Quantcast
Channel: admin – Medrek
Viewing all 3686 articles
Browse latest View live

May must act on Briton detained in Ethiopia, say campaigners – Ekklesia


የአማራ ድርጅቶች የታሪክ አዙሪት ውስጥ ላለመግባት መጠንቀቅ ያስፈልጋቸዋል (ከይገርማል)

$
0
0

26.06.2017

የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በ1960ዎቹ መጨረሻ አካባቢ በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ታሪክ ገዝፎ የወጣ የመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ ነበር። ፓርቲው በዘመኑ ፋሽን የነበረውን የሶሻሊዝም ርዕዮተዓለም አንግቦ ከታች እስከላይ ድረስ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ለማሰባሰብ የቻለ የደርግን ወታደራዊ አስተዳደር ከማንም በላይ የፈተነ ኃይል ነበር። እንደ እኔ እምነት ከሆነ በ1967 ዓ.ም ክረምት ላይ በተካሄደው የድርጅቱ ስብሰባ በገጠር የትጥቅ ትግል ለማካሄድ በሽምቅ ተዋጊነት የሰለጠኑትን ተዋጊወች እየመራ ወደበረሀ የገባው የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበረው ብርሀነመስቀል ረዳ ከሀላፊነት ቦታ ተነስቶ በውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ውስጥ እንደተራ ሰራተኛ ሲመደብ የኢሕአፓ ውድቀት ሀ ብሎ የጀመረው ያኔ ነበር። ከአያያዝ ጉድለት ሁነኛው ወዳጅ ቀንደኛ ጠላት ሊሆን እንደሚችል ያስተማረን አንዱ ክስተት የነብርሀነመስቀሉ የ1967ቱ የስልጣን አመዳደብ ሁኔታ ነበር።

የትኛውም ፓርቲ በቅድሚያ ማድረግ የሚኖርበት እያንዳንዱ አባል የመተዳደሪያ ደንቡን ጠንቅቆ እንዲያውቀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠት እና ለአመራር የሚታጩት ሰዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ነጥቦችን በግልጽ ማስቀመጥ ነው። ከዚህ ቀጥሎ ወደአመራር የሚመጡትም ሆኑ ከአመራር የሚነሱት ሰዎች የህሊና ዝግጅት እንዲያደርጉ የጥንቃቄ ስራ መሰራት አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በድብስብስ የሚደረግ ምርጫ በግለሰቦች ዘንድ የመበለጥ ስሜት ይፈጥር እና ወደጥፋት ሊመራ ይችላል። ብርሀነመስቀል ከአመራርነት ቦታው ሲነሳና በዝቅተኛ ቦታ ሲመደብ የተሰማው የመጠቃት ስሜት ነበር። በዚህም ምክንያት እሱና ተከታዮቹ ከመኤሶን ባልተናነሰ መልኩ የኢሕአፓን ወሳኝ ሰዎች ለደርግ በማጋለጥ የድርጅቱን ውድቀት ዕውን አደረጉ።

ኢሕአፓ ከገበሬው እስከምሁር ማሰባሰብ የቻለ ድርጅት ሆኖ እያለ፣ ከሲቪል እስከወታደራዊ ተቋሞች ዘልቆ ገብቶ ቁልፍ ሰዎችን አቅፎ እያለ፣ ነገር ግን በራሱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ያለውን ሁኔታ አቻችሎ መሄድ አቅቶት አሉኝ የሚላቸውን ወሳኝ ሰዎች በአፈንጋጮች ጠቋሚነት አስበልቶ ወደሞት አዘገመ።

መንግስትን ታግየ የስርአት ለውጥ አመጣለሁ ብሎ የተነሳ ማንኛውም ድርጅት ከእንዲህ አይነት ውድቀት ትምህርት ቀስሞ በቅድሚያ የራሱን አባላት ገርቶ መያዝ ይኖርበታል። ይህን ለማድረግ ከመተዳደሪያ ደንቡ ጀምሮ እስከተግባራዊ ክንዋኔወች ድረስ ግልጽ በሆነና ዲሞክራሲያዊ አሰራርን በተላበሰ መልኩ መፈጸም ይኖርበታል። የመተዳደሪያ ደንቡ አሻሚ አለመሆን፣ የዴሞክራሲያዊ አሰራር መስፈን፣ ልዩነቶች የሚስተናገዱበት አግባብ ግልጽ መሆን፣ ግጭቶች እና አለመጣጣሞች የሚፈቱበት መንገድ ተቀባይነት ያለው መሆን፣ ጥርጣሬወች የሚጣሩበት አሰራር መኖር፣ የአንድን ድርጅት ጥንካሬ የሚያጎለብቱ እና በአባላቱ መሀል ግንኙነትን እና መተሳሰብን የሚያዳብሩ ይሆናሉ። የነገር ጫፍ ይዞ ዕውነቱን ለማጣራት መስራት ገንቢ ሲሆን የነገር ጭራ ይዞ ማውራቱ ጥላቻን የሚወልድ አፍራሽ ተግባር ነው። ማንኛውንም ሀላፊነት በጥንቃቄ ለመስራት መቁረጥ፣ ከዚህ አልፎ ለሚከሰት ግድፈት ስህተትን ማመን፣ ይቅርታ መጠየቅና መቀበልን ባህሪ ማድረግ ያስፈልጋል።

ማንኛውም ሰው ሙሉ አይደለም። በመሆኑም ጠንካራ ጎናችንን እያጎለበትን ድክመቶቻችንን እንድናስወግድ በጥላቻና በንቀት ሳይሆን በቅን ልቦና ልንተራረምና ልንደጋገፍ ይገባል። ተያይዘን አላማችንን ከግብ ለማድረስ የምንችለው በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ጓዳዊ ግንኙነት ስንመሰርት ነው። የአማራ ድርጅቶች ቀዳሚ አላማ በአማራው ላይ እየተፈጸመ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጥቃት መመከት ብሎም ማስወገድ ነው። አማራው አደጋ ውስጥ ነው። ይህን አደጋ ለመቀልበስ የውጪ ኃይል ይደርስልናል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው። በስውርና በግልጽ የሚፈጸመው ግፍ መቋጫ የሚያገኘው ጥፋት እየተፈጸመበት ያለው ኃይል ነቅቶ ራሱን ሲከላከል ብቻ ነው። ለዚያም ነው አማራው በማንነቱ መደራጀት አስፈላጊ የሚሆነው። የአማራ ትግል ለዴሞክራሲ የሚደረግ ትግል ሳይሆን የህልውና ትግል ነው። ማንኛውም አማራ ለራሱና ለወገኑ ህልውና ሲል፣ ዘሩን ለማስቀጠል ሲል፣ ልዩነትን አስወግዶ የሞት ሽረት ትግል ማድረግ ይኖርበታል።

ከተለያየ አቅጣጫ የሚሰነዘሩትን ትችቶች መገምገም አስፈላጊ ቢሆንም ዋናውን አላማችንን ግን የሚያስቀይስ ሊሆን አይገባም። አስፈላጊ ሆኖ ካልተገኘ በስተቀር ለሚሰነዘሩት ትችቶችና ነቀፌታወች ሁሉ መልስ መስጠት ተገቢ አይደለም። ትልቁ ነገር የራስን ግድፈትና ስኬት እየገመገሙ ከድክመቱም ከጥንካሬውም ትምህርት በመውሰድ ለቀጣዩ ስራ የተሻለ ስልት መንደፍ ነው። ምላሽ ወይም መግለጫ ሊሰጥባቸው ይገባል በሚባሉ ነገሮች ላይ የሚቀርበው የቪዲዮ፣ የኦድዮ ወይም የጽሁፍ ምላሽ በቁምነገሩ ላይ ብቻ ያተኮረ፣ በጅምላ የማይወነጅል፣ አስተማሪ፣ የተገራና ተመልካችን የማያስቀይም እንዲሆን ያስፈልጋል። አሉባልታ ለሚያናፍሱና ተራ ስድብ ለሚሳደቡ ሰዎች ምላሽ ለመስጠት ተራ እሽኮለሌ ውስጥ መግባት ልክ አይደለም። እንዲህ ሲሆን ወዳጅን ጠብቆ ከማቆየት አልፎ ጠላት የነበረን በመማረክ ተቃዋሚን ማዳከም ይቻላል።

ያ ትውልድ የሚል መጠሪያ የተሰጠው የ1950ወቹና የ1960ወቹ ትውልድ በየሚያምንበት ቡድን ተሰልፎ በጽናት ታግሏል። ያ ትውልድ የሰራቸው ግድፈቶች እንዳሉ መካድ አይቻልም። እንደሻዕቢያ፣ ወያኔ፣ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ሶማሌ አቦ ያሉት ማዕከላዊ መንግሥቱን አዳክመው ሀገር ለመበተን የተሰለፉት የጎሣና የሀይማኖት ድርጅቶች ዛሬ በምንገኝበት አሳፋሪ የታሪክ ወለል ላይ አስቀምጠውናል። እንደ ኢሕአፓና መኤሶን ያሉት ሀገራዊ ድርጅቶችም ቢሆኑ እርስ በርስ ከመራኮት ጀምሮ በፈጸሟቸው ጥፋቶች አሁን ለምንገኝበት ሁኔታ ያበረከቱት ድርሻ አለ። ያም ሆኖ በገንጣይ አስገንጣይ ረድፍ ተሰልፈው የተዋጉትም ቢሆን ለአላማ በጽናት መቆምን እና መስዋዕትነት መክፈልን አስተምረውናል።

ያ ትውልድ ወደትግሉ መድረክ የገባበት ያ ወቅት የሶሻሊዝም አስተምህሮ ጉልበት አግኝቶ በመላው አለም እንደፋሽን ብርቅ የሆነበት ጊዜ ስለነበር በርዕዮተአለሙ ላይ የሚስተዋሉት ችግሮች የትውልዱ ችግር ተደርገው ሊወሰዱ አይገባም። ዓለም የወዛደሮች ትሆናለች! የዓለም ወዛደሮች ሁሉ ተባበሩ! የሚሉት የወቅቱ መፈክሮች የሶሻሊዝም ስርአት አራማጅ የነበሩትን ሀገሮች በጸረ ኢምፔሪያሊዝም ትግል ያስተባበረ ነበር። ለዚያም ነበር የኢትዮጵያን አንድነትና ሉአላዊነት ለማስጠበቅ የሶማሊያን ወራሪ መንግሥትና የሻዕቢያን ተገንጣይ ኃይል ለመመከት የየመን፣ የኩባና የራሽያ ወታደሮች በኢትዮጵያ ምድር ደማቸውን ያፈሰሱት።

ሶሻሊዝም በተግባር መዋል የሚችል ስርአት ቢሆን ኖሮ ከሚቃወመው በላይ የሚደግፈው እንደሚበልጥ አሁንም በርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ነገር ግን በወዛደሩ ስም ወደስልጣን የመጡት ፓርቲወች አላማውን በሳተ መልኩ አምባገነናዊነትን ስላሰፈኑ እና የከበርቴው ስርአት አራማጆች በጽናት በመታገላቸው ብዙ የተከፈለበት ሶሻሊዝም እንደቀልድ ፍርክስክሱ ሊወጣ ቻለ።

የአሁኑ ትውልድ ያለፈውን ትውልድ ከመክሰስ እና ከመውቀስ ወጥቶ ከድክመቱም ከጥንካሬውም ትምህርት መውሰድና ለተሻለ ነገር መስራት ይኖርበታል። ዛሬ ላይ ቁጭ ብሎ በዚያ ትውልድ ላይ መሳለቅ እወክለዋለሁ የሚለው ሕዝብ ዛሬ በወያኔ እየተሰራበት ያለውን ግፍ ወደጎን ብሎ በሚኒሊክ ጊዜ ተፈጽሟል ብሎ ላለው በደል እንደሚያለቅሰው ኦነግ መሆን ነው።

ኢሕአፓ ትክክል ነው ብሎ ባመነበት መስመር ተሰልፎ ከባድ መስዋዕትነት የከፈለ ድርጅት ነው። አሁንም ቢሆን የሕዝብን ጩኸት ከመጮህና ከመታገል አልቦዘነም። የግንቦት 7ቱን ፕ/ር ብርሀኑ ነጋን ጨምሮ በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል የወያኔን እኩይ አገዛዝ እየተናነቁ ያሉ የዚያ ትውልድ አባላት ብዙ ናቸው። እኒህ ሰዎች እየከፈሉት ያለውን መስዋዕትነት አቅልሎ ማየት አልፎ ተርፎም ከሳሽና ወቃሽ ሆኖ መቅረብ ፍጹም ስህተት ነው።

የዚያ ትውልድ ሰዎች እስካሁን ድረስ በትግል ላይ እንዲቆዩ የተገደዱት ኃላፊነቱን ሊረከብ የሚችል አዲስ ትውልድ ጎልቶ ሊወጣ ባለመቻሉ ክፍተቱን ለመሙላት ነው ብሎ ማሰብ ይቻላል። በአዲስ ኃይል የተዋቀረ የተጠናከረ ድርጅት ሲፈጠር የዚያ ትውልድ አባላት እፎይታ አግኝተው ምክር በመስጠትና ልምድ በማካፈል ይወሰናሉ። ከነዚህ የትናንት ወጣቶች የዛሬ አዛውንቶች በጎ ተሞክሮወችን እና የአላማ ጽናትን መውረስ እና ያጠፏቸውን ጥፋቶች አለመድገም ተገቢ ነው። ከዚያ ባለፈ የችግሮች ሁሉ ምንጭ እንደነበሩ አድርጎ መውቀሥና በጸረ ሕዝብነት መክሰስ ትክክል  አይደለም።

ኢሕአፓና መኤሶን ወደትግል ሲገቡ ኢትዮጵያ ችግር አልባ ሀገር አልነበረችም። በዘውዳዊው አስተዳደር የብዙሀኑ ጭሰኛ መሆን እጅግ መጥፎው ነገር ነበር። አንድ ደጃዝማች የባለብዙ ጋሻ መሬት ባለቤት ሆኖ በመሬቱ ላይ የሰፈሩት ሰዎች መሬት አልባ ጭሰኛ መሆን እጅግ ከባዱ ነገር ነበር። ጭሰኝነቱን ተከትሎ የነበረው የጉልበት ብዝበዛና የመብት ጥሰት ዛሬ ላይ ቁጭ ብለው እንደሚያስቡት ቀላል አልነበረም። በዚያን ወቅት መሬት ላራሹ ብሎ የተነሳው ወጣት በምንም ስሌት በጸረ ሕዝብነት ለመክሰስ አይታሰብም። ጥፋቶች የተፈጸሙት አንድም በርዕዮተአለሙ ግድፈት ሌላም በልምድ ማነስ እንጅ በጸረ ሕዝብነት በመሰለፋቸው አልነበረም። ስለዚህ ድክመቶችን አርሞ ጠንካራ ጎኑን የበለጠ አጠናክሮ የሚያስቀጥል ኃይል ብቻ ነው የሚያስፈልገው።

ወዳጅና ጠላትን መለየት ተገቢ ነው። አሁን ዋናው የአማራ ጠላት ወያኔና ሌሎች አማራን እንጠላለን የሚሉ ድርጅቶች ናቸው። ለኢትዮጵያ አንድነት የሚታገሉ ድርጅቶች በምንም ስሌት የአማራ ጠላት ሊሆኑ አይችሉም። በአንድነት ስም የተደራጁ ኃይሎችም የአማራውን እንቅስቃሴ እንደስጋት ከማየት ወጥተው ተባብሮ ለመስራት መዘጋጀት አለባቸው። እያልሁ ያለሁት የአማራ ታጋይ ድርጅቶች እና የአንድነት ኃይሎች ግብግብ ውስጥ መግባታቸው ፍጹም ስህተት ነው ነው። የአማራ ድርጅቶች የአንድነት ስጋት ሊሆኑ አይችሉም፤ የአንድነት ኃይሎችም ለህልውናቸው የሚዋደቁትን አማሮች ቢቻል መደገፍ እንጅ መሰናክል ሊሆኑባቸው አይገባም። የአንድነት ኃይሉ እና የአማራ ድርጅቶች ቢተባበሩ ይጠቅማል ሲባል የአማራውን የትግል እንቅስቃሴ እንዲዋጥ መፍቀድ ማለት አይደለም። አማራው የብዙ ኃይሎች የጥቃት ኢላማ እንደሆነ ለአፍታም መዘንጋት አያስፈልግም። ስለዚህ የአማራው ትግል ወደኋላ መመለስ የለበትም። ይህንን የተቀጣጠለ እምቢኝ ባይነት ይበልጥ እያቀጣጠሉ መሄድ ካልተቻለ ከበረደ በኋላ እንደገና መልሰን ነፍስ እንዝራበት ቢባል የሚከብድ ይሆናል።

እንደሚመስለኝ የአማራ ድርጅቶች የሚታገሉት በአማራው ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት ለመቀልበስ፣ እንደማንኛውም ዜጋ እኩል መብት እንዲኖረው ለማስቻል እንጅ የስልጣን ተፎካካሪ ሆነው ለመውጣት አይደለም። በጎሣ ተደራጅቶ ለስልጣን መፎካከር አግላይና አንድነትን የሚሸረሽር የሀገር አደጋ እንደሆነ ብዙወችን ያስማማል። የአማራው በዘር መደራጀት ከሌላው የሚለየው መጥፋት አለበት ተብሎ የተወሰነበት በመሆኑ ነው፤ የጥቃት ኢላማ በመሆኑ ራሱን ለመከላከል መደራጀት ስላለበት ነው። በዚህ ከተስማማን ጥቃትን ለመከላከል የግድ ወደአንድ ታላቅ አማራዊ ኃይል መሰባሰብ ይበጃል። የተለያዩ ድርጅቶች አሉ ማለት ድርጅቶችን አንድ የማያደርጓቸው የተለያዩ ነገሮች አሉ ማለት ነው። የተደበቀ ፍላጎት ከሌለ በስተቀር የአማራ ድርጅቶች አላማና ግብ አንድ ነው። በአንድ ማዕከላዊ አመራር ስር ያሉ ክፍሎች በየአካባቢው እንዲቋቋሙ ማድረግ ሕዝቡን ለማሰባሰብ ይረዳል፤ በተጨማሪም የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ የፉክክር መንፈስ ስለሚፈጥር ትግሉን ለማፋፋም ይጠቅማል። ለምሳሌ የጎጃም፣ የጎንደር፣ የወሎ፣ የሸዋ በሚል የሚቋቋሙት ክንፎች/ ክፍሎች በየራሳቸው ሰዎች እየተመሩ በ “አማራ የህልውና እና የነጻነት ፋኖ ድርጅት” ስር እንዲውሉ ቢደረግ ጠቀሜታው ብዙ ነው። እንደወያኔ ያለ አንድን ዘር ለማጥፋት ታጥቆ በተነሳ መንግስት ስር የወደቀ ተጠቂ ሕዝብ ተደራጅቶ ራሱን መከላከል ካልቻለ መጥፋቱ የማይቀር ይሆናል። አማራው በራሱ ክልል ሳይቀር የራሱ ባልሆኑ ሰዎች ተረግጦ እየተገዛ እንዳይቀጥል፣ በተለያዩ ስልቶች ቀስ በቀስ ከመኖር ወደአለመኖር እንዳይሸጋገር ብቸኛው መፍትሄ ጠንካራ ድርጅት መፍጠር ነው። በየክልሎች ተበትነው የሚኖሩት አማሮች መብት ሊከበር የሚችለውም ለመብታቸው የሚታገል ጠንካራ ኃይል ሲኖር ብቻ ነው።

ከዚህ በፊት ደጋግሜ ለመግለጽ እንደሞከርሁት የአማራው ትግል የትኛውንም አማራ የሚያገል ሊሆን አይገባም። እያንዳንዱ አማራ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቶት “የምከፍለው መስዋዕትነት ለራሴና ለቤተሰቤ ነው” ብሎ እንዲያምን ማድረግ ቀዳሚው ተግባር መሆን አለበት። በዘሩ ምክንያት ከመገለልና መድልዖ የዘለለ የዘር መጥፋት ሰለባ እንደሆነ የተረዳ አማራ በምንም ስሌት የጠላት መሳሪያ በመሆን በራሱና በቤተሰቡ ላይ ጥፋት እንዲፈጸም ተባባሪ ሊሆን አይፈቅድም። በኢሕዴን ስር ያሉት አማሮች ከሚታሰበው በላይ ለአማራው ትግል ጠቃሚወች ናቸው። ከላይ እስክታች ድረስ ባለው አደረጃጀታቸው ተጠቅመው መረጃ ከማቀበል ጀምሮ በቀጥታ ተሳትፎ እስከማድረግ የዘለቀ የተግባር ስራ በማከናወን ግዙፍ አስተዋጽዖ ሊያበረክቱ ይችላሉ። እንኳን የዘር ሰለባ የሆነ ሕዝብ ይቅርና በዘሩ ላይ የተቃጣ ጥቃት ያልተፈጸመበት ወያኔ እንኳ በትግሉ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ነው በሚል ብቻ በተለያየ የስልጣን ደረጃ በነበሩ በርካታ ትግሬወች ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲቸረው እንደነበር ይዘነጋል!

አማራነት አንድነት፣ መቻቻል፣ አስተዋይነት፣ ፍቅር፣ ለጠላት አለመንበርከክ፣ ሀገር ወዳድነት መሆኑን በአንደበትም በተግባርም ማስመስከር ያስፈልጋል። እያንዳንዱ አማራ ዕኩል የባለቤትነት መብት ከተሰጠው ለድርጅቱ ተዋጊም ሰላይም ሆኖ እንደሚያገለግል ማመን ይኖርብናል። ነገር ግን ባለማወቅም ይሁን በጥቅም ተገዝቶ ለጥቃት የሚያጋልጥ ሰው ቢኖር ጉዳት ሳያደርስ የሚጋለጥበትና የሚመከርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ተገቢ ነው። ጥንቃቄ የጎደለው አያያዝ፣ ወከባ፣ ከራስ ውጪ ያለውን ሁሉ በጥርጣሬና በክፉ አይን ማየት፣ ገንቢም ተገቢም አለመሆኑ ታምኖ መጀመሪያ ሁሉም ራሱን ማረቅ ይኖርበታል። ማንኛውም ሰው ሀሳቡን በግልጽ የማንሸራሸር ዕድል ቢሰጠው ማትረፍ ይቻላል። የሚሰጡት አስተያየቶች፣ ሀሳቦች፣ትችቶች፣ ነቀፋወች፣ ውንጀላወች፣ ትክክል ካልሆኑ እና መልስ መስጠት ቢያስፈልግ ክብርን በጠበቀ መልኩ መመለስ ይቻላል። ይህን ማድረግ ራስን ማስከበር፣ ለሌላውም ጥሩ ምሳሌ መሆን ነው። መጥፎ ቃላት ከጥሩ ሰዎች አይወጡም።

አክቲቪስት አቻምየለህ ታምሩ “በአማራ መደራጀት ጉዳይ” በሚል ያወጣውን ጽሁፍ አስመልክቶ ብዙ ውርጅብኞች እየወረዱበት ነው። ይህ ትልቅ ስህተት ነው። ትምህርት መውሰድ ያለብን ከሁሉም በመሆኑ ከወያኔም የምንማረው ብዙ ነገር አለ። ወያኔ ካቅሙ በላይ ሆኖ ፈንድቶ ሲወጣበት ካልሆነ በስተቀር ችግሮቹን የሚፈታው ማንም ሳያውቅ ውስጥ ለውስጥ ማለትም በራሱ ነው። በትንሽ በትልቁ መናቆር፣ ቅሬታን አደባባይ ላይ እያወጡ ማስጣት ንቃቃት/መሰነጣጠቅ እንዲፈጠር ምክንያት ይሆንና እንደኢሕአፓ ሁሉ ውድቀትን ያስከትላል። አቻምየለህ አማራ ብሔር አይደለም አለ ተብሎ ሲሰደብ ብሎም እንዲጠረጠር ሲደረግ ለተመልካችም ቢሆን ይቆረቁራል። ከዚህም በላይ የአማራውን ትግል የሚከፋፍል ሆኖ ያልተፈለገ ውጤት ሊያስከትል ይችላል። አቻምየለህ አንድ ሰው ላይሆን ይችላል። እንደትንሽና ቀላል ነገር የምንናገራቸውና የምናደርጋቸው ነገሮች ትልቅ ጥፋት ሊያመጡ ይችላሉ። ለዚያም ነው የምንናገረውን እና የምናደርገውን በቅድሚያ ማሰብ የሚኖርብን። እንደዚያ ካላደረግን ከታሪክ ሳንማር ከወዳጅ መሀል ጠላት እየፈጠርን ከነሰነቅነው አላማ ወደገደል እንገባለን።

በመሰረቱ ብሔር አንድ ወጥ ትርጉም ያለው ቃል አይደለም። የብዙ ነገሮች መመሳሰልና አንድነት ያለው ሕዝብ መጠሪያ አድርገው የሚወስዱ ወይም የሀገር ተለዋጭ ስም አድርገው የሚጠቀሙበት አሉ። ታዲያ ብሔር ማለት ሀገር ማለት ነው ብሎ ቢል ይህን ያህል በብስጭት የሚያወራጭ መሆን አይኖርበትም። መማማር ሲቻል፣ በጨዋ ደንብ መተራረም ሲገባ ወዳጅ ጠላት እስኪታዘብ ድረስ ወዲያና ወዲህ ቆሞ “አሎ ሉሎ” እያሉ መወራረፍ ፍጹም ስህተት ነው። ሞረሾችም እኮ የአማራ ነገድ እንደሚሉ ነው የሚታወቀው። ጎሣ፣ ነገድ፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ የሚሉትን ቃላት ለአንድ ሕዝብ መጠሪያ እያፈራረቁ የሚጠቀሙ ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል፤ እኔም ከነዚህ ሰዎች አንዱ ነኝ። ታዲያ ትክክል ካልሆንሁ ስህተቴን አንስቶ ማስተማር ሲቻል በስሜ አንቀው ይዘው መሬት ለመሬት እየጎተቱ ቢያሰቃዩኝ ተገቢ ነው? ብዙ ቃላቶች አንድ ወጥ ትርጓሜ የላቸውም፤ ያም ሆኖ የጠብ መነሻ ሊሆኑ አይገባም።

 

The post የአማራ ድርጅቶች የታሪክ አዙሪት ውስጥ ላለመግባት መጠንቀቅ ያስፈልጋቸዋል (ከይገርማል) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የአዋሳና የዝዋይ ሐይቆችን ስፋት ያለው ክፍል ከጣና ሐይቅ ላይ ጠፍቷል፤ – ሙሉቀን ተስፋው

$
0
0

ቀደም ባሉት ዓመታት የጣና ሐይቅ አሁን ካለው የቆዳ ስፋትና የውኃ ጥልቀት በእጅጉ ቀንሷል፡፡ እስከ 1990ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የጣና ሐይቅ ስፋት 3673 ካሬ ኪሜ ያክል ይሆን ነበር፡፡ እስከ 1987 ዓ.ም የክረምት ወቅት ድረስ የጎንደር ቤተ መንግሥት የመጨረሻው ፎቅ ማማ ላይ ተሆኖ የጣና ሐይቅን መመልከት ይቻል ነበር፡፡ አሁን ላይ ያለው የሐይቁ ስፋት 3000 ካሬ ኪሜ ብቻ ሲሆን 673 ካሬ ኪሜ የሆነ የሐይቁ አካል ደርቆ ወደ መሬትነት ተቀይሯል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ከጣና ሐይቅ ላይ የዝዋይና የአዋሳ ሐይቆችን በአንድ ላይ ሆነው የሚበልጥ ስፋት ያለው ሐይቅ ጠፍቷል ማለት ይሆናል፡፡ የአዋሳ ሐይቅ ስፋት 129 ካሬ ኪሜ ያክል ሲሆን የዝዋይ ደግሞ 440 ካሬ ኪሜ ያክል ናቸው፡፡ 

የጣና ሐይቅ ከተፈጥሯዊ ይዞታው በ9 ጫማ ወይም ከ1.8 ሜትር ጥልቀት ያክል ከነበረው የውኃ መጠን ላይ ጎድሏል፡፡ ጥቂት የማይባሉ ደሴቶች አሁን የብስ ሆነዋል፡፡ በባሕር ዳር ከተማ የጣና ሐይቅ ዳር ለዳር የተሠሩ አብዛኛዎቹ ሕንጻዎች ቀደም ሲል በሐይቁ የተሞሉ ነበሩ፡፡ የአልማ ቢሮና የሌክ ሾር መናፈሻዎች ይቅሩና የድብ አንበሳ ሆቴል እንኳ ከሐይቁ ዳር ላይ እንደነበር አሁን ሃያ ዓመት የሞላው ልጅ በደንብ የሚያውቀው ነው፡፡ አሁን ላይ ሐይቁ ከድብ አንበሳ ሆቴል በትንሹ ከ500 ሜትር በላይ ይርቃል፡፡ ይህ ሁኔታ በባሕር ዳር ከተማ በኩል ብቻ አይደለም፡፡ የሐይቁን ዳር ተከትለው የሠፈሩ የነበሩ ገበሬዎች መሬት እያስፋፉ ‹የባሕር ሸሽ› ማሽላና በቆሎ በደንብ ነው የሚያመርቱበት፡፡ 

የጣና ሐይቅን ዙሪያውን ለማየት እድሉ ነበረኝ፤ ጣና ቂርቆስ ከአራት ጊዜ በላይ በተለያየ ጊዜ ሒጃለሁ፡፡ የሐይቁ ስፋት በክርስቶስ ሠምራ በኩል እስከ ጉማራ ወንዝ ይደርስ ነበር መጀመሪያ ላይ ስመለከተው በ1998 ዓ.ም አካባቢ፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ጣና ቂርቆስ የሔድኩት በ2007 ዓም ሲሆን ሐይቁ ከጉማራ ወንዝ በእጅጉ የራቀ ሲሆን ከክርስቶስ ሠምራ ቤተ ክርስቲያን ከ1.5 እስከ 3 ኪሎ ሜትር ያክል የሚሆን ርቀት ሸሽቷል፡፡ ቀደም ሲል በሐይቅ ተሸፍኖ የነበረው የሐይቁ አካል አሁን ላይ በበቆሎና በማሽላ ሁዳድ ነው የተሸፈነው፡፡ 

በከምከም በኩል 2001ና 2 ዓም አውቀዋለሁ፤ ቀደም ሲል የአካባቢው አባቶች እንደነገሩኝ ጉባይ ማርያም ይደርስ ነበር የሐይቁ መጠን፡፡ አሁን ከጉባይ ማርያም ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ይርቃል፤ በቆላ ድባ ጎርጎራ በኩል እንዲሁ የተለያየ ጊዜ ለማየት ሞክሬያለሁ፡፡ ሐይቁ ከነበረበት ብዙ ርቆ ሸሽቷል፡፡ በደልጊና በቁንዝላ በኩልም የባሰ እንጅ የተሻለ አይደለም፡፡
የጣና ሐይቅ የደቅ ደሴት ነዋሪዎችን ይውጣል ተብሎ ብዙ ጊዜ ስጋት ነበር፤ አሁን እንኳን ስጋቱ ሞልቶ ይዉጠናል ሳይሆን ሽሽቱ ወዴት ነው የሚል ነው፡፡ የጣና ሐይቅን በርካታ ምክንያቶች አደጋ ላይ ጥለውታል፡፡ 

በጣና ሐይቅ ላይ ጥናታቸው ከሠሩ ምሁራን ዶክተር እሸቴ ደጀን አንዱ ናቸው፡፡ እንደ ዶክተር እሸቴ የጣና ሐይቅን አደጋ ላይ የጣሉ ምክንያቶች ተብለው የቀረቡት የጣና ሐይቅ ብዝሃ ሕይወትን ከመጠን በላይ መጠቀም፣ የአካባቢ ብክለት፣ የአፈር መከላትና ችግሮቹን መገንዘብ አለመቻል ዋነኛዎቹ ናቸው የሚል ድምዳሜ ላይ ነው የደረሱት፡፡ 

አሁን ላይ ለጣና ሐይቅ አደጋ የሆኑ ጉዳዮች ከጥናቱ በላይ ናቸው፡፡ የእምቦጭ አረም የሚባለው በጣና ሐይቅ ላይ ከተስተዋለ ጥቂት የማይባሉ ዓመታት አልፈዋል፡፡ የባሕር ዳር፣ የጎንደርና የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲዎች በጋራ አረሙን ለማጥፋት ማሽን ከማምረት እስከ የሰው ኃይል የማሰማራት እንቅስቃሴ አድርገናል ሲሉን ቆይተዋል፤ ሆኖም ገንዘብ ወጪ አደረግን ከሚሉት ውጭ ጣናን ሲታደጉት አላየንም፡፡ አሁን የእንቦጭ አረም የጣና ሐይቅን ቀላል የማይባል ክፍል ሸፍኖታል፡፡ 

የከፋ አደጋ ያስከትላሉ የሚባሉት ደግሞ በባሕር ዳር ዙሪያ፣ በሜጫና በደራ ወረዳዎች ያሉ የአበባ እርሻዎች ናቸው፡፡ ጥብቅ ቁጥጥር ባለመኖሩ የአበባ እርሻዎቹ የሚጠቀሙት ኬሚካል በጎርፍ ወደ ሐይቁ ገብቶ የሐይቁን ብዝሃ ሕይወት ያጠፈዋል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎችም አሉ፡፡ በዚያ ላይ በእኛ አገር የአበባ እርሻዎች ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከለከሉ መርዛማ ኬሚካሎች ጭምር በአበባ እርሻዎች ላይ አገልግሎት እንደሚሰጡ ታፍነው የቀሩ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ 

የባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ መሪ ቃል ‹‹ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ›› የሚል ነው፤ ዓርማው ደግሞ የጣና ሐይቅ፡፡ እንግዲህ መሪቃሉንና ዓርማውን በሐይቁ ላይ ያደረገ ተቋም መሠረቴ ነው የሚለው ሐይቅ አደጋ ላይ ሲወድቅ ዝም ማለቱ አሳዛኝ ነው፡፡

 

The post የአዋሳና የዝዋይ ሐይቆችን ስፋት ያለው ክፍል ከጣና ሐይቅ ላይ ጠፍቷል፤ – ሙሉቀን ተስፋው appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

በስያትል ከተማ የተካሄደው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጉባዔና እድምታው – ታምራት ይግዙ

$
0
0

ክፍል አንድ

ታምራት ይግዙ

” አሜሪካ ያላቹሁ ኑ ጠላ ቅመሱ
አፍሪካም ያላቹሁ ኑ ጠላ ቅመሱ
እንድ ሻላቃ ዳዊት እንድትጠነስሱ
አውሮፓ ያላቹሁ ኑ ጠላ ቅመሱ
ኢሲያና አውስትራሊያም ያላቹሁ ኑ ጠላ ቅመሱ
እንደ መምህሩ እንደ ጌታቸውም  እንድትጠነስሱ

  • እንደሚታወቀው ሁሉ የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነትን ከጠነሰሱት ግምባር ቀደም ግለሰቦች ውስጥ ፕ/ር ጌታቸው እና ሻለቃ ዻዊት መሆናቸውን እነርሱ በተጋበዙበት የሚዲያ አውታርም ሆነ ህዝባዊ ስብሰባላይ እየተገኙ ስለ አገራዊው ንቅናቄ አስፈላጊነት አበክረው ሲናገሩ ተደምጠዋል:: በሌላ በኩል ደሞ በአገራዊ ንቅናቄ ውስጥ ያሉት የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች እና በቶሮንቶ ህዝባዊ ስብሰባዎችን አካሂደዋል::  የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ የሲያትሉን በመግናኛ ቡዙህን አማካኝነት የተከታተለ  ሲሆን የቶሮንቶውን በአካል በመግኘት ተከታትሎታል: ከመከታተልም አልፎ ጥያቄም ለመጠየቅ ሰልፍም ይዞ ነበር:: ተቀምጦ ይከታተል  የነበረው ስብሰባ ለጥያቄ ተነስቶ ከአምስት እስከ አስር  ደቂቃ በቆመበት ቦታ የተመለከተውን  የተስብሳቢው ሁኔታ በመመልከት ያሰበውን ጥያቄ ሳይጠይቅ እንድቀመጥ አድርጎታል:: : ምክንያቱም ለጥያቄ በሚቆምበት ስፍራ ያሉ ወንድሞች ከነ ፕ/ር ብርሃኑ ከነ ዶ/ር በያና እና ከዶ/ር  ኮንታ አንደበት የሚወጣውን ፖለቲካዊ ንግግር በማድመጥ ግማሹ በተቀመጡበት ውንበር ላይ ሆነው በስሜት ቁጭ ብድግ ሲሉ: አንዳንዶቹ ፉጨት ሲያፎጩ: ሌሎቹ ደሞ በጣም ከመደሰታቸው የተነሳ ግንባራቸው ላይ ያለው ወዝ ያብረቀርቅ ነበር::  ይህ በእንዲህ እያለ ፕ/ር ብርሃኑ በ2012ዓ/ም ላይ ተመስርቶ የነበርው ጥምረት የሚባለው ስብስብና በ2017 የተመሰረትው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ልዩነቱ በይዘት ነው ወይስ በቅርጽ ብሎ መጠየቅ አሊያም? ፕ/ር ብርሃኑ ወያኔን አሳንሶ የማየት ባህሪያቸውን በተመለከተና ከዚህ በፊት የወያኔ ባለስልጣናቶችን  የሰፈር ዱሪዪዎች; የወያኔ መሪዎች የሰፈር ጎረምሶች ብሎ መጥራት   እውነት ከልቦህ ነው ብሎ መጠየቅ?::  ሌላው ደሞ የገንዘብ ነገር ሲነሳ ፕ/ር ብርሃኑ ድርጅታቸው አርብርኞች ግንቦት ሰባት ከማንም ሰው እንደሚቀበል ከሰው አይደለም ቀንድ ካለው ሴጣንም ቢሆን እንደሚቀበል በልበ ሙልነት ሲናገሩ ይህ አነጋገሮት ከምሮት ነው? ብሎ ጠይቆ  በደስታ ውስጥ ያሉትን እድምተኛ ወንድሞችን ከማሳዝን ይልቅ በማለት ነው ጥያቄ ከመጠየቅ እራሱን የገታው ::

 

  • ሌላው ጥያቄ ደሞ ለዶ/ር በያን ነበር ዶ/ር ቢያና በሲያትል በተደረገው ስብሰባ ላይ ሲናገሩ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ለአኦሮሞው; ለአማራው; ለደቡቡ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ ከዛም አልፎ ለአፍሪካ ክዛም ከፍ ሲል ለዓለም ሁሉ ሲሉ ተደምጠዋል:: እውነት ይህንን ሲሉን ሒሊነቸው ያመነበትን ልባቸው የተቀበለውን ነው አንደበታቸው የሚናገረው ለማለትም ነበር የተነሳሁት::

 

  • በሌላ በኩል ደሞ ዶ/ር ኮንቴ በሲያትል ንግግራቸው “ሰለ ባህር እና ሰለ አሳዎች” ተናግረው ተሰብሳቢውን አይደለም እኔንም አድማጩን ከለሁበት ሆኜ አስቆኛል:: የኔ ጥያቄ ለዶ/ር ኮንታ  እርሳቸው ከየትኛው ናቸው ከባህሩ ወይስ ከአሳዎቹ?

ይህንን ከላይ የጠቀስኩትን ጥያቄዎች ለምን ለመጠየቅ እንደተነሳሳው እንደሚከተለው አቀርባለው::

በ2012 ዓ/ም የተቆቆመው ጥምርትና በ2017 ዓ/ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ልዩነቱ በይዘት ነው ወይስ በቅርጽ? የሚለውን ስመለከተው ቡዙም ልዩነት አላየሁበትም  ለምሳሌ በ2012 ዓ/ም ጥምረትን የመሰረቱት ድርጅቶች

1ኛ በዶ/ር ብርሃኑ ይመራ የነበረው ግንቦት7 2ኛ በአቶ ነዓምን ዘለቀ ይመራ የነበረው ድርጅት 3ኛ በአቶ አሎ ይመራ የነበረው የአፋር ህዝብ ንቅናቄና 4ኛ በጀ/ል ከማል ገልጁ ይመራ የነበረው  የኦሮሞ ድርጅት ጥምረት ውስጥ ገብቶ ለመስራት በሂደት ላይ የነበር ሲሆን::   የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄን የመሰሩት ድርጅቶች ደሞ የሚከተሉት ናቸው::

1ኛ በፕ/ር ብርሃኑ የሚመራው ያርበኞች ግንቦት7  2ኛ በዶ/ር ሌንጮ የሚመራው የአኦሮሞ ዲሞክራት ፌደሪሽን 3ኛ በዶ/ር ኮንቴ የሚመራው የአፋር ህዝብ ንቅናቄና  4ኛ የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄ (የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄ ተወካይ በቶሮንቶ ስብሰባ ላይ በአካል ያልተገኙ ሲሆን አርማቸውን ግን ልከዋል) እንግዲህ ይህንን የሁለቱን ስብስብ ስመለከተው   በ2012 ዓ/ም የተቆቆመው ጥምርትና በ2017 ዓ/ም ከተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ልዩነቱ ጥምረትን ከመሰረቱት ውስጥ የአቶ ነአምን ድርጅት  በ2017 ዓ/ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ውስጥ አለመካተቱ ሲሆን ምክንያት ሊሆን የሚችለው በአሁኑ ሰዓት አቶ ነዓምን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር በመሆናቸው  ነው::   በ2012 ዓ/ም የተቆቆመው ጥምርት ውስጥ የሌለው  በ2017 ዓ/ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ውስጥ ያለው የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄ ሲሆን የኔ ፍራቻ የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄን የሚመሩት አቶ ኤፍሬም ማንዴቦ እንዳይሆኑ ነው :: ይህን ያልኩበት ምክንያት” እንሰት የሚለውን ዊብ ሳይት ለተከታተለ ሰው ግምቱን ከፍ ያረግበታል”

ይህ ሆኖ ከተገኘ ደሞ አንዱ የግንቦት ሰባት አባል በበር ሲወጣ ሌላው የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባል የሆነው ግለሰብ አይኑን በጨው አጥቦ በመስኮት መግባቱ ብቻ ነው;;  አልያም በአዲስ ዓምት ንጋት ላይ እናቶቻችን ” የገንፎ ምንቸት ውጣ የጎመን ምንቸት ግባ” እንደሚሉት መሆኑ ነው::  ይህ ለምን እንዲሆን ተፈለገ ቢባል ቡዙ ምርምርና ጥናት አሊያም የፖለቲካ ሳይንስ ሊቅ መሆን አያስፈልገውም ያው አርበኞች ግንቦት ሰባትን አውራ ድርጅት አድርጎ የማውጣት አቤዜ ውስጥ እንዳለን የሚጠቁም ነው:: እውን እኛ ኢትዮጵያውያን የአውራ ድርጅትን መጥፎነት ከወያኔ አልተማርንም ማለት ነው ወይስ !? እዚህ ላይ እኔን የሚያሳስበኝ ነገር  ቡዙዎቻችን ፍርሃትን ፈርተን መኖር ከጀመርን አመታት ያስቆጠርን ስለሆነ ፊት ለፊት የመናገር ብቃታችንን ፍርሃታችን ስለተቆጣጠርው የወጣልን ፈሪዎች ሆነናል  ብል ከእውነት የራኩ አይመስለኝም::  በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳዝነው ፍርሃትን  እየፈራነው  እኛን ኢትዮጵያውያንን በየእለቱ ወንጀል እየሰራን እንገኛለን በፈራን ቁጥር ወንጀላችን እየበዛ ይሄዳል: ወንጀላችን በበዛ ቁጥር ደሞ የአገራችን እጣ ፋንታ ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነ እንደሚገኝ ምስክር መጥራት አያስፈልገውም::  ፍረሃት ወንጀለኛ እንደሚያደርግ ቡዙ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል እስቲ አንድ ሁለቱን ጠቅሼ ልለፍ::  የምናገረው በግልጽ ነው፤ ይሉኝታና ፍርሃት  መጥፎ መሆኑን ከሂደት እና ከእድሜ እየተማርኩ ነው፡፡ በትንሽ በትልቁ መኮራረፍና የሸሚዝን እጄታ መሰብሰብ ባህል በሆነባት ሀገር  ውስጥ ለተወለድን ህብረተሰቦች ሃሳብን እንደወረደ ማቅረብ ቁም ስቅል እንደሚያስከትል ብረዳም ምርጫ የለኝም፡፡

ፍርሃት ወንጀለኛ እንደሚያደርግ ማስረጃ ከሚሆኑኝ ውስጥ ፕ/ር ብርሃነ ነጋ አንዱ ናቸው:  ሁላችንም እንደምናውቀው  ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን ሕወሃት ፍርድ  ቤት ከአንድም ሁለት ግዜ ይሙት በቃ የተፈረደባቸው ኢትዮጵያዊ ናቸው: እወነት በፕ/ር ብርሃነ ነጋ ላይ ይሙት በቃ የፈረዱባቸው ዳኛ በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ላይ ያንን ፍርድ የፈረዱት ጥፋት አግኝቶውባቸው ነው? እኔ እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ነገር ቢኖር  ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለአንድ ደቂቃ ፍርድ ቤት ችሎት ላይ የሚያስቆም ጥፋት የለባቸውም ባይ ነኝ:: ታዴያ እኛ የተከበሩ ዳኛ እንዴት ነው በፕ/ር ብርሃነ ነጋ ላይ ይሙት በቃ የፈረዱባቸው ስል መልሱ ከፈርሃትታቸው የተነሳ ብቻ ነው ባይ ነኝ::እኝህ የተከበሩ ዳኛ  የፈሩት ከስራቸው እንዳይባረሩ ሊሆን ይችላል አሊያም ከድርጅት አባልነታቸው ወ.ዘ.ተ ብቻ ከፍርሃታቸው የተነሳ ይሙት በቃ ፈረዱ ይህ ፍርሃታቸው እኝህን ዳኛ ምን አደረጋቸው? ወንጀለኛ:: ወንጀለኝነታቸው በሀገርም ; በህዝብም; በሒሊነቸውም::  ሌላው ደሞ በፍርሃት ወንጀል እየተሰራ ነው የምለው በነጻ አገር እየኖርን አርብርኞች ግንቦት ሰባት ህዝባዊ ስብሰባ በጠራ ቁጥር የመጀመሪያው ማስጠንቀቅያው  የራሳችን ድምጽና ምስል ቀራጭ ስላለ ድምጽም ሆነ ምስል መቅረጽ አይቻልም   የሚሉት ማሳሰቢያ ነው :: ይህን ማሳሰቢያ በተጠሩ ስብሰባዎች ሁሉ   ተደጋግሞ የሰማነው ሲሆን በ June 3/2017 ደሞ ሊቀመንበሩ ፕ/ር ብርሀኑ ባሉበት ማስነገር በነጻው አገር እየኖሩ  ፍርሃትን በጀርባቸው ትሸክመዋት እንደሚዞሩ  ያመለክታል::  ከዚህ ፍርሃታቸው የተነሳ ድምጽና ምስል ቀራጭ ስላለ ድምጽም ሆነ ምስል መቅረጽ አይቻልም በማለት  ወንጀል እየሰሩ ነው ማለት ነው :: የሚገርመው የግንቦት ሰባት አመራሮች ሰባዊ መብትን; የመናገር ነጻነትንና ዲሞክራሲን ለማስከበር “ከኛ ወዲያ ላሳር” ባዮች ሆነው ሳለ:  ከተግባራቸው እንደምንረዳው ግን እነዚህ የግንቦት ሰባት አበላቶች የመናገር ነጻነትንና ዲሞክራሲን ከሕወሃት ባላነሰ ሁኔታ እየተፈታተኑት እንደሚገኙ ነው::  ለምን ብንል ከፈረሃታቸው  የተነሳ ::  የግንቦት ሰባት ፍርሃት ደሞ “ግመል ሰርቆ አጎንብሶ” መሆኑ ነው የሚገርመው::  በላያችን ላይ ስላለው ፍርሃት ከመጨሬሴ በፊት አገራችንን ኢትዮጵያን ከሕወሃት ነጻ ልናወጣ የምንችለው መጀመሪያ ሁላችንም “ፍርሃትን መፍራት ስናቆም ብቻ ነው” የሚል አቆም ሁላችንም መያዝ ያለብን ይመስለኛል:  ይህ ካልሆነ ግን………..!?

ሲወለድ ያጠለቀውን

ሲሞት አወለቀው

ይህን የአባቶች አባባል ያስታወሱኝ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው ምክንያቱም ግንቦት 7 ከመሰረቱበት ግዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የወያኔ መሪዎች የሰፈር ዱሪዪዎች ነቸው; የወያኔ መሪዎች የሰፈር ጎረምሶች ናቸው;ሲሉን ኖረው   በ June 3, 2017 ስብሰባ ላይ ደሞ የወያኔ መሪዎች የሰፈር ጢቦዎች ነቸው በማለት ሲናገሩ ተደምጠዋል: እውነት ለወያኔ መውሪዎች ይህ ስም ይመጥናቸዋል? እውነት የወያኔ መሪዎች ከጣሊያኑ ማፍያ የሚበልጡ እንጂ የሚያንሱ ሆነው ነው በሰፈር ጢቦ ያስመሰላቸው::  እነዚህ የህወሓት መሪዎች በሃገራችን በኢትዮጵያ ላይና በህዝቦቾ ላይ ያደረሱት ግፍና መከራ ይቅርና በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በመሰረቱትና ላለፈው ስምንት ዓመታት በመሩት ድርጅት በግንቦት 7 ላይ ያደረሱትን መጥፎ ተግባር ሰፈር ጢቦዎች ተርታ ያስመድባል::  በእኔ እይታ አንኮን ሶስት አንኮር ነገሮች ሳቀርብ   የህወሓት መሪዎች የሰፈር ዱሪዪዎች;የሰፈር ጎረምሶችና; የሰፈር ጢቦዎች አለሞሆናቸውን ያሳብቃል::

ይኽውም የግንቦት ሰባት አመራሮች በሰሩት ስህተት 1ኛ በ2010 ዓ/ም የግንቦት ሰባት በመባል የታሰሩት ጀነራሎች እና ግለሰቦች 2ኛ በ2013 ዓ/ም በራሳቸው በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ይመራ የነበረው የስልክ ስብሰባ ( Tel-confers) ተጠልፎ በመገናኛ ቡዝሃን የተሰራጨባቸውና በላፈው ደሞ የድርጅታቸው ቀኝ እጅ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሌላ አገር ማገት ነቸው:: ታዲያ በምን ሚዛን ቢለኮቸው  ነው ፕ/ር ብርሃነ  የህወሓት  መሪዎች የሰፈር ዱሪዪዎች;የሰፈር ጎረምሶችና; የሰፈር ጢቦዎች የሚሎቸው? በሌላ በኩል ህወሓትን ብንመለከተው  በበርሃ እያለ ጠላቱን ንቆ አያውቅም: ኢሕአፓን ለመበተን በርትቶ የሰራ; ኢዲዩን ለማጥፋት ተግቶ የደከም; ኦነግንም ጭዳ ያደረግ ነው::  በእኔ አመለካከት ፕ/ር ብርሃኑ ስለወያኔ ያላቸው አመለካከት መለውጥ ያለበትና ተስብሳቢውም ህብረተሰብ ማዳመጥ የሚፈልገውን ማወቅ የሚገባቸው ይመስለኛል:: ታዳሚው ንግግራቸውን በጽሞና አዳመጠ ማለት አባባላቸው በሙሉ ትክክል ነው ብሎ ተቀበለ አይደለም: ወደ ፊትም እርሳቸው ያሉበትን የስልጣን እርክርን የሚመጥንና ታዳሚውንም ግምት ውስጥ ያስገባ ንግግር ይጠበቅባቸዋል::  ሌላው ደሞ እንዳለመታደል ሆኖ ስድብና ዘለፋ የምናበዛ ሰዎች ሞልተናል፡፡ ይህም የአሸናፊነት ሳይሆን የተሸናፊነት ምልክት ነው፡፡ ዘለፋ፣ ስድብ፣ ዛቻና ፉከራ የሚቀናው ሰው ሊያደርግ በሚያስበውና ሊያደርግ በሚችለው መካከል ያለው ክፍተት የሚፈጥርበት የአቅም እና የአመራር ውስንነት የሚያንገላታው አሳዛኝ ፍጡር ነው ብል ማጋነን አይመስለኝም፡፡  ካልተሳሳትኩ የግንቦት ሰባት ከፈተኛ አመራሮች ከፕሮፖጋንዳ ውጪ ሕወሃት የሚፈታተን አቅም የገነቡ አይመስለኝም ምክንያቱም ድርጅታቸው ሕወሃት አሳንሶ ማየትና አቅመቢሲ አድርጎ መቁጠርን እንደ አሸናፊነት የቆጠረው ይመስላል:: ይህን ዓይነት አመለካከት ይዞ አንድ እርምጃ መሄድ እንደማይችሉ ከወዲሁ መግንዘብ ያለባቸው ይመስለኛል ሌላው ደሞ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲሉ ጋሪውን ከፈረሱ ማስቀደሙ ክጥቅሙ ጉዳቱ እያመዘነ ስለሆነ  ሊያስቡበት ይገባል ባይ ነኝ::

 

የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም

ይህንን  አባባል በተለያየ ግዜ እንዳስታውስ ያደረጉኝ ፕ/ር ብርሃኑ ናቸው ይህውም የገንዘብ ነገር ሲነሳ ፕ/ር ብርሃኑ ድርጅታቸው አርብርኞች ግንቦት ሰባት ከማንም ሰው እንደሚቀበል ከሰው አይደለም ቀንድ ካለው ሴጣንም ቢሆን እንደሚቀበል በልበ ሙልነት ሲናገሩ ተደምጠዋል ይህንን በተመለከት ወደፊት እመለስበታለው

አሁን ያለው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ውጪ አገር ከሚንቀሳቀስት 

የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ አውራ ሆኖ ወጥቶ የሚመራው ድርጅት ያስፈልገዋልን?

አውራ የሚለው ስም ሲነሳ የህወሓት አገር አጢፊነትና; የሻቢያ መሰሪ ተንኮል በሒሊነው የማይመላለስ ኢትዮጵያዊ ይኖር ይሆን”? አውራ ሆኖ ለመውጣት ያሰበ ድርጅት ማን ይሆን? ይህንን ጥያቄ ያነሳሁበት ምክንያት የተለያዩ ወንድሞች  በድርጅት ጉዳይ ሳያወሩ  የሰማሁት ፍንጭ አለ እሱም በዊጪ አገር ከሚገኙት ድርጅቶች ውስጥ አንዱን አውራ ድርጅት አድርጎ የማውጣት ተልኮ ነው:: ይኽውም ቀደም ብሎ በነበሩ አመታቶች በተለያዩ ሙህራኖች ታስቦ የነበረና የተጠነሰሰ  ጉዳይ ለማሳካት በ2015ዓ/ም በቭዥን ኢትዮጵያ ስም ስብሰባ የጠሩት  ግለሰቦች እና ስብስቦች   የአውራ ድርጅት የማውጣት ጉዳይ ላይ ደፋ ቀና ሲሉ መክረማቸው አካሄዳቸውን በጥሞና ለተከታተል ሰው ለማወቅ የሚከብድ አይደለም:: እነዚህን ታዋቂ ግለሰቦች እና ታዋቂ ሙህራኖችን መጠየቅ የምፈልገው ነገር ቢኖር ስለ እውነት ብለን ስለሀገር ጉዳይ እንወያይ ከተባለ ሃገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ውጪ ካሉ ድርጅቶች ውስጥ አውራ ሆኖ ወጥቶ እኔ አውቅልሻለው የሚላት የፖለቲካ ድርጅት ያስፈልጋታልን? ይህንን ጥያቄ ታዋቂ ግለሰቦችና ታዋቂ ሙህራኖችን እንዲመልሱልኝ በአክብሮት እጠይቃለው በተለይ የተከበሩ ፕ/ር ጌታቸው በጋሻው እና የተከበሩ ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊ::

ይህንን የአወራ ድርጅት የማውጣት ጉዳይ ከአንድ ወንድም ጋር ሳወራ እንዴህ ብሎኝ ነበር ” በአሁኑ ሰዓት ውጪ ካሉ ድርጅቶች ውስጥ አንድ አውራ ድርጅት ሆኖ የሚወጣ ያስፈልጋል አለኝ”

እኔም ስመልስለት አይ ወንድሜ የአወራ ድርጅትን መጥፎነት ከህወሓት የተማርን ይመስለኛል ህወሓት ለ25 ዓመት  አገራችንን ከድጡ ወደ ማጡ ሲከታት እያየን እንዴት ነው ስለ አውራ ድርጅት የምታወራኝ ስለው የመለሰለኘን እዲህ በማለት ነበር

” አይ አንተ ሰው ከአሁን ቦሃላ ማን መጣ ማን  የኢትዮጵይ ህዝብ የሚታለል አይለም አለኝ”

ለዚህም ስመልስለት አይ የኔ ወንድም የኢትዮጵያ ህዝብ ከ2005 ዓ/ም ቦሃላ ተታሎ አያቅም ያለበት ችግር የአቅም ችግር ነው አቅም ስለሌለው ነው እንጂ ሕወሃት እየገዛው ያለው ተታሎ እይደለም::  እንደምናየው አቅም አለኝ ብሎ ሲነሳ የሕወሃት አቅም አይሎ በመነሳት የተቀጣጠለውን ሰላማዊ ትግል በመቶዎች የሚቆጠሩትን  በመረሸን በሺዎችየሚቆጠሩትን በየጣቢያው በማጎር   ትግሉን ያኮላሸዋል እውነት እኛ በውጪው  አለም የምንገኝ ኢትዮጵያኖች የሃገራችንን ህዝብ የስልጣን ባሌቤት የማድረግ ህልምና ምኞት ካለን የአገር ቤትን ትግል በገንዘብ; በእውቀትና በጉልበት ከመርዳት ውጪ አውራ ድርጅት ለመፍጠር ጎንበስ ቀና ማለቱ አባቶች እንደሚሉት ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ ነውብዪ ስመልስለት እሱ የሚያስበውን የአውራ ድርጅት ቀፍቅፎ ማውጣት  ስላልተቀበልኩት አርእስት ለውጠን ሌላ ወሬ ጀመርን::

በስያትል ከተማ የተካሄደው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጉባዔ እድምታው ይቀጥላል

 

 

 

 

The post በስያትል ከተማ የተካሄደው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጉባዔና እድምታው – ታምራት ይግዙ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አንድ ሺህ 438ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በመላው አለም ተከበረ

$
0
0

ኢሳት (ሰኔ 19 ፥ 2009)
በአዲ አበባ ታላቁ አንዋር መስጊድና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተከበረው የኢድ አልፈጥር በአል ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ቁጥር በተገኙበት ዩ ኤስ አሜሪካ በተለይም በዋሽንግተን ዲሲ በደማቅ ስነ-ስርዓት መከበሩን ዜናው ያስረዳል።
የፈርስት ሂጂራ ፋውንዴሽን ኢማም ሼህ ካሊድ ኡመር እና የፋውንዴሽኑ ፕሬዝዳንት ሃጂነጂብ መሃመድ በተገኙበት በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ ቨርጂኒያ ግዛት በተከበረው የኢድ አልፈጥር በአል ሙስሊሙ ማህበረሰብ በብዛት መገኘቱም ታውቋል።
በከፍተኛ ሃይማኖታዊ ስርአት በአሉ መከበሩና ሃይማኖታዊ እንዲሁም ሃገራዊ መልዕክቶች መተላለፋቸውም ታውቋል።

The post አንድ ሺህ 438ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በመላው አለም ተከበረ appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.

የመውጫ ቀነገደቡ ቢያበቃም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሁንም ከሳውዲ አለመውጣታቸው ተገለጸ

$
0
0

ኢሳት (ሰኔ 19 ፥ 2009)

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን የውጪ ሐገር ዜጎች ሀገር ለቀው አንዲወጡ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ቢጠናቀቅም ከመቶ ሺዎች በላይ ኢትዮጵያዊያን ከሳውዲ አንዳልወጡ ህወሐት መራሹ መንግስት አመነ ። የጉዞ ሰነድ ከወሰዱት ወደ አገር ቤት የተመለሱት ከ 42 በመቶ በታች ነው።

የሳውዲ ኣረቢያ መንግስት ከመጋቢት 21 ቀን 2009 አ/ም ጀምሮ በነበሩበት ተከታታይ ሶስት ወራት ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው የማንኛውም ሀገር ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው አንዲወጡ የሰጠው ቀነ ገደብ ያበቃው ቅዳሜ ሰኔ 17 ቀን 2009 ቢሆንም ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ኣነስተኛ መሆናቸውን የመንግስት ቃል ኣቀባይ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ገልጸዋል።

የ 2009 አ/ም የበጀት አመት ማጠቃለያን አስመልክተው ለመንግስት፣ ለገዢው ፓርቲ ሚዲያዎችና ለአገዛዙ ቅርበት ላላቸው የሀገር ውስጥ ፕሬሶች መግለጫ የሰጡት ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ እንደገለጹት ከሆነ አስካለፈው ሳምንት መጨረሻ ድረስ ሳውዲን ለቀው ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የጉዞ ሰነድ የወሰዱት ዜጎች 85 ሺ ያህል ብቻ ናቸው። ቃል- አቀባዩ አያይዘው እንደገለጹት የጉዞ ሰነድ ከወሰዱት 85 ሺህ ያህሉ ወደ አገር ቤት መመለስ የቻሉት 35 ሺ ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ ቁጥር በሳውዲ ኣረቢያ ይኖራሉ ተብለው ከሚገመቱ ህጋዊ መኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው በመቶ ሺዎች ኢትዮጵያውያን ጋር ሲነጻጸር አጅግ አነስተኛ መሆኑን በሳውዲ የሚገኙ የኢሳት ምንጮች ተናግረዋል።

ከሳውዲ የመውጫ ቀነ-ገደቡ መጠናቀቁ እየታወቀ ሌሎች የትራንስፖርት አማራጮችን ለመጠቀም አቅደናል በማለት ቃል አቀባዩ መግለጻቸውን ከተጠያቂነት ለመሸሽ እንደሆነ የሚገልጹት በሳውዲ የሚገኙ የኢሳት ምንጮች ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ በመውጣት ወደ ጎረቤት ሀገሮች በመሸሽ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በተለይም መንግስት አልባ ወደ ሆነችው የመን የሚሸሹት ኢትዮጵያዊያን ቁጥራቸው እየጨመረ መሄዱ አሳሳቢ እየሆነ መሄዱንና ተጨማሪ ስቃይና አንግልት የምንሰማበት ጊዜ እንዳይመጣ ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

The post የመውጫ ቀነገደቡ ቢያበቃም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሁንም ከሳውዲ አለመውጣታቸው ተገለጸ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

The Cruel Political Jokes of the T-TPLF in Ethiopia – nazret.com

$
0
0

There is no website configured at this address.

You are seeing this page because there is nothing configured for the site you have requested.
If you think you are seeing this page in error, please contact the site administrator or datacenter
responsible for this site.

ይልቅ ወሬ ልንገርህ ስለ ወልቂጤው ማረሚያ ቤት እስረኛ ግድያ – ቁምነገር መፅሔት

$
0
0

መቼም በየዕለቱ በየሰዓቱ ከአራቱም የሀገራችን አቅጣጫ ስለሚሰማው ዜና ለመገመት ከባድ ነው አይደል? ባለፈው ሰሞን በደቡቧ ከተማ ወልቂጤ ምን ሆነ መሰለህ?
ሰኔ አራት ማታ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ይሆናል፤ እሺ አልክ? በግምት ዕድሜው 25 ዓመት የሚሆነው መስፍን አዳነ የሚባል ወጣት የቀቤና ብሔር ተወላጅ ከሆነችው ወጣት ሲቲና ጀማል ጋር የነበረውን የግል ፀብ መነሻ በማድረግ ጠብ ውስጥ ይገባል አሉ፡፡ መስፍን ዕድሜዋ 28 ዓመት የሆናትን የ8 ወር ነፍሰጡር አስቀድሞ ተዘጋጅቶበት የነበረውን ጩቤ ከጀርባው ላይ ላጥ አድርጎም እዛው አደባባይ ላይ ደጋግሞ ይወጋታል፡፡ 

ወጣቷ ራሷን ለመከላከል ብትሞክርም ህይወቷን ለማትረፍ ሳይቻል ይቀራል፡፡ ወጣት መስፍንም የፀጥታ ሰራተኞች በፍጥነት በቦታው ደርሰው ይዘውት ወደ ወልቂጤ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ይወሰዳል፡፡
እናስ? እናማ ወጣቷ በማግስቱ እዛው ወልቂጤ ውስጥ ባለ ቤተክርስቲያን ቀብሯ ይፈፀማል፡፡ ከቀብሩ በኋላ ግን ለህግም ፤ለሞራልም ከባድ የሆነ ድርጊት ስለመፈፀሙ ነው በወቅቱ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች የሚናገሩት፡ ፡ ምን ሆነ አልክ? 

በማግስቱ ከቀኑ በሰባት ሰዓት ሲሆን የሟች ቤተሰቦችና ዘመዶች ድንጋይ ዱላና ሌሎች ስለት ያላቸውን መሳሪያዎች ይዘው ተጠርጣሪው እስረኛ ወደሚገኝበት ወልቂጤ ፖሊስ ጣቢያ ያመራሉ፡፡ እናስ? እናማ በወቅቱ ፖሊስ ጣቢያው በር ላይ የነበሩት የጥበቃ ሰራተኞችን ረዳት ሳጅን በቀለ በዳሳና ኮንስታብል ትዕግስት አለሙን ጥሰው በመግባት ተጠርጣሪው ወጣት መስፍን አዳነ ላይ የድርንጋይ ውርጅብኝ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ 

በመጣው ሰው ሁሉ በደም ፍላት የተወገረው ወጣት መስፍን ብዙም ሳይቆይ እዛው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ህይወቱ ያልፋል፡፡ ተጨማሪ የፀጥታ ሀይሎች ወደ ፖሊስ ጣቢው ተጠርተው ሲመጡ ግን ጣቢያው ውስጥ የተገኘው የወጣቱ አስከሬንና ሁለቱ የጥበቃ ሰራተኞች ብቻ ነበሩ፡ ፡ ወጣት መስፍንም በማግስቱ በምዕራብ ሸዋ ሸነን ወረዳ ስልክ አምባ ላይ ቀብሩ ተፈፅሟል፡፡
እናስ? እናማ ጉዳዩን በተመለከተ ጭፍጨፋ የፈጸሙ ሰዎች እየተፈለጉ ሲሆን ሁለቱ የጥበቃ ሰራተኞች ዱላና ድንጋይ እንዲሁም ስለት ታጥቀው የመጡ ሰዎችን መከላከል አልቻላችሁም የተባሉት ሁለት ፖሊሶች በሚል በቁጥጥር ስር ሆነው ምርምራ እየተጠራባቸው ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡ ምን ይሄ ብቻ መሰለህ፤ እነዚሁ ሰዎች እንደገና በማግስቱ ዲያስፖራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ያለውን የሟች ቤተሰቦች መኖሪያ ቤትን በእሳት አጋይተውታል ተብሏል፡፡የህግ የበላይነቱስ አልክ? ተግባራዊ ከሆነ ስሰማ እነግርሀለሁ፤ በል ቻዎ…

The post ይልቅ ወሬ ልንገርህ ስለ ወልቂጤው ማረሚያ ቤት እስረኛ ግድያ – ቁምነገር መፅሔት appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


Hiber Radio Weekly News – June 25, 2017

The Cruel Political Jokes of the T-TPLF in Ethiopia | nazret.com – nazret.com

$
0
0

There is no website configured at this address.

You are seeing this page because there is nothing configured for the site you have requested.
If you think you are seeing this page in error, please contact the site administrator or datacenter
responsible for this site.

የሀብታሙ አያሌው ባለ አራት ምዕራፍ ፖለቲካ፣ – ይገረም አለሙ

$
0
0

አቶ ሀብታሙ አያሌው

አቶ ሀብታሙ አያሌው እሱም  ብዙ እያለ ስለ አርሱም እየተባለ ነው፡፡ ፖለቲካችንም ማህበራዊ ኑሮአችንም የተቃኘው በእውነት ላይ ሳይሆን በስሜት ላይ ሆነና አፍቅረን ሰንደግፍ ሆነ ጠልተን ስንነቅፍ ምክንያት ብቻ አይደለም ለከትም የለንም፡፡ሜዳው ላይ ልጆች በዙና፣ጨዋነት እየኮሰመነ ዋልጌነት እየገነነ መጣና ትላልቆቹ እድሜ ጠገቦቹ ተግባራቸው ሀገር ሊያድን፣ ረጋ ሰከን ብሎ ነገሮችን ግራ ቀኝ አይቶና መዝኖ የመደገፍም የመንቀፍም ባህል የሌለን መሆናችን ሰሞኑን በአቶ ሀብታሙ አያሌው ዙሪያም እየታየ ነው፡፡ ሜዳው ላይ ልጆች በዝተው ጨዋነት እየኮሰመነ ዋልጌነት በመግነኑ ትላልቆቹ ስራቸው ሀገር ሊያድን ምክራቸው ትውልድ ሊቀርጽ የሚችሉቱ አፋቸው ከመናገር እጃው ብእር ከማንሳት በመቆጠቡ ነገራችንን በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንዲሉ አድርጎታል፡፡

በአንድ በኩል ሀብታሙ በጠና ታሟል ተብሎ በኦክስጂን እንደሚኖር  የሚያሳይ ፎቶ በፌስ ቡክ እያሰራጨ እንዴት ለማስረገዝ በቃ እስከ ማለት ከደረሰው ሰዋዊ መንፈስ ከሚጎድለው ተቃውሞ፣በሌላ በኩል ብቸኛ የለውጥ አርበኛ አድርጎ እስከ መሳል የደረሰ ድጋፍ እየን እየሰማን እያነበብን ነው፡፡ ይሄ ለአድራጊዎቹም ለሚደረግለት/ ለሚደረግበት ሀብታሙም አይጠቅምም፡፡

ማን ስለሆነ፣ ምን ስለሆነ፣ ምን ስላደረገ ምን እንዲያደርግ ስለምንፈልግ እንደምናደንቅ  እንደምናሞግሰው  የእንደምናወግዝ እንደምናንቋሽሸው በማስረጃ ማሳየቱ በምክንያት መግለጹ ነበር የሚበጀው፡፡ግን አልሆነም ሊሆን የሚችልም አይመስልም፡፡ አጀንዳ ቀርጸን ለጋራ ጉዳያችን ለነገ ግባችን የሚበጅ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር አቅሙም እውቀቱም ፍላጎትም የለሌለን ሰዎች ግለሰቦችን ማእከል እናደርግና ደጋፊና ነቃፊ ሆነን እንሰለፍና ከሙግት ክርክር የዘለለ የቃላት ጦርነት እንከፍታለን፡፡የፖለቲካ ንግድ የፕሮፓጋንዳ ጨዋት እንጀምራለን፡፡ በዚህ መመንገድ ስንቶች አለፉ፣ስንቶችን ዳግም ወደ መድረኩ እንዳይመለሱ አድርገን ሸኘን፤ ስንቶች ህይወታቸውንአጡ ስንቶች ከበሩ፣ስንቶች ተገለባበጡ ስንቶች በማተቤ ልዳኝ (የአቶ አሰፋ ጫቦ ቃል ነች ነብስ ይማር) እንዳሉ አሉ/ይህችን አለም ተሰናበቱ፣ ወዘተ መልስ አልባው ጥያቄ ብዙ ነው፡፡

ስለ ሀብታሙ መነጋገሩ ካለፈው ለመማር ለመጪው ለትግሉ የሚሆን ነገር ለማትረፍ ከሆነ  ዛሬም አንደትናንቱ ምንም አንዳላስገኘው በሆያ ሆዬ መሆን የለበትም፡፡ የሚሻለው ሀብታሙ የተጓዘባቸውንና የደረሰበትን  አራት የፖለቲካ ምዕራፍ  በጥሞና በመፈተሸ መነጋገሩ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ላይ መረጃና ማስረጃ በስፋት ኖሮኝ ዘለግ ብዬ ብሄድበት በወደድኩ ነበር፡፡ግና የለኝምና ይህ በሌለበት መጻፍ ደግሞ ከመነሻው የተቃወምኩት ከእውነት የተፋታ አጉል ደፋርነት ወይንም አጉላ ዘለልነት ስለሚሆን አልሞክረውም፡፡ የዝምታ ድባቤን ጥሼ ግዝት መሀላየን አፍርሼ ይችን ጽሁፍ የመጻፌ ዓላማም ሆነ ፍላጎት የሚያውቁ እንዲነግሩን ለመጠየቅ ብዙ እያወቁ ዝምታ የመረጡትን እሽኮለሌው አስጠልቷቸው ነገሩ የልጅ ጨዋታ ሆኖባቸው የዳር ተመልካች መሆንን የመረጡ ወገኖችን እባካችሁ ዝምታ አጥፊን ያበረታታል አሉባልታን ያሰፋል ሀሰትን በእውነት ላይ ያነግሳልና በቅ በሉ የምታውቁትን ጻፉ ተንፍሱ ንገሩን አስተምሩን ለማለት ነው፡፡ ለመነሻም ለመኮርኮሪያም ይሆን ዘንድ ሲባል ከባጀው ትንሽ ልነካካ፡፡

ምዕራፍ አንድ፣  የሀብታሙ ፖለቲካ፣እሱም እንደሚነገርን እኛም እንደምናውቀው  የወያኔ የወጣት ማህበር ሊቀመንበር ሆኖ ነው የሚጀምረው ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም አቶ ጌታቸው ረዳ አንድ ሰሞን የግንኙነት መስሪያ ቤቱ ምኒስትር የነበረውና አሁን የትና እንዴት እንዳለ የማይታወቀው በአንድ የቴሌቭዝን ክርክር ወቅት ከሀብታሙ ጋር  መንግሥትንና ተቀዋሚን ወክለው ግራና ቀኝ ተቀምጠው አንተ እኮ በዚህ ጉዳይ ከእኛ በላይ ስትከራከር ነበር ብሎ የመሰከረለት እንበለው የመሰከረበት ደንበኛ ካድሬ ነበር፡፡ ካድሬም ሆነ የወጣት ሊቀመንር የነበረ መሆኑ በተለይ ንስሀ ከመግባቱ ጋር ተያይዞ ሊያስውቅሰውም ሊያስነቅፈውም አይገባም ባይ ነኝ፡፡ የመደራጀት መብት ይከበር ስንል ወያኔ መሆንንም ጭምር መሆን አለበት፡፡ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ስንል የሚጥመንንም የሚጎመዝዘንም ሀሳብ የሚያራምዱትን መሆን አለበት፡፡ ነገርን ከስሩ ውሀን ከጥሩ ነው ከተባለ ጥያቄ ሊሆን የሚችል የሚመስለኝ አገባቡ እንዴት ነበር? በቆይታው ምን ሰራ? ከጳጳሱ ቄሱ ለመሆን ይዳዳው ነበር ወይ? ወዘተ የሚለው ነው፡ ይህ መታወቁ በቀጣዮቹ ምዕራፎች ለሆኑት ጉዳዮች እንዴትነትና ምንነት  መሰረት ይሆናሉ፡፡

ምዕራፍ ሁለት፣ የሀብታሙ ምዕራፍ ሁለት የአጭር ግዜ ጎዞ ፖለቲካውን ከኢኮኖሚው ያዛመደ ወይንም በፖለቲካው መሰላል ወደ ኢኮኖሚው ለመንጠላጠል የሞከረበት ነው፡፡ የደቡብ አፍሪካው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር፡፡ ደቡብ አፍሪካ ተገኝታችሁ ጨዋታውን መከታተል ትችሉ ዘንድ አመቻችተንላችኋል ብሎ ከአያሌ ኢትዮጵያውያን ከዘረፈው  አጭበርባሪ ሰው ጋር ተባባሪ ሆኖ መስራቱ በሰፊው ሲወራ ነበርና ይህን ማወቁም መጨረሻ ላይ ሊነሳ ለሚችለው ጥያቄ መደላድል ይፈጥራል፡፡በተለይም ከዚህ በኋላ ነውና ወደ አንድነት የገባው፡፡

ምዕራፍ ሶስት፣የሀብታሙ ምዕራፍ ሶስት የፖለቲካ ጉዞ አንድነት የገባበት ነው፡፡እዚህ ምዕራፍ ላይ ትንሽ ቆይትም ዘለቅም እንበል፡፡በምዕራፍ አንድና ሁለት ማንነቱን ያየነው ሀብታሙ አንድነት ፓርቲ መግባቱ በወያኔ ስለተገፋ፣ ወይንስ እዛ ያለው የነበረው ሁኔታ እንደሚፈልገው ስላልሆነለት ስላልተመቸው፣ ወይንስ የወያኔዎቹ ነገረ ስራቸውን ተጸይፎ በእምነት በአመለካከት ተለይቶ፣ ወይንስ…. ብዙ ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ሌላው ከመምጣቱ ለሹመት መብቃቱ የእሱ ብቃት ወይንስ አንድነት የሰው ድርቅ የመታው ስለነበረ ወይንስ ሌላ ምክንያት ነበረው? ሹመት ያዳብር ተብሎ ሳይጠግብ በውስጡ ያለው እምነት ቀርቶ በሸሚዝና በጃኬቱ ላይ የነበረው የወያኔ ጠረን በቅጡ ሳይለቅ በአደባባይ ወያኔን አውጋዥ ለመሆን መብቃቱስ፣ ተቀዋሚነት ወይንስ ቂም የመወጣት ስሜት? የትግል ቁርጠኝነት ወይንስ እዛ ያጣሁትን እዚህ አገኘሁት እዩኝ ማለት? ወይንስ አንደ ስየ አብርሀ አንድነትን በቁልቁለት መንገድ የማስሮጥ ስልት፣ ሌላም ሌላም ጥያቄ ማንሳት ይቻላል፡፡ ግን ሂሳብ ለማወራረድ ሳይሆን ከትናንት ለመማር፤ ለዛሬ መራመጃ ለነገ መዳረሻ  የሚሆን ነገር ለማትረፍ፡፡

በረራው ከተገቢው ፍጥነት በላይ ሲሆን መጠርጠር የደህንነት ሰራተኞች ብቻ ሳይሆን የፖለቲከኞችም ተግባር መሆን አለበት፡፡ይህ ግን የለም አብሮ መብረር ወይንም ዳር ቆሞ ውግዘት ነው፡ ትናንትም ዛሬም ያለው፡፡ አንድነተን ለሞት ያበቃውም ሌሎቹንም በዳዴ የሚያስኬደውም ይሄው ነው፡፡ ከወያኔነት ወደ ተቀዋሚነት ያውም በአባልነት ሳይሆን በሹመት ከዛ በቅጽበት ወደ ፉከራ መሸጋገር ፉከራው ተሰምቶ ሳያልቅ ወደ እሰር ቤት፣እስር ቤት ከእርሱ ቀድመው ከታሰሩም አብረውት ከገቡትም በላይ ስሙ መግነን፤  ከዛ በነጻ መሰናበት፣ከዛ ወደ ምዕራፍ አራት ሽግግር፡፡ ይህ እንዴት ሆነ ብሎ  ያልመረመረና በስሜት ሳይሆን በእውነት፣በአጉል ጥላቻ ወይንም ፍቅር ሳይሆን በመረጃና ማስረጃ ጭብጡን ያልጨበጠ ተቃውሞም ሆነ ድጋፍ ከንቱ ነው፡፡ምን አልባት አንዱ ወገን እርሱን ከፊት አስቀድሞ ገንዘብ የመቃረም፣ ሌላው በእርሱ ላይ የጥላቻ ናዳ በማውረድ እንዲሁ ፈረንካ የማግኘት እቅድ ካልተያዘ በስተቀር፡፡

ምዕራፍ አራት ሀብታሙ በአሜሪካ፡፡ ዲያስፖራውና የኢትዮጵያ ፖለቲካ አንድ ራሱን የቻለ መጽሀፍ ሊያጽፍ የሚችል ነው፡፡ሙያውና ፍላጎቱ ብሎም ለነገሩ ቅርበቱ ላለው፡፡እነርሱ ሀብታሙን ይቃኙት ወይንም እርሱ እነርሱን መንገድ ያሲዛቸው በርቀት የለኝ ምልከታ ይህን ለመረዳት የማያስችለኝ ቢሆንም ለግዜው ሰምና ወርቅ ሆነው ዓላማና ግቡ ባይታወቅም ከከተማ ከተማ እያዞሩ እያናገሩት ነው፡፡ዓላማና ግቡ ባይታወቅም ስል ምክንያት አልባ አይደለም፡፡ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው፤ስለ ወያኔ ማንነትና ምንነት እንዲያስረዳ ነው፣ ወያኔ ስለሚፈጽመው ግፍ የአይን ምስክር እንዲሆን ነው ወዘተ የሚባል ከሆነ ሀያ ስድስት አመት ያልደረሰብን ያላየነውና ያልሰማነው ምን አዲስ ነገር በሀብታሙ አንደበት ተነገረ የሚል ጥያቄ ማንሳት ይቻላል፡፡

የወያኔ ድርጊት መች ነጋሪ መች አስረጅ ይሻና፡፡ በይፋ በአደባባይ የሚፈጸም አይደለም እንዴ፡፡ እየነገሩን አይደለም እንዴ ሁሉን የሚያደርጉን፡፡ ሰምቶ የሚቆጨው፣ አይቶ የሚመረው፣ ቁጭት የሚያንገበግበው ቁጥሩ ሚዛን አልደፋ ማለቱ እንጂ ክፋቱ፡ ከንፈር እየመጠጠ የሚያልፈው፣ ሞኝ የሰማ እለት እንዲሉ ትናንት የሰማውን/አይደለም የተፈጸመበትን  ዛሬ አንደ አዲስ  ደግመው ሲነግሩት እየየ! ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ  ነገ መልሶ የሚረሳው፣ የወያኔን ባላሥልጣኖች በተናጠልም ሆነ ድርጅቱን በጅምላ በማህበራዊ ድረ- ገጽ ተሳድቦ በዚሁ ረክቶ ለሽ ብሎ የሚተኛው  መብዛቱ እንጂ ችግሩ፤ አየር ላይ በቃላት የሚዋጋው(ይህም እርስ በአርስ ነው)  ተግባሩ ላይ መሳሳቱ እንጂ ጉዳቱ መች የወያኔን ማንነት አለማወቅ መች ነጋሪ አስረጅ ማጣት ሆነና፡፡

እናም አበው ነገርን ከስሩ ውሀን ከጥሩ እንደሚሉት ሀብታሙን ለመደገፈፍም ሆነ ለመቃወም እነዚህን አራት ምዕራፎች ሌላ የሚታወቅም ካለ ተጨምሮ በቅጡ ተመርምሮ የተጓዘው እየተገለባበጠ ወይንስ እምነት አመለካከቱን እየለወጠ፣ ለትግሉ ራሱን እየሰጠ ወይንስ ለጥቅም ጌታ እያማረጠ፣ እንዲሁም በእያንዳንዱ ምዕራፍ ከእርሱ እውቅና ውጪም ይሁን በእርሱ ይሁንታ በሶስተኛ ወገን የተሰራ ካለ   ይህን በቅንነት ለመነታረኪያ በሚሆን ሳይሆን ለመማሪያ በሚበጅ መልኩ መቃኘቱ ለነገረ ጭብጡ መሰረት ሊሆን የሚችል የሚገባም ይመስለኛል፡፤እናም የምታውቁ አንድ በሉ፡፡

ይህችን አስተያየት ለመጻፍ ሳስብ አንዳንድ አንድነት ቤት የነበሩ ሰዎችን ለማግኘት ሞክሬ ነበር፣ ከአንድነት መፍረስ በላይ የሚያሳዝኑም የሚያሳፍሩም የሚያበሳጩም ነገሮች ነው የሰማሁት፡፡ ለሁሉም ግዜ አለውና አንድ ቀን ይወጣ ይሆናል፡፡ነገረ ስራው ሁሉ የወረት ፣የአንድ ሰሞን ሁካታና ጫጫታ የሆነው አብዛኛው ዲያስፖራ ሌላው ቀርቶ ዛሬ ከእስር ቤት ተፈቶ ከወያኔ መንጋጋም ተላቆ በነጻነት ሀገር በነጻነት ከሚኖረው ጋራ እየሆነ ያለውን ሲሆን ፣ከሀብታሙ ቀድመው የአንድነት አባል የነበሩ (እንደውም መስራቾች) በወያኔ እስር ቤት በስቃይ ላይ እያሉ ከእነ ስማቸውም መርሳቱ ሁሉ ነገራችን የተመሰረተው በእውነት ላይ ሳይሆን በስሜት፣በምክንያት ሳይሆን በቡድንተነኝነት፣ብሎም በጥቅም ትስስር ላይ ስለመሆኑ አጋላጭም አረጋጋጭም ነው፡፡እንዴት ናትናኤል ይረሳል፣አንዱአለም እንኳን አልፎ አልፎም ቢሆን ስሙ ይነሳል፡፡( ለአብነት ሁለቱን አነሳሁ እንጂ ከሰዎቹ የሰማሁት ብዙ ) ለነገሩ ለታሰሩ አባሎቻቸው እንኳን ሲሉ ነገሮችን በውይይት ማስተናገድና ወንዙን መሻገር ተስኖአቸው ፓርቲን ለመፍረስ የዳረጉ ሰዎች፣እነዚህንም አይዟችሁ እያሉ እስከ ቀብር የሸኙ ሰዎች  እንደምን እስር ቤት ያሉ አባሎቻቸውን እንዲያስታውሱ ይጠበቃል፡፡

እነዚህ ከነመኖራቸው የተረሱ ወገኖች የታሰሩበት ፓርቲ አመረራር አባላት የነበሩ ሰዎች ከፓርቲው በዘረፉት ንብረት ሀብት አካብተው ቢጠሩዋቸው የማይሰሙ ሆነዋል ተብሎ በማስረጃ ቢነገርዎት ምን ይሰማዎታል፡፡ እኔ ዓሳ ጎርጓሪ ዘነዶ ያወጣል ሆኖብን ይሄ ነው ያጋጠመኝ፡፡ ለእውነት ስለ እውነት የቆምን ቢሆን ሙስናና ዘረፋን ክህደትና በስልጣን መባለግን አንባገነንነትንና ህገ ወጥነትን ወዘተ የፈጻሚውም ሆነ የተፈጸመበት ማንነትና ምንነት ሳያግደን እኩል መቃወም መቻል ነበረብን፡፡ ግን ጉዳዩ ከዚህ በተቃራኒ ሆነና በፓርቲ ንብረት የከበሩ፣ በእስር ቤት በሚሰቃዩ ዜጎች መስዋዕትነት የሚነግዱ ወዘተ ወገኖችን አይተን እንዳላየን እናልፋለን ወይንም የጥቅም ተጋሪ ሆነን አፋችንን እንለጉማለን፡፡

ነገርን ነገር ያነሳዋል ሆኖብኝ ከርእሰ ጉዳዬ ወጣሁ፡ልመለስ፡፡ድጋፋችንም ሆነ ተቃውሞአችን አንድ ሰሞን የሞቅታ  የሚሆነው የቆምንለት ዓላማና አሸጋግረን የምናየው የጠራ ግብ የሌለን  ወይንም ግዜያዊ የሆኑት አለማዊ ጉዳዮች ይህን እየጋረዱብን  በመሆኑ ይመስለኛል፡፡ ባይሆን ኖሮ ለእያንዳንዱ ንግግራችንንም ሆነ አድራጎታችን መነሻ የምናደርገው ዓላማና ግባችንን፡ ድርጊቶቻችንን  የምንመዝነውም ለዓላማችን ስኬት ወደ ግባችን ለመዳረሻ ጎዞአችን ፍጥነት ምን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ  በሚል ይሆን ነበር፡፡ የሀብታሙ አያሌው በየመድረኩ እየተገኘ ወያኔ ገዳይ ነው፣ ገራፊ ነው ማለቱ ታማኝ በየነ እንደሚለው የእኛ ብሶት ማውራት ለቅሶና ኡኡታ ማሰማት እነርሱን ያስደስት ሌላ ማሰቃያ ሌላ ማስለቀሻ ማስጮሂያ ስልት እንዲያስቡ ያደርግ ካልሆነ በስተቀር  ሀያ ስድስት አመት የተባለ እንደመሆኑ አዲስ ይዞት የመጣ ፋይዳ አይታየኝም፡፡ የሰው ልጅ ከደረሰበት በደል በላይ ስለ በደሉ ሲነግሩት ያለቅሳል እንዲሉ ማስለቀስ ካልሆነ በስተቀር፡፡ ይህንም ለምደን ተለማምደነዋል፣አዳራሹ ውስጥ አልቅሰን አጨብጭበን ገና ከበሩ ሳንወጣ ምን እንደተባለ እንኳን እንረሳዋለንና ሌላ ሌላ ጥቅም ካለው እኔ አላውቅም እንጂ ዛሬም ብሶት ማውራት ዛሬም ወያኔን ማውገዛ ማጥላላት መዝለፍ መፎከር የትም አያደርስም፡፡ በዚህ በዚህ ቢሆን ወያኔ ሀያ ስድስት አመት አይደለም አስር አመት አይቆይም ነበር፡፡በዚህ በዚህ ቢሆን እነ አንቶነኔ ዛሬ የምናያቸው ምንይልክ ቤተ መንግሥት ነበር፡፡ አቦ ሰከን እንበል! አንገት የተሰራው አዙሮ ለማየት ነው የሚባለው ለምን ይሆን!

 

The post የሀብታሙ አያሌው ባለ አራት ምዕራፍ ፖለቲካ፣ – ይገረም አለሙ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አንዳርጋቸው ጽጌ የጽናታችን እና የቁርጠኝነታችን ዓርማ ነው! (አርበኞች ግንቦት 7)

$
0
0

የንቅናቄያችን መስራችና ዋና ጸሀፊ የነበረው ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ በዘረኛው የህወአት አገዛዝ ከየመን አየር ማረፊያ ታግቶ እስር ቤት ከተወረወረ እነሆ ጁን 23 2017 ዓም 3 አመት ሞላው።

ህወአት አንዳርጋቸውን ባገተበት ወቅት የንቅናቄያችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ይሽመደመዳል የሚል ተስፋና እምነት ነበረው። ይህንን እምነቱን ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ በሚፈጸምበት ሰቆቃ ውስጥ ሆኖ እንዲያረጋግጥለትና ነጻነት ናፋቂ የሆነው ህዝባችን ተስፋ እንዲቆርጥ ብዙ ጥሯል፣ ደክሟል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በሚከፍለው ግብር የሚተዳደረው የአገራችን ዋናው ቴለቪዥን ጣቢያና ህወሃት ህዝባችንን በፕሮፖጋንዳ ለማደንዘዝ ያቋቋማቸው ሌሎች ሚዲያዎ በሙሉ በመረባረብ ከጓዳችን መታገት ጋር ተያይዞ ግንቦት 7 አከርካሪውን ተመቶአል፤ ሌሎች የንቅናቄው አመራሮች የአውሮጳና የአሜሪካ የምቾት ኑሮዋቸውን ትተው ወደ በረሃ የመሄዳቸው ጉዳይ የማይታሰብ ነው የሚል ከንቱ ትንበያ ከማራገብ አልፈው የህዝባችንን ቅስም ለመስበር ያመቸናል የሚሉትን የፈጠራ ድራማዎችን በማቀነባበርና በማሰራጨት ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን ብቻ ሳይሆን ግምቱ የማይታወቅ የአገራችንን ሃብትም አባክነዋል።

ህወሃት ከህዝብ በተዘረፈ ገንዘብና በጠመንጃ ሃይል በተያዘ ሥልጣን ልቡ ያበጠ እብሪተኛ ድርጅት መሆኑን በገሃድ ያስመሰከረው ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌን ለማገት ከተጓዘው ርቀት እና ከወሰደው የድፍረት እርምጃ በተጨማሪ ለነጻነት የሚደረገው ትግል አብቅቶለታል ብሎ ለመደምደም ያሳየው ጥድፊያ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ትግል ፤ ለፍትህ ለእኩል ነትና ለአገር ባለቤትነት የሚደረግ ትግል መሆኑ መረዳት ያልቻለው የህወሃት አገዛዝ ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ ከአፍላ የወጣትነት ዕድሜው ጀምሮ የቆመለትና ዋጋ እየከፈለለት ያለው ይህ ክቡር አላማ ከግለሰብ ተክለ ሰውነት በላይ ግዙፍ እንደሆነ አንዳርጋቸውና የትግል ጓዶቹ ጠንቅቀን እናውቃለን።

ወያኔ አገር ውስጥ ያሉትን ተቃዋሚዎች እግር በእግር እየተከተለ ለማዳከም በየቀኑ የሚወስደው የእስር፤ የእንግልትና የግዲያ እርምጃ አልበቃ ብሎት ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌን ከባህር ማዶ አግቶ ለመውሰድ ለየመን ጸጥታ ሃይል በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከፍሎአል። በዚህ የወያኒ የእብሪት እርምጃ የተበሳጨው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘር፤ ቋንቋና ሃይማኖት ልዩነት ሳያከፋፍለው ‘”እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” በሚል ቁጣ ተነስቶ በአምባገነንነትና በዘረኝነት ላይ የሚደረገውን ትግል ወደ ሌላ ምዕራፍ እንዲሸጋገር አድርጎታል። ከዚህም በተጨማሪ ህወሃት ከአንዳርጋቸው መታገት በኋላ በአመራር እጦት ይበተናል ያለው የነጻነት ትግል ከኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ጋር በተደረገው ውህደትና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመታገል በተፈጠረው ጥምረት መክሸፉን አስመስክሯል።

ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ በታገተ ሰሞን የንቅናቄያችን አመራር ወደ ምድር ወርዶ ትግሉን ለመምራትና ለመታገል ያስተላለፈውና እየተገበረው ያለው ውሳኔ በጠላት ካምፕ ከፍተኛ መደናገጥን ሲፈጥር በወገን ካምፕ በኩል ከፍተኛ ተስፋንና አለኝታነትን የጫረ ሆኖአል።

የንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 አባላት እና ደጋፊዎች በየምንሰበሰብባቸው የስብሰባ አዳራሾችና በየምንሰማራባቸው የትግል መስኮች እየዘመርነው ያለው የ”ላንቺው ነው አገሬ” ግጥም ደራሲ የሆነው ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ የምንታገልለትን አላማ በአጭሩ እንዲህ ሲል በስንኞቹ አስቀምጦአል።

በባርነት ሸክም ጀርባሽ የጎበጠው፣
በባለጌ መዳፍ ክብርሽ የጎደፈው፣
የስቃይሽ ስቃይ ሰማይ የነደለው፣
ዓይንሽ እስኪጠፋ ደም ለምታነቢው፣
ላንቺ ነው ሀገሬ ህይወት የገበርነው፣
ላንቺው ነው ሀገሬ እኛ የምንሞተው።

ለናዱት አንድነት ላረከሱት ሀገር፣
ለቀሙን ነጻነት ለጫኑብን ቀንበር፣
መልሱ ሆኖ መጥቷል ደረትን ለአረር፣ እያለ ይቀጥላል።

ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ ይህንን ግጥም በደረሰበት ወቅት በእአምሮ ውስጥ ይመላለስ የነበረው አገራችን የገባችበት አዘቅትና የህዝቦቿ ጉስቁልና እንደሆነ መገንዘብ ከባድ አይሆንም። ይህንን ለመለወጥ ደግሞ ትግሉ የሚጠይቀው ቁርጠኝነትና የመንፈስ ጽናት ደረጃ እስከምን እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦአል።

መላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊዎች መሪያችን አንዳርጋቸው ጽጌ በጠላት እጅ የወደቀበትን ሶስተኛ አመት ስናስታውስ እርሱና ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላቶቻችን እስከዛሬ የከፈሉትንና በመክፈል ላይ የሚገኙትን መስዋዕትነት እያሰብን ይህ ሁሉ ዋጋ የተከፈለለትን የነጻነት ትግል ከዳር ለማድረስ ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ በመግለጽ ነው ።

ዛሬ በየእስር ቤት ውስጥ ሆነው በንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 ሥም የተለያየ መከራና ስቃይ በመቀበል ላይ ያሉትም ሆኑ በትግሉ ላይ እያሉ ውድ ህይወታቸውን ለዚህ ክቡር ዓላማ የገበሩ ወገኖቻችን የሚካሱት እነርሱ ዋጋ የከፈሉለትን አላማ ከግብ ለማድረስ ባለን ጽናትና ቁርጠኝነት ብቻ ነው።

የጀመርነው ትግል ምንም አይነት ዋጋ ቢያስከፍለን የኋላ ኋላ በአሸናፊነት እንደሚደመደም ምንም አይነት ጥርጣሬ የለንም። መታሠር፣ መገረፍና መገደል የነጻነት ትግል ማደናቀፍ የሚችል ቢሆን ኖሮ የህወሃት የመንፈስ አባት የሆነው ፋሽስት ጣሊያን እስከዛሬዋ ደቂቃ ድረስ በባርነት ሲገዛን ይኖር ነበር።

ውድ ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ እና በተለያየ የወያኔ ማጎሪያ ቤቶች ውስጥ ፍዳችሁን እያያችሁ ያላችሁ ወገኖቻችን ሆይ! የታሠራችሁበት የብረት ሰንሰለትና የታገታችሁበት የእስር ቤት በሮች የሚበረገዱበት ቀን ሩቅ እንደማይሆን እኛ የትግል ጓዶቻችሁ እናረጋግጣለን። በአረአያነት ያስተማራችሁን ጽናታችሁና ቆራጥነታችሁ በደማችን ውስጥ ነፍስ እንደዘራ አትጠራጠሩ።

ዘለአለማዊ ክብር ለነጻነት ስሉ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖቻችን ሁሉ!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

The post አንዳርጋቸው ጽጌ የጽናታችን እና የቁርጠኝነታችን ዓርማ ነው! (አርበኞች ግንቦት 7) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የመቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን አሳዛኝ ታሪክ – ማህሌት ፋንታሁን

$
0
0

የመቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን “ነፃ” ነት

መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን

መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን በአማራ ክልል፤ ምዕራብ ጎጃም ዞን የመኢአድ ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ነበር። ከዚህ በፊት በ1989ዓ.ም‹‹የመአድ አባል በመሆን መንግስት ለመገልበጥ ሞክረሃል››በሚል ከነፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ጋር ተከሶ 20 ዓመት ተፈርዶበት፤በአመክሮ 14 ዓመት ከ6 ወር ታስሮ በ2003 ዓ.ም ነበር የተፈታው፡፡ በእስር ሳለም ‹‹ከእስር ቤት ልታመልጥ ሞክረሃል›› ተብሎ በጥይት እግሩን ተመቶ ለረጅም ጊዜ ይሰቃይ ነበር። ከተፈታ ከአራት ዓመታት በኋላ፤ በ2007ዓ.ም በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ከታሰሩት በአማራ ክልል የሚገኙ 16 የመኢአድ፣ የአንድነት እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አንዱ ነው። በአሁኑ ሰአት እድሜው 48 የደረሰው መቶ አለቃ ጌታቸው፤በእስር ላይ እያለ የልጅ አባት ሆኗል:: መቶ አለቃ ጌታቸው ከታሰረ ከአንድ አመት ከስምንት ወራት እስር በኋላ ጉዳዩን የሚከታተለው የከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 9/2009ዓ.ም ቀን በሰጠው ብይን”ነፃ” ተብሎ ዳግም ከ”እስር” ተፈቷል።

የክሱ ሒደት

በመዝገቡ 1ኛ ተከሳሽ የሆነው መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን ከሌሎቹ 15 የተቃዋሚ አመራሮች ጋር ‹‹የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ናችሁ›› ተብለው የፀረ ሽብርተኝት አዋጁን አንቀፅ 7(1)ን በመተላለፍ በሚል ክስ ተመስርቶበታል። ከአራት ወር በላይየማዕከላዊ የስቃይ ቆይታ በኋላ ግንቦት 18/2007 ፍርድ ቤት ቀርቦ የተነበበለት ክስ የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆን የፀረ ሽብር ህጉን አንቀፅ 7(1)ን በመተላለፍ፡

“ከጥቅምት ወር 2004 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን) አባል በመሆን እንዲሁም ጥር ወር 2006 ላይ በሑመራ በኩል ኤርትራ እንዲገባ እና ከሽብር ድርጅቱ ጋር እንዲቀላቀል የቀረበለት ጥያቄ በመቀበል በየካቲት ወር 2006 የሽብር ድርጅቱን በአባልነት በመቀላቀል፤ ከባህር ዳር ከተማ በመነሳት ወደ ኤርትራ በመሄድ ከሽብር ድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመገናኘት የሽብር ድርጅቱ አባል በመሆን፤ ከዛም ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ አባላትን መልምሏል።”

የሚል ነው። አቃቤ ህግ ክሱን ያስረዳልኛል ብሎ ያቀረበው ማስረጃ በማዕከላዊ የሰጠውን 10 ገፅ የእምነት ቃል እና ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ የቀረበ የስልክ ልውውጥ ብቻ ነበር።

መቶ አለቃ ጌታቸው ማዕከላዊ ከመምጣቱ በፊት የነበረበት ደህንነት ቢሮም ሆነ ማዕከላዊ ከባድ ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡ ማዕከላዊ እያለ ብልቱ ላይ ሁለት ሊትር ‹የሃይላንድ ውሃ› አስረውበት መርማሪዎች አድርገሃል ያሉትን እንዲያምን ያሰቃዩት እንደነበረ፤ በዚህም ብልቱ እንደቆሰለ እና ሕክምና እንዳያገኝ ተከልክሎ እንደቆየ ግንቦት 18/2007 ቀን ክሱ በችሎት የተነበበ ቀን ለዳኞች አስረድቷል። በድብደባ የደረሰበትን አደጋ ለማሳየት ዳኞችን ሲጠይቅ በመከልከሉ ሱሪውን አውልቆ ብልቱ ላይ ያለውን ቁስለት ለዳኞችና ችሎቱን ለታደሙ ማሳየቱና ዘሩን መተካት እንዳይችል መደረጉን መናገሩ የሚታወስ ነው። ከማዕከላዊ ወጥቶ ቂሊንጦ ከተዛወረ በኋላ ለመንቀሳቀስ እጅግ ይቸገር እንደነበር ይናገራል።

ፍርድ ቤቱ ሰኔ 21 ቀን 2008 ዓ.ም ቀን በዋለው ችሎት የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል በተበየነው መሰረት አራት የሰው ምስክሮችን አስደምጧል። ምስክሮቹ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን ማዕከላዊ እያለ ለፓሊስ የሰጠው ቃል በግዳጅ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ያስረዱ ናቸው።

ጉዳዩን የሚከታተለው የከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛ ችሎት ዳኞች የጥፋተኝነት ፍርድ ሰኔ 9/2009 ቀን ባሰሙ ወቅት መቶ አለቃ ጌታቸውን በተመለከተ ያነበቡት ብይን በአጭሩ እንዲህ የሚል ነው

“ተከሳሹ በማዕከላዊ እያሉ አካላቸው [ብልታቸው ለማለት ነው። ዳኞች የአካሉን ስም እንደማይጠቅሱ ተናግረዋል።] በድብደባ የተጎዳ መሆኑ እና በዛ አካላታቸውም መገልገል እንደማይችሉ ፍርድ ቤቱ እየከለከላቸውም ቢሆን በችሎት ያሳዩት ጉዳይ በመሆኑ፤ ከፊሎቹ መከላከያ ምስክሮችም አብረዋቸው በማዕከላዊ ‹ሳይቤሪያ› የሚባለው ጨለማ ክፍል የነበሩ ሲሆን ብልታቸው ላይየደረሰውን መቁሰልያዩ እናበድብደባ ሳቢያ ‘ከምትሞት የሚሉህን ፈርም‘ ብለው የቀረበበትን ክስ አምኖ ቃል እንዲሰጥ መምከራቸውን የመሰከሩ በመሆኑ እንዲሁም የተቀሩት ምስክሮች በማዕከላዊ ለመከሰስ የሚዘጋጁ እስረኞች በሚቀመጡበት ‹ሼራተን› ክፍል ተከሳሹን ያገኙት መሆኑን ገልፀው ‘ከምሞት ብዬ ያሉኝን ፈረምኩ‘ ብሎ እንደነገራቸው በመመስከራቸው”

በማዕከላዊ የሰጠው ቃል በግዳጅ እንደሆነ የሚያሳይ ነው በማለት አቃቤ ህግ ያያዘውን የመቶ አለቃ ጌታቸው ቃል ውድቅ እንዳደረጉት ገልፀዋል። ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ የቀረበው ማስረጃን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ፡”ከኤጀንሲው የቀረበው ማስረጃ ላይ የስልክ ልውውጡ የተደረገበት ስልክ ባልተጠቀሰበት ሁኔታ” የስልክ ልውውጡ መቶ አለቃ ጌታቸው ያደረገው ነው ለማለት እንደሚያስቸግር በመግለፅ፤ አቃቤ ህግ ያቀረበበትን ማስረጃ በበቂ ሁኔታ በመከላከሉ በነፃ እንዲሰናበት ውሳኔ ተሰጥቷል።

አስገድዶ የእምነት ቃል መቀበል

መቶ አለቃ ጌታቸው ብቻ አይደለም “መርማሪ” ባደረሰበት ድብደባ አካሉ የጎደለ። በተመሳሳይ መዝገብ 4ኛ ተከሳሽ የሆነው አወቀ ሞኝሆዴም በ “ምርመራ” ወቅት ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶበት በተመሳሳይ “ነፃ” ተብሎ ከእስር ወጥቷል፡፡ መቶ አለቃ ጌታቸው እና አወቀ ሞኝሆዴም ብቻ አይደሉም፤ በ “መርማሪዎች” ድብደባ ህይወታቸውን ያጡ፣ አካላቸው የጎደለ፣ የእድሜልክ በሽታ የሸመቱ፣ አካላቸው እንዲጎድል የሆነ፤የስነ ልቦና ችግር ተጠቂ የሆኑ በርካቶች ናቸው። የወንድ ብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠል፣ የውስጥ እግር መግረፍ፣ ሃይለኛ ጥፊ፣ ከባድ ድብደባ፣ የሴት ጡት መግረፍ፣ ማህፀን ውስጥ ባእድ ነገር ማስገባት፣ መድፈር፣ እርቃን ማስቆም፣ ስፖርት ማሰራት፣ ጥፍር መንቀል፣ ማዋረድ፣ መስደብ፣ ማስፈራራት፣ መዛት፣ ቤተሰብ እና ጠበቃ አለማገናኘት፣ እና ስነ ልቦናዊ ጫናዎች የሚያደርሱ ሌሎች መሰል ኢ-ሰብአዊ እንዲሁም ኢ- ሕገመንግስታዊ ድርጊቶች በ ”ምርመራ” ወቅት “መርማሪዎች” ጠርጥረናችኋል የሚሏቸው ግለሰቦች ላይ የሚፈለገውን ‹ወንጀል ሰርተናል› ብለው እንዲያምኑ እና ቃል እንዲሰጡ የሚፈፅሟቸው ወንጀሎች ናቸው። ይህ አይነት ወንጀል በአብዛኛው በሽብርተኝነት ወንጀል የተጠረጠሩ ወይም የተከሰሱ ግለሰቦች ላይ የሚፈፀም ቢሆንም በሌላ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ወይም የተከሰሱ ግለሰቦች ላይም ወንጀሎቹ የሚፈፀሙባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት አይደሉም።

ሕጉ ምን ይላል?

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስተ አንቀፅ 19(5) ላይ፡ “የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል የእምነት ቃል እንዲሰጡ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም። በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም።” ይላል። የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ሕጉም በተመሳሳይ አንቀፅ 27(1) ላይአንድ ግለሰብ ለቀረበበት ክስ ወይም የክስ አቤቱታ ቃሉን ለመስጠት እንደሚጠየቅ ይገልፃል፤ አንቀፅ 27(2) ደግሞ፡ “ሰውየው ምላሽ እንዲሰጥ ለማስገደድ አይቻልም። ነገር ግን ምላሽ ለመስጠት ነጻ እንደ ሆነና ፈቅዶ የሚሰጠው ማናቸውም ቃል በማስረጃነት የሚቀርብ መሆኑ ጠያቂው ፓሊስ ለተጠያቂው መንገር ይገባዋል።” በማለት ይገልፃል። በቅርቡም ከሰበር ሰሚ ችሎት በተሰጠ ብይን (ያልታተመ)፤ ተጠርጣሪዎች ለፖሊስ ቃላቸውን የሰጡት በማስረጃነት የሚቀርብ መሆኑ ሳይነገራቸው ከሆነ ማስረጃው (ቃሉ) ተቀባይነት እንደማይኖረው የሕግ ትርጓሜ ተሰጥቶበታል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ በምርመራ ወቅት በሕግ የተከለከሉ ተግባራትን የሚፈፅሙ ፖሊሶች በወንጀል እንደሚጠየቁ ይደነግጋል።

ይሁን እንጂ በሕጎቹ ላይ የተደነገጉት የተከሰሰ ወይም የተጠረጠረ ሰው መብቶች ከወረቀት ባለፈ ሲተገበሩ ማየት የማይታሰብ ነው።

የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ

በሕገ መንግስቱ እና በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ሕጎ ላይ ላይ ከተደነገገው በተፃራሪ የማስረዳት ሸክምን በሚያቀል መልኩ፤ በ2001 ዓ.ም የወጣው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀፅ 23 ላይ ተቀባይነት የሚኖራቸው ማስረጃዎችን ይዘረዝራል። በአዋጁ አንቀፅ 23(5) ላይ “በሽብርተኝነት ድርጊት ከሚጠረጠር ሰው በፅሁፍ፣ በድምፅ መቅረጫ፣ በቪዲዮ ካሴት፣ ወይም በማናቸውም ሌላ ሜካኒካል ወይም ኤሌክትሮኒክ መሳሪያ የተቀረፀ የእምነት ቃል።” ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ መሆኑን ያትታል፡፡በዚህም ምክንያት አቃቤ ህግ በሽብርተኝነት የሚከሱትን ግለሰብ በግዳጅ የተቀበሉትን የ ”እምነት” ቃል ብቻ [ሌላ ምንም ማስረጃ ሳይኖረው] በማያያዝ ክስ ለመመስረት ያስችለዋል። በተግባርም እየሆነ ያለው ይሄው ነው።

የፍርድ ቤት ውሳኔ

አንድ ግለሰብ የፀረ ሽብርተኝት አዋጁን በመተላለፍ የተከሰሰ እንደሆነለ “መርማሪ” ፖሊስ ወንጀል እንደሰራ አምኖ በግዳጅ የሰጠው ቃል ማስረጃ ሆኖ ይቀርብበታል፤ ክሱንም እንዲከላከል ለማስፈረድ የሚያስችል ማስረጃ ነው። ተከሳሹ በሚከላከልበት ወቅት በማስረጃነት የቀረበበት ቃል በግዳጅ ወይም በኃይል የተሰጠ መሆኑን የማስረዳት ግዴታ አለበት። አለበለዚያ ተከሳሹ ለ “መርማሪ” ፖሊስ ወንጀል እንደሰራ አምኖ በግዳጅ በሰጠው ቃል ብቻ ጥፋተኛ ተብሎ የእስር ቅጣት ይበየንበታል።

በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው እንደ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን ቃላቸውን መከላከል ችለው ከክሳቸው “ነፃ” ሲባሉ ያየኋቸው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው። ተከሳሹ በማስረጃነት የቀረበበት ቃል በግዳጅ የሰጠው ስለመሆኑ “መርማሪ” ፖሊስ አስገድዶ ቃሉን ሲቀበል በአይን ያዩምስክሮችን ማቅረብ ይኖርበታል። ከተከሳሹ ጋር አንድ ክፍል የነበሩ ምስክሮች፤ ለምርመራ ሲጠራ ጤነኛ እንደነበረ ሲመለስ ግን እመን እየተባለ በደረሰበት ድብደባ አካላቱ ቆስሎ/ጎድሎ እና መራመድ እያቃተው መመለሱን ማየታቸውን እንዲሁም እርዳታ ያደርጉለት እንደነበረ ሲመሰክሩ“መርማሪው ሲደበድበው አይተኻል ወይ?”፣ “የእምነት ቃል እንዲሰጥ መገደዱን እንዴት አወቅክ?” እና “አደጋው የደረሰበት ወደ መርመራ ማዕከሉ [ማዕከላዊ] ከመምጣቱ በፊት የተከሰተ ነገር አለመሆኑን በምን እርግጠኛ ሆንክ?”የሚሉ መስቀለኛ ጥያቄዎች ከአቃቤ ህግ እንዲሁም ተመሳሳይ ማጣሪያ ጥያቄዎች ከዳኞች በተለያዩ መዝገቦች ላይ ሲሰነዘሩ እንደ መስማት የሚያሳምም ነገር ምን አለ? እንዴት አንድ የፍትህ ስርዓትአካል የሆነ [ዳኞች እና አቃቢያን ህግ] ይህን መሰል ታሪክ ለብዙ ዓመታት እየሰማ እንዳልሰማ በዝምታ ማለፍ ይቻለዋል?!

ጥቂቶቹ፤ የደረሰባቸውን ቋሚ ጉዳት በችሎትለማሳየት የደፈሩ፣ በአይን የሚታይ ጉዳት የደረሰባቸው፣ ወንጀሉ በተፈፀመባቸው ወቅት እድለኛ ሆነው የህክምና ማስረጃ ማግኘት የቻሉ እና“መርማሪ” ፖሊስ በግዳጅ ቃላቸውን ሲቀበላቸው በአይን ያየ/ዩ ምስክር/ሮች የሚያገኙ ተከሳሾች በማስረጃነት የተያያዘባቸውን ቃል ዳኞች ውድቅ የሚያደርጉባቸው አጋጣሚዎች ውስን ቢሆንም አልፎ አልፎ ይከሰታል። ልክ እንደ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን። ዳኞች በመቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን ጉዳይ የቀረበላቸውን ማስረጃ መዝነው፤ በግዳጅ በተለይም ደግሞ አካሉን አጥቶ (ሰብዓዊ መብቱ ተጥሶ)፤የሰጠው የእምነት ቃል መሆኑንን አረጋግጠውማስረጃውን (በግዳጅ የተሰጠውን ቃል) ውድቅ አድርገው ከክሱ “ነፃ” ነህ ብለው ውሳኔ ሰጥተዋል። ነገር ግን ዳኞቹ ማስረጃውን ውድቅ ከማድረግ ባሻገር መስጠት የሚገባቸው ተጨማሪ ውሳኔ ወይም ትእዛዝ መኖር አልነበረበትም ወይ? መቶ አለቃ ጌታቸው አንድ አመት ከስምንትወራት አላግባብ መታሰሩእንዲሁምበ “ምርመራ” ወቅት የደረሰበት የአካል ጉዳት በምንድነው የሚካሰው?ወንጀሉን የፈፀመው አካል ዝም መባል አለበት ወይ? ከክሱ ነፃ መባሉ ብቻ ፍትህ አግኝቷል ያስብላል ወይ?

“መርማሪዎች” ተከሳሾች እና ተጠርጣሪዎች ላይ በሚፈፅሙት ወንጀል መጠየቅ ያለባቸው ፍ/ቤት ድርጊቱን ባረጋገጠበት ጊዜ ብቻ አይደለም። ነገር ግን ቢያንስ ፍርድ ቤት ድርጊቱን ባመነበት አምኖም ተከሳሹን ከክሱ ነፃ ባወጣበት አጋጣሚ ግን ተከሳሹ የሚካስበትን እና ወንጀሉን ያደረሰው አካል/ግለሰብ ደግሞ በሕግ የሚጠየቅበትን አግባብ ፍርድ ቤቱ ራሱ ሐላፊነቱን ወስዶ ተበዳይ ወገን ፍትህ እንዲያገኝ ማድረግ አለበት ብዬ አምናለሁ።

The post የመቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን አሳዛኝ ታሪክ – ማህሌት ፋንታሁን appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ሌ/ጄነራል ጻድቃን ፣ ህወሃት ፣ ኤርትራ እና ቀይ ባህር – በነጻነት ቡልቶ

$
0
0

ክፍል አንድ

ጄነራል ጻድቃን፣የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፓሊሲእና  “የፓለቲካ ችግሮች

በግሪክ አቴናና በስፓርታ መካከል የተካሄደውን የጦርነት ታሪክና ከጦርነቱ ጋር የተያያዙ ስትራቴጃካዊ ጽንሰ ሃሳቦች በማፍለቅ ከሚደነቀው ጥንታዊው የታሪክ ጸሃፊ  የቱስዳይስ  The Peloponnesian war  ጀምሮ  እስከ  የጀርመኑ ካርል ቮን ክልሽዊትዝ  On War ፣  የባህር ሃይል  ስትራቲጂ አባት አልፌሬድ ማሃን The influence of Sea Power Upon History፡ ከዘመን ተሻጋሪ  የስትራቴጂ አስተምሮዎች ፈላስፋ ቻይናዊው ከሰን ዡ The Art of War  አንስቶ እሰከ ሉትዋርክ፣ ኮሊንስ የመሳሰሉ የዘመናችን የስትራቴጂና የደህንነት ጥናቶች ታላላቅ ተመራማሪዎችና  ምሁራን  የጻፏቸውንና ያፈለቁዋቸውን የስትራቴጂ ጽንሰ ሃስቦችና ቀመሮች  በጥልቀት ማጥናትና ማወቅ አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው፡፡  የሴኪዩሪቲና የስትራቴጂ እውቀቶችን ባካበቱ ምሁራንና ተመራማሪዎች የሚጻፉ የአብይ ስትራቴጂ (Grand strategy) ንድፈ  ሃሳቦችና ጽንሰ ሃሳቦች፣  ከነዚህ የሚመነጩ የብሄራዊ ደህንነት ስትራቴጂ ቀመሮችን ተመርኩዞ  የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፓሊሲዎችን መንደፍ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለተጋረጡባት ድርብርብ የፖለቲካ ችግሮችና ከችግሮቹም የሚመነጩትን ዘርፈ ብዙ የደህንነት አደጋዎችን ለመከላከል የማይናቅ ድርሻ አላቸው። በእነዚህም ዙሪያ  ጥልቀት ያላቸው ጥናቶችን ማድረጉ አስፈላጊ ነው። እነዚህንም የሚያስፈጽሙ አካላት መኖርና መጠናከር ለኢትዮጵያም ሆነ ለማንም ሀገር አስፈላጊ ከሆኑ ተቋማት ውስጥ በቀዳሚነት የሚቀመጡ መሆናቸው አይካድም። ከዚህ አኳያ ጄነራል ጻድቃን በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ፖሊሲዎችና ተቋማት ለአንድ ሃገር የሚበጁ እንደሆኑ ወደ አደባባይ ጉዳዩን ማቅረባቸው ያስመሰግናቸዋል።

ነገር ግን በዋነኝነት በአንድ ሀገር ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ስርአት መሪዎች ባህሪ ፣ የፖለቲካ ታሪካቸው (track record)፣ የሚከተሉት ኣካሄድና የፓለቲካ ፍላጎት በሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ ላይ ቀዳሚና  ወሳኝ (Decisive) ድርሻ እንዳላቸው ክርክር የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም። ይህንን ቀላል ዕውነት መረዳት የችግሮቻችንን መሰረት ለማወቅ ፣ አውቆም በቀዳሚነት የሚያስፈልገው ያለፈው 26 አመት ህወሃት የዘረጋውን  የፓለቲካ ስርአትና ተከትሎት የመጣውን  ግዙፍ  የደህንነት አደጋዎች ለመገንዘብ ይረዳናል።  ይህን አደጋ ለመቀልበስ ደግሞ ቁርጠኝነትና  የፓለቲካ ወኔ (Political will)  መኖር   ዋናው ቁልፍ ነው። ይህም በመሆኑ ነው “የፓሊሲዎች ቈንጮ የሆነውን የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲ” በባለቤትነት፣ በአስፈጻሚነትና በኣስተግባሪነት አሁን ላለው የሀገሪቱ የደህንነት ስጋት ዋና ቀፍቃፊ ምንጭ ለሆነው  የሕወሃት አመራር መስጠት ውሻን ሉካንዳ ቤት እንዲጠብቅ ከማድረግ ይቆጠራል ብዬ የምከራከረው። የብሄራዊ  ደህንነት አደጋዎች አመንጪና አሽከርካሪ (driver) የሆነውን አካል የዚህ ፖሊሲ ባለቤትና አስፈጻሚ ማድረጉ ስርአቱን ትንሽ ጠጋግኖ ለማስቀጠል ይረዳ እንደሆን እንጂ በዘለቄታው የኢትዮጵያን የደህንነትና ተያያዥነት ያላቸውን ዘርፈ ብዙ የፖለቲካ  ችግሮች  ማስወገድ አይቻልም። እንዳውም በተቃራኒው እነዚህ  ዘርፈ ብዙ የሀገሪቱ የፓለቲካ ችግሮች ተወሳስበው መቀጠላቸውና  ሀገሪቱንም ሆነ የአፍሪካ ቀንድን ለከፋ ትርምስና የደህንነት ኣደጋ ማጋለጣቸው አይቀሬ ነው።

ህወሃት የስልጣን ዕድሜውን ማስቀጠያ መርህ ወይም ከልቡ የሚያምንበት ገዢ ሃሳብ ከጠፋበት ሰንበትበት ብሏል። ህወሃቶችንና ኢህአዴጎችን አጣብቆ የሚያቆያቸው መርህ ፍርክርክ ባለበት፤ በተለይ ከቀድሞ መሪያቸው ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በእውር ድንብር በሚሄዱበት፤ በውስጣቸው የሚገኘው ቅራኔና ክፍፍል በጦዘበት፤ ሆኖም ላንሰራፉት የአንድ ብሄር የበላይነትና የዘረፋ ስርአት መሳሪያ የሆነን የመንግስት ስልጣን እንዳያጡ ተጣብቀው የሚገኙበት ሁኔታ ላይ ነው ያሉት። የኢትዮጵያን ህዝብ የሚያማልሉበት፣ የሚያሳምኑበትና ከጎናቸው የሚያሰልፉበት ሃሳብ እንደሌላቸውም ግልጽ ከሆነ ቆይቷል። ባጠቃላይም በህወሃት የበላይነት ስር የሚገኘው የፖለቲካ ስርኣት የቅቡልነት፣ የህጋዊነት፣ ብሎም የራስ መተማመንና የውህድ አመራር እጦት ድርብርብ ቀውሶች ታማሚ ሆኖ በሚማቅቅበት በአሁኑ ቀውጢ ሰዓት ላይ ጄ/ል ጻድቃን አንድ መላ ይዞላቸው የመጣ ይመስላል።  ምናልባትም “የሕዝብ የአስተሳስብ አንድነት” ሊያመጣ የሚችል ሁሉን አሰባሳቢ ገዢ ሃሳብ ነው ብለው ገምግመው ሊሆን እንደሚችል ከግምት ውስጥም ማስገባት ያስፈልጋል።

“ከህገ መንግስቱ በታች የፓሊሲዎች ቁንጮ” የሆነው የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፓሊሲ በአግባቡ ተቀርጾ፣ ይህንን በቋሚነት የሚሰራ ኣስፈጻሚ አካል ማደራጀት ዋነኛ የኢትዮጵያ የፓለቲካ ችግሮች መፍቻ ምትሃታዊ አቅም (ማጂክ ዋንድ) ወይም የብር ጥይት (ሲልቨር ቡሌት) እንዳለው ተደርጎ በጄነራሉ ሰፊ ትንታኔ የተሰጠበት አይነተኛ ምክንያትም ከላይ የተዘረዘሩትን ግቦች ለማስፈጽም እንዲረዳ ታስቦ ሊሆን ይችላል። በመሰረቱ የኢትዮጵያ ዋነኛ ችግር ራሱ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነው። አገዛዙ የሚያራምዳቸው ዘርፈ ብዙ ጸረ-ህዝብና ጸረ -ዲሞክራሲያዊ ተግባሮቹ  በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ችግሮች ዋነኛ ምንጭና ተዋናይ መሆኑን በገሃድ የሚያሳዩ ምስክሮች ናቸው። ለዚህም ነው ጄ/ል ጻድቃን በሰፊው ትንታኔ የሰጠበት የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፓሊሲ መኖር አለመኖር ወይም ይህን ፓሊሲ የሚከታተልና አማራጭ ሃሳቦችን የሚያቀርብ ቋሚ አካል መኖር አለመኖር ሕወሃትን ቀስፎ ከያዘውና ከሚያሰቃየው የውስጥ ደዌው ጋር እምብዛም ተያያዥነት የለውም ብሎ መከራከር የሚቻለው። ጄ/ል ጻድቃን “የፓለቲካ ችግሮች”  በሚል ጥቅል ሀረግ አደባብስው ያለፉዋቸውን ሕወሃት ሰራሽ የሆኑ ችግሮችን እንደሚከተለው ማቅረብ ይቻላል።

ዋናው የኢትዮጵያ የደህንነት ኣደጋ የሀቀኛ ዴሞክራሲያዊ ስርአት አለመኖር ነው። ትልቁ የደህንነት አደጋ የኢትዮጵያን የብሄር ችግሮች ፈትቷል ተብሎ ከጅምሩ ሕወሃት እንደ ትልቅ ስኬት ሲመጻደቅበት የቆየው ፌዴሬላዊ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ዴሞክራሲያዊም ፌዴራላዊም አለመሆኑ ነው! የህወሃትን ፍላጎት፣ የበላይነት፣ የዘረፋ፣ የኣድሎአዊነትና የዘረኝነትን ስርዓት ማስጠበቂያና ማስቀጠያ መሳሪያና ጭንብል ከመሆን በዘለለ የተባለውን ሐቀኛ ዴሞክራሲንም ሆነ ፌዴራሊዝምን እውን አለማድረጋቸው ነው።

ህወሃት መራሹ የኢትዮጵ እገዛዝ ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ በባርነት ቀንበር ውስጥ ጠፍንጎ ይዞ፣ ስልጣን ከላይ እስከ ታች ድረስ በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር አስገብቶ አይን ያወጣ ዘረፋ፣ ግድያና አፈና መፈጸሙና ማስፈጸሙ የህዝብና የዜጎች የዕለት ተዕለት ትእይንት የሆነባት አገር ናት ኢትዮጲያ!  ህዝቦቿ ባዶ እጃቸውን አደባባይ ወጥተው የመብትና የዴሞክራሲን ጥያቄ ባቀረቡ ቁጥር መልሳቸው በአጋዚ ቅልብ ጦርና በፌዴራል ፖሊስ  እንደ ጠላት በጥይት የሚቆሉባት፣ ዜጎቿ በጅምላ የሚታሰሩባት፣ የሚፈናቀሉባት፣ በየአመቱ በ10 ሚሊዮን የሚቆጠሩ ልጆቿ የሚራቡባት፣ በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለተሻለ ሕይወት ወደ ስደት ሲሄዱ በባሕር ላይ የዓሳ ነባሪ ቀለብ ሆነው የቀሩባት፣ እህቶቻችን የአረብ ገረዶች ሆነው ለወሲብ ጥቃት የተጋለጡባት፣ ከፎቅ ላይ እየተወረወሩና በፈላ ውሃ እየተቀቀሉ በየቀኑ ሬሳቸው ወደ አገር ቤት የሚጫንባት፣ ነዋሪዎቿ በቆሻሻ ክምር ናዳ የሚያልቁባት አገር ሆናለች ኢትዮጲያ!  ከዚህም በተጨማሪ ዜጎች የመኖር ዋስትና ተነፍጓቸው በሰላም ከቤታቸው ወጥተው በሰላም መግባት የሚችሉበት ሕይወት የሩቅ ዘመን ትዝታ ከሆነ ሰነባብቷል።  እንደ አሸን የፈሉ የስርዓቱ ሰላዮች እስከ ቤተክርስቲያንና መስጊድ ድረስ ሳይቀር ለመሰለልና አለመተማመንን ለመፍጠር  የተሰማሩባት፣ ዘረፋ፣ ውሸት፣ ሌብነትና ማጭበርበር ባህል የሆነበትና ሰዎችን እንደሸቀጥ የማዘዋወር ንግድ እየተንሰራፋ የመጣበት አስደንጋጭ ሁኔታም ተፈጥሯል። እነዚህና ሌሎች እዚህ ላይ ያልተዘረዘሩ ተወራራሽ ችግሮች ህወሃት በሚመራው አገዛዝ የተፈጠሩ ናቸው።

ጄነራል ጻድቃን በእድገትም፣ በዲፕሎማሲም ሆነ በሰላም ማስከበር ወዘተ በአለም ማህበረሰብ ዘንድ የሃገራችን ተቀባይነት ጨምሯል በማለት የህወሃትን አገዛዝ “ስኬቶች” እውቅና በመስጠት ችግሩ በዋነኛነት የውጪና የደህንነት ፖሊሲ ችግር ነው በሚል አገላለጽ  ለማድበስበስ ሞክረዋል። እንዲሁም ብጥብጥና ትርምስ የፈጠሩት የጸረ ሰላም ሃይሎች በቀጥታ ከሻዕቢያ ወይም በሻዕቢያ መንግስት አቀነባባሪነት የተፈጠረ ነው የሚል አንደምታ ያለውም ሃሳብ አስቀምጠዋል። በተለይም ደግሞ ጄነራሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ያነሳውን ተደጋጋሚ የመብትና የነጻነት ጥያቄ በሻዕቢያ ተላላኪነት የፈረጇቸው ሽብርተኞችና የጸረ ህዝብ ሃይሎች ሴራ አድርገው ለማቅረብ የሞከሩበት ሂደት በጣም አስገራሚ ነው።

የህወሃት ትግራዮች የበላይነት በሌሎች ህዝቦች ኪሳራ በኢኮኖሚ፣ በፓለቲካ፣ በወታደራዊ፣ በደህንነት ተቋማት ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ እንዲኖራቸው መደረጉና ይህም ኢፍትሃዊ አሰራር በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ የፈጠረው የበይ ተመልካችነት፣ የባይተዋርነትና የሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ስሜት በህዝቦች አብሮ የመኖር እድል ላይ አሉታዊ ጥላውን አሳርፏል። ይህም ጤናማና የተረጋጋ ማህበረሰብ ለዘለቄታው ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት ላይ የራሱን ሳንካ ማሳረፍ ብቻ ሳይሆን ህዝብ ለህዝብ፣ ብሄር ለብሄር በጎሪጥ ኣንዲተያይ፣ በተቃርኖ እንዲቆምና ወደ ግጭት ምናልባትም ፍጅት ወደሚያስከትል ደረጃ ያደርሰው እንደሁ እንጂ  የብሄራዊ ደህንነትን ወደሚያረጋግጥ፣ የሰላምና መረጋጋትን ዋስትና ወደሚያስቀጥል መንገድ ፈፅሞ ሊመራው አይችልም።

እጅግ ጥልቀት ያለው የደህንነት ፖሊሲ ተቀመረ አልተቀመረ ፋይዳ ቢስ ነው። መሰረታዊ ምክንያቱም ይህ ፓሊሲ ሊከላከላቸው የሚችሉ የደህንነት አደጋዎች መሰረታዊ ምንጫቸው የደህንነት ፖሊሲ አወጣለሁ የሚለው ራሱ ህወሃት የዘረጋው አምባገነናዊ፣ ዘራፊ፣ ዘረኛ፣ አድሎአዊ የአፓርታይድ መሰል ስርአት በመሆኑ ነው! ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል እንዲሉ ህወሃት ራሱ የሃገሪቱ ዋነኛ የደህንነት ስጋት ሆኖ ሳለ “በጥልቀት የተጠናና ምልእኡ የሆነ የሃገሪቷን የደህንነት ፖሊሲ አስፈጻሚ/አስተግባሪ ምሆኑ በጣም አስቂኝ ያደርገዋል። ጄነራሉም ቢሆኑ ህወሃትን የሃገሪቷ የደህንነት ስጋቶችና አደጋዎች የሚያመንጭ ኃይል ሆኖ ሳለ ራሱ መፍትሄ ብሎ የሚያስቀምጠውን የደህንነት ፖሊሲ ባለቤትና አስፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል መረዳት የገባዋል። በህወሃት የበላይነት የሚዘወረው አገዛዝ የሃገሪቷ ትልቁ የደህንነት ስጋትንና አደጋ ስለመሆኑ መካካድ አያስፈልግም። ጄነራል ጻድቃን ይህንን ሐቅ ጠንቅቀው የሚረዱት ይመስለኛል።

ከላይ እንደተጠቀሰው እጅግ ከባዱ የኢትዮጵያ የደህንነት አደጋ ህወሃት በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያንሰራፈው የትግራይ የበላይነት ወይንም የገዢ መደብነት ስርአት ነው። ይህም ስርዓት በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በመንግስታዊ ተቋማት፣ በመከላከያ፡ በደህንነት  “እንወክለዋለን የሚሉትን” የትግራይ የህዝብ ቁጥር ፈጽሞ የማይመጣጠን የአናሳ ብሔር አባላትን የተጠቃሚነት፣ የፈላጭ ቆራጭነት፣ ኢፍትሀዊ በሆኑ መንገዶች ለዘመድ አዝማዶቻቸው ሁሉ ሳይሰሩ በአንድ ጀንበር ባለሃብት የሚሆኑበትንና የሚከብሩበትን መንገድ በግልጽና በስውር ያመቻቸ እኩይ ስርዓት ነው። በሌላ በኩልም  በየእስር ቤቶቹ የሌሎች ብሄር ተወላጆች “አንተ አማራ፣ አንተ ኦሮሞ፣ አንተ  ጉራጌ. ሽንታም ” በማለት እያዋረዱ ትግሪኛ ተናጋሪ በሆኑ የሰርዓቱ ሰዎች የሚፈጸሙ እጅግ ዘግናኝ ግፎችና ሰቆቃዎችን እዚህ መዘርዘሩ ለቀባሪው ማርዳት ነው። የዚህ መጥፎ ስርዓት ሰላባ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሃያ ስድስት ዓመታት ያየው፣ የሰማው፣ የደረሰበትና ያንገፈገፈው የግፍ ዋንጫ ነውና! በብዙ መገለጫዎች የሕወሃትን የበላይነት፣ መሰሪነት፣ ስግብግብነት፣ ጭካኔ ማሳየት ይቻላል። ለዚህም ነው ህወሃት የሚዘውረው አገዛዝ ከመቼውም ጊዜ በላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የደህንነት ስጋትና አደጋ ተደርጎ የሚቆጠረው። ጄነራል ጻድቃን ይህን ራሱ ስጋት የሆነውን ሃይል ነው እንግዲህ ሃገሪቷን የሚያረጋጋና ከተደቀኑባት የደህንነት አደጋዎችም መጠበቅ የሚያስችል የደህንነት ፖሊሲ እንደሚያወጣና የፖሊሲው ይዘትም ምን መሆን እንዳለበት የተናገሩት!

የኢትዮጵያ ህዝብ በፍትህ ህይወቱን የሚመራበትን፣ የህግ የበላይነት በሰፈነበት ስርአት የሚዳኝበትን፣ ፍትሃዊ የሆነ የስልጣንና የሐብት ክፍፍል፣ ማህበራዊ ፍትህ  የሚሰፍንበትን ስርዓት ከምንም ጊዜውም በላይ ይናፍቃል። ዜጎች በነጻነት አብረው የሚኖሩባት ፣ የዘላቂ ሰላምና ደህንነት ዋስትና የተረጋገጠባት፣ ብዙሃኑ እየተራበ ጥቂቶች በጥጋብ የማያገሱባት፣ ማሕበራዊ ፍትህና ብልጽግና ለሁሉም አካባቢዎች በተግባር የሚተረጎምባትን ኢትዮጲያን ማየት ይመኛል። ሆኖም ከምኞት ባሻገር ለነኚህ የተቀደሱ ዓላማዎች መሳካት ዜጎች ሁሉ ከልብ ሊጨነቁባቸው፣ ብሎም በጽናት ሊታገሉላቸው የሚገቡ ግቦች መሆን አለባቸው። አሁንም እደግመዋለሁ!   ዛሬ  በኢትዮጳያ  ውስጥ የተንሰራፋው የሕወሃት ገዢ መደብ ሁሉንም በባለቤትነትንና በበላይነት  ይዞ በሚገኝበት እጅግ አስፈሪና አሳፋሪ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን።

ይህ ዐይን ያወጣ አድሎአዊና ኢፍትሀዊ የስልጣን፣ የሀብትና የጥቅም ክፍፍል ብሎም ይህ ክፍፍል የፈጠረው አስከፊ የሆነ ብሄሮች የጎሪጥ የሚተያዩበት ሁኔታ ሊካድ አይገባውም። እንደውም የብልህና አርቆ አሳቢ፣ ዘመን ተሻጋሪ፣ ባለራይና  የፓለቲካ መፍትሄ አመንጪነት መነሻ መሆን ያለበት ይህን መራር ሐቅ ከምንም በፊት አስቀድሞ በመቀበልና በመጋፈጥ መሆን ይኖርበታል።፡ ምክንያቱም ይህ ነባራዊ   ሁኔታ ለዘለቄታው የሕዝብ አብሮ መኖር፣ ሰላም፣ መረጋጋትና ባጠቃላይ ለሀገሪቱ ህልውና የሚያሰጋ ትልቁ  የደህንነት ፈተና  በመሆኑ ነው። እናም ይህንን  አደገኛ አካሄድ በትዕግስት፣ በጥበብና በቁርጠኝነት በመቀልበስ  የአገሪቱን ህልውና፣ የሕዝቦችን  በእኩልነትና በሰላም መኖር ለማረጋገጥ መጨነቅና መታገል ሲገባ ነው እንጂ ጄነራሉ እንዳነሱት ሃሳብ የችግሮቹን ዋና ምንጭ ትተው ጉዳዩን ከውጪና ደህንነት ፖሊሲ ጋር  በዋነኘት በማያያዝ አይደለም።አለባበሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ እንዳይሆን።

በኢትዮጵያ ውስጥ መጥቶ የነበረው የጸጥታ ችግር አስቀድሞ ሊታይ ይችል ነበር። በሰው ህይወት፣ በንብረት ላይ ጉዳት ሳያስከፍል፣ የጊዜአዊ ኣስቸኳይ ኣዋጅ ሳያስፈልግ ለመከላከል ይቻል ነበር። ሀገር ተናውጦ “በጊዜያዊ አስቸኳይ አዋጅ ነው የቆመው” ይላሉ ጄ/ል ጻድቃን!  እውን የመጣው የህዝብ ቁጣና አልገዛም ባይነት የፖሊሲ አለመኖር ወይንስ የሕወሃት/ኢህአዴግ ፖሊሲዎች ጸረ-ህዝብነት ያመጡት ነው ብሎ ለጠየቀ ሰው መልሱ ግልጽና ግልጽ ሆኖ ይታየዋል። በተለያዩ ጊዜያት የተተገበሩ የህወሃት ፓሊሲዎች ያመጡት ድርብርብ ችግሮች መሰረቱ የስርዓቱ ጸረ- ዲሞክራሲያዊና ጸረ- ህዝብነት መሆኑ ላይ ነው። ሌላ ምንም ሚስጥር የለውም! ይህን መሰረታዊ ችግር በደህንነት ፖሊሲ ምሉዕነትና አፈጻጸም ያለመኖር  የመጣ ችግር ነው ብሎ ለማቅረብ መሞከር ሃገሪቱ አሁን የገባችበትን ቅርቃር በሚገባ ባለመገንዘብ ወይንም ኃላፊነት በጎደለው መንፈስ ሆነ ተብሎ ለራስ በሚሰላ ጥቅም አማካኝነት ችላ የማለት ጉዳይ እንደሆነ ተደርጎ ነው የሚወሰደው።

ጄ/ል ጻድቃን የስርዓቱን ዝቅጠት “የውስጥ የፓለቲካ ችግር” ሲሉ በደምሳሳው ቢገልጹትም የሀገሪቱን የፓለቲካ ችግሮች ዋና ዋና ገጽታዎች ከዚህ በፊት በጻፉት ጽሁፍ በስሱም ቢሆን እንደገለጹት በዚህኛው ቃለ ምልልሳቸው ሊገልጹና ሊዘረዝሩ አልደፈሩም። መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄዎችና ከላይ የተዘረዘሩት እውነታዎች የሚቀየሩበት መሰረታዊ ለውጦች እስካልመጡ ድረስ “የህዝብ የአስተሳሰብ አንድነት” ሊመጣ ከቶም አይችልም። በሀገሪቱ የሚገኙ ችግሮች ስርአቱ የወለዳቸውና ያሳደጋቸው እንደመሆናቸው መጠን በዚህ ስርአት የህዝብ ጥያቄዎች መልስ ሊያገኙ እንደማይችሉ ያለፉት ሃያ ስድስት አመታት ስለ ስርአቱ ማንነትና ምንነት ብዙ አሳይቶናል፤ ብዙም አስተምሮናል። በዚህ ረዥም ሂደት ውስጥ ህወሃት ይበልጥ ከህዝቡ እየተነጠለ ዛሬ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የስርአቱን መውደቅ የሚናፍቅበት ሁኔታ ውስጥ ይገኛል። ህወሃት የህዝቡን የአስተሳሰብ አድማስ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ለመምራት ቀርቶ የራሱንም ህልውና ለማቆየት ከማይችልበት አዘቅት ውስጥ መግባቱን ለማሳየት  ብዙ መድከም የሚያስፈልግ አይመስለኝም። እንዳውም ዋናው ጥያቄ መሆን ያለበት ““ሕወሃት የወደቀበት አዘቅት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ በሕይወት ይቆይ ይሆን?” የሚለው ይመስለኛል።

በመቀጠልም አሁንም ትልቅ የደህንነት አደጋ  “እያረገዘ ያለ ሊኖር ይችላል” ይላሉ ጄ/ል ጻድቃን። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እነዚህ የተረገዙ ችግሮች የፖለቲካ ስርዓቱ መሰረታዊ ለውጥ እስካላመጣ ድረስ መፈንዳታቸው አይቀሬ ነው። ለማርቀቅና ለማጸደቅ ውይንም ለማሻሻል እያሰቡት ያለው የደህንነት ፓሊሲ ይህን የለውጥ ሱናሜ ሊያቆመው ከቶም አይቻለውም። ሌሎች የስርአቱ ፓሊሲዎች ሁሉ የሚመነጩት ከዚህ የህወሃት መለያ ከሆኑት ስግብግብነቱ፣ ጸረ ዲሞክራሲያዊና ጸረ ህዝብ ባህሪያቶቹ በመሆኑ ነው።”መከለስ ያለበት” የውጪና የደህንነት ፖሊሲም ከህወሃት ጸረ ህዝባዊነትና ጸረ ዲሞክራሲያዊነት የሚመነጭና የስርአቱን እድሜ ለማራዘም ተብሎ የሚቀመር በመሆኑ ከመነሻው ጄነራል ጻድቃን እንደተመኙት የችግሮቹ መፍትሄ ሆኖ ሊመጣ አይችልም።

መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄዎች በመሰረታዊ ለውጦች እስካልተመለሱ ድረስም “የህዝብ የአስተሳሰብ አንድነት” ሊመጣ አይችልም። የሀገሪቱን ዘርፈ ብዙ የፓለቲካ ችግሮች ለመፍታት የማይፈልግ፣ ይህን ካደረግኩ ስልጣኔን አጣለሁ በሚል ስሌት ዘረኛና አምባገነን የሆነውን የህወሃት የፓለቲካና ኢኮኖሚያዊ የበላይነት ለማስቀጠል የሚተጋ፣ በተንኮልና በመሰሪነት እንዲሁም በጭካኔው የተካነ መሆኑ የተረጋገጠለት ስርዓት የአገሪቱን የጸጥታና የደህንነት ችግሮች ለዘለቄታው ሊፈታ የሚችል ሃይል ሊሆን አይችልም።ከገለማ እንቁላል ጤናማ ጫጩት አይፈለፈልም እንዲሉ! ራሱ የሃገሪቷ የደህንነት ስጋት ስለሆነ ከማንም በላይ የችግሮቹ ምንጭና መንስኤ ነው!

አርበኞች ግንቦት 7ም ሆነ ኦነግ እንዲሁም ሌሎች ጄ/ሉ ያልጠቀሷቸው ሃይሎች ህልውና መሰረት በሃገር ውስጥ ህወሃት የፈጠራቸው ሁኔታዎች፣ ጸረ ህዝብነቱና ጸረ ዴሞክራሲያዊነቱ፣ ራሱ ያወጣውን ህገ-መንግስታዊ መብቶች በተደጋጋሚ በመርገጥ ስላማዊ ህጋዊ ትግልን ለማድረግ ፈጽሞ በማይቻልበት ደረጃ የፖለቲካ ምህዳሩን በማጥፋቱ እንጂ እነዚህን የፓለቲካ ሃይሎች ሚረዱ ሁሉ፡  ኤርትራን ጨምሮ ስለፈለጉ ሊሆን አይችልም። ጭቆና ባለበት ጭቆናን የሚታገሉ ሃይሎች መኖራቸው ተፈጥሯዊ እውነታ ነው። የነዚህን ሃይሎች ተጽዕኖ ለመቀነስና ጨርሶውኑ ለማጥፋት የደህንነት ፖሊሲ አይነቶች ቢደረደሩ ምንም የሚፈጥረው ፋይዳ የለም። የነዚህ ሃይሎች የህልውና መሰረት ስርዓቱ የፈጠራቸው ዘርፈ ብዙ “የፖለቲካ ችግሮች“ ናቸው። የስርዓቱ ጸረ ህዝብነትና ጸረ ዲሞክራሲያዊነት እስካለ ድረስ በየፊናው የሚደረገው ትግል እያደገና እየሰፋ እንደሚሄድና ህዝቡ ከዚህ አስከፊ ቀንበር ነጻ ለመውጣት ምንም አይነት መስዋዕትነትን ከመክፈል ወደኋላ እንደማይል ጄኔራሉ የሚጠፋቸው አይመስለኝም።

(ይቀጥላል)

ነጻነት ቡልቶን ቀጥሎ ባለው የኢሜልና ፌስቡክ አድራሻ ማግኘት ትችላላችሁ

Netsanetbulto2017@gmail.com

https://www.facebook.com/netsanet.bulto.58

 

The post ሌ/ጄነራል ጻድቃን ፣ ህወሃት ፣ ኤርትራ እና ቀይ ባህር – በነጻነት ቡልቶ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የትግሬ ወያኔዎች አዲስ አበባን ለኦሮሚያ አስተዳደር ለማስረክብ ረቂቅ አዋጅ በሚኒስትሮች ምክርቤት መፅደቁ ታወቀ

$
0
0

ሰበር ዜና፡ የትግራይ ወያኔዎች አዲስ አበባን ለኦሮሞዎቹ በይፋ ሰጡ!

የትግሬ ወያኔዎች አዲስ አበባን ለኦሮሚያ አስተዳደር ለማስረክብ ረቂቅ አዋጅ በሚኒስትሮች ምክርቤት መፅደቁ ታወቀ

The post የትግሬ ወያኔዎች አዲስ አበባን ለኦሮሚያ አስተዳደር ለማስረክብ ረቂቅ አዋጅ በሚኒስትሮች ምክርቤት መፅደቁ ታወቀ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


The Gulf crisis and the spiral in anti-Qatar’s hypocrisy

$
0
0

 

 Zecharias Zelalem, Special to Addis Standard

Addis Abeba, June 27/2017 – Although some experts say there was bound to be a head on collision within the Gulf States sometime in the not too distant future, the speed in which the recent diplomatic crisis unfolded has caught many off guard. It began on June 05 when Saudi Arabia, with the backing of Egypt, Bahrain and the UAE, abruptly severed diplomatic ties with Qatar accusing it of sponsoring terrorism and destabilizing the Gulf region.  Although the Gulf States have in the past frequently found themselves at odds for one reason or another, it was clear from the get go that the recent crisis was no ordinary spat amongst cousins.

Qatar, which over the past several years worked so hard to solidify itself as a regional peacemaker and a diplomatic channel for disenfranchised states such as Eritrea, has all of a sudden seen its hard work trashed in a matter of hours. Everything, from allegations of supporting Israel and Iran, to accusations of funding terrorist organizations, has seen Doha scramble to defend its reputation. It happened fast, so fast that Qatari officials who retired for the night as honored dignitaries on June 04 woke up the next morning and found themselves surrounded by their once friendly neighbors turned snarling wolves gnashing their teeth at them.

Not as spontaneous as it looks

For those who closely follow political events in the Gulf States, it is quite evident that this was no spontaneous outbreak of rage.

First, let’s dissect the official explanation given by Riyadh. Qatar’s alleged funding for “terrorist organizations.” This long standing allegation has stirred up strife and civil war in several conflict hotspots, meriting the globe’s condemnation against Qatar for the sake of the peace seeking people of the Middle East, Asia and Africa. With most mainstream media outlets hesitating to go into detail with what is referred to as “terrorism,” the Saudis seem successful in dominating the narrative that Qatar is the main financial backer of what is arguably the most influential terrorist group, Daesh (aka ISIS).

A good deal of the outrage against Qatar among social media users in the west is born of the assumption that evidence linking Qatar to the Raqqa based “caliphate” was recently unearthed, triggering the standoff.  But this isn’t true. Qatari state funding of Daesh is as of yet unverified by independent sources and cannot be taken as fact. Despite rumors of wealthy Qataris openly funneling money to the group and facing no repercussions for it at home, no high level diplomat has produced an evidence beyond a reasonable doubt implicating Qatar’s attempt of directly aiding Daesh financially or militarily.

 Hamas: Much ado about nothing   

At a press conference in Paris, Saudi Arabia’s Foreign Minister Adel Al-Jubeir added a further demand for Qatar, this time, to end all support for the “extremist groups undermining the Palestinian Authority and Egypt,” namely Hamas and the Muslim Brotherhood.

Saudi Foreign Minister Adel al-Jubeir, speaks during a joint new conference with U.S. Secretary of State John Kerry, at Riyadh Air Base in Saudi Arabia, Thursday, May 7, 2015. Kerry sought to secure a pause in Yemen's war after he arrived to Saudi Arabia to meet with the king and other top officials, citing increased shortages of food, fuel and medicine that are adding to a crisis that already has neighboring countries bracing for a mass exodus of refugees. (AP Photo/Andrew Harnik, Pool)

                      Saudi Arabia’s Foreign Minister Adel Al-Jubeir    (AP Photo/Andrew Harnik, Pool)

However, Qatar’s alleged support of the likes of Hamas can by no means be what triggered the recent Gulf crisis. For starters, Qatar made no secret of its official recognition of Hamas for years. The militant group’s leader Khaled Meshal recently choose Doha to announce Hamas’s new political charter. Several high ranking Hamas officials have also met with Qatari diplomats and leaders, including the former Emir Hamad bin Khalifa.

Hamas Khaled Meshaal

Hamas leader Khaled Meshaal announced a new policy document in Doha, Qatar, on May 1, 2017. Photo: Reuters

This well known liaison between Qatar and Hamas was by no means a new phenomenon. Nor is Qatar the sole provider of funds and resources for Hamas and/or its military wing. In fact, it the beginning of the 2000s, Saudi Arabia, not Qatar, was widely known to have been the principal financier of Hamas. Hamas’s claims to adhere to Sunni Islam virtues meant that Riyadh sought to bring them under their wing and away from the influence of Iran, which, despite being a majority Shia Muslim nation, also sought to support Hamas.

According to American research group Stratfor, Saudi’s support for Hamas diminished in the wake of the latter’s act of taking open responsibility for the campaign of terror waged against Israel as a part of the “Second Intifada” conflict of the 2000s. Under pressure from the likes of the United States, Riyadh began scaling back their support of Hamas. Nevertheless, Hamas continued to enjoy support from several other wealthy donors and governments from Kuwait to Jordan, Syria and Iran as well as Qatar and Saudi Arabia. It would be quite difficult to name a single Arab or majority Muslim country in the region that hasn’t at one point or another, offered support to Hamas.

The Saudi Foreign Minister’s reference of Hamas as “terrorists” in the wake of the latest Gulf crisis therefore holds no water. Supporting Hamas is hardly a lone Qatari initiative, nor was it ever openly referred to as a “terrorist” organization by most leaders in the Gulf States.

Muslim Brotherhood charge bogus in nature

As for accusing Qatar of supporting the Muslim Brotherhood, it is not, once again, a new phenomenon that the Egyptian based Muslim Brotherhood enjoys recognition and support by the state of Qatar, which has chosen to shelter many of its members in the wake of President Abdel Fattah Al-Sisi’s crackdown against the organization since 2014.

Although have hesitated to do the same as Qatar in supporting the Muslim Brotherhood, Egypt’s  efforts to get a universal support in having the group designated as a terrorist organization haven’t bore fruition for the most part. As such, the Muslim Brotherhood has only been declared a terrorist organization by the governments of Bahrain, Russia, Saudi Arabia, Syria and the UAE. To Egypt’s continued disdain, the exiled members of the Muslim Brotherhood operate a website based in London and even have a certified Twitter page, much to the chagrin of hordes of Egyptian Twitter users. Partly owing to its 2012 ascendance to power through free elections, global condemnation against the Muslim Brotherhood will probably be extremely slow to come by, too.

Qatar’s funding of the Muslim Brotherhood is not therefore the collective reason that led the Saudi camp to cut diplomatic ties and implement a blockade against Qatar; but they all have their own different reasons and none of them involve “regional destabilization.”

Egypt’s grudge against Qatar goes back to 2013

Most media outlets were quick to point fingers at President Donald Trump’s recent trip to the Middle East and his meetings with a host of leaders as the key trigger of the current Gulf crisis. For instance, Germany’s Foreign Minister Sigmar Gabriel referred to the diplomatic buildup against Qatar as a “Trumpification of the Qatar-GCC dispute”.  Indeed President Trump assumes his own share of responsibility for creating the tension and fostering division amongst the traditionally allied Gulf States.

Germany’s Foreign Minister Sigmar Gabriel

Germany’s Foreign Minister Sigmar Gabriel believes“Trumpification” is at play. Photo: Press TV

But what should not ignored is the fact that long before June 05, Egypt had maintained a firm anti-Qatar stance, stemming from Qatar’s official disapproval of the 2013 overthrow of the Muslim Brotherhood party leader Mohammed Morsi from his position as Egypt’s President. Egypt has also blocked broadcasts of Al Jazeera from the country since August of 2013, accusing it of bias and defamation.  Although both Egypt and Qatar form part of the Saudi led anti Houthi coalition of the war in Yemen, and both are major co-financiers of oil pipelines in the Red Sea, President Al-Sisi has long been working to turn the region against Qatar .

Al-Sisi vs Trump: A friendship with benefits

Egypt may have played the most crucial role in executing the hostilities against Qatar by obtaining the support of the United States. Al-Sisi and Trump have a well established friendship that goes beyond the normal state protocol. Trump had had a sit down with Al-Sisi in New York already in September 2016. The Trump campaign released a communiqué at the time in which candidate Trump made promises that “under a Trump Administration, the United States of America will be a loyal friend, not simply an ally that Egypt can count on in days and years ahead”. Trump’s America may have just made good on that promise. President Trump has also expressed his personal admiration for his Egyptian counterpart. “I have been close to him since the first time we met. We agree on so many things. This has been the perfect opportunity President Al-Sisi this has been waiting for.

 But the US has no reason to go after Qatar

Few days after Qatar’s diplomatic crisis, Trump told journalists that “the nation of Qatar, unfortunately, has historically been a funder of terrorism at a very high level”. When one considers the fact that candidate Trump had never publicly admonished Qatar throughout his campaign, which was fraught with pledges to get rid of terrorist organizations, this statement comes as rather a surprise. Bear in mind that Qatar was also not among the seven mainly Muslim countries included in president Trump’s infamous travel ban, popularly named as “Muslim ban.” To make matters more complicated Qatar was an active participant in the war against the Houthis in Yemen, a position endorsed by the United States. It also hosts USCENTCOM, a US military base, going a step farther than many countries in the region when it comes to accommodating America’s foreign policy manoeuvring. The Al Udeid Air Base in the country is still jointly operated by Qatar and the US as part of the larger effort to combat terrorism.

This fact strengthens explanations that president Al-Sisi has effectively twisted president Trump to submit to his will regarding Qatar. But unlike president Al-Sisi, Uncle Sam has no plausible excuse for going after Qatar. President Al-Sisi is may be in for a further disappointment because the US is less likely inclined to name the Muslim Brotherhood a terrorist organisation; far less likely to take actions against its members based in America. To this end, exactly what the US expects to get in return for aligning itself with Egypt in the Qatar’s diplomatic crisis is not clear.

 Seething sectarian Saudis seek Shia solution

This brings us back to Saudi Arabia. It is not hard to realize that Qatar’s rapprochements with Iran, fake news or not, only served to intensify suspicions that Qatar doesn’t maintain the same anti-Shia Muslim stance that the royalty in Riyadh strongly adhere to. Qatar had initially provoked the ire of Saudi Arabia in the aftermath of the January 2016 storming of Saudi embassy offices in Iran. The main embassy in Tehran was among those attacked by mobs protesting the Saudi government’s execution of a Saudi Shia Sheikh Nimr Baqir Al-Nimr. The offices were ransacked and set ablaze by hundreds of angry Iranian demonstrators. There weren’t any casualties as no staff or embassy personnel were present. But the incident left a sour taste in the mouths of Saudi Arabia. A day later, Foreign Minister Al-Jubeir announced that his country was severing all ties with Iran and gave Tehran 48 hours to evacuate all of its diplomats from the Kingdom. Saudi Arabia and Iran have always been at odds due to the Sunni-Shia divide. For far too long, Saudi Arabia sought to politically isolate Iran much like the way it is doing to Qatar today. They called on all their allies to cut ties with Tehran. The likes of Bahrain did so promptly while African nations Somalia, Sudan and Djibouti soon followed suit. But in the aftermath of the embassy blaze, there was one nation that refrained from totally cutting Iran off: Qatar.

Although Qatar had temporarily recalled its ambassador from Tehran and condemned the defiling of the sanctity of an international embassy by Iranian rioters, it was among the last to issue a statement condemning Iran, which didn’t go unnoticed in Riyadh. Qatar’s envoy to Iran eventually returned and all appeared to return to normal again between the two, further irking the house of Saud [19]. Qatar’s reluctance to support a decisive action against Iran appears to have been taken as lack of will to actively participate in diminishing Shia influence in the region, which is Saudi Arabia’s central demand from all its allies.

 Hacking, “Fake News” and all

With tension building up throughout most of 2016, the hacking on May 23 of the Qatar News Agency and a subsequent release of a news that Qatar firmly asserted was “fake news” is now seen as the last straw that broke the camel’s back. Among other stories, the news item allegedly quoted Qatar’s Emir Tamim bin Hamad Al-Thani as saying Iran was an “Islamic power.” Expressing open admiration for Iran puts one in the crosshairs of Riyadh. Qatar, already under scrutiny for its decision to maintain its consular services in Tehran, was presented as having crossed the red line. The Saudis, who by this stage must have already confided their intentions with Egypt to take decisive action against Qatar, knew there would be no turning back now.

Hackerson May 23,  Qatar’s News Agency was targeted Russian hackers, according to the FBI 

Although the FBI sent a team of investigators to Qatar and it is now widely believed that the Qatar News Agency had been hacked by Russian hackers when the statements were published, the Saudi camp didn’t seem to reverse the course of its diplomatic assault against Qatar.               

It’s about Al Jazeera: A Qatari weapon of mass disruption

On Friday June 23, Saudi Arabia and co. have issued a list of 13 demands that Qatar should meet in just 10 days if it wanted a return of normalcy. Among the sweeping demands was the complete shutdown of the Al-Jazeera news network. Although this demand is now tabled officially, Egypt and Saudi Arabia have long wanted Qatar to stop transmissions of the Doha based news channel, which is widely accepted by millions of its viewers around the world as the most successful disruptive media. Al-Jazeera’s coverage of the Arab spring has undoubtedly sent chills through several Arab countries, most notably Egypt; however, the latest rage appeared to be over Al Jazeera’s decision to publish emails of the Emirati ambassador to the US, Yousef Al-Otaiba, showing details of a communications between the ambassador and Israeli lobbyists.

Al Jazeera is widely credited for bringing the Arab Spring to the television screens of millions of people around the world. The network has particularly given extensive coverage of the political dynamics in post-Mubarak Egypt and the government’s misdealing and bloody crackdowns on civilian protesters. More importantly, Al-Jazeera news network has brought immense disruptions within the Arab world, shattering long established narratives of patriarchal autocracies the region is known for.  Demanding the shutting down of the network is therefore nothing but an attempt to prevent millions of people living in the Arab world from questioning and holding power accountable.  It has nothing to do with the alleged accusations of Qatar’s sponsorship of terrorism.

Funding Terrorism is a regional problem, not just a Qatari problem

When it comes to the problems of funding terrorism, Saudi Arabia finds itself among nations with an extensive track record. A Wikileaks release of emails between former US Secretary of State Hilary Clinton and her former campaign manager John Podesta revealed their belief that the likes of Daesh are thriving on consistent sources of revenue coming from members of the Saudi government, or wealthy Saudi businessmen.

In 2006, a UN Security Council report published revealed that Qatar, Egypt and Saudi Arabia were among several nations providing weapons and funds for Somalia based Union of Islamic Courts, an Al Qaeda linked terrorist group that had captured parts of Somalia’s capital Mogadishu earlier that year. These facts indicate that funding terrorism is used as de facto diplomatic arm twisting between several regimes in the Gulf.  It is therefore certainly not up to Saudi Arabia and Egypt to look down condescendingly upon Qatar accusing it of funding terrorism when both are far from being model nations to the contrary. Power, personal feuds, the age old Shia-Sunni sectarian divide and vengeance are what have fueled the current diplomatic crisis in the Gulf. The upping of the ante by Riyadh and Cairo is hypocritical; America’s flagrant and inconsiderate involvement is a flat out mockery; and Qatar’s fate of being ostracized as the black sheep in the neighborhood is outright farcical.

UNSC

Three weeks into the crisis, many are hoping the tension will subside as influential third party states, most notably Kuwait, are trying to bring everyone back to the negotiating table. However, any hope for a diplomatic solution was thrown into the fray where the Saudis and its bloc came up with unrealistic demands that should be met by Qatar.  If anything, the 13 points of sweeping demands are an indication that the Saudi bloc will continue to bribe, brownnose and intimidate more players into adopting similar stances, sending unto the unknown any sense of morality in solving the crisis though diplomatic means.

Whether we realize it or not, in the long run the free world will end up paying the price if it silently watches Qatar continued to be bullied into total submission. AS

The post The Gulf crisis and the spiral in anti-Qatar’s hypocrisy appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና አቶ ሸፈራው ሽጉጤ በዘረጉት የሙስና ሰንሰለት ከፍተኛ ገንዘብ እየመዘበሩ መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ

$
0
0

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና አቶ ሸፈራው ሽጉጤ

ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ሸፈራው ሽጉጤ በዘረጉት ከፍተኛ የዝርፊያ ሰንሰለት በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ መዝረፋቸውን ከአስተማማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ አመልክቷል። የምንጮቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል፣ ምረመራውን ያካሄደውን የኦዲት ክፍል ለመግለጽ ባንችልም፣ መርምራውን የካሂዶት ኦዲተሮች ግማሾቹ ማስፈራሪያ ደርሶአቸው ስራቸውን ለቀዋል።

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደቡብ ክልሉ ወንዶ ኢንዶውመንት ኩባንያዎች በየቀኑ ከ50 ሺ ብር በላይ ገንዘብ ይቀበላሉ። ወንዶ ድርጅት ከደቡብ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚሄደውን ጫት ቀረጥ እንዲሰበስብ ስልጣን የተሰጠው ሲሆን፣ በየኬላዎቹ ጫት ጭነው ከሚመጡ መኪኖች በኪሎ ግራም ለቀረጥ ለኮቴና ለተለያዩ ወጪዎች በሚል 11 ብር ይቀበላል። አንድ መኪና በአማካኝ እስከ 5 ሺ ኪሎ ግራም ጫት የሚጭን በመሆኑ፣ በመኪና እስከ 55 ሺ ብር ከፍያ ይፈጸማል።
ወንዶ ድርጅት ለመንግስት የሚያስገባው በቀን 60 ሺ ብር ሲሆን ይህም ከአንድ መኪና ጫት ከሚገኘው ገቢ ጋር ተመጣጣኝ ነው። በእየቀኑ እስከ 20 መኪና ጫት የሚቀረጽ ሲሆን፣ በቀን እስከ 1 ሚሊዮን 100 ሺ ብር ይሰበሰባል።
አዲተሮች በ2005 ዓም ባደረጉት ምርመራ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አለመሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን፣ ኦዲተሮቹ መቀሌ ለስልጠና ትፍለጋላችሁ ተብለው ከተጠሩ በሁዋላ ፣ በስፍራው በተገኙት የደህዴን ባለስልጣናት ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። የኦዲተሮች ሪፖርትም ይፋ እንዳይደረግ ተደርጓል። ከ2005 ዓም በሁዋላ ወንዶ ከጫት የሚሰበስበው ገንዘብ በቀን 110 ሺ ብር የደረሰ ሲሆን፣ ለእነ አቶ ሽፈራው የሚተላለፈውም ገንዘብ በዛው ልክ ከፍ ብሎአል። ስራውን የሰሩት ኦዲተሮች ከማስጠንቀቂያው በሁዋላ ስራቸውን በመልቀቃቸው ከ2005 ዓም ወዲህ ያለውን የገንዘብ መጠን ለማወቅ አይቻልም።
ኦዲተሮች ከአዋሳ ይልቅ መቀሌ ለምን እንደተጠሩ እስካሁን ባያውቁም፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩ ከደቡብ እስከ ትግራይ የተዘረጋ መሆኑን እንዳመላከታቸው ያምናሉ። አቶ ሽፈራው በራሳቸውና በዘመዶቻቸው በኩል የያዙዋቸው የንግድ ድርጅቶች ከፍተኛ ሲሆኑ፣ ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር በፈጠሩት ከፍተኛ የጥቅም ቁርኝት አንድም ቀን ጥያቄ ቀርቦባቸው አያውቅም።
ሌላው የደቡብ ክልልን ሲመሩ የነበሩት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝና ቤተሰቦቹ በታናሽ እህታቸው የተሰየመ ቤትሄሌም ሶሊዳሪቲ የሚባል የጤና ሙያተኞች ማሰልጠኛ ተቋም የመሰረቱ ሲሆን፣ ሃዋሳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን ኦዲት ባደረገበት ወቅት፣ 24 ሚሊዮን ብር ገንዘብ ተገኝቶበታል። የኦዲት ምርመራው ሃዋሳ በሚገኘው የጉምሩክ ሃላፊ ትእዛዝ ይፋ እንዳይሆን የተደረገ ሲሆን፣ ምርመራውን ያካሄዱት 3 ሰራተኞች ከስራ ተባረዋል።
በክልሉ የሚፈጸመው ሙስና ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን የሚገልጹት ምንጮች፣ በተለይ በመሬት ሽያጭ ባለስልጣናቱ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እየመዘበሩ ነው። ከላይ እስከታች ያሉ የክልሉ ባለስልጣናት የሙስና ሰንሰለት በመዘርጋታቸው አንዱ ሌላውን ለመጠየቅ አቅም እንደሌለው የመረጃው ምንጮች ገልጸዋል።

The post አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና አቶ ሸፈራው ሽጉጤ በዘረጉት የሙስና ሰንሰለት ከፍተኛ ገንዘብ እየመዘበሩ መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Spotlight: Marcus Samuelsson Brings Red Rooster to London

$
0
0

By Tadias Staff
June 27th, 2017
New York (TADIAS) — Chef Marcus Samuelsson has expanded his popular Harlem restaurant business across the pond, opening a new Red Rooster in London late last month. The restaurant, which is housed inside the elegant Curtain Hotel in the East London neighborhood of Shoreditch, is the first Red Rooster location outside of New York City.

As Bloomberg News points out: “Red Rooster became a hit in Harlem thanks to chef Marcus Samuelsson’s take on Southern comfort food — and became internationally famous because former President Barack Obama was a huge fan. He even held a fundraiser there. The first foreign outpost of Red Rooster opens at the new Curtain Hotel in London’s hip Shoreditch neighborhood. About half the menu will be the same as the New York location: There will still be chicken ’n waffles for £10 ($13), fried yard bird (£19) and the Obama short ribs (£33), a recipe fit for a president. But he’s using some local ingredients and adding dishes to reflect his background, such as Uncle T’s herring (£8). Plus, there will be a taqueria called Tienda Roosteria.”

Why London?

The Ethiopian-born, Swedish-raised celebrity chef and author says that like New York he is attracted to London for it’s multiculturalism. “New York is a world city, and so is London, but London has a different kind of diversity than New York and I thrive off that,” Marcus told The Globe and Mail. “We wanted to find a neighbourhood that matched the excitement of Harlem, and felt that Shoreditch and London, as a town, really matches New York.” He added: “It has incredible mystique, funk and coolness. I’ve been asked to open a new Red Rooster every week for the past four and a half years, and I always say no. When you walk into the restaurant, the first thing you’ll see is a taqueria inspired by the barrio. We have a huge Latin community in east Harlem.”

“Samuelsson, 46, became a star early in his career more than two decades ago,as he earned a three-star review from The New York Times as the chef at Aquavit. Now his brand and marketing empire has expanded to restaurants in Bermuda, Sweden, and Norway, and he’s a regular on shows such as Chopped and Iron Chef America.”

The post Spotlight: Marcus Samuelsson Brings Red Rooster to London appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.

ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ክልል ላይ ያለውን መብት የተመለከተው ረቂቅ አዋጅ በሚኒስትሮች ም/ቤት መጽደቁ ተነገረ

$
0
0

ኢሳት (ሰኔ 20 ፥2009)

ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን መብት የተመለከተው ረቂቅ ኣዋጅ በሚንስትሮች ም/ቤት መጽደቁ ተሰማ። በቀጣዩ ሳምንት ፓርላማ ቀርቦ እንደሚጸድቅም ይጠበቃል።

ከሳምንት በፊት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተወያይቶ ያሳለፈው ይህ ረቂቅ ኣዋጅ አዲስ አበባ የሚባለው የከተማው ስያሜ በነበረበት እንዲቀጥል ፊንፊኔ የሚለውም መጠሪያ በተጨማሪነት እንዲያገለግል ወስኗል።

በሚኒስትሮች ም/ቤት ማክሰኞ እለት የጸደቀው ረቂቅ አዋጅ ኦሮምኛ ከአማርኛ ጋር በአዲስ አበባ ከተማ የስራ ቋንቋ እንዲሆን የፈቀደ ሲሆን የአከባቢ መጠሪያ ስሞች እንደአስፈላጊነቱ ወደ ቀድሞ ስማቸው እንደሚመለሱም አስፍሯል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሰራተኞች የሆኑና ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ እንደ አዲስ አበባ መስተዳድር የመንግስት ሰራተኞች ጋር መኖሪያ ቤቶችን የሚያገኙበትን መብት ይሰጣል።  የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለመንግስታዊና ማህበራዊ ተቋማትና ሌሎች ቦታዎችን ከሊዝ ነጻ እንዲያገኙ የሚፈቅደው ይህ አዋጅ የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ለኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች ውሃን የማድረስ አና የመሳሰሉ መብቶችን የሚሰጥ ሲሆን በፊንፊኔ ዙሪያ ያሉ የኦሮሚያ ዞኖች ውስጥ ውሃን የማመንጨትና ደረቅ ቆሻሻን የማስወገድ ስራዎችም በጋራ እንደሚሰራም ተመልክቷል። የትራንስፖርት አገልግሎት አውቶቡስና ባቡርን ጨምሮ በአዲስ አበባ ዙሪያ ላሉ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞኖች የአዲስ አበባ መስተዳደር እንዲያቀርብም በህጉ ላይ ተመልክቷል።

በአዋጅ የተቀመጡትን መብትና ጥቅሞች በተመለከተ ለማስፈጸም ከአዲስ አበባ መስተዳድርና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጣ ም/ቤት እንደሚመሰረት የተገለጸ ሲሆን ይህ የጋራ ም/ቤት ተጠሪነቱ ለፌደራሉ መንግስት እንደሚሆንም ማክሰኞ ሰኔ 20/2009 በሚኒስትሮች ም/ቤት የጸደቀው አዋጅ ይደነግጋል። ይህ አዋጅ በስራ ላይ የሚውለው በቀጣዩ ሳምንት በፓርላማ ቀርቦ ከጸደቀና በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ከታተመ በኋላ እንደሚሆንም መረዳት ተችሏል።

ቀደም ሲል በረቂቁ ላይ በዝርዝር ቀርበው የነበሩ ጉዳዮች  በአዲሱ ወይንም በሚኒስትሮች ም/ቤት በጸደቀው ላይ መታለፋቸውንም መረዳት ተችሏል።

The post ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ክልል ላይ ያለውን መብት የተመለከተው ረቂቅ አዋጅ በሚኒስትሮች ም/ቤት መጽደቁ ተነገረ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

እነ ለገሰ ወ/ሃና የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው!!! – ነገረ ኢትዮጵያ

$
0
0

በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ የዓቃቢ ህግ ምስክሮች ሳይቀርቡ ቀሩ!!!
(በሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)
በሶስት መዝገቦች ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው 49 ሰዎች ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ቀረቡ፡፡
፨ሁለት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አባላትን ጨምሮ አስር ሰዎች በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ፣38 እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 3/1/ እና/4/ ስር የተመለከተውን በመተላላፍ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ከሚገኙ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት ጋር የትጥቅ ትግል እናካሂዳለን በሚል ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ እጃቸው እስከተያዘበት 2009 ዓ.ም ድረስ በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ ከሚገኙ በህቡዕ ከሚንቀሳቀሱ አባሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ለአመፅ ለማነሳሳት የሽብር ተልዕኮና የገንዘብ ድጋፍ በመቀበል የጦር መሳሪያ ቦንብ እና ሌሎች ቁሳቁሶች በመግዛት በተለያዩ ጊዚያት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በመፈፀም የሰው ህይወት እንዲጠፋ ንብረት እንዲወድም አድርገዋል በሚል የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ለሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡በዚህ መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች፡-
ክንዱ ዱቤ
ዘመነ ጌቱ
ደበበ ሞገስ
ዘርዓይ አዝመራው
ገብረስላሴ ደሴ
መርጌታ ዲበኩሉ ሰማረ
ሀብታሙ እንየው
ብርሀኑ አያሌው
መላኩ አለም
ለገሰ ወልደሀና ናቸው፡፡

፨በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ ለዛሬ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቶ የነበሩ የዓቃቢ ህግ ምስክሮች ዛሬም አለቀረቡም፡፡ዓቃቢ ህግ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው የጠየቀ ሲሆን የተካሰሾች ጠበቆች በበኩላቸው ተደጋጋሚ ጊዜ በመቀጠሩ የደንበኞቻቸውን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታቸውን የሚያሰጣ በመሆኑ ዓቃቢ ህግ ምስክሮችን ማቅረብ እንዳልቻለ ተቆጥሮ በቀረበው ማስረጃ ብይን እነዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ፍርድ ቤቱም ዓቃቢ ህግ ምስክሮቹን እንዲያቀርብ ለመጨረሻ ጊዜ ለሀምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡በዚህ መዝገብ ክስ የቀረበባቸው ንግስት ይርጋ፣በላይነህ አለምነህ፣ቴድሮስ ተላይ፤አለምነው ዋሴ፣ያሬድ ግርማ እና አወቀ አባተ ናቸው፡፡

፨በተመሳሳይ የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቢ ህግ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ፣38 እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 7/1/ እና አንቀፅ 4 ስር የተመለከተውን ተለልፈው የሽብር ወንጀል ፈፅመዋል በሚል 35 ሰዎች ላይ የሽብር ክስ መስርቶባቸዋል፡፡በዚህ መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች፡-
1ኛ. ተሻገር ወ/ሚካኤል ላቀው
2ኛ. ነጋ ዘላለም መንግስቴ
3ኛ. ተስፋሁን ማንዴ ሰላምሰው
4ኛ. አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም ካሴ
5ኛ. አባ ገ/ስላሴ ወ/ሀይማኖት
6ኛ. ሰኢድ ኑርሁሴን ኑርሰይድ
7ኛ. በለጠ አዱኛ መንግስቱ
8ኛ. ተስፋሚካኤል አበበ ላቀው
9ኛ. እንዳለው ፍቃዴ አበበ
10ኛ. ስለሽ ግርማይ ነጋሽ
11ኛ. ይታይ ክብረት አታላይ
12ኛ. አዛናው ሲሳይ ገዛኸኝ
13ኛ. ዮሃንስ አየሁ ዘለቀ
14ኛ. አለማየሁ መኳንንት ካሴ
15ኛ. አሸናፊ ዮሃንስ ዘሪሁን
16ኛ. እዮኤል በሪሁን ይማም
17ኛ. ዓለምሰገድ ዋኛው በሪሁን
18ኛ. አበበ አበጀ ሽመልስ
19ኛ. መንግስቴ ተስፋሁን አረጋ
20ኛ. ሰለሞን ፀኃይ እንግዳ
21ኛ. አዝመራው ተሰማ አዕምሮ
22ኛ. ነበቡሽ ደሳለኝ መንግስቴ
23ኛ. ታደሰ ይግዛው ገብሬ
24ኛ. ቢራራ ልጃዓለም አብርሃም
25ኛ. አብርሃም ድረስ አለሙ
26ኛ. አማረ ገ/ሚካኤል ገ/ስላሴ
27ኛ. ሲሳይ ተስፋ ደሴ
28ኛ. አራጋው እንዳለ አሰፋ
29ኛ. ፍቅሬ ግርማይ ምትኩ
30ኛ. ደጀኔ ደምሴ ወርቅነህ
31ኛ. ሙላቱ ፍስሃ ገብሩ
32ኛ. ማርሸት አሰፋ ባዬ
33ኛ. ክንድሽህ ሀጎስ ታዬ
34ኛ. መንግስቴ አማረ ያዜ
35ኛ. ተስፋሁን ሙሌ መኮንን ናቸው። የክስ መቃወሚያ ለማቅረብ ለሀምሌ 11/2009 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡

The post እነ ለገሰ ወ/ሃና የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው!!! – ነገረ ኢትዮጵያ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Viewing all 3686 articles
Browse latest View live