፈጸሙ የኦሮሞ ጀግኖች ታሪክ እንዲዋረድ ተደርጓል፡፡ ጀግኖቹ በአብዛኛው ከክርስቲያን ኦሮሞ ስለነበሩ ይህን ሆን ተብሎ ነበር ዘመቻው የተካሄደው፡፡ ጀግኖቹን አለም ሳይቀር መዝግቧቸዋል የኦሮሞ ሕዝብ ግን የገዛ ጀግኖቹንና ታሪኩን አጥቶ ምልከት የሌለው የመከነና ተቅበዝባዥ ወኔው የከዳው ሆኗል፡፡ ጎበናን ያቃልላል ያልታወቀ የሰፈር ሽፍታ እያመጡ ጀግና ይሰይሙለታል፡፡ ገበየሁ ጎራን፣ ባልቻ ሳፎን፣ እና እልቆ መሳፍርት የኦሮሞ ጀግኖች በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የሉም፡፡ እና ምን ባዶ ምልክት የሌለው ሕዝብ ምን ወኔና አቅም ይኖረዋል እንደፈለጉ ለሚዘውሩት ራሱን ሰጥቶ፡፡ ከዚህ ነበር የጀመረው የኦሮሞ ሕዝብ ውድቀት፡፡

በኃይለሥላሴም በደርግም ኦሮሞ እንደማኝኛውም ዜጋ የራሱ ድርሻ ነበረው፡፡ ይህ የኦሮሞ ትውልድ ግን ድርሻ አልነበረኝም ይላል፡፡ ዛሬ ግን አስተውሉ አሮሞ ምንም ውስጥ የለም፡፡ ሲስተማቲካል ሙልጭ ብሎ ከኢትዮጵያ ተሳትፎ ውስጥ ወጥቷል፡፡ ኦሮሞ በንግድ ውስጥ የለም፣ በስልጣን የለም፣ በትልልቅ ተቋማት የለም፣ ድሮ በሚታወቅበት በመከላከያ ሰራዊት መሪነት ውስጥ እንኳን ባዶ እንዲሆን ነው የተደረገው፡፡ ብልጦቹን የኦሮሞ ልጆች ሲስተማቲካሊ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ተደረገ፡፡ አሮሞን ዛሬ ብታዩት ምንም የለውም፡፡ ባለሀብት ጥሩ! ባለስልጣን ጥሩ! ኦሮሞ ምንም ውስጥ የለም፡፡ ኦሮሞ ኦሮሚያ የምትባል የቅዠት አገር ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ አሮሞ የለም፡፡ ይሄው ዛሬ 26 ዓመት አለፈው አሁንም አልነቃ ብሏል፡፡ ቋንቋ፣ ከተማ፣ የቦታ ሥያሜ ምናምን እያሉ ይደልሉታል፡፡ መሠረታዊ ማንነቱንና በአገሪቱ ያለውን ኢኮኖሚያዊም በሉት ማህበራዊና ፖለቲካዊ ድርሻ ግን እንዳይኖረው ተደርጎ ተጠርንፏል፡፡ ናዝሬት አዳማ፣ ደብረዘይት ቢሾፍቱ፣ ዝዋይ ባቱ፣ ተባሉ መልካም፡፡ ግን ለኦሮሞ ምን ጠቀመው;   ኦሮሞ በእንደነዚህ አይነት መደለያዎች እንደሚዘወር ስለተረዱት ታሪክም እውነትም መጠበቅ አያስፈልግም ብቻ ኦሮምኛ በማድረግ ኦሮሞን አፉን መዝጋት እንደሚቻል ሰዎቹ ተማምተናዋል፡፡ አዳማ በትክክልም ታሪካዊ ሥያሜዋን እንዳገኘች አልጠራጠርም መልካም ይህ ለኦሮሞ ሳይሆን ሌላውም ይጋራዋል፡፡ ዝዋይን ባቱ ብሎ መሠየም ግን ኦሮሞን ለመደለል ከተከደበትም አካሄድ በላይ ታሪካዊ ስህተትና የሌሎችን ታሪክ የሚጋፋ ነበር፡፡ ይህ ቦታ ከጥንት ጅምሮ ከዜይ ሕዝብ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ከኦሮሞም ሕዝብ በፊት የዜይ ሕዝብ በዚህ ቦታ ይኖር ነበር፡፡ ሀይቁ በእነዚሁ በዜይ ሕዝቦች ስም ዝዋይ ተባለ ከተማው ደግሞ ከሀይቁ ሥያሜውን አገኘ፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው በወያኔና ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊነት ቦታ ድራሹን ያጠፉት በቅዠት አገር በሚያኖሩት ነው፡፡ ኦሮሞን የከበበው ሕዝብ ሁሉ ኦሮሚያ የምትባለው አገር እውን ብትሆን ኦሮሞ ዋና ጠላታቸው እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ ለአለፉት 26 ዓመት የኦሮሞ ሕዝብ ያልተጋጨው አዋሳኝ የለም፡፡ ምክነያቱም በኦሮሞነት ሌላውን እንዲጠላ በመደረጉ ነው፡፡  እናም ዛሬ ኦሮሞ ሲባል የትኛውም ሕዝብ በበጎ አያይውም፡፡ እንደውም አማራ ከተባለው ጋር በተወሰነም ቢሆን መግባባቱ አለ፡፡

አሁን አዲስ አበባን ለኦሮሞ ጥቅም ማስከበር በሚል የተደረገው ይሄው ለዘመናት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሲቆመር የነበረው አሰራር ነው፡፡ አሮሞ በሌሎች ሕዝቦች እንዲጠላ ማድረግ የበለጠ ባዶ እንዲሆን የበለጠ እንዲምታታ ማድረግ፡፡ ኦሮሞ ከአልታገለ ወያኔ ብዙ እድሜ እንዳላት ታውቃለች፡፡ የወያኔ መጥፊያዋ ኦሮሞ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር የተባበረ ዕለት ነው፡፡ በወሳኝነት ቦታ እንዲሳተፍ አይፈለግም፡፡ ምክነያቱም በራስ መተማመን እንዳያመጣ፡፡ እንዲሁ የተወናበደ በራሱ የማይተማመን ኦሮሞ ነህ በሚል እየተደለለ እንዲኖር ነው በዋናነት እየተሰራበት ያለው፡፡ አስቂኙ የኦሮምን ጥቅም ያስጠብቃል የተባለው የአዲስ አባባ ከተማ አዋጅ ፍፁም ሕገ ወጥ ከመሆኑም በላይ ዳግም አሮሞን ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ሕብረት እንዳይኖረው የሚያደርግ፣ ግን ምንም አይነት ትቅም እንዳይኖረው የተቆለፈበት ነው፡፡ በግልፅ ግን የኦሮሞ ገበሬዎች በስፋት እንደሚፈናቀሉ ደንግጓል፡፡ አላማውም መሬቱን ከኦሮሞ ማጽዳት ነው፡፡ ልብ በሉ ዛሬ ሰዎቹ ገንዘብ ስላላቸው መሬቱን ሊገዙት ይችላሉ፡፡ ለኦሮሞ ገበሬውም በቂ ገንዘብ ሊሰጡት ይችላሉ፡፡ በዚህ ሂደት አዲስ አበባና ዙሪያዋ ከኦሮሞ የጸዳች  አካባቢ ይሆናል፡፡ ቀመሩ ይህ ነው፡፡

ለኦሮሞ ወጣቶች ሥራ እንሰጣለን የሚለው ሌላው አሳዛኝ ንቀት ነው፡፡ የኦሮሞ ወጣት የሀብት ባለቤት ሳይሆን የሚሆነው ተቀጣሪ ባሪያ ነው፡፡ ሀብቱ ውስጥ መቼም እድል እንዳይኖረው ሰርተውበታል፡፡ የእነሱን ፋብሪካዎችና ድርጅቶች ለማንቀሳቀስ ኦሮሞ ያስፈልጋል፡፡ ድሮስ የጉልበት ሠራተኛ የሚሆነው ማን ነው; ይህ አሳዛኙ ነገር አንዱ ነው፡፡ በአጠቃላይ ይህ አዋጅ አሮሞን በቀጣይም ከተሳትፎ በማራቅ በራስ መተማመኑን ሁሉ በማጥፋት የተገዥነት እውነታውን አሜን ብሎ እንዲቀበል የተደረገ ነው፡፡ አዲስ አበባን የሚሟገተው ኦሮሞ መላው ኦሮሚያ የተባለውን አገሩን ራሱ እንዳጣ አያውቅም፡፡ በዚህ አዋጅ ብዙዎች ጮቤ ረግጠዋል፡፡ ይህ ይጠበቅ ነበር፡፡ ይህንንም ታስቦ ነበር አዋጁ፡፡ አዋጁ የኦሮሞን ሕዝብ ዝም ለማሰኘት ታስቦ የወጣ እንጂ ወያኔ የደረሰችውን ሕገመንግስቷ አንቀጽ49/5 የሚለው ጋር ምንም አይገናኝም፡፡ አዋጁ አዲስ አበባ በኦሮሚያ እምብርት ላይ በመሆኗ እያለ በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡ ይህ ማሳከር ነበር፡፡ አንቀጽ ተብዬው የሚለው አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል ስለሚገኝ ነው የሚለው፡፡ መሀል ማለት አካለ ነው ማለት አደለም፡፡ ራሱን የቻለ አስተዳደርም አለው፡፡ አዲስ አበባ የራሱ መስተዳደር እንዲኖረው የሆነበት ብዙ ምክነያቶች ይዘረዝራል፡፡ አዲስ አበባ ከሥያሜዋ ጀምሮ ሕገ ምንግስት ተብዬው ያጸደቀው ነው፡፡ አሁን ፊንፊኔ ምናምን ኦሮሞን ለማስደሰት ነው፡፡ የኢስ አባባ መንገዶችና ሰፈሮች እንደአስፈላጊነቱ በኦሮምኛ ይሰየማሉ ይላል፡፡ ይህም ያው አሮሞን ለመደለል ነው፡፡ በእንደእነዚህ ያ ነገሮች እንደሚረካ እናውቃለን ብለው ስለሚያስቡ፡፡ ሲጀምር የአዲስ አበባ መንደሮች የኦሮምኛን ሥያሜያቸውን አጥፍተውም አያውቁም፡፡ አሁንም ቢሆን ፒያሳና መርካቶን እንቀይር ካልተባለ የኦሮምኛ ሥያሜዎች እንዳሉ ናቸው፡፡ ከጊንፊሌ፣ ቀበና፣ የካ፣ ቦሌ፣ ጉለሌ፣ ምናም፡፡ እንግዲህ 7ኛ አብነት ምናምን የሚባሉትን ኦሮሞ እንደሚያስበው አማራ አልሰየማቸውም፡፡ ለቡ፣ አቃቂ፣ ቃሊቲ፣ ለመሆኑ ግን አማርኛው የት ነው፡፡ ምን አልባት መገናኛ፡፡ ኮተቤም አማርኛ አደለም፡፡ መንገዶቹም አሁን ተሰይመው ያሉት በአብዛኛው በሌሎች ሕዝቦች ነው፡፡ መቼም ኦሮሞ ነፍጠኛ የሚላቸው አንዱንም መንገድ በሥማቸው አልሰየሙም፡፡ እንዲህ ነው በኦሮሞ ላይ እየተሰራ ያለው ድራማ፡፡ ኦሮሞ በዚህ ከቀጠለ በቁጥርም አናሳ እንደሚሆን ይሰማኛል፡፡ በአለፉት 26 ዓመት ከምንም ነገር ውስጥ እንዳይታይ ተደርጎ በፖለቲካ ውዥንብር ውስጥ ከሌሎች ጋር እንዲቃርን ሲደረግ ነው የኖረው፡፡ አሁንም ብዙው አልነቃም፡፡

ሰሞኑን አቶ ለማንና ቡድናቸውን የሚያወድስ ጽሁፍ ጽፌ ነበር፡፡ እርግጥ ትንሽ ማየት እንዳለብን ተናግሬም ነበር፡፡ እስከዛሬ እየመጡበት በአለው ነበር ለገመግም የሞከርኩት፡፡ በዚች በአዲስ አበባዋ አዋጅ ዋና ጮቤ ረጋጭ እንደሆኑ ሳይ ግን እስካሁንም ለካ ሕዝብን በእነሱ ቀለበት ውስጥ ለመክተት ነው የሚል ጥርጣሬ አደረብኝ፡፡ ከጥርጣሬም በላይ እነለማ የኦሮሞን ሕዝብ ለቀጣይ አመታት ለሽያጭ እንዳቀረቡት ተሰማኝ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ይህ አዋጅ ዛሬ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን አዋጁን ራሳቸው እንደሚፈልጉት አዘጋጅተው የተወሰነ በተለያዬ ሚዲያዎች ሕዝብ ምን ይላል የሚለውን ለማወቅ ሲለቁና አይ እኛ አናውቀውም ሲሉ ከርመው ያው አሁን ያወጁት በዛ መሠረት ነበር፡፡ እነ ለማ አሳምረው ያውቁ ነበር፡፡ በሕግም በሞራልም፣ በምንም ዋስትና የሌለውን አዋጅ በኦሮሞ ሕዝብ ሥም አውጀው እነሱ ዋጋ ተቀበሉበት፡፡ በዚህ አዝናለሁ፡፡ አቶ ለማን መስሎኝ መጀመሪያ ሥራዎ የታሰሩ የሕዝብ ልጆች እንዲለቀቁ ማድረግ ነው የሚል ምክርም ሞክሬ ነበር፡፡ ለነገሩ ብዙ ሌሎች የኦሮሞ ልጆችም አቶ ለማን በዚህ ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጡ መክረዋል፡፡ አሁን ግን ሳይ ገና የተናገሩት እንኳን ከሰው ጆሮ ገብቶ ሳይደመጥ የኦሮሞን ሕዝብ የገበያ ማቅረባቸው አሳዝኖኛል፡፡ እንደእኔ ይህን አዋጅ የአቶ ለማ ቡድን መቀበል አልነበረበትም ብቻ ሳይሆን በዚህ ወቅት ምንም አይነት ነገር በዚህ ጉዳይ ላይ ተባባሪ መሆን አልነበረበትም፡፡ ይህ 23ዓመት ሥራ ላይ ያልዋለ አዋጅ ዛሬ ሕዝቡ ፍጹም ከዚህ የተለየ ጥያቄ እየጠየቀ በአለበት ወቅት ነው ለማ የ23 ዓመት ሻጋታ ሕዝብ ትዝ የማይለውን ጉዳይ ያነሱት፡፡ እሱም የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ ለለስኩልህና አርፈህ ተቀመጥ ለማለት፡፡

በአጠቃላይ የኦሮሞ ሕዝብ ወደነበረበት ማንነቱ ከአልተመለሰ እንዲሁ ይቀጥላል፡፡ አሁን አማራውንም እንደኦሮሞው ከታሪክና ማንነት ለማምከን ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ኦሮሞን በተሳካ ሁኔታ እንዳመከኑት የተረዱት አሁን አማራውን ብሄረተኛ በሚል እያጦዙት ነው፡፡ ልብ በሉ በወያኔ የዘወር የነበረው የኦነግን እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ሲኦል ማድረግ ነበር፡፡ 26 ዓመት ሕዝቡን ከኢትዮጵያዊነቱ አመከነው፡፡ ጀግኖች አባቶቹን አስጣለው ዛሬ ወኔ የሌለውና አላቃሻ አናሳ ከሚባሉትም በታች አቅም የሌለው ሆነ፡፡ ለዘመናት እየተገደለም እየታሰረም ቢሆን አማራ የተባለው ወያኔን ሲፈታተናት ነበር፡፡ ይህም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው እምነቱ ጽኑ በመኆኑ ነው፡፡ አሁን ወያኔ ኦሮሞን እንዴት እንዳመከነቸው የሰራላትን ሥልት በአማራው ላይ በከፍተኛ ትኩረት እየሰራችበት ነው፡፡ ዛሬ አማራ የሚባለው እንደ አሸን የበዙ ድርጅቶች አሉት ሁሉም ይነታረካሉ፡፡ ብዙ ትውልድ ቤተ አማራ የተባለ የወያኔ ተላላኪ ተከታይ ሆኖ ገደል እየገባ ነው፡፡ አማራ በአማራነቱ አደለም ታሪክ ያለው፡፡ በኢትዮጵያዊነቱ እንጂ፡፡ ኢትዮጵያዊነት ከሌለ ጉልበት፣ ወኔ፣ ኣላማ የለም፡፡ አማራ በጊዜ ከአልነቃ በኦሮሞ የሆነው መምከን እንደሚመጣበት አትጠራጠሩ፡፡ ዛሬ ኦሮሞ የሰፈረበት ምድር የሌሎች ሆኖ ቢሆን ወያኔ አዲስ አበባ ላይ አደለም ደደቢት ቦታ ባልኖራት፡፡   አማራን ነፍጠኛ ሲሉት ያጣጣሉት መስሏቸው ነበር፡፡ ግን አዎ ነፍጠኛ ነኝ እኮራለሁ በዚህ ሲል ጭራሽ  ወኔና ጉልበት እንደሆነው ገብቷቸዋል፡፡ አሁን የሚያዋጣው አማራን ተበዳይ ነህ በሚል የበታችነት ስሜት እንዲኖረው ማድረግና እንደኦሮሞ ከታሪክም፣ ከወኔም ማምከን ነው፡፡ ኦሮሞም ተጨቁነሀል እየተባለ ነው የክብር ታሪኩንና ጀግኖች አባቶቹን ጥሎ ዛሬ ከምንም የሌለ መካን የሆነው፡፡  አንዴ ከታሪክና ከማንነቱ ከወጣላቸው የሚያደርጉትን እነሱ ያውቃሉ፡፡ ቤተ አማራ አማራውን ከታሪክና ከማንነት ለማምከን ኦነግ የተባለው የኦሮሞ ኮፒ በአማራ እንደሆነ ሰው ልብ ሊል ይገባዋል፡፡ ኦሮሞን ይሄው ዛሬ መላውን ኦሮሚያን ነጠቀውት አዲስ አባባንም ሰጠንህ ሲሉት እየተደሰተ ነው፡፡ ጊዜ በአገኙ ቁጥር ከቁጥሩም ያሳንሱታል፡፡ እነሱ በአዲስ አበባ ብቻ አደለም በሌላውም ዋና ዋና የኦሮሞ ግዛቶች ይስፋፋሉ፡፡

አመሰግናለሁ

ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!

አሜን!

ሰርጸ ደስታ

The post አዲስ አበባንና አካባቢዋን ከኦሮሞ የማጽዳት አዋጅ – ሰርጸ ደስታ       appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የቁልቁለት መንገድ አዲስ አበባ ገደል ስትገባ!! – አገሬ አዲስ    

$
0
0

በየትኛውም ዓለም ከተማ ውስጥ የሌለና ያልታዬ ታሪክ በአገራችን ዋና ከተማ በሆነችው አደስ አበባ ውስጥ ለበለጠ የህዝብ ልዩነትና  አገራዊ ቀውስ የሚዳርግ እቅድ ሰሞኑን በወያኔ ካቢኔ በህግ ጸድቆ ይፋ ወጥቷል።ህጉን ምክርቤት ተብየው የወያኔ ሆድ አደር መንጋ ካሳለፈው ለዘመናት ኢትዮጵያውያን በደምና በአጥንታቸው፣በእውቀትና በሃብታቸው የገነቡትን የጋራ ከተማ የሚንድና የአዲስ አበባን ሁልንተናዊነት አጥፍቶና ንዶ የጠበበች፣ የግጭትና የልዩነት አውድማ አድርጎ የሚያደራጅ ነው።

የወያኔ ዘላቂ ዓላማ ኢትዮጵያን በታትኖ የራሱን ጠባብ ክልል አገር አድርጎ ለመፍጠር እንደሆነ ምርምር አያሻውም።በዚያው አኳያ በኢትዮጵያዊነት የተሰሩትንና የተገነቡትን እየናደ፣የሚያስተሳስረውን ድርና ክር እየመዘዘ ማዳከም ለዘላቂው ዓላማው መጀመሪያው እርምጃ ነው።ባይሆንልን ብትንትኗን አውጥተን እንመለሳለን ከሚለው ነባር ዓላማ ጋር የተያያዘ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባውም።

የወያኔ መራሹ የጎሰኞች ስብስብ አገር አቀፍ ህዝባዊ ተቃውሞ ዓላማውን እንደሚያጨናግፍበት በመረዳት  የትግሉን ትስስር ለመበጠስና ለማዳከም የተካነበትን የማለያየት ስልት፣አንዱን የጠቀመና መብቱን ያስከበረለት በመምሰል ሁሉንም የሚጎዳና ለበለጠ ግጭት የሚዳርግ ስልቱን  ሰሞኑን በአዲስ አበባ አስተዳደር ዙሪያ በመጀመር ይፋ አድርጓል።በዚህ ይፋ ባደረገው አዲስ የህገመንግስት አንቀጹ አዲስ አበባ የሁሉም ከተማ መሆኗ ቀርቶ የአንድ ማህበረሰብ ከተማ እደሆነች በማመን ዘርና ጎሳን ተንተርሶ ያልወጣላት ስሟም የኦሮሞ ተገንጣዮች በሚጠሯት ስም  ፊንፊኔ በሚለው ጭማሪ እንድትጠራ(ይህ እራሱን የቻለ ውዥንብር የሚፈጥር ነው፤የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በየትኛው ለመጥራት ግራ ይጋባል፤ከተማዋም ለሚኖራት ግንኙነት ሁሉ እንቅፋት ይፈጥራል)።ሁሉም ነዋሪ የሚጠቀምበትና የሚግባባበት ቋንቋ ቀርቶ አንድ ማህበረሰብ ብቻ የሚናገረው የኦሮሞ ቋንቋ የአስተዳደሩ ተጨማሪ የስራ ቋንቋ  ለማድረግ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅቱን ጨርሶ ህጋዊ ሽፋን ሰጥቶት መወሰኑን ባወጣው መንግስታዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል።ይህ ተንኮል ግን ኦሮሞውን ለመጥቀም ሳይሆን የተነሳበትን ተቃውሞ ለጊዜው ለማብረድና በስፋት የያዘውን የዘረፋ ዕድሜ ለማራዘም ሆን ተብሎ የተተመነ ስልት ነው።የኦሮሞም ሆነ የሌላው ማህበረሰብ  ተወላጅ ጥያቄው ቋንቋየን እየተናገርኩ ከሌላው ተነጥዬ ልረገጥ ሳይሆን የሰብአዊና የዜግነት መብቴ ይጠበቅ፣ከድህነትና ከዃላቀርነት የሚገላግለኝ የጋራ ስርዓት ይመስረት፣የዴሞክራሲ መብቶች ይከበሩ፣በጎሳ ማንነት መጠቀምና መጎዳት ይቅር ለወደፊቱም አይኑር፣ከትውልድ የወረስኩት መሬቴን  እየተቀማሁ አልፈናቀል… የሚል ነው።

አዲስ አበባ የአገራችን የፖለቲካና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መዲና ፣የአገሪቱም የኤኮኖሚ እምብርት መሆኗ እየታወቀ የአንድ ነጠላ ማህበረሰብ ጥቅም ብቻ የሚከበርበት አንቀጽ  ህጋዊ መመሪያ አድርጎ መደንገግ፣በከተማዋም ሁለገብ ህይወትና በነዋሪው እጣፈንታ ላይ የአንድ ማህበረሰብ የበላይነት ማስፈን  ፍትሃዊና ለሰላማዊ ኑሮና ለህዝብ ጤናማ ግንኙነት የሚረዳ አይደለም።የከተማዋ እድገትና ህይወት ሁሉም የኢትዮጵያ ክፍለሃገሮችና የተለያዩ ማህበረሰቦች ተወላጆች ያበረከቱት ድርሻ ውጤት ነው።ከተማዋ የተገነባችው ከሁሉም ያገሪቱ ክፍሎች በሚሰበሰበው የግብርና የእውቀት መዋጮ ነው።ስለሆነም ሁሉም እኩል የባለቤትነት ድርሻ ሊኖረው ይገባል።ኦሮሞኛ ለሚናገረው ቅድሚያና ብልጫ ጥቅም ይሰጠዋል፣መብቱም ይከበርለታል ማለት በዘረኛው አፓርታይድ ስር  እንደ ቀድሞዋ ደቡብ አፍሪካና ከሚሊዮን ህዝብ በላይ በጎሳ ውዝግብ እንደተጨፈጨፈባት ሩዋንዳ ከባሰ ቀውስ ውስጥ የሚከት ነው።ለመሆኑ ኦሮሞኛ የማይናገረው አዲስ አበባ ውስጥ ተወልዶ ያደገው የኦሮሞ ልጅ ምን ይውጠው ይሆን?ኦሮሞኛ የሚናገረውስ የሌላው ማህበረሰብ ተወላጅ የጥቅሙ ተካፋይ ይሆን ይሆን?ወይስ የጀርባ አጥንቱ እየታዬ ለጥቃቱ ሰለባ ይሆናል?

በሌሎቹስ ክፍላተ ሃገሮች ውስጥ የተቋቋሙትና የተፈጥሮ ሃብት ምንጭ የሆኑት አካባቢ ህዝብ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ያገኛልን? የኤሌክትሪክ ምንጭ፣የወርቅና የተለያዩ ማዕድኖች ቁፋሮ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች ህዝብ የጥቅሙ ተካፋይ የሚሆንበት አሰራርና ህግ መቼ ተፈጠረለት?የበይ ተመልካች ከመሆን ያለፈ ዕድል መች አገኘ?

ይህ እንደ አዲስ የወጣ የማጠናከሪያ ደንብና መመሪያ ምናልባት የኦሮሞውን ማህበረሰብ የሚጠቅም ሊመስል ይችል ይሆናል።አርቆ ለሚያስብ የኦሮሞ ተወላጅ ግን ተቃውሞውን ለመግታትና አገራችንን ለመበታተኑ ሂደት የመጀመሪያው መንደርደሪያ እንደሆነ፤ ብቻውን ነጥሎ የሚያስመታውና የሚያስጠቃው የወያኔ ሰይጣናዊ ብልሃት መሆኑንም ሳይረዳው አይቀርም።

የዘፈን ዳርዳሩ እስክስታ ነው እንዲሉ ወያኔ ስልጣን ከመያዙ በፊት ከአጋሩ ከኦነግ ጋር ሆኖ በጀርመን አገር ውስጥ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ከፈረንጆቹ በኩል « ኦነግ ተሳክቶለት ስልጣን ላይ ቢወጣ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚኖረው ከሁሉም ክፍለሃገር የተውጣጣ ህዝብ ምን ዕድል ይገጥመዋል?» ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ የኦነጉ መሪ የዛን ጊዜው አቶ የአሁኑ ዶክተር ዲማ ነገዎ(ዩሃንስ ነገዎ) የሰጠው መልስ «ለኦሮሚያ የሚጠቅመው መኖሪያ ፈቃዱን እያሳደሰ ሲኖር የማይጠቅመው ደግሞ ወደ መጣበት እንዲመለስ ቀዳዳ መንገድ(safe corridor) ይከፈትለታል» ብሎ ነበር።ይህንን ባለ በስድስት ወሩ ሻእብያ፣ወያኔና ኦነግ ከሌሎቹ በአማራው ስም ከተደራጁት አሽከሮቹ ጋር ስልጣኑንc ጨበጡ።ይህንን የተናገረው ዲማ ነገዎ(ዩሃንስ ነገዎ)የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሆነና በውጭ አገር በመዘዋወር ስለተመሰረተው አገዛዝ መብራሪያ ለመስጠት በውጭ አገር እየተዘዋወረ በየስብሰባው መድረክ ላይ ብቅ አለ። በስብሰባ ላይ ያንን ቀድሞ ጀርመን የተናገረውን በአካል ካዳመጥነው ውስጥ አንዱ ቢጠይቀው« አይኔን ግንባር ያድርገው!፣እንዲህ ያለ ቃል ካፌ ወጥቶ አያውቅም» ሲል ሸመጠጠ።ይባስ ብሎም በጠያቂው  ላይ በስብሰባው የተሳተፉት አብዛኛዎቹ የወያኔና የሻእብያ ደጋፊዎች እንዲዛበቱበት የግለሰቡን  አስተያየት አጣጥሎ ለማቅረብ ሞከረ።

እውነትና ጀንበር እያደር ይጠራል! ነውና የኸው ዛሬ ከሃያ ሰባት ዓመት በዃላ የዚያ አስተሳሰብ እንቁላል ተፈልፍሎ በአደባባይ ይፋ ወጣ።

የአዲስ አበባ ከተማ በሸዋ ክፍለሃገር የምትገኝ እንጂ ኦሮሞ የሚል ክፍለሃገር እንዳልነበረና በዚያ  ክፍለሃገር ውስጥ የምትገኝ ከተማ እንዳልነበረች ሁሉም ያውቃል።የሸዋ ክፍለሃገር ደግሞ ኦሮሞውን ብቻ ሳይሆን አማራውና  የተለያዩ ማህበረሰቦች የሚኖሩበት ክፍለሃገር ነው።ስለሆነም  የባለቤትነቱ ጥቅም ይከበርለት ቢባል እንኳን የዚያው የሸዋ ጠ/ግዛት ህዝብ ይሆናል እንጂ የአንዱ ማህበረሰብ ብቻ ሊሆን አይገባውም።

የከተማውንም አስተዳደር በሚመለከተው የአንድ ከተማ አስተዳደር የሚዋቀረው በነዋሪው ብዛትና አኳያ ሊሆን ይገባዋል።አዲስ አበባ በክፍለ ከተማ ና ወረዳ እንዲሁም ቀበሌና መንደር የተዋቀረች በመሆኗ፤በነዚህም የከተማዋ እርከኖች  ውስጥ ከተለያዩ ማህበረሰቦች የፈለቀና የተዋለደ ህዝብ ስለሚኖር አስተዳደሩም(ማዘጋጃቤቱም)የነዋሪውን ገጽና ስብጥር የሚያካትት ሊሆን ይገባዋል።የሚጠቀምበትም የስራ ቋንቋ የከተማው ህዝብ የሚግባባበትና በአገሪቱ ህግ የጸደቀው የአማርኛ ቋንቋ ሊሆን ይገባዋል።ይህ ማለት ግን በከተማዋ ውስጥ ብሎም በአገር አቀፍ ደረጃ ተጨማሪ ቋንቋዎች አይነገሩ ማለት አይደለም።ማንኛውም ዜጋ ከጎሳው አባል ጋር እርስ በርሱ ሊግባባበት የሚችለውን ቋንቋ መናገሩ በህግ ብቻ የሚጸድቅ ሳይሆን ከቤተሰብና  በትውልዱ ያገኘው ችሎታና መብቱ ነው።ኦሮሞው ከኦሮሞው ጋር ለመግባባት ኦሮምኛ ይቀለዋል፤እንደዚህም ያለው ግንኙነት ለዘመናት የቆየና ያለፉት ስርዓቶችም የከለከሉት አሰራር አልነበረም፤በወያኔ መራሹ ስርዓት  ብቻም እውቅና የተሰጠውም አይደለም።ሰው ከሌላው ጋር ለመግባባት የሚመርጠው ቋንቋ ከሁኔታው ጋር የሚያየውና በግላዊ ውሳኔው የሚወስደው እንጂ በህግ ተገዶ የሚከተለው መሆን የለበትም።ብዙ ማህበረሰብ በሚኖርበት አገር ውስጥ የአንድ ማህበረሰብ ተወላጅ የሆነ ዜጋ በራሱ የጎሳ ቋንቋ ቢናገር ከጎሳው ተወላጅ በስተቀር ከሌላው ጋር ሊግባባ አይችልም፤ስለሆነም የሚግባባበት የጋራ ቋንቋ መኖሩ ችግሩን ያቃልልለታል።በታሪክ አጋጣሚ የሁላችን ቋንቋ የሆነው አማርኛ በሌሎቹ ማህበረሰብ ተወላጆች ላይ በግድ የተጫነ ሳይሆን በህብረተሰቡ ቅልቅልና መስተጋብር ሂደት ቃላት እየወረሰ ያደገና የተስፋፋ ቋንቋ ነው።

በኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ የተወለደ የየትኛውም ማህበረሰብ ተወላጅ ኦሮምኛ ለመናገር ዕድሉ ከፍ ያለ ነው።ይናገረዋልም።የሌላውም በሌላውም ቦታ እንዲሁ ነው።የሁሉም ቅልቅል በሚኖርባትም የአዲስ አበባ ከተማ ኑዋሪ በሚያግባባው የጋራ ቋንቋ በአማርኛ መናገሩ ሊሻርና ሊገደብ አይገባውም።በአዲስ አበባ ብቻም ሳይሆን በተቀሩት ክፍለሃገር ውስጥ የሚኖረው ህዝብ ከየማህበረሰቡ የተውጣጣ በመሆኑ አንድ ቋንቋ አማርኛ መናገራቸው ከነጠላ ጎሰኝነት አጥር ውስጥ ፈልቅቆ ሊያወጣቸው ችሏል ለወደፊቱም ይችላል።የከባቢ ቋንቋ ብቻ ይነገር ከተባለ ከሰማንያ በላይ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ሳይግባቡ ይኑሩ ብሎም በቋንቋቸው ተዋረድ የየራሳቸውን ክልልና መንግስት አቋቁመው እርስ በርሳቸው እየተጋጩና እየተዋጉ ይለቁ ብሎ መፍረድ ይሆናል።አዲስ አበባም ውስጥ የሚኖሩት  አማራና ኦሮሞ ብቻ ስላልሆኑ ሁሉም የማህበረሰብ አባል የጎሳዬ ቋንቋ የአስተዳደሩ ቋንቋ ይሁንልኝ የማለት ጥያቄ እንዲያቀርብ በር ይከፍታል። ወያኔና ግብረአበሮቹም  የሚወጡት የሚወርዱት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ብሎም በአጠቃላይ በአገራችን ኢትዮጵያ በዚህ አይነቱ ዘዴ ትርምስምስ እንዲመጣ ለማድረግ ነው።በትርምሱ የሚያልቀው የፈረደበት ህዝብ ነው።እነሱ ቤተሰባቸውን ይዘው ቀድሞ ወዳዘጋጁት አገር ይሾልካሉ፤ቀድመውም የሾለኩና ያሾለኩ ብዙ ናቸው።።የደርግ መሪዎች የመጨረሻው ታሪክ ትዝ ሊለን ይገባል።የወያኔና ተባባሪዎቹ ገንዘብና ንብረት በውጭ አገር ማካበታቸው የሚታበል አይደለም።ህዝቡን ኦሮምኛ፣ትግርኛ… ተማር፣ተናገር እያሉ ሲያስጨንቁት ልጆቻቸውን ግን በሚሸሹበት አገር ችግር እንዳይገጥማቸው በከፍተኛ ወጭ በቤትና በውጭ አገር ት/ቤቶች ቋንቋ ያስተምራሉ። ሁለትና ሶስት የውጭ አገር ቋንቋ የማይናገር የባለስልጣን ልጅ ተፈልጎ አይገኝም።

የኦሮሞን ተወላጅ ጥቅም ለማስከበርና ለተጎዳው ካሳ መክፈል የሚለው የማታለያ ስልት ዕድሜን ከማራዘም ሌላ ትርጉም የለውም።በአዲስ አበባ መሬቱን የተነጠቀውና የተፈናቀለው ኦሮሞው ብቻ አይደለም።ከተማዋ ከተቆረቆረችበት ጀምሮ ለብዙ ዓመታት ከአያት ቅድመአያት ሲወርስ ሲወራረስና ገዝቶ ቤት ሰርቶ የኖረውም ኦሮሞ ያልሆነው ዜጋ የጥቃቱ ሰለባ ሆኗል።ወያኔና የሱ ባለሟል የሆነው የከተማዋን አስተዳደር በመያዝ መሬቱን እየነጠቀ ለከበርቴዎች በመሸጥ የባለስልጣኖች የገቢ ምንጭ ያደረገው ኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት( ኦፒዲኦ) የተባለው በኦሮሞ ህዝብ ስም ስልጣን ይዞ መልሶ ኦሮሞውን የሚያጠቃውና የሚያስጠቃው ቡድን ነው።ካሳ መክፈልም ያለበት ይኸው ድርጅትና የገበያው ሸሪኮቹ ናቸው። ካሳ ይከፈል ከተባለ ደግሞ መሬቱን የተነጠቀውና ቤቱ የፈረሰበት፣መጠለያ አጥቶ ለመከራ የተጋለጠውንና ጥቂት የገንዘብ መደለያ እንዲቀበል ተገዶና ተታሎ መሬቱ ለከፍተኛ ዋጋ የተሸጠበት ያዲስ አበባ ኑዋሪ ሁሉ ይመለከተዋል።በሌሎቹም ያገሪቱ ከተማዎች ተመሳሳይ ግፍ የተፈጸመ ሲሆን የካሳ ጉዳይ ከተነሳ በተመሳሳይ መንገድ ተግባራዊ ሊሆን ይገባዋል።

ቋንቋን በተመለከተ  ኦሮምኛም ሆነ የሌሎቹ ቋንቋዎች ማደግ ተገቢ ነው ።ሌላው ቀርቶ የውጭ አገር ቋንቋዎች የሚሰጡበት ትምህርት ቤት በተከፈተበት ከተማ የኦሮምኛም ሆነ የሌሎቹ አገር በቀል ቋንቋዎች ትምህርት ቤት መክፈቱ ለቀና ዓላማ እስከሆነ ድረስ ጉዳት የለውም።የፈለገ ሰው  ጎሳው ሳይታይ  ሊከታተለው ይችላል።ለአማራውም ሆነ ለሌላው ኦሮሞ ላልሆነውም ቢሆን አማርኛ ከማይችለው ኦሮሞ ወገኑ ጋር የሚግባባበትን ዕድል ከፍ ያደርግለታል።ጥንቃቄ የሚያሻው ነገር የተገንጣዮች ዓላማ መሳሪያ እንዳይሆን መከላከሉ ነው።እውነት ለኦሮሞ ህዝብ የሚያስቡለትና የአፍላቂነት ችሎታ ቢኖራቸው ኖሮ ከነጮችም  ተጽእኖ እንዲድን ቢፈልጉ ኖሮ የላቲን ፊደላትን አምጥተው ባልጫኑበት ነበር። ለኦሮሞ ህዝብ አዲስ የፊደል ባለቤት ባደረጉትና ሁላችንም ኢትዮጵያኖች የምንኮራበት ተጨማሪ እሴት እንዲኖረን ባደረጉ ነበር።የጠባብ ጎሳ ምሁራን ግን ቆምንለት ያሉትን ወገናቸውን ለውጭ አገር ባዕዳን ተጽእኖ በቋንቋው ጀርባ አሳልፈው ሰጥተውታል።እነሱ ግን አማርኛን ከአማራው በላይ እየተናገሩ በስልጣኑ ላይ የተቀመጡ ነበሩ፤ናቸውም።የቀና ልብ ባለቤቶች ቢሆኑማ ኖሮ  ልዩነትን የሚፈጥሩ ነገሮችን እያጠፋ አንድነትን በሚያመጡት ላይ ማተኮር በቻሉ ነበር።የዓለም ህዝብ ሊግባባ የሚችልበትን ቋንቋ በፍላጎቱ እየተማረ ካገሩ ወጥቶ እየተግባባ ሲኖር የአንድ አገር ህዝብ የሚግባባበትን ቋንቋ  እንዲጠላና በጎሳው ቋንቋ እየተናገረ እንዳይግባባ ማድረግ ጸረ አገር  ብቻ ሳይሆን ጸረ ህዝብ አሰራር ነው።

የአዲስ አበባን አስተዳደር በሚመለከተው ዙሪያ የወጣውን መመሪያ ከሌሎቹ የሰለጠኑ የዓለም ከተማዎች አሰራር ጋር ሲነጻጸር የሌሎቹ በጎሳ ዙሪያ የተቀነባበረና የተዘጋጀ ሳይሆን የከተማው ነዋሪ የሚሳተፍበትና  ብሎም የአገሪቱ ዜጋ ሁሉ የሚጠቀምበት ሁኔታን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው።አስተዳደሩም የሚመሰረተው ከጎሳ አንጻር ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቶች በፍልስፍና ላይ በተመሰረተ መርሃ ግብር አኳያ በምርጫ ወቅት ባገኙት የህዝብ ድምጽ መጠን አንዱ ብቻውን  ወይም ከሌሎቹ ጋር በጥምር ሁሉም የሚካፈልበትና የሚጠቀምበት አስተዳደር ይቋቋማል እንጂ አንዱን ነጠላ የጎሳ ማህበረሰብ ብቻ በሚጠቅም ሌላውን  በሚጎዳ፣ባይተዋርና ባዳ በሚያደርግ  እኩይ ጽንሰሃሳብ የሚመራ አስተዳደር አይመሰረትም።

በጣም የሚያስፈራውና የሚያሳስበው ነገር አዲስ አበባ የኦሮሞም ዋና ከተማና የአገሪቱም ዋና ከተማ  እርስ በርሱ በሚቃረን በክልላዊነትና በአገር አቀፍነት መልክ ሆና መቅረቧ በሁለት የተለያዩ አስተዳደሮች በጥቅም ፍጥጫና ግጭት ለመፈራረስ በሚያስችል ተንኮል እንድትዋቀር ማድረጉ ነው። ይህንን አደገኛ በማር የተጠቀለለ መርዝ  በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምነውና የሚኮራው፣ለኢትዮጵያም አንድነት ህይወቱን ለመስጠት ወደ ዃላ የማይለው፣የጎሳን ፖለቲካ አንቅሮ የተፋውና የሚቃወመው  የኦሮሞ ማህበረሰብ  ተወላጅ ከሌላው ማህበረሰብ ተወላጅ ጋር ተባብሮ ሊከላከለው ይገባል።በህብረት የመሰረታትን አገሩን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ  በቅድሚያ ምሰሶ የሆነችው አዲስ አበባ በጎሰኞች የተቀነባበረ ሴራ ለመፈራረስ ስትዘጋጅ በዝምታ ሊያየውና ሊያልፈው አይገባም።አሁን በተለያዩት  በሰሜኑና መካከለኛው ያገሪቱ ክፍለሃገራት በተለይም በጎንደርና አካባቢው የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ትግል ለመቅጨትና የአማራውን ማህበረሰብ ለማጥፋት የታቀደውን ዘመቻ ከኦሮሞው ኢትዮጵያዊው በኩል ተቃውሞና ከህዝቡ ትግል ጋር ተሳትፎ እንዳይኖረው ለማድረግ የተሸረበ ሴራ ነው።

«ከጠላት የጎረሱት በሶ ይወጣል ደም ጎርሶ» ነውና ወያኔና ግብረአበሮቹ የሚወረውሩት አሳሳች የጥቅም ፍርፋሪ የኦሮሞን ማህበረሰብ ከኢትዮጵያዊነት የሚነጥልና የሚያስጠቃ፣ተባብሮ በመታገል የእድገትና የእኩልነት  ባለቤት ሊሆኑ ከሚችሉበት ሰልፍ ውስጥ የሚነጥል ስለሆነ« እኛም  አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል» እንዳለችው አስተዋይ ጥንቸል የማዘናጊያውን መርዝና አደጋውን ተባብሮ ማክሸፍ ይኖርበታል።

ሌላው የአዋጁ አስፈላጊነት ወያኔና ግብረአበሮቹ ለገጠማቸው ውጥረት ማስተንፈሻና ምናልባትም በውጩ ግፊት ለውይይት  ከተገደዱ ከጠንካራ አክራሪ አቋም(from a strong position) በመነሳት ቀድሞ ወደ ነበሩበት ቦታ ለመመለስ የሚረዳቸው ስልት አድርገው ሊጠቀሙበት በማሰብ ይሆናልና ከወያኔ ጋር ተደራድረን ለውጥ እናመጣለን ብለው የሚያስቡ ከወዲሁ ምኞታቸውን እንዲያጤኑት ያስፈልጋል።ወያኔ ቀለሙን እንጂ ውስጣዊ ምንነቱን የማይቀይር እስስት መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።

በተቃዋሚውም ጎራ ከወያኔ ጋር ለመደራደር የሚሹ እንዳሉ አይካድም።ከነዚያም ውስጥ የኦነግ መሪዎች ለተመሳሳይ ዓላማ ስማቸውን ቀይረው በተመሳሳይ የጎሳ ስብስብ መልክ ተደራጅተው የመጡ ስለሆነ ለዳግመኛ የስቃይ ኑሮ ላለመዳረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጸረ ወያኔ ከሚያደርገው ትግል ጋር የነዚህንም ስብስብ ሊታገለው ይገባል።ወያኔን ተሸክመው አምጥተው  ላለፉት 27 ዓመታት የስቃይና የመከራ ስርዓት እንዳሰፈኑት ሁሉ ለሌላ 27 ዓመታት ተመሳሳይ ስርዓት እንዳይጭኑበት  ተባብሮ  ወግዱ ሊላቸው ይገባል።የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው የሚሉት ፈሊጥ አሁን አገራችን ባለችበት ሁኔታ ላይ አይሰራም።ትግሉ አገር የማዳን ስለሆነ አደጋውም በጎሰኞች ምክንያት የመጣ ስለሆነ ከነሱ ጋር ምንም አይነት የዓላማ አንድነት አይኖርም። ዓላማችንና ተልእኳችን ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያን የማዳን ሊሆን ይገባዋል።ያ ደግሞ በጎሳ  ለተደራጀ ድርጅት አለርጅኩ ነው። በኢትዮጵያዊነታቸው የማያወላውል አቋምና ታሪክ ያላቸው ብዙሃን ስለሆኑ ድሉ የማታ ማታ የነሱ ይሆናል። እንደዚያማ ባይሆን ኖሮ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አትኖርም ነበር።

የወያኔንና የግብረአበሮቹን አደገኛ ስልት ተባብረን እናክሽፍ።

አገሬ አዲስ

 

The post የቁልቁለት መንገድ አዲስ አበባ ገደል ስትገባ!! – አገሬ አዲስ     appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የኦሮሞ ህዝብ እኩልነት እንጂ ልዩ ጥቅም ፈላጊ አይደለም –   ገለታው ዘለቀ

$
0
0

ገለታው ዘለቀ

የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮችም ሆኑ ዜጎች በጋራ ከመሰረቱት ሃገር ልዩ ጥቅም ፈላጊዎች አይደሉም። ኢትዮጵያውያን በመሬት ዙሪያ በኢኮኖሚ ዙሪያ ለየቡድናቸው ልዩ ጥቅም ( special interest)  ይዘው በአንድ የፓለቲካ ጠገግ ዘንድ ለማረፍ አይስማሙም። አልተስማሙም። ኢትዮጵያውያን ለእንደዚህ ዓይነት ራስ ወዳድ ስምምነት ሃይማኖታዊም ባህላዊም መሰረት የላቸውም። ለእንግዳ እንኳን ቅድሚያ የሚሰጥ ባህል ነው ያላቸው።  ለነገሩ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን እጅግ ብዙ የዓለም ሃገራትም ቢሆኑ በመሬትና በኢኮኖሚ አካባቢ “ልዩ ጥቅም” የሚል ስምምነት በህገ-መንግስታቸው ላይ አያሰፍሩም። ልዩ ጥቅም የሚለው ፅንሰ ሃሳብ ራሱ ከፍትህ ምንጭ አይቀዳም። ራስን ያስቀደመ ስግብግብ ፍልስፍና በመሆኑ የሰው ልጆች ፓለቲካዊ ጠገግ ሲሰሩ  “በልዩ ጥቅም” አይስማሙም። ቡድኖች አገር ሲመሰርቱና ጠገጉን ሲሰሩ አንዱ ትልቁ ኪዳናቸው የጋራ እኩልነት፣ ፍትህ ነፃነት ናቸው። በጋራ የሚያቆሙት ይህንን ነው።  መንግስትም ዘብ ቆሞ ይህንን እሴት  እንዲጠብቅላቸው ይሻሉ። ይሁን እንጂ በታሪክ አጋጣሚ ብሄርን ለይቶ በኢኮኖሚ ወይም በማህበራዊ ጉዳይ ያልተመጣጠነ እድገት ካለ እነዚህ በአንድ ላይ የሚኖሩት ህዝባች ቀደም ብለው ለፍትህና ለእኩልነት በህገ መንግስታቸው ላይ ቃል በገቡት ጠቅላላ የፍትህ ሥርዓት መሰረት እንደየ ሁኔታው የተለያዩ ካሳዎች (affirmative actions) እየተጠቀሙ ለእኩልነት ሊሮጡ ይችላሉ።  ይህ ማለት ግን ልዩ ጥቅም በሚል ሃብትን መሬትን ለመቀራመት ሳይሆን  እኩልነትን በፍጥነት ለማረጋገጥ የሚወሰድ የማስተካከያ ርምጃ  ነው።

አሁን በቅርቡ በኢትዮጵያ ሚንስትሮች ምክር ቤት የወጣው መግለጫ ይዘት ካሳ ወይም afirmative action ሳይሆን ከብሄር ፌደራሊዝሙ አስተሳሰብ የመነጨ ከተፈጥሮ ሃብትና የመሬት የብሄሮች ቅርምት የመጣ ዶክትሪን ነው። ይህ አስተሳሰብ ደግሞ አደገኛ ነው። ይህ የብሄር ፓለቲካን መሰረት ያደረገ ፓሊሲ በሃገሪቱ የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም በኢኮኖሚ ክፍፍል ላይ ብዙ የሚያተራምሱ ችግሮችን የያዘ ነው። ለምሳሌ ህገ-መንግስቱ አዲስ አበባ አካባቢ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ያነሳል። ይህ ስሜት ግን ብዙ ጥያቄዎችን ይለምናል። ራስን በራስ ማስተዳደርና የራስን እድል በራስ መወሰን ዋና መመሪያችን ከሆነ ቡድኖች ሰብሰብ ብለው በሚኖሩባቸው ከተማዎች ሁሉ የልዩ ጥቅም ጉዳይ ይነሳባቸዋል።  ለምሳሌ አዋሳን እናንሳ። አዋሳ የደቡብ ክልል ዋና ከተማ ስትሆን ነገር ግን የሲዳማ ህዝብ በአዋሳ ላይ ልዩ ጥቅም ሊጠይቅ ይችላል ማለት ነው። ምክንያቱም የክልሉ ርእሰ ከተማ ሲዳማ እምብርት ላይ ስለምትገኝ።  አዋሳ ብቻ ሳትሆን አሶሳም፣ ጋምቤላም ይህንን ጥያቄ ያነሳሉ። የሚገርመው ይህ ችግር እስከ ዞን ከተሞችም ሊወርድ ይችላል። ብሄሮች ሰብሰብ ብለው  በሚገኙበት ከተማ አካባቢ የልዩ ጥቅም ጉዳይ ሊነሳ ይችላል። ውሎ እያደር ማለት ነው።  ይህ የሚያሳየው ልዩ ጥቅም የሚባለው ነገር  እንዴት የፍትህ ስርዓታችንን እስከ ታች እንደሚያበላሽብን ነው።  ይህ ጥይቄ ከፍ ሲል እንዳልኩት የተበደለን ለመካስ ሳይሆን የመሬትና የተፈጥሮ ሃብት ቅርምትን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ከፍትህ የተጣላ እርስ በርስ የሚያናቁር ነገር ነው። በመርህ ደረጃ ያለውን ችግር ማንሳቴ ነው። ወደ  ተግባራዊ ጉዳዮች እንግባ ካልን ደግሞ በርግጥ የኢትዮጵያ መንግስት ለኦሮሞ ህዝብ ልዩ ጥቅም በዚህ አዋጅ አምጥቷል ወይ? ብለን መገምገምም አለብን።   በመግለጫው ላይ የተጠቀሰውን አንዳንዱን እናንሳ። የትምህርትን ጉዳይ እናንሳ። አንዱ የኦሮምያ ልዩ ጥቅም ማሳያ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይከፈታል የሚል ነው። ይሄ ልዩ ጥቅም ሳይሆን መብት ነው። ኦሮሞው ብቻ ሳይሆን ጉራጌም፣ ትግሬም ሊፈቀድላቸው ይገባል። የንፁህ መጠጥ ውሃ ጉዳይም እንደ ልዩ ጥቅም አይታይም። የግድ በማናቸውም መልኩ ይህ ህዝብ ንፁህ ውሃ ማግኘት አለበት። እስካሁን አለማግኘቱም ይገርማል። የቋንቋ ጉዳይ ሲነሳ መታየት ያለበት ጉዳይ ዲሞ ግራፊው ነው። በዛ ያለ አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ባለበት ወረዳ ወይም የታችኛው የስልጣን ርከን አካባቢ የዚያ ቋንቋ ተናጋሪዎች ቋንቌቸው ኦፊሽያል ሊሆን ይገባል።  ሁሉንም  ቋንቋዎችም በዚህ መንገድ ኦፊሺያል በማድረግ ፍትህን ማውረድ ይቻላል። ኦሮምኛ የስራ ቋንቋ መሆኑ ሲነገር መልካም ነው። ታዲያ ከኦሮሞ ቀጥሎ በቁጥር ብዙም የማያንሰው የጉራጌ ብሄርስ? ስለዚህ ዓላማው  የተጎዳን የመካስ ጉዳይ ከሆነ ቋንቋዎች ሁሉ አሰራራቸው ተቀይሮ ለተጠቃሚው አገልግሎት እንዲሰጡ መደረግ አለበት። መግለጫው ፊንፊኔ የሚለውን ስያሜ ህጋዊ አድርጎታል። መልካም ነው። ሸገር፣ ፊንፊኔ፣ አዲስ አበባ እየተባለች ብትጠራ የሚከፋ አይኖርም። በተለይ ፊንፊኔ የሚለውን መጠሪያ ብዙ ሰው ከወደደው ይህ ስም እውቅና ቢሰጠው የሚደገፍ ነው።  ይልቅ ሌላው በመግለጫው ውስጥ የተቀመጠው አስገራሚ ነገር የመሬት አቅርቦትን የሚመለከተው ነው። የኦሮምያ መንግስት ለህዝብ ጥቅም የሚሆኑ ህንፃዎችን ለመስራት ሲያስብ ከሊዝ ነፃ ይሆናል ይላል። ይሄ በውነት ያሳዝናል።ይሄ አይደለም እኮ የኦሮሞ ጥያቄ። ለመሆኑ የኦሮምያ መንግስት የሊዝ ክፍያ የማይከፍል ከሆነ ማን ነው እንዲከፍል የተፈረደበት? ለምሳሌ የአማራ መንግስት ለህዝብ ጥቅም የሚሆን የሙዚየም ህንፃ አዲስ አበባ ለመገንባት ቢያስብ ይከፍላል ማለት ነው? ትግራዩ ቢያስብ ይከፍላል ማለት ነው? ጋምቤላ ቢያስብ ይከፍላል ማለት ነው? ለመሆኑ ኦሮሞስ በዚህ ይደሰታል? ይሄ አይሰራም። ወይ ሁሉም ይከፍላል። ወይ ሁሉም አይከፍልም። አለቀ። የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ አዲስ አበባ ውስጥ መሬት ለእኔ በነፃ ይሰጥ ሌላው ይክፈል አይደለም። የእኩልነት ጥያቄ ነው ያነሳው። ከተማዋ ስትስፋፋ ለሚፈናቀለው ገበሬ ተገቢ ካሳ ይሰጥ ነው እንጂ መሬት በነፃ ይሰጠኝ አይደለም።  ሌላው ጉዳይ የሥራ እድል ነው። ከፍ ሲል እንዳልነው  በቡድኖች መካከል ያለን የኢኮኖሚ እድሎች  የትምህርት እድሎች መራራቅ ለማስተካከል ካሳ (affirmative action ) በርግጥ አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ አዲስ አበባ ከተማ አቅም አግኝታ ካሳ ካሰበች የተጎዱትን ሁሉ ማሰብ አለባት። ኦሮሞን ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባን የማያውቁ ብሄሮች አሉ። እነዚህ ብሄሮች ባህላቸውን በከተማዋ እንዲያስተዋውቁ ራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ እድሎችን ማስፋት ተገቢ ሊሆን ይችላል። የአካባቢ ስሞችን በሚመለከት እንደየ ሁኔታው በቀድሞ የኦሮምኛ ስም እንዲጠራ ይደረጋል ይላል የሚንስትሮች ምክር ቤት መግለጫ።  ይህ በውነት ሚዛን አይደፋም። ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎ ሥልቻ ነው ነገሩ። አዲስ አበባ ውስጥ ፒያሳ የሚለው ስም ተቀይሮ በአንድ የኦሮምኛ ስም ቢተካ ለኦሮሞ ህዝብም ቢሆን ትርጉም ያለው አይመስለኝም። ከተማይቱ ፊንፍኔ እንድትባል ሰዎች አሳብ ሲሰጡ እሰማለሁ። የየሰፈሩ ስም በኦሮምኛ መሆን አለበት የሚል ጥያቄ ግን አይሰማም። የኦሮሞ ህዝብ ስንት ግዙፍ ችግር እያለበት በስም ለውጥ ልቡን ማድረቅ በደል ነው። ይልቅ አንዳንድ አዳዲስ መንገዶች ሲሰሩ መንደሮች ሲሰሩ ስማቸውን በኦሮምኛ ብቻም ሳይሆን በሌሎችም ቋንቋዎች ቢሰየም ደስ ይላል። በአማርኛ በእንግሊዘኛ በጣሊያንኛ የተሰየሙ ቦታዎች እንደገና ቢቀየሩ የሚሰራው ያጣ መንግስት ሥራ ይሆናል ሥራው።  በአማራ ክልል አንዳንድ የኦሮሞ ስያሜ ያላቸው ቦታዎች አሉ፣ በደቡብ አንዳንድ የአማርኛ ስም ያላቸው ቦታዎች አሉ፣ በደቡብ የኦሮምኛ ስም ያላቸው ቦታዎች አሉ ወዘተ. ሃገሪቱ በቦታ ስም ለውጥ መታወክ የለባትም። ይህን ሁሉ እንዴውም የህብረታችን ጌጥ አድርገን ልናይ ነው የሚገባን። ይህን ካልኩ በሁዋላ ትንሽ ስለ ካሳ (Affirmative. Action ) ውይይት ልቀጥል።

 

በኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ እኩልነትን ለማምጣት የተጎዳን መካስ በጣም ጥሩ መንገድ ነው። ይህ ጉዳይ ለብሄራዊ እርቅም መሰረት ነው። በርግጥ ሁሉም ቡድን ባለፉት ሥርዓቶች ተጎድቷል። ሁሉንም እንደየ ጉዳቱ መካስ ደግሞ ይቻላል። በአሁኑ ሰዓት ሃገራችን አፌርማቲቭ አክሽንን ተግባራዊ ማድረግ ከሚገባት መስክ አንዱ በኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎት አካባቢ ነው። እውነተኛ የአፌርማቲቭ አክሽን ከፈለግን የኢኮኖሚውን ያልተመጣጠነ የቡድን ሃብት ክምችት ነው ማየት ያለብን። እውን ይህ መንግስት ካሳ  ከፈለገ በህወሃት ሃብትና በኦህዴድ ሃብት መካከል ያለውን ልዩነት መመልከት ያስፈልጋል። የኦህዴድ ሃብትና የኤፈርት ሃብት ሲወዳደር ልክ አላሙዲንን አንድ በተለምዶ ሸምሱ ከሚባል ትንሽ ባለ ሱቅ ጋር የማወዳደር ያህል ነው። ግዙፍ የሃብት ልዩነት አለ። ደቡብ ደሞ በጣም ያንሳል፣ አፋር ጋምቤላ ሌሎች ብሄሮች ደግሞ ጨርሶ የላቸውም መሰለኝ።   አልማ ከህወሃት አይወዳደርም።  ይሄ ነው ማስተካከያ የሚሻው። ህወሃት ኦሮሞን ሊክሰው ካሰበ የአዲስ አበባ የሰፈር ስም በኦሮምኛ ሊሆንልህ ነው አይልም። ህወሃት ሌሎቹን ብሄሮች በመጫን ያከማቸውን ሃብት ወደ ብሄራዊ ሃብት ካዛወረ ነው ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ ካሳ። ኢትዮጵያን ከተደቀነባት አደጋ ለመታደግ አንዱ ትልቁ ርምጃ  ኢትዮጵያን ወደ አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብነት መለወጥ ነው። ይህ በራሱ ብዙ ነገር የሚለውጥ ሲሆን በሂደት የተመጣጠነ የማህበራዊ አገልግሎት ማቅረብ ተገቢ ነው። መንግስት የያዝከው የተከፋፈለ ኢኮኖሚ የሃገርን አንድነት እያናጋ ለግጭት መንስኤ እየሆነ ነው ሲሉት ሽንጡን ገትሮ አንድ የኢኮኖሚና የፓለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየሰራሁ ነው ይላል። አስቸጋሪ ነገር ነው የገጠመን በውነት። በሌላ በኩል    በህገ መንግስቱ ላይ መብታችን እስከመገንጠል ነው ይላል። ልክ የኢትዮጵያ ብሄሮች  እቃቸውን ሸክፈው  አንድ ቀን ብሽ ሲላቸው ለመበተን የተዘጋጁ አድርጎ ያሳያቸዋል። ኧረ ይሄ ነገር ጥሩ አይደለም ዲክተተር ብትሆኑ ይሻላል ይህን እስከ ሃቹ የሚጎዳንን ነገር እባካችሁ ሰርዙ  ሲባሉ አፍጠው መጥተው የአንድነታችን ዋስትና ነው ይላሉ። በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው።

 

 

ምን ይሻላል?

 

አሁን ያለንበት የፓለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታ የኢትዮጵያን መስዋእቶች ሁሉ አጭዶ የበላ ነው። አንድ የኢኮኖሚና የፓለቲካ ማህበረሰብ ይፈጠር ዘንድ መሰረታዊው ነገር ቡድኖች ያሏቸውን የተፈጥሮ ሃብትና መሬት ኢኮኖሚ እውቀት ሁሉ ለኢትዮጵያዊነት መስዋእት ማድረግ አለባቸው። ይህን መስዋእት ማድረጋቸውን የሚያሳይ ለትውልድ የሚያሳልፉት አንድ አዲስ ኪዳን መግባትም አለባቸው። ይህ ኪዳን የሚይዘው ዋና ነገር የመስዋእትነት ጉዳይን ሆኖ ይህ ኪዳናቸው አንድ የኢኮኖሚና የፓለቲካ ማህበረሰብ ሆነው ጠንካራ የመኖሪያ አገራዊ ጠገግ እንዲመሰርቱ ያደርጋቸዋል። በመሆኑም የሚነሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይህንን የሃገርን የመስዋእት ጉዳይ ከፍ አድርገው ማሳየት አለባቸው። የአሁኑ የብሄር ፌደራሊዝም የሃገርን መስዋእቶች ሁሉ የዘረፈ ነው። የወሰድነውን መስዋእት እንመልስ። የተከፋፈለ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ እየፈጠርን እንደገና ለአንድነት እንሰራለን ማለቱን ትተን በጋራ ለአዲሲቱ የተባበረች ኢትዮጵያ መስራት አለብን። ኢትዮጵያውያን ሁሉ ነፍስ ሳይቀርላቸው ለሃገራቸው ያላቸውን መስዋእት አድርገው ጠንካራ አንድ የኢኮኖሚና የፓለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር መነቃነቅ ወጣቶች መመካከር አለባቸው። ይህን ስናደርግ ሁላችንን የሚክስ ስርዓት እንፈጥራለን።

 

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

geletawzeleke@gmail.com

 

 

The post የኦሮሞ ህዝብ እኩልነት እንጂ ልዩ ጥቅም ፈላጊ አይደለም –   ገለታው ዘለቀ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

A response to Tsadkan Gebretensae’s call to wage war on Eritrea

$
0
0

By Shiferaw Abebe

In a recent interview to Addis Zemen, posted on Zehabesha TV the former TPLF General, Tsadkan Gebretensae harped on Ethiopia’s inability to influence geopolitical developments in the Red Sea region and how this weakness is putting the country’s long term security in danger. He primarily fingered at Eritrea for his worry and blamed it for, among other things, leasing the Assab port to Arab countries (United Arab Emirates/Saudi Arabia) for a military base, and for supporting Ethiopian armed opposition forces.

The retired TPLF General stated more than once that he was not privy of what the regime is thinking or doing to address his anxieties, but he left no doubts that his trust and faith still rests with the regime for solving any strategic challenges the country faces. He therefore advised the regime to do two things to (re)assert Ethiopia’s geopolitical interests in the Red Sea region:

First, he advised to do whatever is necessary to get the Esaya’s regime removed from power, by military force if need be. He believes removing the current Eritrean government will somehow change the geopolitical dynamics in the Red Sea region in Ethiopia’s favor because, among other things, he thinks Eritreans by and large will welcome TPLF’s hegemony in the region once Esayas is gone.

Second, he argued Ethiopia must flex its muscle to get the attention of the forces that are gaining a foothold or establishing their dominance in the Red Sea region.  He mentioned the two Sudans, Egypt, Arab countries from across the Sea, Western powers such as the US and France, and even China as positioning themselves in the region without paying any notice to Ethiopia’s interests. He didn’t elaborate on what specific actions Ethiopia must take to get their attention or what these forces may have to do to address Ethiopia’s national security concerns.

The concern about Ethiopia’s long term geopolitical and security interests may appear reasonable, even supportable, if one didn’t know who is talking. The fact that this concern is expressed so belatedly by someone who cut his teeth as a TPLF fighter eventually taking the highest military post of Chief of Staff should given any anti-TPLF Ethiopian a pose before offering a wholesale endorsement of his views, let alone his recommendations.

Tsadkan is the wrong person to air this concern now because, for all we know, there is no evidence that he cares about Ethiopia’s national security more than he cares about the continuity of TPLF’s rule. If he were genuinely concerned about Ethiopia, he would have seen the real and present danger for Ethiopia’s security – TPLF itself – the menace that is pulling the country to its demise faster than any real or imagined external foe may have a chance to do any harm to it. Any national security concern of tomorrow is meaningless when the very existence of the nation itself is in question today.

In case Tsadkan suffers from selective amnesia, Ethiopia lost its sea outlet back in 1991 because he and his comrades fought hard to make it the largest landlocked country in the world. TPLF had a second chance to correct that historic sin during the 1998-2000 Ethio-Eritrea war, but it blew it wilfully against the advice of notable Ethiopians like Dr. Yocob Hailemariam and others who made a compelling case under international law to pursue a peaceful and legal avenue for Ethiopia’s access to a sea outlet.

No one within TPLF – not the retired General who now has the temerity to lecture Ethiopians about national security threats from the comfort of his lavish retirement, not even those who were eventually kicked out of TPLF – raised a whisper when Meles ordered not to include any negotiation on a sea outlet in the Alger’s negotiations. They said nothing or challenged that mindless decision in public. They kept and handled Ethiopia’s affair as if it were their family or party affair.

TPLF and Tsadkan will go to the grave with this burden hanging on their neck. Ethiopians would have to be too foolish to shed a drop of blood for another war that TPLF or its former Generals want for their own security. TPLF and the General can march to the Red Sea and sink in it for all the people of Ethiopia care.

Tsadkan’s advising to going to war with Eritrea is nuts on the face of it and quite likely driven by a sinister objective.  We must not forget for a moment that, TPLF is, above all things, a master of division, diversion, and deception. The General is a graduate of that school. Nothing he says can be taken at face value.

TPLF has a simple and, to this point, very effective strategy to stay in power – keep Amharas down by among other things pitting them against the Oromos, and keep Eritreans out by making them an eternal enemy to Ethiopians. In the last few years, this strategy has started crumpling on both fronts as the Oromos and the Amharas at long last started to look at each other’s pain and appreciate their common destiny, and as Eritreans and Ethiopians started mending their tattered relationship outside TPLF’s orbit. These developments have no doubt scared the devil out of TPLF.

Relationship between Ethiopians and Eritreans is improving as Ethiopians broadly and Eritreans in general are softening their feelings toward each other; friendly interaction are slowly taking place at individual and community levels especially in the Diaspora; with social events featuring Eritrean and Ethiopian singers sharing a platform to entertain their mixed audiences. The goodwill the Eritrean government extended to Ethiopian unity forces to have a base inside Eritrea, and ESAT’s on the ground documentary of Eritreans attitude toward Ethiopia and Ethiopians have contributed to the regeneration of this relationship. Much new information has also come to light including learning from Gebru Asrat’s book, Democracy and Sovereignty in Ethiopia, that contrary to popular belief, EPLF or Shabia was actually against TPLF’s ethnic divide and rule politics from the very beginning.

With this backdrop, Tsadkan’s advice to go to war with Eritrea is nothing more than a veiled attempt in the name of national security to sever the slowly recovering relationship between Eritreans and Ethiopians. A sinister plot designed to exploit still lingering doubts among Ethiopians about a mutually beneficial relationship between the two countries. Ethiopians must not give another TPLF ploy a working space in their thoughts.

Under no pretext concocted or imagined by TPLF must Ethiopians go to war against Eritreans. Not again. This is the 21st century and wasting any life and resources to fight a 20th century war would be utterly foolish. The chapter of war or animosity with Eritrea or any other neighboring country for that matter must remain closed.

The solution to alleviate any national security threat must include a strategy that brings Ethiopia and Eritrea closer, not tear them further apart.  Eritreans understand Ethiopia’s stake in having a reliable sea outlet; it is too obvious to fail to notice.  But the strategy must be to work out a mutually agreeable and mutually rewarding arrangement peacefully, a task that cannot be entrusted to TPLF.

Ethiopians cannot also be a party to any diplomatic effort to make Eritrea a target of international sanctions and isolation, as Tsadkan is promoting. Any effort by the TPLF regime to play such a role on Ethiopia’s behalf must be opposed by Ethiopians. There is absolutely nothing Ethiopians will profit from a diminished Eritrea. Ethiopians’ number one headache is TPLF. They need to fix this problem first before thinking about addressing any other concern.

Finally, the times of Tsadkan’s media appearances are too coincidental to ignore. The last time he penned a TPLF-apologetic piece was when Ethiopia was engulfed by a popular uprising in the Oromo and Amhara regions, a time when TPLF appeared visibly shaken. At that time, Tsadkan urged Ethiopians to calm down and seek a solution to the crisis within the TPLF political framework.  Today, he refers to those uprisings derogatorily as “huket and bitbit” or “disorder and disturbances”.

This time, he is back on the air waves likely because he is concerned with the resistance in Gondar and the armed struggle that is gaining a footing there.  Predictably, he calls these fighters “Shabia mercenaries”, the same garbage he copied from TPLF’s propaganda book. Eternally loyal to TPLF, Tsadkan simply cannot see or reconcile with the possibility of an Ethiopia that is not ruled by TPLF.  The reason why Ethiopians must ignore his advice!

The writer can be reached at shiferawabebe1@gmail.com

The post A response to Tsadkan Gebretensae’s call to wage war on Eritrea appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.

World-Bank Sign New 5-Year Parnership Agreement

$
0
0

June 29, 2017 – Ethiopia, World Bank agreed on a new five-year partnership to build on development gains achieved over the past decade and boost institutional accountability.

The renewed partnership stresses sustainable and inclusive growth, placing a focus on education, increased access to markets and job creation for young people.Improved governance and social accountability to help tackle corruption make up another important plank of the agreement.

“The Country Partnership Framework intensifies our support for poverty reduction in Ethiopia and seeks to address key challenges facing the country,” said Carolyn Turk, World Bank country director for Ethiopia.

“Among other things, our interventions will support increased citizen engagement, greater resilience to the effects of climate change, more inclusive growth, and youth employment.”

The partnership also hopes to facilitate a bigger role for private investment in supporting Ethiopia’s development, and a shift away from public funds.

Adamou Labara, country manager for the International Finance Corporation in Ethiopia, said: “In the past, Ethiopia’s development model was based on public investment but there are increasing needs and opportunities to unlock the potential of the private sector.

“IFC’s strategy is to create markets and mobilise private capital, including offering products aimed at de-risking investments to make more investment possible.”

Ethiopia has an ambition to achieve lower middle-income status by 2025 but is hampered by some significant regional inequities and stubborn pockets of poverty.

In some parts of the country, people have very little access to services. The World Bank said it hoped a ‘spatial approach’, which focuses on access to land, infrastructure and housing, would overcome these regional disparities.

Ethiopia has seen some significant economic and social gains over the past decade. The poverty rate has fallen from 55% in 2000 to 34% in 2011, while real GDP growth averaged 10.5% a year between 2003 and 2015. Life expectancy has risen from 52 to 65 years.

Source: public finance international

The post World-Bank Sign New 5-Year Parnership Agreement appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.

Viewing all 3686 articles
Browse latest View live