Quantcast
Channel: admin – Medrek
Viewing all 3686 articles
Browse latest View live

አማራነት ከጎሳነት፣ ከነገድነት የተለየ ነው – ከአሰፋ እንደሻው (ለንደን፣ እንግሊዝ)*

$
0
0

እንደአዲስ የትግል ፈሊጥ ሆኖ አማራን ለብቻው በተቃዋሚነት እናደራጀው የሚል ክስተት ከተሰማ ውሎ አድሯል፡፡ ከዚያም አልፎ የአማራ ሬዴዮ ሆነ ቴሌቪዥን ወይም ሌላ መገናኛ አውታር ለብቻው በተቃዋሚነት ማቋቋም ይገባናል የሚል ተናፍሶ የተባሉት ነገሮች ብቅ ብቅ ብለዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሩጫ አላማው ጥቃትን ለመቋቋም፣ ያማራን መብት ለማስጠበቅ ነው እስከተባለ ድረስ ምንም ክፋት የለውም። በመንግስቱ ስር እንደተቋቋመው ሁሉ በተቃዋሚዎችም ሊመሰረት ይችላል። የኦሮሚያ መገናኛ መረብ ባገር ውስጥም በውጭም አለ። ሌሎችም ብቅ ብቅ እያሉ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም አማራን ለብቻው ማቋቋም ምንትስ እያሉ የሚነሱትና ሃሳቡን የሚደግፉት አስፈላጊውን አስተዋጽኦ ከማድረግ የሚከለክላቸው የለም። ደግሞስ ዴሞክራሲ ሲባል የህዝብን መብትና ፍላጎት ለመቅረጽ የሚያስችል ማናቸውም ጎዳና መጠቀም ስለሆነ እንዴት ተቀባይነት ሊነፈገው ይችላል? የተሻለ ሃሳብ ይኖራል ከሚል አንጻር ካለሆነ በስተቀር ምንስ ክርክር ያስነሳል;

ይሁንና ግልጽ መሆን ያለበት አንድ ትልቅ ቁም ነገር አለ። ስለ አማራ ማንነት ብዙ የተምታታ ነገር ሲሰራጭ ኖሯል። ከጎሳነት፣ ከነገድነት ጋር የሚያያይዙት በርካታ ናቸው። የአማራነት እውነተኛውና አሳማኙ ገጽታ ግን ከአክሱም አገዛዝ ምስረታና መስፋፋት ጋር የተያያዘና በኢትዮጵያ አቻ የሌለው አፈጣጠር መጎናጸፉ ነው። ስለአማራ አወላለድና እድገት ከመዘርዘራችን በፊት ጎሳ፣ ነገድ፣ ብሄረሰብና ብሄር እንዲሁም አገር እንዴት እንደሚለያያሉ እናሳይ። እነዚህን ማምታታት አይገባምና!

ማህበራዊ (የህብረተሰብ) አደረጃጀትና አገራዊ (ያገዛዝ ወይም ያስተዳደር) አደረጃጀት የተለያዩ ናቸው። ማህበራዊ አደረጃጀት መነሻው በይበልጥ የተፈጥሮ ጉዳይ ነበር። ጥንት በህብረተሰቦች ታሪክ በተፈጥሮ ብቅ ያሉት ጎሳዎች፣ ነገዶች ነበሩ። መጽሃፍ ቅዱስ በወጣበት ዘመን እነዚህ እንደነበሩ አገላብጦ ማየት ይቻላል።

ከዚያ ወዲህ እስከአውሮጳ 15ኛው መቶ አመት ድረስ ይኸው ሁኔታ ቀጥሎ ባውሮፓ ነገዶች እየተዋዋጡ ባንድ አገዛዝ ስር በርካታዎች ተሰባስበው ነበር። የግብርና ስልተምርት (ኢኮኖሚ) እየተለወጠ መጀመሪያ ንግድ ከዚያም ኢንዱስትሪ ባውሮፓ ሲስፋፋ የማህበራዊ አደረጃጀቱም ተለወጠ። በኢኮኖሚው መለዋወጥ ምክንያት ጎሳዎችና ነገዶች እየተጨፈለቁ ከከተማ መስፋፋት ጋር ብሄር ብቅ አለ። የፈረንሳይ ብሄር፣ የእንግሊዝ ብሄር ከሁሉም ቀዳሚዎች ናቸው። ከነሱ ተከትለው በኢኮኖሚያቸው ወደኋላ የቀሩት ሩሲያ፣ ጀርመን፤ ጣልያን ወደብሄርነት ተሻገሩ። ሌሎች ያለም ክፍሎች ይህንን ሽግግር ለማካሄድ ባለመቻላቸው እስካሁንም እየተውተረተሩ ይገኛሉ።

የብሄር መፈጠር ከጎሳና ከነገድ መፈጠር የሚለየው በኢኮኖሚው መለዋወጥ (ንግድና ኢንዱስትሪ) ፍጥነት ምክንያት ብዙ ጎሳዎችንና ነገዶችን በመዋጡ ነው። ያለኢኮኖሚ መለዋወጥ ማለትም ከግብርና ወይም አርብቶአደርነት አልፎ መሄድ ካልተቻል ማንም ህዝብ ብሄር ሊሆን አይችልም። ይህ ደግሞ ራሱን የቻለ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ሽግሽግን የሚያቅፍ ክስተት ነው፡፡ ያለምንም መስፈርት አንድን የቋንቋ ስብስብ “ብሄር” በማሰኘት የሚያምር ስምና ማእረግ ለመስጠት ወይም ለመሸለም ወይም የመኩረራት መንፈስ ለመፍጠር የሚቃጣ አይደለም።

በርግጥ ከጎሳነትና ከነገድነት አልፈው የሄዱት ነገር ግን ሽግግሩን ያልጨረሱትን የማህበራዊ ሳይንስ ተጠባቢዎች ብሄረሰብ የሚል ስያሜ ሰጥተዋቸዋል። በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሶስተኛው አለም ባጠቃላይ ባብዛኛው ብሄረሰቦች ናቸው ያሉት። ስለሆነም አንዱን ወይም ማንንም ብሄረሰብ ለይቶ ብሄር ሊያሰኝ የሚችል ሁኔታ ሳይኖር ለመንፈስ እርካታ ተብሎ እንደሹመት የአማራ፣ የትግራይ፣ የሶማሌ ብሄር ብሎ መጥራት የተሳሳተ ነው።

እዚህ ላይ ጽንሰ ሃሳቡ በአማርኛ እንዴት ሊመረጥና ሊገለጽ እንደቻለ ልናነሳ እንወዳለን፡፡ ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ ህብረተሰባችን የተጓዘበትን ማህበራዊ አደረጃጀት ራሳችን አጥንተን በበቀል ቋንቋዎቻችን ስያሜ (መገለጫ) ስላላዎጣንላቸው የውጭ (በተለይ የእንግሊዝኛ) አባባሎችን ወስደን ትርጓሜ ይሆናሉ ያልናቸውን ስንጠቀም ቆይተናል። ለምሳሌ ብሄር የሚለው የግእዝ ቃል ሆኖ የስር ትርጓሜው በውል ሳይታሰብ ለእንግሊዝኛው “ኔሽን” እንደአቻ ተወስዶ ዛሬ ከሊቅ እስከደቂቅ የሚጠቀምበት ሆኗል። እንደፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ ያሉ የግእዝ አዋቂዎች ብሄር የሚለውን ቃል አበሻቅጠው ጭራሽ ጎሳ የሚለውን እንድንጠቀም ይጎተጉታሉ። ቃሉ አስቀድሞ በግእዝ ምን ትርጓሜ እንዳለው ተመዝኖ የተወሰደ አለመሆኑ ማንንም ሳያግድ ዛሬ በአማርኛ ቋንቋ ውስጥና በተራው ህዝብ መካከል የማይናወጥ ተቀባይነት አግኝቷል። ግእዛውያን ወደዱ ጠሉ።  በሌላ በኩል ደግሞ ብሄረሰብ የሚለው ቃል በጥንታውያኑ ዘንድ የባሰ ጉድፍ ያዘለ ይሆንባቸዋል። “ብሄር” የሰዎች ስብስብ መሆኑ እየታወቀ “ሰብ” የሚለውን በመጨመር ብቻ ፍጹም የተለየና ራሱን የቻለ ጽንሰሃሳብ እንደሚገልጽ መወሰኑ ሊያበሳጫቸው ይችላል። ነገር ግን እላይ እንዳልነው የራሳችን ምሁራን አጥንተው ተገቢ ስያሜ ስላልሰጡን ተብሎ ህብረተሰቡ ቆሞ አልጠበቀም። የተማሪው ንቅናቄ ለእንግሊዝኛዎቹ ጽንሰሃሳቦች አቻ ትርጓሜ ለማብጀት በመገደዱ ዛሬ የምንገለገልባቸውን ትቶልናል። ስያሜው በዛሬ አይን ሲታይ የሚነቀፍ ቢኖረውም፡፡ ደርግም እነሱኑ ስያሜዎች ወይም ጽንሰሃሳቦች ተረክቦ በህብረተሰቡ አእምሮ ውስጥ ከቷቸዋል። ይሁንና ጎሳ፣ ነገድ፣ብሄረሰብ፣ ብሄር ከተሰኙት መሰረታዊ የህብረተሰባችን ክፍልፋዮች በተጨማሪ ብቅ ጥልቅ የሚሉ ሎሎችም መሰማታቸው አልቀረም። ዘር፣ ዘውግ፣ “ዘመድ”፣ “ወገን” (እነዚህ ሁለቱ ከጌታቸው ሃይሌ በአቻ ትርጔሜነት የቀረቡ ናቸው) ሌላም እየተሰነዘሩ በንግግርም በጽሁፍም እየገቡ አናያቸዋለን፡፡ እነዚህ ሁሉ ከውጭ ቃላት ጋር ባቻነት እንዲገቡ የተደረጉ ከመሆናቸው በተጨማሪ በምን መልክና ይዞታ በህዝብ መሃል እንዲሁም በቀለም ቀመሱ ክፍል ዘንድ ተቀባይነት እንደሚያገኙ አስቀድሞ ለመናገር አይቻልም። ያው ሁሉም የመሰለውን ከማቅረብ የሚከለክለው ሃይል ስለሌለ፡፡

ባገሪቱ ከሚታየውና ከሚሰማው እውነታ ከተነሳን ግን በህብረተሰቡ ውስጥ ብሄርና ብሄረሰብ የሚሉት ስያሜዎች በእኩልነት ተስፋፍተው በተራው ህዝብ አስተሳሰብና አነጋገር ላይ ተሳፍረዋል፡፡ ባገሪቱ ዳር እስከዳር፡፡ ይሁንና በተለይ በአጼው ዘመን ጀምሮ በውጭ አገሮች ተሰራጭተው የሚኖሩት ወገኖች እንዲሁም አልፎ አልፎ በቀለም ቀመሱ መካከል መምታታቱ እንደቀጠለ ነው። ብሄርና ብሄረሰብ ከውጭ የመጡ ስያሜዎች እንደሆኑ አድርገው የሚቆጥሩም አሉ፡፡ ስለዚህም ያው ጎሳና ነገድ የሚለውን በመጠቀም የውጭ “ተጽእኖን” ለመቋቋም የወሰኑ አይታጡም፡፡ የብዙሃኑ ህዝብ አጠቃቀም እያደር እየገነነ መሄድ ግን ህብረተሰቡ ይመስላል የስያሜውን ውዝግብ የሚዘጋው፡፡ (የእንግሊዝኛውን ቃሎች “ትራይብ” “ክላን” ቅኝ ገዥዎች ያመጡብን ነው የሚለው ሙግት እያየለ ቢሄድም በብዙ ያፍሪካ አገሮች ቀለም ቀመሶች ዘንድ አሁንም በስራ ላይ እየዋለ ነው፡፡ በስነጽሁፍ ውስጥ ግን ኤትኒክ ወይም አዝማድ የሚለው ተክቶታል፡፡ ባንድ በኩል ጎሳነት የኋላቀርነት ሽታ አለው በሚል መንፈስ፡፡)

እላይ እንደተባለው ያገር ወይም ያስተዳደር አደረጃጀት ከማህበራዊ አደረጃጀት ይለያል። እንደስልጣን ባለቤቶቹ አቅም፣ ግዛቱ ሊስፋፋ ወይም ሊጠብ ስለሚችል። የፖለቲካ ሃይሎቹ ንጉሳዊ፣ ሪፑብሊካዊ፣ ቀሳውስታዊ፣ ሸካዊና ሌሎች ሆኑ አልሆኑ በአገር ደረጃ ከላይ ወደታች የስልጣን እርከኖች ፈጥረው ስለሚገዙ ህዝባዊ መሰረታቸው እስከፈቀደላቸው ድረስ ያሻቸውን ያከናውናሉ።

በኢትዮጵያ ከአክሱም አገዛዝና ስራዊት መደራጀትና መስፋፋት ጋር የተፈጠረው አማራ የተባለው ህዝብ ሆነ ከሱው በፊት ጀምረው አገሪቱ ውስጥ የኖሩት ሌሎች (ጥቂቶችን ለመጥቀስ አገው፣ አጋመ፣ ባሪያ፤ ኩናማ፣ ትግራይ፣ ትግረ፣ አፋር፣ ኩናማ፣ ሳሆ፣ ሶማሌ፣ ኦሮሞ፣ ሲዳማ፣ ሃዲያ፣ ከምባታ፣ ካፋ፣ ህናሮ፣ ቤኒ ሻንጉል) ኢትዮጵያን በሃገርነት አካለው ይዘው ቆይተዋል። ላሊበላ ላይ ከተዋቀረው ብቸኛው የአገዎች ስርወ መንግስት ጀምሮ ከመካከላቸው ስልጣንን የተቆናጠጠው ወገን ሁሉ አማርኛን “ልሳነ ንጉስ” እያደረገ በጎሳና በነገድነት ከዚያም አልፎ በብሄረሰብነት የተቋቋሙትን አሰባስቦ ሲገዛ የ1966 አብዮት ድረስ ቆይቷል። ሆኖም የአገሪቱን ጎሳዎች ወይም ነገዶች እንዲሁም ብሄረስቦች መብት ማስጠበቅ አንዱ የፖለቲካው ህይወታችን ገጽታ እንዲሆን የሚያምኑትና የሚሹት ሁሉ በምን መልክ አገዛዙ እንደሚዋቀር እስካሁንም ንትርካቸውን አልቋጩም።

በሌላ በኩል ግን አማራ የሚባለውን ህዝብ በተመለከተ ዛሬም ብዙ የተምታታ አስተሳሰብ እንደሰፈነ ነው፡፡ እቅጩን ለመናገር፣ አማራ ተጀምሮ እስኪጨረስ ጎሳ አይደለም። አልነበረምም። አንዳንድ የቆዩና እንዳዲስ የተነሱ የአማራ እንቅስቃሴዎች መሪ ነን የሚሉ ሰዎች በጽሁፎቻቸውና በንግግሮቻቸው ይህንን እጅግ መሰረታዊ ጽንሰሃሳብ አልጨበጡም። አማራ ባፈጣጠሩ ከሌሎች የህዝብ ስብስቦች (ትግሬ፤ ኩናማ፣ ሳሆ፣ ኦሮሞ ወዘተ) የተለየ ነው። እላይ እንደጠቀስነው አማራ የሚባል ህብረተሰብ የተቋቋመው የአክሱም ጦር ሰራዊት ከየጎሳውና ከየነገዱ እየመለመለ በያቅጣጫው ሲሰማራ ነው። የአክሱም መንግስት ራሱ የውጭጩ መንግስት ነበር። አክሱም የአገው ከተማ ቢሆንም መንግስቱ  ግን ከየጎሳው የተውጣጣ ነበር። አገዎች ያካባቢው ትልቁ ጎሳ ስለነበሩ በስራዊቱና በመንግስቱ ውስጥ ተሳትፎዋቸው ትልቅ ነበር። ነገር ግን ለብቻቸው መንግስቱን አልያዙም። ባጭሩ የአክሱም መስፋፋትና የጦር ስራዊቱ ከያካባቢው ጎሳዎች እየመለመለ አስተዳደሩን በያቅጣጫው መዘርጋት በሰራዊቱ ውስጥ ለታቀፉ የተለያዩ ጎሳዎች መቀላቀል ብሎም ለአዲስ ቋንቋና ህዝብ መፈጠር ምክንያት ሆነ። ልብ አድርጉ መጀመሪያ ቋንቋው ነው የተፈጠረው፣ ከዚያ ቀጥሎ ህዝቡ ተከተለ። አማርኛን የሚናገረውና በተለይ ደግሞ ክርስቲያን የሆነው ራሱን አማራ ማለት ጀመረ። (ይህን ታሪካዊ ሂደት አጠር ባለ መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ ደራሲው አክሱም « ኢትዮጵያ–የህዝቦች ስብጥርና የአገዛዞች አወቃቀር አጭር ታሪክ  በሚለው መጽሃፉ አቅርቦታልና ያንን መመልከት ያሻል፡፡)

የአክሱም አገዛዝ አገዎችን እንደመነሻ፣ መረማመጃና ድጋፍ ይዞ ሲስፋፋ መዋቅሩን ከስር መሰረቱ ሳያዛንፍ የተለያዩ ስርወ መንግስታትን በዘመተበት ቦታ ሁሉ በማቋቋም ነበር። ከሱ በፊት ከነበሩት ዳማት ምናልባትም ፑንት ወይም ዳሞት አገዛዞች በመከተልና በመቀጠል ስለተዘረጋ ከአክሱም ላይ የተቋቋመው አገዛዝ ከቤጃዎችና ከኦሪታውያን አገዎች ጋር ባካሄደው ተደጋጋሚ ጦርነት ሲሸነፍ እሱም በተራው መጀመሪያ ወደሮሃ (የዛሬዋ ላሊበላ)፤ ከዚያ ወደሰል (አምባሰል)፣ ቀጥሎ ወደአንኮበር፣ ወጂንና ፊንፊኔ (በኋላ አዲስ አበባ) መንበረ መንግስቱን አዝምቷል። (በአህመድ ኢብራሂም የተመራው የምስራቁ ቆላ ህዝብ እንቅስቃሴ ባስነሳው ጦርነት ሳቢያ ከወጂን ማለትም ደቡብ ምስራቅ ሸዋ ተነቅሎ ወደበጌምድር የተሻገረው ስርወመንግስት ወደመቀሌ ቀጥሎም አንኮበር መዘዋወሩን ሳንረሳ፡፡) በነዚህ ዋና ዋና የመስፋፋት ጉዞዎች ሰራዊቱ ጎሳን ከጎሳ ነገድን ከነገድ እያዋሃደና እያዋዋጠ ሲገሰግስ አማርኛን እያሰራጨና እያጠናከረ ሄዷል። የዚያ ውጤትም ራሳቸውን ከየጎሳዎች አባልነት ይልቅ አማራነት የሚሰማቸው የህዝብ ስብስቦች የበዙ ሆኑ፡፡ እምነታቸው ክርስትና በመሆኑም አማራነትና ክርስቲያንነት ያንድ አካል ሁለት ስሞች እንደሆኑ ተደርገው ቀጠሉ።

ዛሬ በአራቱ የአጼው ጠቅላይ ግዛቶች (ማለትም በሸዋ፣ ወሎ፣ በጌምድርና ጎጃም) ብቻ ሳይሆን በሁሉም አካባቢዎች አማራ ነን የሚሉት ቁጥራቸው ብዙ ነው። በኦሮሚያ ውስጥ እንኳን 10 ሚሊዮን እንዳሉ ተደጋግሞ ተወርቷል። በሌሎችም ውስጥ ተመሳሳይ ሁኔታ አለ። ባጭሩ አማራነት ከደም ጥራት ወይም ስጋነት ጋር ሳይያያዝ ከቋንቋው ጋር  በተቆራኘ መልክ ባገሪቱ ሲስፋፋ የቆየና አሁንም ያልቆመ ነገር ነው። አሰፋ ጫቦ ባንድ ቃለ ምልልስ ላይ በጋሞ ጎፋ ራሳቸውን አማራ ብለው የሚጠሩት “ነፍጠኞች” ከሸዋ የዘመቱ ኦሮሞዎች እንደነበሩ የመሰከረው ለዚህ አባባል ዋቢ ነው። እንደገና በኦሮሚያና በደቡብ ከተሞች አብዛኛው የከተማ ኗሪ ባልሳሳት ራሱን አማራ አድርጎ የሚቆጥር ነው። ከዚህም በተጨማሪ በትውልዱና በጎሳው በተለይ ደግሞ የተቀላቀለውና የተዋለደው ይኸ ወይም ያ ብሄረሰብ ነኝ ብሎ መናገር የሚያቅተው ሁሉ ራሱን አማራ ወይም ኢትዮጵያዊ አድርጎ ይቆጥራል።

ባንጻሩ ግን አገሪቱ ውስጥ በተቀሰቀስው የዴሞክራሲን ስርአት የመመስረትና የማስረጽ ትንቅንቅ ውስጥ ሁሉንም ብሄረሰቦች በማስተባበር ከመታገል ይልቅ በየዘሩና በየጎሳው የመከለል ሙከራ ፋይዳ እንደሌለው እየታየ ነው። በይበልጥ ደግሞ በታሪኩና በተከሰቱት ፖለቲካዊና ወታደራዊ ውጥንቅጦች የተወለደውን አማርኛ ተናጋሪ ህዝብ እንደጎሳ እየቆጠሩ ና ለብቻህ ተቀፍድደህ ቁም፣ ተቆጠር ማለት አላዋቂነት ነው። ሁሉም የአለም ህዝቦች እየተቀራረቡና አየተዋዋጡ ባሉበት የመረጃ አብዮት ዘመን በኢትዮጵያ ከየብሄረሰቡ እየተውጣጡ እየተቀላቀሉ ያሉት ሁሉ ራሳቸውን አማራ ነን ወደሚል ሲተሙ ያንን ሂደት ለማደናቀፍ መሞከር ጅልነት ነው። የማይሳካ ከመሆኑም ሌላ በአይናችን እያየን ለሚካሄደው ማህበራዊና ፖለቲካዊ መለዋወጥ ጀርባ መስጠት ነው።

በሌላም በኩል በአለም ያልተቋረጠ ብቸኛ ትልቅ ታሪክ ከነበራቸው ከግብጽ፣ ኢራንና ከቻይና ጎን የምትሰለፈው ኢትዮጵያ በውስጧ የተፈጠረውን (የተፈለፈለውን) ሰው ስራሽ ማህበራዊ ስብስብ (አማራን) ማንም ሊያጠፋው ቀርቶ ሊገድበው አይችልም። አማርኛን ባገሪቱ የመገበያያ ቋንቋነት ያስቀመጠው ዘርፈ ብዙ ሂደት ተቀልብሶ ወደሌላ መሽጋገር የማይቻለውን ያህል በዚያ ቋንቋ ዙሪያ የሚሰባሰበውን ህብረተሰብ በጠባብ ክፍል ውስጥ ለማሸግ የሚደረገው ማናቸውም መወናጨፍ ከተራ ልፈፋ አያልፍም። ለለፋፊዎቹ አልታያቸው ስላለ እንጅ ከተሜነት ራሱ ከአማራነት ጋር የተቆላለፈ ሂደት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ባገሪቱ ዳር እስከዳር ከተሜነት እየተስፋፋ ሲሄድም ያማራነትን መለያ የሚላበስ ክፍል እየጨመረ ያለሰው ሰራሽ (ብሎም መንግስታዊ) አስገዳጅ ተቀባይነት እያገኘ መጥቷል፡፡

በዚሁ አኳያ አንዳንድ ቀባጣሪ የፖለቲካ ማይም እየተነሳ ላማራ ለብቻው “የጎሳ” መብት ለማሰጠት እንታገል፣ እንደራጅ ሲል ዝም ማለት አይገባም። አማራው ማንንም አይመን፣ ብቻውን ተደራጅቶ ይንቀሳቀስ የሚሉት ፈሊጥ የት እንደሚያደርሳቸው መገመት ባለመቻላቸውና ከአለም ስልጣኔ ሰፊ ጎዳና ወጥተው ራሳቸው በሚያበጃጁት ዋሻ ውስጥ ስለሚከታቸው የትም አይደርሱም ሊባሉ አይችልም። በምድሪቱ ላይ ያሉት የመንግስቱ ተቀናቃኞች በሙሉ ወደአንድ አቅጣጫ ማለትም ህብረት ፈጥረው ስልጣኑን መውሰድ (መረከብ) ወደሚያስችል ጎዳና እንዲገቡ ስንወተውት ኖረን ያንን ጥረት ለመበተን የሚሟዘዙትን በመናቅ ብቻ መተው ተገቢ አይደለም፡፡ የጎንደር፣ የባህርዳር ህዝብ “በቀለ ገርባ ይፈታ፣ መሪያችን ነው”፣ “የኦሮሞ ደም የኛም ደም ነው” ሲል መልእክቱ ምን እንደሆነ እንዴት መረዳት ያቅታል?

የፈረደበትን ኦነግን ዛሬም እንደበፊቱ የስልጣን ተጋሪና ወሳኝ ተብሎ እየቀረበ፣ ካመቸው ከወያኔ ጋር ተመልሶ እንደሚተቃቀፍና አማራን እንደሚወጋ የሚለውም ጊዜ ያለፈበት ቅዠት መሆኑን በድፍረት ማጋለጥ ይጠበቃል፡፡ የዴሞክራሲን ፈለግ ከሚከተል ሁሉ። ባሁኑ ወቅት ኦነግ በመንፈስነት (በባንዲራ) ከመራገቡ በላይ የኦሮሞ ፓለቲካ እንቅስቅሴው አደራጅና መሪ አይደለም። ከዚህም በላይ የኦሮሞው ህዝብ ቀስ በቀስ የኢትዮጵያ አገዛዝ ወደዴሞክራሲ መግባቱ ለራሱም ሆነ ለሁሉም ብሄረሰቦች አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን እየተረዳ ነው። የኦሮሞው ቀለም ቀመስ ልሂቃኑ ይበልጥ ይህንን እየተገነዘበ ነው። (ይኸ ጉዳይ ራሱን የቻለ ትንታኔ የሚያስፈልገው ስለሆነ በሌላ ጊዜ እንመለከተዋለን፡፡)

የትግራይን ህዝብ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ቆርጠን እንጣል ይል የነበረውን እብድ ዛሬ ሌላ ተከታዮች እየተገኙ መሄደቸውና ህዝቡ ላይ የሚነዙት መርዘኛና የጥላቻ ወግ እጅግ አሳዛኝ ነው! ወያኔ መነሻው ከትግራይ መሆኑ የወጣበት ህዝብ እንዴት ወንጀለኛ እንደሚባል ጭንቅላት ላለው ሰው አስቸጋሪ ነው። ደራሲውንና ፖለቲከኛውን ሁሉ ከህዝብ መሃል ስለወጣ ዘሩን ፈልገን እናውግዝ? ምን አይነት የድንቁርና ዘመን ውስጥ ተመልሰን ልንገባ ይሆን እንዲህ አይነት መርዞች በየቦታው ሲረጩ!

ያገሪቱ ህዝብ እድል እንደገና በተቀናበረ እጁ ሊገባ እየተቃረበ ባለበት ወቅት ከፋፈይና በታኝ ቅዠቶችን ማሰራጨት ተቀባይነትም ተገቢነትም የለውም። ይልቁንስ የትግል ህብረቶች እንዲዳብሩ ህወሃት/ ኢህአዴግም በሰላማዊ መንገድ (ማለትም ከጦርነት መለስ) ስልጣኑን እንዲያስረክብ ዘዴዎችና ስልቶች መቀየስ ሲጠበቅ ሁሉም ተበታትኖ የግዛት ዘመናቸው እንዲቀጥል መሞገት የወጣለት መሰሪነት ነው።

 

*አስተያየት ካለ፡–a_endeshaw@yahoo.co.uk

The post አማራነት ከጎሳነት፣ ከነገድነት የተለየ ነው – ከአሰፋ እንደሻው (ለንደን፣ እንግሊዝ)* appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


በጀርመን የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል በበርሊን ከተማ June 3 & 4  በቅርብ መነጽር ሲታይ – ካሱ ለገሰ

$
0
0

09/06/2017

ዘንድሮ ይህ ፌስቲቫል ሲካሄድ በብዙ መልኩ ከቀድሞዎቹ ዝግጅቶች በተሳካ ነው ብሎ መጀመሩ የዚህን ጽሁፍ መጠነኛ የይዘት አቅጣጫ ይጠቁማል።

የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ በቅርብ መነጽር ያለበት ምክንያት ፌስቲቫሉ ከጀመረበት 1 ቀን በመቅደም ከፌስቲቫሉ ቦታ 50 ሜትር ባልራቀበት ሆቴል በማረፉና አካባቢያዊ ግንዛቤውም ቀድሞ በመጀመሩ ከዚያም እስከተጠናቀቀበትም ሰዓትና ደቂቃ በቅርብ ከማየቱም ባሻገር የዝግጅቱንም ሂደትና መልክ አብሮ በመቅረጹም በኩል ከኢትዮ ጀርመን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ጋር በመሆን ሲመክርበት እንደነበረ ለመጠቆም ይወዳል።

ከዚህ በፊት የነበሩት ዝግጅቶች የ 1 ቀን ብቻ በመሆናቸው ከጉዞ ርዝመት ከነበሩት የአየር ንብረት ሁኔታ ጋር ተደማምረው ከነበረው ግዜ መጣበብ ጋር  የነበሩብንን ጫናዎች ለማቅለል የሁለት ቀን ማድረጉን ተግባራዊ ለማድረግ ተመክሮበት ለዚህ ስኬታማ ውጤት በመደረሱ ሁሉም በዚህ ጉዳይ ቅድመ ሃላፊነት ተሰምቶት የመከረና ያስተባበረ የፌዴሬሽኑ አባሎች ምስጋና ሲያንሳችሁ ነው።  መወያየትን መምከርን ግልጽነትን እውቀትን ከተላበስን ሁሉን ነገር በቅንነት ለመመርመር ይስችላልና በርቱ።

እንዲህ ነበር ያለፈው

ጁን 3 እና 4 ማለትም ቅዳሜና እሁድ በርሊን ከተማ ከመሃል ከተማው አንስቶ ገዙንድ ብሩነን የተባለውን የከተማውን ኣንድ ክልል ከወትሮው በተለየ የኢትዮጵያውያን መንደር ለማለት በሚያስችል መልኩ በአረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለማት የተዋቡ ሴቶች እህቶቻችን ህጻናትና በኮፍያ ስከርቭና በዋልያዎቹ ደማቅ ማልያዎች የተዋቡ አባቶችና እናቶች ከነልጆቻቸው ወጣት ሴቶችና ወንዶች  አቅጣጫቸውን ወደ ፌስቲቫሉ በማድረግ በከተማ የህዝብ ማመላለሻ ባቡርና በምድር ውስጥ የከተማ ባቡር እንዲሁም በግል መኪና በማሽከርከር  በቅርብ ሆቴሎች የሰፈሩት ደግሞ በእግር መኳተን የጀመሩት ገና ከማለዳው 3 ሰዓት ሳይሆን ነበር።

ቅዳሜ በማለዳ ተፈጥሮም እለቱን በብርሃን ለማጀብ ከማንም ቀድማ ጸሃይዋን ልካ ነበርና የመጀመርያ አድራሻቸውን ፌስቲቫል ሜዳው ላይ ያደረጉትን የኢትዮ ሽቱትጋርት ስፖርተኞችን ማሞቅ በመጀመር ዓርብ ምሽቱን ዝግጅቱን ባጠናቀቀው ዲጄ አገራዊ የእረኛውን ክላሲካል  ሙዚቃ ሲለቀው በሰማይ የሚበሩ ወፎችን እንደመፈለግም ቁልቁለት እንዲሚፈስም የወንዝነት ድምጽ እያስተጋባ ፍጹም ልዩ በሆነ መልኩ ወደ አገርቤት ልብን እየሰለበ  የፌስቲቫሉም ጠረን ከቅርብ እንድናሸተው ማድረግ የጀመረው ገና ከጅምሩ ነው። ከግራና ቀኝም  ቀድመው የመጡ ስፖርተኞችም በሙሉ ውበት ያለውን የተለያየ ማልያ ተላብሰው ሜዳ ውስጥ ውር ውር ሲሉ የፌስቲቫል አዘጋጆችም እዛው ያደሩ ይመስል በየስራ ድርሻቸው ተከፋፍለው ቅድመ ዝግጅታቸውን ጨርሰው በተያዘው ፕሮግራም መሰረት የስፖርትና ቴክኒክ ክፍሉ የቡድን ምዝገባ ሲጀምሩ ክለቦችም ኢትዮጵያ ሀገሬ የሚለውን የቴዲ አፍሮን ዘፈን እየጨፈሩበት ከአውቶቡሳቸው እየወረዱ ወደ ፌስቲቫሉ ግቢ ሲገቡ ማየት እጅግ ልብ ይማርክ ነበር።

ተሳታፊ ክለቦች በተወካዮቻቸው አማካይነት ምዝገባቸውን እንደጨረሱ በሁለት ምድብ በመከፈል በሁለቱ ሜዳ ላይ እንዲጫወቱ ድልድሉ አልቆ ዳኞችም ተመድበው ስፖርታዊው ውድድር በሰዓቱ ተጀምሯል።

ሁል ግዜ እንደሚደረገው አንድ ሁለት ጨዋታ ከተከናወነና ታዳሚዎ ችም በርከት ሲሉ ዝግጅቱ እንደሚከፈተው ሁሉ ወደ 13 ሰዓት ገደማ በስነ ስርዓት ተከፍቷል።

የመክፈቻ ስነስርዓት  በትናንሽ ባንዲራዎች አረንጓዴ ቢጫ ካኒቴራዎች ለብሰው ጣዕም ባለው ዜማ የበርሊን ህጻናት እማማ  ኢትዮጵያ ሀገሬ እያሉ በመዘመር የመክፈቻ ስነስርዓቱን አድምቀውታል። ይህን ሲሰማ ስንቱ ሆዱ ባር ባር ብሎት ይሆን እጅግ ይመስጥ ነበር። ይህ በህጻናቱ እንዲሆን ያዘጋጀው የበርሊን እናቶችና ህጻናት ማህበር ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል። ህጻናቱንም በጥበብና በክብር እግዚአብሄር ያሳድግልን።

  የክብር እንግዳ የዘንድሮውን ፌስቲቫል የዝግጅት ደረጃ ከፍ ካደረጉት ክንውኖች መካከል የክብር እንግድነት ደረጃው አንደኛው ነው ለማለት ግድ ይለኛል። አቶ ፍቅሩ ኪዳኔን የመጀመርያው የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኛ የአፍሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽንና የአለም የኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል የወቅቱ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዚደንቱ አማካሪን በእንግድነት ከፓሪስ እዚህ ፌስቲቫል ላይ እንዲገኙ ማስቻል ማለት ምን ያህል የኢትዮ በርሊን የስፖርት ማህበር ለስፖርታዊው ዝግጅት ትኩረት እንደሰጠው ለቀጣይ ታዳጊ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ለሀገርና ለወገን የደከሙ ባለአደራዎችን ድካማቸውን እውቅና በመስጠት እንዲሁም ራእያቸውና ብልህ አመራራቸው ወደ ትውልዱ ሰርጾ እንዲገባ ለማስቻል በእንደዚህ አይነት ኢትዮጵያውያን በሚገኙበትና እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከምንም በላይ ደምቃ በስፋት በምትወደስበት ፌስቲቫል ላይ ማቅረብ የስፖርት ማህበሩን አመራሮችንም ክብርና ሃላፊነት ከፍ ያደርገዋል። በዚህ ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል። በመቀጠልም አቶ ፍቅሩ በበዓሉ መክፈቻ ላይ እንዲሁም በዶቼ ቬሌ የራድዮ ቀጥታ ስርጭትና ከዝግጅቱም በኋላ ያስተላለፉት ጥልቅ ንግግርና ምክር እንድታዳምጡ እጠቁማለሁ።  http://www.dw.com/overlay/media/am

ዳኞች የኢትዮ በርሊን ስፖርት ማህበር ከፍተኛ አጽንዖት ከሰጣቸው ተግባሮች መካከል ስፖርታዊ ይዘቱ የፊፋን ህግ እንዲከተል በማለት የከተማውን 4 ፕሮፈሽናል ዳኞችና አንድ ኢትዮጵያዊ ዳኛ(አቶ ጥላሁን ጉደታን)በማቅረብ ተግባራቸውን በትክክል እንዲወጡ በማስቻል እግርኳሱም ለስፖርተኞችም ለተመልካችም እንዲጥም እንዲሆን አድርገዋል። በዚህ ልዩ ምስጋና እንዲቸራቸው ያሻል።

 ክለቦች በእግርኳስ ጨዋታው በኩል ሁሉም ክለቦች በሚባል መልኩ በጣም በወጣቶች በመደራጀታቸው ያለው የጨዋታ ብስለት ፉክክር ቴክኒክ ልብ የሚማርክ ሲሆን ካለው ዝቅተኛ የሆነው የቱርኒር ሰዓት አመዳደብ የተነሳ የልባቸውንና የአቅማቸውን ያህል ሳይጫወቱ እያለቀባቸው ተሸናፊ ቡድኖች ላይ የሚያሳድረው ቁጭት ሃይለኛ ነበር።

 አሰልጣኞች የአብዛኛው ክለብ አሰልጣኞች ቅድመ ኢትዮጵያ ላይ በእግርኳሱ ዘርፍ አሻራቸውን አሳርፈው የመጡ በመሆናቸውና እግር ኳስን ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆናቸው በሜዳው አካባቢ የሚያሳዩት ተግባር ከዳኛ ጋር ያላቸው የንግግር ደረጃና ስነምግባር ከፌዴሬሽኑ አመራሮችና ከአዘጋጅ ቡድን ሃላፊዎች ጋር የነበራቸው ግንኙነት እጅግ የሚያኮራ ነበር።

የቅዳሜ ወይም የጁን 3 ቀን ውሎ ሁሉም ክለቦች በየምድባቸው ያለውን የርስ በርስ ውድድር እንዲጨርሱ ማስቻል ነበርና  በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት እንደታቀደው ሆኖ ከየምድባቸው ሁለት ሁለት ቡድኖች እንዲያልፉ ሆኗል። በዚህም

ከምድብ 1 ኢትዮ ሽቱትጋርትና ኢትዮ ኮለን ከምድብ ሁለት ኢትዮ አዲስ ፍራንክፈርትና ኢትዮ ዘ በርሊን ኣልፈው ለእሁዱ ማጣርያ ራሳቸውን አዘጋጅተዋል።

ፌስቲቫሉ ቤሄም ሽትራሴ የተባለውን የከተማውን ረጅም ጎዳና ተደግፎ የተንጣለለው ባለ ሁለት እግርኳስ ሜዳ (በፊፋ ደረጃ) የፌስቲቫል ቦታ  ሙሉ በሙሉ የታጠረ በመሆኑ መግቢያ በሩም አንድ ብቻ በመሆኑ ከፍ ብሎ በተሰቀለው ሰንደቅ አላማችንና የእንኳን ደህና መጣችሁ ጽሁፍ ስር ማለፉ እያንዳንዱን ታዳሚ ኢትዮጵያዊ ልባሱን ደርቦ ለመግባት ያስችል ነበር። በጸጥታ አስከባሪዎች በመስተናገድ በቀጥታ በግራና ቀኝ በተጣሉ ድንኳኖች ውስጥ ባህላዊ አልባሳት ኮፍያዎች ስከርቮች ቲሸርቶችን ለህጻናት የሚሆኑ ጌጣጌጦችን  ወዘተ እየሸመቱ ወደ ዝነኛው የኢትዮጵያ የጀበና ቡና ድንኳን ያመራሉ።

በበርሊን  የኢትዮጵያውያን የእናቶችና ህጻናት ማህበር ሙሉ በሙሉ የሚስተናገደው የቡና ድንኳን ሙሉ ቅዳሜና እሁድ ያለፋታ  የቡና አቅርቦቱን ከቡና ቁርስና መዓዛ ካለው አገራዊ እጣን ጋር ያለ ድካም በፍቅር ሲያስተናግድ ስለነበር ለነበረው

አገልግሎት በቦታው ለነበሩት እህቶችና እናቶች ምስጋና ይገባቸዋል።

የፌስቲቫሉ አስተዋዋቂና ዲጄ ሙሉ በሙሉ የተዋጣለት የመድረክ አስተዋጽኦ እንዲሆን በማሰብ የተሳካለት የማስተዋወቅ  አገልግሎት ከዲጄ ጋር እንዲሆን በማሰብ የኢትዮ በርሊን ስፖርት ማህበር እውቁን አስተዋዋቂና ፌስቲቫል አጋጋይ አቶ ዘለአለምን ከታዋቂ ዲጄ ጋር በመመደቡ እጅግ የሚበረታታና የተሳካ አገልግሎት እንዲሆን አስችሏል። ያለምንም እክል የሙዚቃም ሆነ የግንኙነት መስመር ለደቂቃ ሳይቋረጥ የተዋጣለት በሚባል መልኩ አገልግለዋል።በዚህም የህዝቡን ልብ ትርታ እየተካከተሉ ያጫውቱ የነበረው ወቅታዊ ሙዚቃዎችና እራሳቸውም ከመድረክ ላይ ሆነው በሚያሳዩት ባህላዊ ዳንኪራዎች የፌስቲቫሉ ድምቀቶች ነበሩ። በዚህም ኮርተንባቸዋል።

ምግብና መጠጥ  የታዳሚውን ህብረተሰብ በርክቶ መምጣት ግንዛቤ በመውሰድ በርካታ የምግብ መደብሮች በመኖራቸው መጉላላት የሚባል ነገር ሲጀምር የሚታሰብ አልነበረም። ሲቀጥል ደግሞ ሰሃን የሚደፋው የምግብ ብዛት በስስትና በንግድ ላይ ያላማተረ ህዝባዊ አግልግሎት እንደነበረ የሚያሳይ ለልጆችም የሚሆን ከህጻናት ምግብ እስከ አይስክሬም ለስጋ ወዳጅ ወገኖቻችን ደግሞ በግሪል ወይም በፍም የጋለ ስጋ በሃምበርገር መልኩ ሲያስተናግዱ ከርመዋል።

የመጠጥ አገልግሎቱም የለስላሳ መጠጥና ቀዝቃዛው የጀርመን ቢራ  ያለ ማቋረጥና ያለ ወረፋ በቂ ሰራተኞች በመመደባቸው እክል ያልገጠመው አገልግሎት ተካሂዷል።

የመጀመርያ  ህክምና እርዳታ የእርዳታ ሰጪዎች በሁለቱም ሜዳዎች ላይ በመገኘት መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ተጫዋቾች ሲረዱ ተስተውሏል።

ስነስርዓት ሲጀምር እስከዛሬ በየፌስቲቫሉ ሲታዩና እንደ አንድ አስቸጋሪ ነውርና ተግባር የነበሩት የጫትና የሺሻ ስርጭቶች ወይም አገልግሎቶች አንድም አልነበሩም። ይህም ትልቅ የትውልድን መሻሻል ለቀጣይ ህጻናት የማሰብን ባለአደራነት ያሳያል።

ይህ ደግሞ  ከየትም የመጣ አይደለም፡፡ ከኛው ከህብረተሰባችን የመጣ ብርታት እንጂ። የቡድኖችን የተጨዋቾች ተዋጽኦ ሲታይ

ያ የእከሌ ልጅ ነው ይህ የእከሌ ልጅ ነው መባሉ ራሱ ክለቦችን ቤተሰባዊ ቅርርብ የማድረግን ወላጆችም ለእንደዚህ አይነት ስብስቦች ግዜና ትኩረት የመስጠት በዛው ደግሞ ተወራርሶ የሚሄደው ደግሞ ጨዋነት ክብር ማንነት በመሆኑ እነዚህ ደግሞ የአስነዋሪ እጽ ማራቂያና ስፖርቱ ደግሞ ወላጆችንና ልጆቻቸውን  ከወገኖቻቸው ማቀራረብያ  በመሆኑ ሁሉም ከተባበረ አስነዋሪ ነገሮችን አብሮ ማገድ ስለሚቻል ዘንድሮ አንድ የጫት ዘለላ ያልታየበት አንድም የሺሻ መቃ ያልታየበት እንዲሁ ብቻ ፌስቲቫል ፌስቲቫል ሲጫጫስበት የነበረ በመሆኑ የተሟላ ስነ ስርዓት ነበር በሚያስችል መልኩ ተፈጽሟል።

የእሁድ ውሎ ጁን 4

የቅዳሜው ዝግጅት ሲቆለፍ የእሁዱን አጀማመር አስምሮበት ነበርና ያደረው ከማለዳ ጀምሮ ሊኖር የሚችለውን ቅድመ አየር ንብረት ማለትም ከማለዳው ጀምሮ እንደሚያካፋ ወፏ አሳብቃ ስለነበር ከዚያም ባላፈ የበርሊን ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስትያንም ታቦት የሚነግስበት እለት በመሆኑ ሁለቱን ዝግጅቶች በማናበብ ከቀኑ13 ሰዓት ጀምሮ እንዲቀጥል ተደርጎ በመታደሩ  ስፖርታዊ ውድድሩም ከ 14 ሰዓት እንደሚጀምር በመነገሩ ዝናቡም በቀጠሮው መሰረት እሁድ ከጠዋት ጀምሮ እየረገጠ ወደ ከሰዓት በኋላው ግን ደመናውም እየተገለጠ ዝናቡም እየለቀቀ በተያዘለት የግዜ ሰሌዳ መሰረት ደቂቃ ሳይዛባ ውድድሮቹም ፌስቲቫሉም በየሰዓታቸው ተጀምረዋል።

የበርሊን ቅዱስ ዓማኑኤል ቤተ ክርስትያን ድርሻ የዚህ ፌስቲቫል ልዩ መሆንና ውበት በተለይ በጀርመንና አካባቢው ለሚኖሩ ህዝበ ክርስትያን በማሰብ የኢትዮ በርሊን ስፖርት ማህበርና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የበርሊን የቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስትያን አባት ካህንና የሰበካ ጉባኤ አባሎች በመቀናጀት በመተባበር ሰዓቶቻቸውን በማቀራረብ ያደረጉትን ትብብር ሳናደንቅ አናልፍም። ቤትክርስትያኗም ምዕመኗን በቤትክርስትያን ዝግጅታቸውና በፌስቲቫሉ ቦታ ላይ በማሰማራት ያደረግችውን የተሳካና  የተዋጣለት እርዳታ ብዙዎች ሲያመሰግኗት ከፌስቲቫል ቦታው መስማት እጅግ ያረካ ነበር።

ስፖርታዊው ውድድር የጀመረው በኢትዮ ሽቱትጋርትና ኢትዮ ዘበርሊን መካከል ሲሆን በድምሩ 40 ደቂቃ ተጫውተው ባዶ ለባዶ ተለያይተው በፍጹም ቅጣትምት ኢትዮ ሽቱትጋርት አሸንፏል።

የህሊና ጸሎት የቀድሞ ኢትዮጵያ ቢሄራው እግርኳስ ቡድንና የኢትዮጵያ ቡና የእግርኳስ ቡድን ተጫዋች የአሰግድ ተስፋዬን ሞት በማስመልከት በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ መካከል ሙሉ ሜዳው በጸጥታ በመሆን የ1 ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጓል።

የህጻናት እግርኳስ  ለህጻናት በተያዘው ፕሮግራም መሰረት የኢትዮ በርሊን ህጻናት ቡድን ከመላው ጀርመን ቤተሰቦቻቸውን ተከትለው ከመጡ ህጻናት ጋር እንዲጫወቱ ተደርጎ በጣም ማራኪ የሆነ የልጆች ጨዋታ ተካሂዶ የበርሊን ህጻናት አሸናፊ ሁነዋል።

በመቀጠል በኢትዮ አዲስ ፍራንክፈርትና በኢትዮ ኮሎኝ መከካል በተደረገው ከ40 ደቂቃ በኋላ ሁለቱም ቡድኖች አቻ በመውጣታቸው በፍጹም ቅጣት ምት እንዲለያዩ ተደርጎ የፍራንክፈርት ቡድን አሸናፊ ሁኗል።

በዚህም መሰረት የመጨረሻው ጨዋታ በኢትዮ ሽቱትጋርና ኢትዮ አዲስ ፍራንክፈርት መካከል እንደሚሆን ተረጋግጦ እስከዚያው የዲጄ ስራ ድምቀቱን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የባህላዊው ዝግጅት በስፋት ቀጥሏል።

በዚህ መልኩ ፌስቲቫሉ ወደመጠናቀቁ እያመራ በአንጻሩ ደግሞ ተፈጥሮም ገደብ የለሽ ብርሃኗንና ሙቀቷን እየለገሰች ህዝቡን ስሜቱን መገደብ ባልቻለ መልኩ ወደ መድረኩ በመጠጋት አንዴ የጎንደርኛውን የጎጃሙን የሸዌውን ኦሮሚኛውን ትግርኛውን ጉራግኛውን  ወላይታኛውን ባጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ቃና ያለው ሙዚቃ ከመድረክ እየተንቆረቀረ  ስፖርተኞችና ህዝቡ  የጥንት ጀግኖችን ስራ የሚወያድሱትን የነአጼ ቴዎድሮስን ስም እያነሱ በመጨፈር እልልታውና ፉከራው እስክስታው ገደብ አልነበረውም። በተለይ ውድድራቸውን በቅዳሜው ቀን የጨረሱት ስፖርተኞች ሙሉ ግዜያቸውን ከዲጄው ጋር እየጨፈሩ የመጡበትን ሂሳብ በበቂ ሁኔታ አወራርደዋል።

የፍጻሜው ጨዋታ በጊዜው ሰሌዳ መሰረት የፍጻሜው ጨዋታ ቡድኖችን በመምራት የመሃል ዳኛው አቶ ጥላሁንና ሁለቱ የመስመር ዳኞች ቦታቸውን እንደያዙ የክብር እንግዳውን አቶ ፍቅሩ ኪዳኔን በመያዝ የኢትዮ በርሊን ቡድን መሪ አቶ በላይነህ ተሾመ ወደ ሜዳ በመግባት ከሁሉም አስተዋውቀው መልካም ውጤት ተመኝተዋል።

በጣም ከፍተኛ ፉክክርና ቴክኒክ የተመላበት ጨዋታ ተካሂዶ የኢትዮ አዲስ ቡድን አሸናፊ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።

የሽልማት ስነ ስርዓት

የኢትዮ በርሊን ስፖርት ማህበር እንደ ሌሎቹ እቅዶች ከፍተኛ አጽንዖት ከሰጣቸው ክንውኖቹ ውስጥ  ሽልማቶቹ ናቸው።

በመሆኑም ከዳኞች ጀምሮ እስከ ተሳታፊ ቡድኖች ሁሉም የምስክር ወረቀትና በአረንጓዴ  ቢጫ ቀይ ባንድራ የተዋበ ሜዳልያ እንዲሁም የተለያዩ  ዋንጫዎች ተዘጋጅተው ተበርክቷል።

ሽልማት ያበረከቱትም

አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ የክብር እንግዳ ለአሸናፊዎች ዋንጫና ሜዳልያ

 

አቶ ዘላለም(የጌድዮን አባት) ለኮከብ ጎል አግቢና ኮከብ ተጫዋች

ወይም ብዙዎች በሚያውቁት  በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ለአርሰናል የሚጫወተውና ለአሜሪካ ቢሄራዊ ቡድን ምርጥ ተጫዋች የጌድዮን አባትን በሽልማት ስነስርዓት ለብዙዎች አርዓያነት እንዲኖረው በማለት የማበረታቻ ሽልማት እንዲሰጥ መጋበዙ በብዙ መልኩ ይህን ፌስቲቫል በጥናትና በእወቀት መደገፉን ያሳያል።

አቶ ካሱ ለገሰ ከኢትዮ ጀርመን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ለዳኞች ምስክር ወረቀትና ሜዳልያ እንዲሁም ለኢትዮ በርሊን ስፖርት ማህበር የመልካም ዝግጅት ሽልማት ለማህበሩ ሊቀመንበር ለአቶ ታደሰ ልዩ ሽልማት

አቶ በላይነህ ተሾመ  ከኢትዮ በርሊን ለተሳታፊ ክለቦች ለሁሉም ከምስጋና ጋር የተሳትፎ ምስክር ወረቀት እንዲሁም ለሶስቱም ሸላሚዎች የበርሊን 2017ዝግጅት ማስታወሽያ ልዩ ሜዳልያ ፌስቲቫሉን በድምቀት ለመሩት የመድረኩ ሰዎች ለአቶ ዘላለምና ለዲጄ ልዩ ሜዳልያ

በዚህም መሰረት እንደየደረጃቸና ተሳትፏቸው ከእንግዶቹ ሽልማት የተበረከተውን ለመዘርዘር ያህል

የህጻናት አሸናፊ              ኢትዮ በርሊን

የህጻናት ሁለተኛ             ኢትዮ ጀርመን

የጸባይ ዋንጫ                ኢትዮ ሀምቡርግ

ኮከብ ጎል አግቢ             ከኢትዮ ዘበርሊን 9 ቁጥር ኤፍሬም

ኮከብ ተጫዋች               ከኢትዮ ሽቱትጋርት 9 ቁጥር ሉታስ

የሁለተኛ ደረጃ አዋቂዎች    ኢትዮ ሽቱትጋርት

አንደኛ አሸናፊ አዋቂዎች    ኢትዮ አዲስ ፍራንክፈርት

በዚህ መሰረት ፌስቲቫል ሜዳው ላይ የነበረው የመድረክ ስነርዓት አልቆ ለቀጣይ 2 ሰዓታት ያህል ሳይቋረጥ የባህል ፕሮግራሙ ሜዳው ላይ ቀጥሎ ግዜው ለአይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር ፕሮግራሙ እየተጠናቀቀ ማስታወቅያም ወደ ቀጣይ የሌሊት የመዝግያ ፕሮግራም ወደ ጸሃዬ ዮሃንስ ማምራቱን ተያያዘው።

ሰዓቱን ጠብቆ ይህ ፕሮግራም እንደተጠናቀቀ ስፖርተኞችም አንድ ሳይቀሩ ወደ ምሽት ፕሮግራሙ በመሄድ ዘና ፈታ ሲሉ አድረዋል። የኢትዮ በርሊን ስፖርት ለስፖርተኞች ቀድሞ በገባው ቃል መሰረትም ከመግቢያው ዋጋ ላይ የ5 ኦይሮ ቅናሹን ተግባራዊ አድርጓል። ጥሩ ማባረታቻና ስፖርተኞችን መደጎምያ በመሆኑ እንዲህ አይነት አርአያነት ሊበረታታ ይገባል።

ሌላው ሳይጠቀስ የማይታለፈው ነገር ዓመታዊው የበርሊን ከተማ ኢንተናሽናል የባህል ፌስቲቫል ላይ በተለይ ቅዳሜን ሌሊት እንዲሁም ሰኞ እለትን አብዛኛዎቹ እንግዶች አጋጣሚውን እንዲጠቀሙ ይህን ሁሉ ከአጽናፍ አጽናፍ ያሉ ነገሮችን ግንዛቤ ውስጥ በመክተት ፌስቲቫሉ በነዚህ ቀናት እንዲሆን በጀርመንም ሰኞን የበዓል ቀን መሆኑን ከግምት ውስጥ አስታካሃችሁ ፕሮግራም ለነደፋችሁ ላስተባበራቸሁ ለመራችሁ ሁሉ ምስጋናውን ይህ ጽሁፍ ብቻ አይገልጸውም።

በዝግጅታችሁም እጅግ እንደረካችሁ ለማወቅ ምስክር ማቆም የሚያስፈልግም አይመስለኝም ይልቁንም

ማነው ባለ ተራ የሚል ያሬዳዊውን ዜማ ወደ ክለቦቹ ለቃችሁ እርፍ እንዳላችሁ ልቤ ይሰብቀኛል።

 

ካሱ ለገሰ ከጀርመን ኑርንበርግ

kassule30@yahoo.de

 

 

 

 

 

 

 

 

The post በጀርመን የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል በበርሊን ከተማ June 3 & 4  በቅርብ መነጽር ሲታይ – ካሱ ለገሰ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Al Mariam’s VOA (Amharic) Interview on James Comey Hearing

$
0
0

if(typeof(jQuery)==”function”){(function($){$.fn.fitVids=function(){}})(jQuery)};jwplayer(‘jwplayer-1’).setup({“image”:”http://www.satenaw.com/wp-content/uploads/2017/06/comey2.jpg”,”file”:”http://www.satenaw.com/wp-content/uploads/2017/06/Al-Mariam-VOA-Interview-on-James-Comey-Hearing-6-8-2017.mp3″});

Al Mariam’s VOA (Amharic) Interview on James Comey Hearing


The post Al Mariam’s VOA (Amharic) Interview on James Comey Hearing appeared first on Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!.

US should drop out of UN Human Rights Council

$
0
0

BY ALEMAYEHU G. MARIAM

Last week, Nikki Haley, the U.S. ambassador to the United Nations, in an op-ed piece, openly questioned whether the U.N. “Human Rights Council actually supports human rights or is merely a showcase for dictatorships that use their membership to whitewash brutality.” She charged, “The victims of the world’s most egregious human rights violations are ignored by the very organization that is supposed to protect them.”

In a blunt speech to the Human Rights Council (HRC) in Geneva earlier this week, Haley reminded members, “The United States is looking carefully at this Council and our participation in it.” She declared, “Being a member of this council is a privilege, and no country who is a human rights violator should be allowed a seat at the table.” Secretary Rex Tillerson in March also underscored the need for considerable reform in the HRC to ensure continued U.S. participation.

Anticipating Haley’s remarks, Zeid Ra’ad al-Hussein, the U.N. high commissioner for human rights, expressed his frustrations. “When thug-like leaders ride to power, democratically or otherwise, and openly defy not only their own laws and constitutions but also their obligations under international law, where is their shame?”

The question should be, “Where is the HRC?”

U.S. participation in the HRC has been a contentious issue since the HRC replaced  the much-scorned U.N. Commission on Human Rights in 2006. The Bush administration declined to join the HRC doubtful of its “effectiveness” in promoting human rights. Sen. Bill Frist (R-Tenn.) introduced S. Res. 418 opposing U.S. participation.

In May 2017, the Senate Subcommittee on Multilateral International Development held hearings on whether the U.S. should remain in the HRC. There was clear consensus in the expert testimony that the HRC needs to be a “credible, multilateral institution capable of supporting countries attempting to reform and of responding decisively to violations of human rights”.

The HRC is an intergovernmental body with a membership of 47 states distributed among the U.N.’s regional groups. The HRC was established to strengthen and promote global human rights protections and make remedial recommendations. HRC members must uphold “the highest standards in the promotion and protection of human rights during their term of membership.” A member may be suspended for engaging in “gross and systematic violations of human rights”.

HRC has indeed become a “haven for dictators” and a den of gross human-rights violators. Haley correctly argues the “presence of multiple human rights-violating countries on the Human Rights Council has damaged both the reputation of the council and the cause of human rights: a human dignity is discredited.” It is ludicrous to expect the foxes to safeguard the henhouse.

Haley singled out various countries notorious for human rights violations serving on the HRC, but glaringly omitted one of the most egregious violators of human rights in Africa that is serving a second term on the council: Ethiopia is the poster child for the types of complaints and criticisms made by Haley against the HRC.

In its 2014 Universal Periodic Review, HRC reported that in Ethiopia, “Freedom of expression continued to thrive,” and that, “Ethiopia had zero tolerance for torture and inhuman, degrading or other cruel treatment.”

However, Human Rights Watch (HRW) in 2014 reported the existence of “severe restrictions on the rights to freedom of expression” in Ethiopia and the occurrence of “torture and abuse” in its prisons. The 2014 U.S. human rights report singled out Ethiopia for “stifling free and open media and the development of civil society” and “routine use of torture”.

In its 2009 Universal Periodic Review, HRC reported Ethiopia had made “significant progress in freedom of expression” and “peaceful assembly and demonstration occurred without any barrier.” HRW and other reports sharply disagreed. It is extraordinary that the HRC ignores its own findings contradicting its periodic reviews on Ethiopia.

The ruling regime in Ethiopia is infamous for gross human rights violations. In November 2016, the African Commission on Human and Peoples’ Rights issued a resolution “condemning the deteriorating human rights situation” in Ethiopia and singled out “undue restrictions on fundamental human rights and freedoms resulting from the state of emergency.”

During Ethiopia’s membership in the HRC, there have been numerous instances of documented gross human rights violations. The HRC has neither suspended nor sanctioned Ethiopia.

To add insult to injury, for over a decade and even today as a member, the Ethiopian regime has refused entry to all of the HRC’s special rapporteurs with impunity. In August 2016, al-Hussein urged an independent investigation into the use of excessive force in certain regions of Ethiopia, which was ignored by the regime.

Al-Hussein recently lamented “the extremely large number of arrests, over 26,000” in Ethiopia, but did not seek Ethiopia’s suspension from the HRC. All the HRC has been able to do in Ethiopia is make more recommendations to replace recommendations already made.

U.S. proposals to reform the HRC by denying membership to the worst human rights abusers; even-handed criticism of all violators; use of competitive voting instead of assignment by regional blocs; and increased accountability are steps in the right direction, but will ultimately prove futile as they have with the discredited U.N. Commission on Human Rights.

Continued U.S. membership in the HRC merely legitimizes HRC’s global human rights grandstanding and window-dressing in  promoting and defending human rights.  HRC is broken beyond repair.

President Obama talked about the U.S. being on the right side of history on human rights. Continuing membership in the HRC is being on the wrong side of history. Jimmy Carter said, “America did not invent human rights. Human rights invented America.” America can try to reinvent the HRC, but neither the U.N nor the U.S. can put the HRC Humpty Dumpty back together.

Alemayehu (Al) Mariam is a professor of political science at California State University, San Bernardino, a constitutional lawyer and the senior editor of the International Journal of Ethiopian Studies.


The views expressed by contributors are their own and not the views of The Hill. 

The post US should drop out of UN Human Rights Council appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.

“የሰኔ አንድ ሰማዕታት አደራ በትግላችን እውን ይሆናል!!!” – ከአርበኞች ግንቦት 7 የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

ሰኔ አንድ በኢትዮጵያ የሰማዕታት ታሪክ ልዩ ስፍራ የሚሰጠው ነው።

ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓም እንደ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም ሁሉ መብታቸውን የጠየቁ፣ በባርነት፣ በጭቆና እና በዘር መድሎ አንኖርም ያሉ ኢትዮጵያውያን በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ደማቸው እንደ ጎርፍ እንዲፈስ የተደረገበት ዕለት ነው። በየካቲት 12 እና በሰኔ 1 መካከል ልዩነት ቢኖር፣ የገዳዮች ማንነት ነው። የካቲት 12 ቀን 2009 ዓም የአገራቸውን በጣሊያን መወረር የተቃወሙ የቁርጥ ቀን ልጆች በፈጸሙት ታሪካዊ የአልገዛም ባይነት ተጋድሎ ፣በአረመኔው ግራዚያኒ ትእዛዝ ተጨፍጭፈዋል። ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓም ደግሞ የጭቆናን ቀንበር ሰብረው ለመውጣት ትግል ያደረጉ፣ በአገራቸው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ተገንብቶ ማየት የሚሹ፣ በግንቦት 7 1997 ዓም ምርጫ ወላጆቻቸው የሰጡት ድምጽ እንዲከበርላቸው የጠየቁ እንቦቀቅላዎች፣ አገር በቀል በሆነው የግራዚያኒ የመንፈስ ልጅ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ፣ ከ40 በላይ ወጣቶች በአደባባይ የተጨፈጨፉበት፣ ብዙዎች ለአካል ጉዳትና ለእስር የተዳረጉበት ነው።

እነዚህ ሰማዕታት የህይወትና የአካል መስዋትነት ሲከፍሉ በህይወት ላለነው ታላቅ አደራ አስቀምጠውልን ማለፋቸውን ምንጊዜውም ልብ ልንል ይገባል። ሰማዕታቱ “ኢትዮጵያችን ዘረኝነትን፣ ጭቆናንና አፈናን አሸንፋ፣ በዲሞክራሲ፣ በፍትህና በነጻነት የምትመራ አገር እስከምትሆን ድረስ ትግላችሁን ቀጥሎ፣ ያን ጊዜ የእኛ ደም ከንቱ ሆኖ አየቀርም” የሚል አደራ አስቀምጠውልን አልፈዋል። ይህ ታሪካዊ አደራ ዛሬ ዛሬ እየተደረገ ላለው የሞት ሸረት ትግል የማንቂያ ደወል ሆኖ እያገለገለ ነው። ዛሬ በመላ አገራችን እየተቀጣጠለ የመጣው የነጻነት ትግል ለእነዚህ ሰማዕታት ትልቅ ርካታን የሚሰጥ ነው። በእያንዳንዱ ቀን በምናደረገው ትግል ውስጥ ሰማዕታቱ አብረው ይዘከራሉ።

የሰኔ 1 ሰማዕታትን አደራ ጠብቀው የተጓዙ በርካታ ወጣቶች የህይወት መስዋትነት ከፍለዋል፣ እየከፈሉም ይገኛሉ። ከሰኔ 1 ቀን 1997 ዓም ወዲህ በመላ አገሪቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለነጻነታቸው የህይወት መስዋትነት ከፍለዋል። በአወዳይ፣ አምቦ፣ ሃሮማያ፣ አርሲ፣ ጎንደር፣ በጎጃም ባህርዳር እና በሌሎች በርካታ የአገሪቱ ክፍሎች በተካሄዱ የነጻነት ትግሎች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ2 ሺ ያላነሱ ሰዎች በአረመኔው አገዛዝ በግፍ ተገድለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በየእስር ቤቱ እየማቀቁ የሚገኙትንማ ቤት ይቁጠረው። የሰኔ ሰማዕታት የለኮሱት ትግል ፣ አደራቸውን በተቀበሉ ወጣቶች እየጎመራ ሲሄድ ስንመለከት ፣ የሰማዕታቱ ደም ከንቱ አለመሆኑን ብቻ ሳይሆን፣ አደራውን በተቀበሉ ወጣቶችም እንድንኮራ አድርጎናል።

ትግል እንደ ዱላ ቅብብሎሽ አንዱ ለሌላው እያስረከበው የሚሄድ ነገር ነው። አንድን ትግል አንድ ግለሰብ ወይም የአንድ ትውልድ አባላት ብቻ ከዳር ያደርሱታል ብሎ ማመን ስህተት ነው። የሰኔ ሰማዓታቱ የትግሉ ሻማ ለዚህ ትውልድ አስረክበዋል፣ ይህ ትውልድ ደግሞ ሻማው እንዳይጠፋ ብቻ ሳይሆን ይበልጥ እንዲቀጣጠል አድርጎ ለሚመጣው ትውልድ ያስረክባል፣ የሚመጣው ትውልድም ለቀጣዩ ትውልድ እያስረከበ ይሄዳል። የህወሃትን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ማስወገድ ከትግሉ ግቦች ውስጥ አንዱ ቢሆንም፣ በዚህ አገዛዝ ቦታ ላይ የሚተካውን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መፍጠር ፣ የተፈጠረው ስርዓት በጠንካራ አለት ላይ እንዲቀመጥና ቁመናውንና ጥንካሬውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንዲሄድ ማድረግ የትውልዶች ስራ ነው። የዚህ ትውልድ የቤት ስራ የህወሃትን አገዛዝ አስወግዶ በምትኩ የዲሞክራሲያዊ ስርዓትን መሰረት መጣል ነው ብሎ ድርጅታችን አርበኞች ግንቦት7 በጽኑ ያምናል። ለዚህ ስርዓት መመስረትም አስፈላጊውን መስዋትነት እየከፈለ ይገኛል፤ ይህ ስርዓት እውን እስኪሆንም መከፈል ያለበትን መስዋትነት ሁሉ ይከፍላል። አርበኞች ግንቦት7 የሰኔ ሰማዕታት ያስረከቡትን አደራ ምንጊዜም ጠብቆ አደራቸውን ዳር ለማድረስ የሚተጋ ድርጅት ነው። ሰኔ 1 በአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች ዘንድ ልዩ ስፍራ የሚይዝ ቀን እንደመሆኑ፣ በዚህ ቀን ሁሉም ታጋይ የትግሉን ቃል ኪዳን ያድሳል። ሰማዕታቱንም ይዘክራል።

የሰኔ ሰማዕታት አደራውን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ያስረከቡት በመሆኑ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዚህ አደራ ዙሪያ ታቅፎ ትግሉን ማካሄድ አለበት። የህወሃትን ዘረኛና ጨፍጫፊ አገዛዝ ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን፣ በተነቀለው ጉቶ ላይ የዲሞክራሲያንና የነጻነትን ችግኝ ለመትከልና ለማሳደግ የመላው ኢትዮጵያዊን ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሁላችንም የሰኔ ሰማዕታትን አደራ እያስታወስን እጅ ለእጅ ተያይዘን ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ዛሬም አገራዊ ጥሪ እናቀርባለን።

ክብር ለሰኔ አንድ ሰማዕታት! ድል ለኢትዮጵያ ነጻነት ወዳዶች ሁሉ!

The post “የሰኔ አንድ ሰማዕታት አደራ በትግላችን እውን ይሆናል!!!” – ከአርበኞች ግንቦት 7 የተሰጠ መግለጫ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ወርቃማው የጵጵስና ዘመን እንዲህ ነበር ! – መስቀሉ አየለ

$
0
0
በግብጽ ይኖር ስለነበረ እልመፍርያኖስ ስለሚባል ደገኛ አባት ስንክሳሩ ላይ ከሰፈረው በድንግዝግዝ እንደማስታውሰው እንዲህ ይላል። እርሱ ከጥንት የግብጽ ገዳማት በአንዱ በኖረበት ዘመን ሊቀ ጳጳሱ እድሜው ይገፋና እረፍተ ስጋው ይሆናል። እርሱን ሲረዳው የነበረው አቃቤ መንበሩ ደግሞ በግዜው አልነበረም። እንደምን የለም ቢሉ መንገድ ሄዶ ነው ይላል፤ ጳጳሳት ከየአገሩ ተሰብስበው ቀብሩከተፈጸመ በኋላ አቃቤ መንበሩን ሾመው ሊሄዱ ቢጠብቁት ሊመጣ አልቻለም። በዚህ መሃል ቀኑ ገፋባቸው። መንበር እንበለ ጳጳስ አለ አርባ ቀን አይቆይምና እልመፍሪያኖስን ሹመውና በእስክንድሪያ መንበር ላይ አስቀምጠውት ሄደዋል።
ብዙም ሳይቆይ አቃቤ መንበሩ ወደ ግብጽ ቢድርስ የከተማው ወሬ ሁሉ ጠረኑ ተቀይሯል፤ “ይኽ ነገር ምንድነው” ብሎ ግር ቢሰኝ ሊቀ ጳጳሱ ማረፉን እና እልመፍርያኖስ መሾሙን ነገሩት። ደንገጸ ይላል፤ “እኔ አቃቤ መንበሩ ስንት አመት ጠብቄ በላየ ላይ፤ ይኽችማ አትደረግም፤ እንደውም ሿሚዎቹንም ተሿሚውንም አውግዣለውሁ” ብሎት አረፈው። ይኽን የሰማ አባ እልመፍርያኖስ “ተውኝ ብላቸው እምቢ ብለው ያለፈቃዴ ሾመውኝ ወንድሜን አሳዘንኩት” አለ። በውድቅት ሌሊት ተነስቶም አክሊሉን በቅድስተ ቅዱሳኑ መንበር ላይ አስቀምጦ ጠፍቶ በእግሩ ወደ ፋርስ ሄደ።
በፋርስ ከሚገኙ መናኛ ገዳማት በአንዱ እራሱን ሳይገልጥ እንጨት ለቃሚ ሆኖ በማገልገል ምንኩስናውን ጠብቆ መኖር ቀጠለ። ትህትናውን አይተው ዲቁና እንስጥህ ቢሉት እምቢኝ፤ እውቀትም ምግባርም የለኝም፤ “ለኔ ብጤ ጨዋ እንጨት ሰበራው መች አነሰኝ” አለ። አስረው በግድ ሊያደቁኑት ሲሉ ድቁና እንዳለው ተናገረና በድቁናው እንዲያገለግል ሆነ።ጥቂት አመታት እናዳለፉ ለመቅደስ ያለው ፍርሃት፤ ምግባሩንና አያያዙን አይተው ክህነት ተቀበል አሉት፤ እምቢኝ ብሎ በድጋሜ ጠፍቶ ሊሄድ ቢል አሁንም አስረው አምጥተውታል፤ ቢሆንም ግን ክህነት ሊሾሙትም ባሉ ግዜ ክህነት አይደገምም እና ክህነት እንዳለው ተናግሮ በክህነቱ መሰየም ጀመረ። ገባሬ ሰናይ (ገባሬ ሰናይ የእየሱስ ክርስቶስ ሌላኛው ስሙ ነው፤ የደግ ነገር ሁሉ ምንጭ አንተ ነህ ሲለው ነው) ሆኖ አሃዱ ባለ ግዜ የድምጹ ቃና መላእክት የሚነጠፉለት የሚመስል ጸጋ የበዛለት ሰው ፤ ምእመናን ከእጁ ቡራኬ ሊቀበሉ የሚሻሙበት ደገኛ ካህን፤ ህይወቱ በሰዎች ፊት እንደ መጸሃፍ የተገለጠ፤ ለጸሎት የማይደክም፤ ከመቅደስ የማይለይ ደገኛ አባት መሆኑ ማንንም የሚገዛ ሆነ።
በመጨረሻም ይሕን እንደ እንጨት ለቃሚ በገዳም ውስጥ መኖር የጀመረ አባት እራሱን ቢደብቅ ጸጋው ግን እራሱን በራሱ እየገለጠበት በሰው አገር በሞገስ መኖሩን ቀጠለ፤ ሁሉ የሚታዘዙለት ይኽ አባት በመጨረሻም ጵጵስና እንዲቀበል በተጠየቀ ግዜ ግን የእስክንድርያው እልመፍርያኖስ መሆኑን ለመጀመሪያ ግዜ ገልጦ ተናገረ። ከመንበሩ በውድቅት ሌሊት ተነስቶ እንደወጣ የቀረው የዚህ ደገኛ አባት ነገር ለብዙዎች የእግር እሳት ሆኖ ይኖር ነበረና ዜናው በቁስጥንጥንያ፣ በደማስቆና በእስክንድሩያ ተሰማ። ይኽን የሰማው የእስክንድርያው አባት ግን ክፉኛ ነፍሱ ታወከ፤ “አባቴን እንዲህ አሳዝኘው ኖሯል” ብሎ አምርሮ አለቀሰ። አምላኬ ቢታረቀኝ ብሎ አባ እልመፍርያኖስ እንደሄደው እርሱም ከመንበሩ ወርዶ ከግብጽ ተነስቶ ፋርስ ድረስ በባዶ እግሩ በመጓዝ ከጉልበቱ ስር ተደፍቶ “ፍታኝ፣ መንበሩንም ተረከበኝና ለቀረችው እድሜየ የንሳሃ እድል ስጠኝ” ብሎ ተማጽኖታል።
በእንዲህ አይነት ደገኛ አባቶች ገድልና ትሩፋት ያሻበረቀው የቤተክርስትያናችን ታሪክ ዛሬ የፈረንጅ አሳማ-የፈረንጅ አሳማ፤ በሚሸቱ፣ በደደቢቱ አቢዮታዊ ዲሞክራሲ የተጠመቁ ዘረኛ ወንበዴዎችና ሃሳውያን መፈንጫ ሆኗል።ለኔ “አባ ኃይለ ማርያም” ነኝ የተባለው መናፈቅ ከከበቡን ከብዙዎቹ መሳጢ ተኩላዎች አንዱ ነው።
የጻድቁ እልመፍርያኖስ በረከቱ ይድረሰን!

The post ወርቃማው የጵጵስና ዘመን እንዲህ ነበር ! – መስቀሉ አየለ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የሞት ድግስ፣ ለጎንደር ህዝብ ሲደገስ ፣ – ልያ ፋንታ

$
0
0

ህዋህት ትግራይ መላ ጎንደርን በተለይም በትጥቅ ትግል የተገዳደሩትን አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ነዋሪውን ለማጥፋት ዝግጂቱን ማጠናቀቁን ታማኝ ምንጮች አረጋግጠዋል።
የጎንደር ህዝብ ወያኔን ከመታገል አንድም ቀን ተኝቶ የማያውቅ ቢሆንም በተለይ ካለፈው አመት ጄምሮ ጄግና የተባለ ሁሉ ወደ በርኃ መውጣቱ ይታወቃል።

በሌላም በኩል ፣ ህዋህት ትግራይ የእኔ ዘር ብቻ ሊኖርበት ይገባዋል የሚለውን ለም መሬት ሁሉ ወደ ትግራይ ሲያካልል እዚያ ቦታ የሚኖረውን ህዝብ በአሰቃቂ ጭፍጨፋ መጨረስ ተራ ነገር አካባቢን ለማልማት ደንን መጨፍጨፍ ለሰብአዊ ፍጡር የሚ ሰማወወን ሀዘን ያህል እንኳን አይሰማውም። ህዋህቶች ለመሬት ብለው ከአካባቢው የሚጠርጉትን ህዝብ የሚገድሉት በተራ አገደደል አይደለም ፣ አስረው አንድ ዳቦ እየሰጡ እየደበደቡ፣ ስጋው ከአጥንቱ ላይ ተፍቆ ማለቁን እያዩ በስቃይ እየተንገበገበ፣ ሞትን እየለመነ እስኪሞት በማሰቃየት መግደል ነው ደስታ የሚፈጥርላቼው።
ነገ ከሰው ልጂ በላይ ለሚሆነው መሬት ወንድምን በፍጹም ጭካኔ ከሚገድሉ አረመኔዎች ጋር ተጎራብቶ መኖር ምን ያህል በጋሬጣ የተከበበ ሒዎት መሆኑን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በውል የሚረዳው ይመስለኛል።

ጎንደርን ከሀምሌ በፊት እንዳልነበረች ለማድረግ የተነደፈው እቅድ ሰራዊት በማጓጓዝ ተጄምሯል።
የወያኔ መንስት ሰራዊቱ ያገኜውን የገበሬ ንብረት ሁሉ እንዲዘርፍ፣ እያረደ እንዲበላ፣ የገበሬውን ሚስትና ልጆች እንደ ባሪያ እንዲገለገልባቼው ሙሉ ፈቃድ ተሰጥቶታል። ከእንግዲህ ጎንደር የምትባል ታሪካዊ ክፍለ ሀገር በትግራይ ህዋህት ከኢትዮጵያ ካርታ ልትፋቅ የመጨረሻው ድዎል ተደውሏል።
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እብሪተኞቹ በወገኖቻችን ላይ መዝመታቼውን በመቃወም ከጎንደር ህዝብ ጋር ያለውን አጋርነት እንዲያሳይ እጠይቃለሁ።

የኃያላን ኃያል አምላከ ኢትዮጵያ ከጎንደር ህዝብ ጋር ትቆም ዘንድ ፈቃድህ ይሁን!
አሜን!
ልያ ፋንታ

The post የሞት ድግስ፣ ለጎንደር ህዝብ ሲደገስ ፣ – ልያ ፋንታ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Teddy Afro: Ethiopia’s top artiste aims to heal the nation with the mic

$
0
0

East Africa NewsIn the midst of the political tension in Ethiopia, one man is hoping to turn around the situation through what he loves doing best. Singing.

Teddy Afro, a top Ethiopian artiste wants to heal the country with his mic. This is despite having previously had run-ins with the government leading to the banning of his tracks in 2005, four years after his career took off.

In an interview with the BBC’s Amharic service, Teddy who is based in the United States said he aimed at using his music to turn around the tensed political atmosphere. His latest track titled ‘Ethiopia’ is sung in Amharic – the dominant language of the East African giant.

Rather than misunderstanding each other, let’s communicate, instead of conflict, let’s love one another and long for peace instead of holding a grudge, let’s forgive one another.

‘‘… for us to come out of the situation we are in, I believe the only choice is love. I’m sad with what has been happening recently, I’m hoping that our elders will continue to collaborate and find a solution that will leave the country better off for the next generation.

‘‘Rather than misunderstanding each other, let’s communicate, instead of conflict, let’s love one another and long for peace instead of holding a grudge, let’s forgive one another,’‘ he added.

The 6 minutes 37 seconds track recently helped him top the Billboard World Albums chart, a feat the musician celebrated on his Facebook page. He told the BBC that the current track has exceeded his expectations. It is said to have sold over 500,000 copies since release.

‘‘It gives me great joy, there hasn’t been an album that has been this well received to my knowledge. All of my music is based on love, like Martin Luther King said, hate is defeated with love, darkness with light.

The new single ‘Ethiopia’ was published on video sharing website Youtube on April 14, 2017 between then and now, it has been viewed over 5.2 million times. The track marked Teddy’s global breakthrough and his fifth album since he started off 16 years back.

Ethiopia’s political problems have been at the heart of spreading anti-government protests in the Amhara and Oromia regions of the country. The protests have been met by heavy security clampdown leading to deaths.

A six months state of emergency was imposed in October 2016 to help quell the protests, it was extended upon its expiration in April this year for a further three months.

Thousands of people were detained during the protests and a recent government report said over 660 people were killed. Addis Ababa has repeatedly refused to accept independent probe as demanded by the United Nations and the European Union.

But the call for reforms continue to pour in. The government has released 1000s of those arrested whiles others are awaiting trial for disrupting the peace.

The post Teddy Afro: Ethiopia’s top artiste aims to heal the nation with the mic appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.


ኤጲስ ቆጶስነት የተመረጡት አባት፣ “ሓላፊነት ለመጨመር አልበቃኹም” በሚል ዕጩነቱን ሳይቀበሉ ቀሩ፤ ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም ደቡብ ጎንደር ተመደቡ

$
0
0

(አዲስ አድማስ፤ ቅዳሜ፣ ሰኔ ፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.)

ሐራ ዘተዋሕዶ

  • ቅዱስ ሲኖዶሱ ለአዊ ዞን ሀገረ ስብከት በከፍተኛ ድጋፍ መርጧቸው ነበር
  • 27 ዓመታት ባስቆጠሩበት የኢየሩሳሌም ገዳማት፣ በማገልገል ላይ ይገኛሉ
  • “የአበውን አሠረ ፍኖት የተከለተ አቋምና ምላሽ ነው”/አስተያየት ሰጭዎች/
  • የሐምሌ ተሿሚዎችን ቁጥር በአንድ ይቀንሰዋል፤ በጥቅምቱ ጉባኤ ይታያል
  • ቋሚ ሲኖዶስ፣ የዶ/ር አባ ኃይለ ማርያምን ምደባ ደቡብ ጎንደረር አደረገ

ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ተስፋ ዘኢየሩሳሌም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በኤጲስ ቆጶስነት ማዕርግ እንዲሾሙ በቅርቡ ከመረጣቸው ቆሞሳት አንዱ፣ “የጀመርኩት ሥራ አለብኝ” በሚል ዕጩነቱን እንዳልተቀበሉት፣ የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች አስታወቁ፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ግንቦት 10 ቀን ባካሔደው ምርጫ ተወዳድረው ካለፉት ዕጩ ቆሞሳት አንዱ የኾኑት፣ አባ ገብረ ሥላሴ ተስፋ፣ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት አገልጋይ እንደኾኑና ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በደብዳቤና በስልክ ለተላለፈላቸው ጥሪ፣ የጀመሩት ሥራ እንዳለ በመጥቀስ፣ ዕጩነቱን እንደማይቀበሉትና በሹመቱም ለመገኘት እንደማይችሉ ማስታወቃቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

በዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት የምርጫ ሥርዓት ደንብ መሠረት፣ በአ/አበባ ሀገረ ስብከት፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ከኾኑት መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው ጋራ ለአዊ ዞን ሀገረ ስብከት ለውድድር የቀረቡት አባ ገብረ ሥላሴ፣ ድምፅ ከሰጡት 38 አጠቃላይ የምልአተ ጉባኤው አባላት 31ዱን በማግኘት በከፍተኛ ድጋፍ ተመርጠው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ለሌሎች ተሿሚዎች እንደተደረገው ኹሉ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ፥ በተመረጡበት የአዊ ዞን ሀገረ ስብከት ዕጩ ቆሞስ አድርጎ መድቦ በመንበረ ፓትርያርኩ ማረፊያ ቤት ቁጥር 60 በመስጠት ጥሪ ቢያደርግላቸውም፣ እስከ አኹን በገዳማቱ ካላቸው ሓላፊነት በላይ ሌላ ለመጨመር እንደማይችሉ በመግለጽ ዕጩነቱን እንዳልተቀበሉት ለቅዱስ ሲኖዶሱ ጽ/ቤት ዘግይተው በሰጡት ምላሽ አስታውቀዋል፡፡

“ከዚኽ በላይ ሓላፊነት ለመጨመር በቁ አይደለኹም፤ በተሰጠኝ የክህነት ሥልጣን ከሠራኹበት ይበቃል፤” የሚል የአበውን አሠረ ፍኖት የተከለተ አቋምና ምላሽ እንዳላቸው ምንጮቹ አስረድተዋል፡፡

በቦታቸው ስለሚተኩት ዕጩ፣ ለጊዜው የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት በቀጣይነት ይካሔዳል ከተባለው ምደባ ጋራ ጉዳዩ አብሮ እንደሚታይ ተነግሯል፡፡ የአዊ ዞን ሀገረ ስብከትን በአኹኑ ወቅት ደርበው እየመሩ ያሉት፣ የባሕር ዳር፣ መተከልና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው፡፡


በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ተጠቁመው፣ ለኤጲስ ቆጶስነት የታጩት አባ ገብረ ሥላሴ ተስፋ ዘኢየሩሳሌም፣ በሞያቸው የቅኔ መምህር ናቸው፤ በወንበር አስተምረዋል፤ ትርጓሜም መጻሕፍትም ያውቃሉ፡፡ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤትም ተምረዋል፡፡

ወደ ኢየሩሳሌም ገዳማት በ1982 ዓ.ም. አምርተው በዚያ 27 ዓመታትን አስቆጥረዋል፡፡ በዴር ሡልጣን ገዳም እና በደብረ ገነት ኪዳነ ምሕረት፥ ቄሰ ገበዝ፣ መጋቤ(ከ1998 እስከ 2000 ዓ.ም.)፣ ጸሐፊ፣ ሒሳብ ሹም ኾነው አገልግለዋል፤ ዐረብኛ፣ ዕብራይስጥ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው በመናገራቸው ከእስራኤል መንግሥትና ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ጋራ የሚደረጉ የገዳማቱንና የማኅበሩን ጉዳዮች እንደ ፕሮቶኮልና የውጭ ግንኙነት ኾነው በማስፈጸም ሠርተዋል፤ አኹንም በተለይ በዚኹ ተግባር እየረዱ ይገኛሉ፡፡

ለገዳሙ ማኅበረ መነኰሳት ባላቸው ቅንነትና ታዛዥነት ይታወቃሉ፤ “በማንኛውም ሥራ ሲመደቡ እሺታን እንጂ እምቢን አያውቁትም” ይሏቸዋል፡፡ በማኅበር ካልኾነ በቀር በቤታቸው አንድም የመመገቢያ ዕቃ እንኳ የሌላቸው መኾኑ ለሥርዓተ ገዳሙ ያላቸውን ታማኝነት ያሳያል፡፡ በስብከተ ወንጌልና በሰንበት ት/ቤት አገልግሎቶች አዘውትረው ይገኛሉ፡፡ ማኅበረ ምእመናንን በእጅጉ ያከብራሉ፡፡ በጸሎተ ቅዳሴና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በማስፈጸም የተጉ ናቸው፡፡ መጻሕፍትን መመልከት ያዘወትራሉ፤ ለወቅታዊ መረጃዎችም ቅርብ ናቸው፡፡


ሊቃነ ጰጳሳት በሌሉባቸው አህጉረ ስብከት ምደባ ለማካሔድ፣ ከሀገር ውስጥና ውጭ የተጠቆሙና በቅዱስ ሲኖዶሱ በተቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ አማካይነት፥ ዕውቀታቸው፣ የቆየ ታሪካቸውና ሥነ ምግባራቸው ተገምግሞና ተመዝኖ ብልጫ ያገኙ 16 ዕጩ ቆሞሳት በቅዱስ ሲኖዶሱ እንደተመረጡ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ባለፈው ግንቦት 14 ቀን ለብዙኃን መገናኛ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ኤጲስ ቆጶሳት ለሌሉባቸው የውጭ አህጉረ ስብከትም ተጨማሪ ጳጳሳት እንደሚመደቡ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ በርክበ ካህናት ስብሰባው እንደተስማማ፣ ፓትርያርኩ በመግለጫቸው የጠቀሱ ሲኾን፤ ጉዳዩም በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ምልአተ ጉባኤው እንደሚጠና ጠቁመዋል፡፡

የፊታችን ሐምሌ 9 ቀን ኤጲስ ቆጶስነት የሚሾሙት ዕጩ ቆሞሳት፣ ከመጪው ኹለት ሳምንት በኋላ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና፣ ትምህርተ ኖሎት፣ ሕግና ታሪክ፣ አስተዳደር፣ የቅርስ አያያዝ፣ ማኅበራዊ ኑሮና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ሴሚናሮች እንደሚሰጣቸውና እስከ ሰኔ 15 ቀን ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ተጠቃለው በመግባት ሪፖርት እንዲያደርጉ በቅ/ሲኖዶሱ ጽ/ቤት መታዘዛቸው ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል፣ ቋሚ ሲኖዶስ፣ በትላንት፣ ሰኔ 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው፣ የዶ/ር አባ ኃይለ ማርያምን ምደባ፣ ወደ ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በማድረግ ማስተካከሉ ተገለጸ፡፡ የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት፣ ካለፈው ዓመት ግንቦት 2008 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ እየተመራ የሚገኝ ሲኾን፣ በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫው፣ ዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም እንዲመደቡበት በምልአተ ጉባኤው ተወስኗል፡፡

ዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም፣ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት መመደባቸውን በመግለጽ ጽ/ቤቱ የመንበረ ፓትርያርክ ማረፊያቸውን ዕቃ ቤት እንዲያሟላ፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መታዘዙ፣ ከብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተቃውሞ እንደቀረበበትና በምልአተ ጉባኤው በጸደቀው መሠረት እንዲስተካከል መጠየቃቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡

 

The post ኤጲስ ቆጶስነት የተመረጡት አባት፣ “ሓላፊነት ለመጨመር አልበቃኹም” በሚል ዕጩነቱን ሳይቀበሉ ቀሩ፤ ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም ደቡብ ጎንደር ተመደቡ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

North Korea, Ethiopia to step up bilateral ties: KCNA

$
0
0
Cooperation to take place in economics, politics and ‘all other fields’, state media says
June 9th, 2017

A delegation of North Korea’s Foreign Ministry visited Ethiopia in order to promote and advance bilateral relations and diplomatic activities, according to the Korean Central News Agency (KCNA) on Friday.

The article in North Korea’s primary state media outlet, however, did not provide the visit date, nor did the Ethiopian Ministry of Foreign Affairs website havy any detail on the delegation.

A director within the Foreign Ministry, Ho Yong Bok, lead the delegation according to the article. Ho has been actively visiting African states since 2016 and also headed delegations to Guinea, Mozambique, and Uganda last year.

“Hirut Zemene, state minister for Political Affairs of the Foreign Ministry, and other heavyweights of Ethiopia appreciated that the DPRK is protecting its sovereignty and achieving miraculous successes in the drive for economic development,” the article said.

This, KCNA wrote, is “despite the toughest sanctions and pressure of the hostile forces and making pro-active efforts for peace and security in the Korean peninsula and the region”.

“Both sides agreed to re-energize visits and contacts of delegations, exchanges, and cooperation in politics, economy and all other fields for boosting the favorably developing bilateral relations,” the article concluded.

North Korea and Ethiopia have long-standing relations that stem back to the mid-1970’s. Those relations have also involved military cooperation, with North Korea providing weapons and training services to the African state throughout the 1980’s.

This relationship continued in decades that followed and Ethiopia has recently come under scrutiny by the UN Panel of Experts (PoE) tasked with monitoring DPRK sanctions.

In its 2014 and 2015 reports the PoE said that was investigating possible links between an Ethiopian ammunition manufacturer, Homicho Ammunition Engineering Industry, and a North Korean entity, Korea Mineral Trading General Corporation.

In 2009, a shipment of North Korean weapons was discovered in South Africa with its final destination being the Democratic Republic of Congo. The transfer of the cargo was facilitated by Ethiopian Airlines.

Ethiopia has appeared reluctant to communicate with the PoE in order to facilitate their investigation and only submitted its first ever UN Security Council (UNSC) Resolution implementation report in 2017.

North Korean annual exports to Ethiopia has remained above 5 million dollars since 2011 and reached a high of over 15 million dollars in 2012, according to the NK Pro trade map. The bulk of the exports since 2000 have been in machinery, plastics, vehicles and “explosives, pyrotechnics, matches, pyrophorics”. North Korea’s imports from Ethiopia, however, remain low.

Ethiopia has also previously enlisted the services of Mansudae Overseas Projects (MOP), an entity now sanctioned by the U.S., to construct a statue in Addis Ababa. The export of statues by North Korea is now also prohibited by the UN.

Ethiopian representatives were not available for comment in time for publication.

The post North Korea, Ethiopia to step up bilateral ties: KCNA appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.

ወጣት የነፃነት ታጋይ እድሜ ልክ የግፈኞች የበቀል ፍርድ የተቀበለው የፖለቲካ እስረኛ አንዱአለም አራጌ ለሁለተኛ ጊዜ የመደብደብ ሙከራ እንደተፈፀመበት ከቃሊቲ ተሰማ

$
0
0

ስንታየሁ ቸኮል

ወጣት የነፃነት ታጋይ በእስር ቤት እረፍት እንዳጡ ነው ፡፡ እድሜ ልክ የግፈኞች የበቀል ፍርድ የተቀበለው የህሊና እና የፖለቲካ እስረኛ አንዱአለም አራጌ ለሁለተኛ ጊዜ ካለበት ክፍል በአንድ እብሪተኛ ታሳሪ የመደብደብ ሙከራ እንደተፈፀመበት ከቃሊቲ እስር ቤት ምንጮች ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱአለም አራጌ ላይ ምንም አይነት ችግር ባይደርስበትም ለፀብ የተጋበዘው ተደባዳቢ ግለሰብ ከግቢ በማውጣት ወደ ሌላ ዞን መወሰዱ ተሰምቷል፡፡ መረጃው በዝርዝር ሲደርሰን እናሳውቃለን፡፡

The post ወጣት የነፃነት ታጋይ እድሜ ልክ የግፈኞች የበቀል ፍርድ የተቀበለው የፖለቲካ እስረኛ አንዱአለም አራጌ ለሁለተኛ ጊዜ የመደብደብ ሙከራ እንደተፈፀመበት ከቃሊቲ ተሰማ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

በሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ለሚደርሰው ሞትና መከራ አገዛዙ ተጠያቂ ነው! (ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ)

$
0
0

ባለፉት ሃያ ስድስት አመታት በውጭ ስለሚኖሩ ዜጎቻችን የምንሰማው ዜና በአሰሪዎቻቸው ተደበደቡ፣ ከፎቅ ላይ ተወረወሩ፣ ተደፈሩ፣ ተገደሉ እና የመሳሰሉ አሳዛኝ ዜናዎች ሲሆኑ በዚህም ሂደት ገዥው ቡድን በዜጎቻችን ላይ የሚፈፀሙ በደሎችን ለመከላከል ፍላጎት የለውም የሚል ወቀሳ ነው፡፡

ከዚህ የስደትና የመከራ ሕይወት ጋር በተያያዘ በአሁኑ ወቅት የሳውዲ አረቢያ መንግስት በሐገሩ የሚገኙ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ዜጎች ሐገሩን ለቀው እንዲወጡ የቀነ ገደብ የወሰነ ሲሆን በተሰጠው ጊዜ በማይወጡ የውጭ ዜጎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ እያስጠነቀቀ ይገኛል፡፡ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተሰጠው የጊዜ ገደብ ያችን ሐገር ለቀው ካልወጡ የሚጠብቃቸው ሞትና እንግልት መሆኑን እያወቁ ለመውጣት ያደረጉት ዝግጅት አነስተኛ መሆኑ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በሐገራቸው በሚደርስባቸው የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ መገልል ምክንያት በኢትዮጵያ ከመሞት በባዕድ ሐገር መሞትን የመረጡ ይመስላል፡፡ ይህ አሳዛኝ የዜጎች ምርጫ ዛሬ ሐገራችን ያለችበት አገዛዝ የዜጎችን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ ኑሮ ችግሮች ለማቃለል የማይችል መሆኑንና ዜጎች የሕይወት ዋጋ ለመክፈል በመጋፈጥ ጭምር እያረጋገጡት ይገኛል፡፡

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት በወሰደው የውጭ ዜጎችን ከሐገሩ የማስወጣት እርምጃ በርካታ ወገኖቻችን ከፍተኛ የሆነ ኢሰብአዊ ድርጊት ተፈፅሞባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በጭካኔ ተገድለዋል፣ ተደፍረዋል የአካልና የኢኮኖሚ ጉዳትም ደርሶባቸዋል፡፡ በወቅቱ ሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ መንግስት የተወሰደውን አረመኔያዊ ድርጊት አውግዞ የሳውዲ መንግስት ይህንን የጭካኔ ተግባር ባስቸኳይ እንዲያቆም ለመጠየቅ በኢትዮጵያ የሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ጽ/ቤት ያደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ የእኛው ገዥ ቡድን ታጣቂዎች በሰልፈኞች ላይ በፈፀሙብን አረመኔያዊ ድብደባ ሰልፉን በትነዋል፡፡ ገዥው ቡድን ከሳውዲ አረቢያ ለተመለሱ ዜጎች ተገቢውን ማቋቋሚያና ድጋፍ ባለማድረጉ ባለፈው ከተመለሱት መካከል አብዛኛዎቹ እንደገና ተመልሰው ወደ ሳውዲ አረቢያ መጓዛቸው ይነገራል፡፡ ዜጎች በሐገራቸው ሰርተው የመኖር ተስፋቸው እየመነመነ በመሔዱ ለሕወታቸው አደገኛ የሆኑ ጉዞዎችን በመጋፈጥ አሁንም መሰደዳቸውን አላቆሙም፡፡

አገዛዙ ለሌሎች ሐገር ስደተኞች ሳይቀር ድጋፍና እንካካቤ አድርጋለሁ በማለት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ብዙ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያገኘ ሲሆን የራሱ ዜጎች ሰርተው የሚኖሩበት መንገድ ሊፈጥር ባለመቻሉ በተለይ ባለፉት ሦስት ዓመታት ችግሩን ለመፍታት ምንም የሰራው ነገር ባለመኖሩ ችግሩ እስካአሁኑ ሰዓት ድረስ ተከትሎን ይገኛል፡፡ አገዛዙ አሁንም በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎች እንዲመለሱ ተራ የማታለያ ፕሮፓጋንዳ ከመንዛት ውጭ ዜጎች ወደ ሐገራቸው ቢመለሱ ሰርተው መኖር የሚችሉበት ዋስትና ሊያቀርብላቸው ባለመቻሉ የገዥውን ቡድንና የአስመሳይ አርቲስቶችን ጥሪ ሰምተው ከመምጣት ይልቅ ባሉበት ሐገር ሆነው ሞትን መጠበቅ ምርጫቸው አድርገዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በዜጎቻችን ለሚደርስባቸው ሞትና መከራ ገዥው ቡድን ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡

የሳዉዲ መንግስት ስደተኞችን ከሐገሩ ለማስወጣት የሚወስዳቸው እርምጃዎች አረመኔያዊ መሆኑን ባለፈው ጊዜ በዜጎቻችን ላይ የደረሰው መከራና ሞት በቂ ማሳያ መሆኑን እያስታወስን አሁንም የሳውዲ መንግስት የሚወስዳቸው እርምጃዎች ለዓለም ዓቀፍ የሰው ልጅ መብትና ለሰው ልጅ ፍጡር ያለን ክብር የጠበቀ እንዲሆን እናሳስባለን፡፡ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ዓለም ዓቀፍ የስደተኞች ድርጅት፣ ዓለም ዓቀፍና አገር አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በስደተኞች ላይ የሚፈፀም ኢሰብአዊ ድርጊት እንዲቆም እና በስደት ላይ ላሉ ሁሉ አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎ በሕይወት የመኖር መብታቸው እንዲከበር የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፈለን፡፡

በመጨረሻም በሳውዲ የሚገኙ ዜጎቻችንም ከሳውዲ አረቢያ መውጣትን አስመልክተው የሚወስኗቸው ውሳኔዎች ሕይወታቸውን አደጋ ውስጥ የማያስገባ መሆኑን ማጤን እንዳለባቸው እንመክራለን፡፡ በሐገርና ከሐገር ውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ይሕን በዜጎቻችን ላይ ያንዣበበ አደጋ በቅርበት በመከታተል የሚደርስባቸወን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለሚመለከታቸው ሁሉ በማጋለጥ የበኩላችሁን እንድትወጡና የሚደርሰውንም ሞትና መከራ መቀነስ እንድንችል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ሰኔ 3 ቀን 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባ

The post በሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ለሚደርሰው ሞትና መከራ አገዛዙ ተጠያቂ ነው! (ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Fire Destroys Ethiopian Federal Police’s Store, Barrack in Gumruk, Laghar, Addis Abeba: State Media

$
0
0

(function(d, s, id) { var js, fjs = d.getElementsByTagName(s)[0]; if (d.getElementById(id)) return; js = d.createElement(s); js.id = id; js.src = “//connect.facebook.net/zh_CN/sdk.js#xfbml=1&version=v2.3”; fjs.parentNode.insertBefore(js, fjs);}(document, ‘script’, ‘facebook-jssdk’));

የቀድሞ የጉምሩክ ግቢ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ዕቃ ግምጃ ቤት የእሳት አደጋ ደረሰ፡፡

EBC 发布于 2017年6月10日

The post Fire Destroys Ethiopian Federal Police’s Store, Barrack in Gumruk, Laghar, Addis Abeba: State Media appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.

የፍጹም ሰላም የከፍታ ነጥብ (The Quantum understanding of peace) የት ላይ ነው ?… (በጽሞና ውስጥ ካሰላሰልኩት)

$
0
0
መስቀሉ አየለ
አዳም አጸብ ከድቀቱ በፊት በበጎ ህሊና ይኖር ነበር ሲባል መጥፎ ነገር ለማሰብ አይችልም ማለት ነው።ለምሳሌ መግደል፣ መዋሸት መመኘት ክህደት ኑፋቄ የተባሉ ስጋዊ ጠባዮች በአእምሮው መዝገብ ውስጥ አልተጻፉምና አያውቃቸውም። ለምሳሌ አዳም ምንም ቅሉ የሰላሳ አመት ጎልማሳ ሆኖ ቢፈጠረም ልቡናው እንደ ህጻናት ልቦና ነበረና ሃፍረተ ስጋውን አላየውም። ስለሆነም ልብስ አላስፈለገውም ነበር። እጸ በለስ በበላ ግዜ ግን ክፉና ደግ ለይታ የምታሳውቀውን የእውቀት ፍሬ በላና የሚኖርበትን አለም መጥፈፎውን ጎን ያይ ዘንድ አይኑ ተገለጠ። አንድ ግዜ ከጸጋ በታች ወድቋልና በመሆንና ባለመሆን በማድረግና ባለማድረግ ክፉ ምኞት ተዋጠ።ሃፍረተ ስጋውን አይቶ ልብስ ፍለጋ የሮጠው ያን ግዜ ነው። ሰላሙ ተወስዶበት የምኞት ባሪያ ሆኗልና በምኞት የሚፈተን አይምሮ ይዞ ደግሞ በገነት መኖር አይቻልም፤ ስለዚህ የቁርበት ልብስ አልብሶ ውጣ፣ እስከ ዕለተ ሚጠት ድረስ በዛው ቆይ ብሎታል።አዳም በገዛ ኑፋቄው ከገዛት ክፉ ምኞት ጋርም ወደ ተረገመችው መሬት ወርዷል።
ኑሮ በገነት ምን ይመስላል የሚለውን እንዲህ ማየት የሚቻል ይመስለኛል
በገነት ውስጥ መኖር ማለት ፍላጎት ምሉእ የሆነበት አለም ውስጥ መኖር ማለት ነው። ከምኞት ውጭ መኖር ማለት ነው። ይህም ማለት ሰው የሆነ ነገር ማግኘት ሲፈልግ አግኝቶታል። የሆነ ቦታ መድረስ ሲፈልግ ደርሷል። በጥቅሉ በዚህ አለም ላይ ያለው የታይም እና ስፔስ ሊሚቴሽን በርሱ ላይ ስልጣን የላቸውም ማለት አንድን ነገር በመመኘት ቀጥሎም በመፈለግና ፈልጎ በማግኘት መካከል የሰከንድ ክፍተት የለም፤እንዲሁም አንድ ቦታ መሄድ በመፈለግና ያሰበው ቦታ በመድረስ መካከል ምንም አይነት ዲስታንስ ሊሚቴሽን ወይንም የቦታ ውሱንነት የለም ማለት ነው ማለት ነው።
ባጠቃላይ ምኞት ሲሸነፍ ፍላጎት ምሉዕ ሆኗል ማለት ሲሆን የፍጹም ሰላም መገኛዋ ነጥብም እርሷ ናት። አዳም ሰላሙን አስረክቦ ስደት የወጣው ከዚህ አይነት አለም ነው።
እንግዲህ አዳም ወደ ተረገመችው መሬት ሲመጣ ይዞ የመጣው ደግሞ የሞት እዳ ብቻ ቢሆን እዳው ገብስ ነበር። ነገር ግን የነበረውን ፍጹም ሰላም ተገፎ ክፉ ምኞት ተጭኖበት መውረዱ ነው ሰላማችንን ወስዶ ጣዕራችንን ያበዛው።
በምኞት ውስጥ መሬት ላይ መኖር ምን ማለት ምን ማለት ነው ፤
ከዘፍጥረት (ቢግ ባንግ) ጀምሮ እስከ ምጻት( ዘቢግ ክራንች) ድረስ ኢንፋይናትሊ የተለጠጠና አሁንም ድረስ በየሰከንዱ ያለማቋረጥ ከብርሃን ፍጥነት በላይ በሆነ ፍጥነት እየተለጠጠ በሚሄድ ዩኒቨርስ(ህዋ) ውስጥ በዚያው ልክ ያልተገደበ ምኞት የተጫነብን ነገር ግን ደግሞ በጣም ውሱን የሆነ አቅም ብቻ ገንዘብ ያደረገ ስጋ ለባሽ ይህን ፍላጎት እንዴት ማስታረቅ እንደሚፍል አለማወቁ ነው ትልቁ ሰላሙን የሚነሳው ነገር። ህይወታችንን ሙሉ እርካታ በተለየው የማያቋርጥ ሲቃ ውስጥ እንድንኖር የሚያደርገንም ይዅው ነው። ነገር ግን በምንፈልገውና ፈልገን በምናሳካው መካከል ያለው ልዩነት በጣም ትልቅ በመሆኑ የተነሳ በሁለቱ መሃል ያለችውን ልዩነት ማስታረቅ (ባላንስ) ማደርግ የቻለ፤ በሌላ አነጋገር አንጻራዊ በሆነ መልኩ ምኞቱን ለመገደብ አቅም ያደረገ ሰው ማለት የተሻለ ሰላም ያለው ሰው እርሱ ነው ።
እንግዲህ አንድ ሰው ከላይ ወደ ገለጽነው የሰላም አገር ለማዝገም አንዱ አቋራጭ መንገድ (ዲስፕለስመንት) የህይወት ዘመን ስኬቱ አንጻራዊ የሆነ ሰላም ያለበት እንዲሆን ታሳቢ ያደረገ ከሆነ ነገሩ መለካት ያለበት በሚያከማቸው ሰፊ የሃብት ክምችት ሳይሆን በዋናነት በሚከተለው የህይወት ሲምፕሊሲቲ ነው ማለት ነው።ለዚህም ቀላሉ ምሳሌ ሱስ ካለበት ሰው ይልቅ ሱስ የሌለበት ሰው ቀላልና የተሻለ ሰላም ያለው ህይወት እንደሚገፋው ማለት ነው።
ሌላው ሰላማችንን ከሚያናጋው የአይምሮ ጠንቅ ውስጥ በዋናነት ለራሳችን በምንሰጠው ግምት እና ሰዎች ስለኛ ያላቸው ሚዛን አለመግጠም ነው። ለምሳሌ እየሱስ ክርስቶስ በስጋ ማርያም በመውለዱ አንድ ጌዝ እራሱን ባዶ አደረገ ስንል የዚህ አለም ትናንሽ የሆኑ ነገሮችን መምረጡን ለማሳየት ነው፤ በበረት ከመወለድ ጀምሮ፣ ከደሃ ወገን መወለዱ፣ በዚህች ምድር ላይ ዛኒጋባ እንኩዋን ሳይኖረው በተናቀ ሞት መሞቱና የተቀበረበት መቃብር እንኩዋን የሌላ ሰው መሆኑን ሁሉ ለማለት ነው።። ስለሆነም እራሱን አንድ ግዜ በዚህ ደረጃ ዝቅ አድርጓልና እርሱን በሰደቡትም፣ በተፉበትም፣ በተሳለቁበትም ግዜ ሁሌ በለበሰው ስጋም ቢሆን ክብሬ ተነካ ብሎ ሲናደድ የታየበት አንድም አጋጣሚ የለም።ሁሉንም ነገር በጽትታ ውስጥ ያልፈው ነበር። ይኽ እንግዲህ ስለ ቤተክርስቲያኑ ቅናት የታየበትን ንዴት ሳይጨምር ማለት ነው።የክርስቶስ መዋዕለ ስጋዌ የሚያሳየው ማንም ቢሆን አንድ ግዜ ከሰዎች ከበሬታን ሳይሻ እንዲሁ በጥትና መኖርን ገንዘብ ቢያደርርግ ሌላኛውን ወደ ሰላም አገር መድረሻውን ጫፍ አግኝቶታል ማለት ነው። እራስን ከማንም ሳያወዳድሩ በት ሁት ሰብዕና የመኖር ዘይቤ ከህይወት ሲምፕሊሲቲ ጋር የሚገናኙበት ነጥብ ዘኳዋተም አንደርስታንዲንግ ኦፍ ፒስ ማለት እርሱ ይመስለኛል።

The post የፍጹም ሰላም የከፍታ ነጥብ (The Quantum understanding of peace) የት ላይ ነው ?… (በጽሞና ውስጥ ካሰላሰልኩት) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ሰበር ጥብቅ መረጃ . . . .በተለይ በአማራዉ ክልልና በአዲስ አበባ አካባቢ ለምትገኙ. – በልኡል አለሜ

$
0
0
ሰኔ 3/2009
ህወሃት በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ምክንያት አዋቅሮት ሲሰራበት የነበረዉ የመረጃ ደህንነት ሰራዊት በኮማንድ ፖስቱ የበላይ ተጠሪነት ለአፈና ዝግጅቱን መጨረሱን ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል። በዚህም መሰረት
• በሶሻል ሚዲያ ዉስጥ በመሳተፍ ከፍተኛ የተቃዉሞና የአመጽ ስራዎችን ያከናወኑ
• ህዝብ መንግስት ላይ ያለዉን ታማኝነት ኣንዲያጣ በማድረግ ሶሻል ሚዲያ ላይ የተሳተፉ
• በተለያዩ ሐገር በቀል የፖለቲካ ፓርቲዎች ዉስጥ በመሳተፍ ከህገ መንግስቱ ደንብ ዉጪ ህዝብን በማደናገር የተሳተፉ
• ከሐገር ዉጭ ከሚንቀሳቀሱ የሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር በሚስጥር የተገናኙ ( ከህዝብ ወይም በግል ገንዘብ አሰባስበዉ ለሽብረተኛ ድርጅቶች የላኩ)
• ከሀገር ዉጭ ከሚንቀሳቀሱ የሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር በግልጽ የተገናኙ
• የመንግስትን ሚስጥራዊ መረጃዎች አሳልፈዉ የሰጡ
• የመንግስት ሰራተኛ ሆነዉ በስራቸዉ ላይ ሐገርን በመበደል የተሳተፉ ሰራተኞችን የሚቀሰቅሱ
እና የመሳሰሉት 107 ምክንያቶችን በዝርዝር በያዘ ሰነድ በመታገዝ ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ዉጭ ለእገታ ትእዛዝ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
በተለየ መልኩ አፈናዉ በአማራዉ ክልል ላይ አብዝቶ ያተኮረ ቢሆንም አዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልልም ላይም በብርቱ ተፈጻሚ እንደሚሆን ታዉቋል… ኮማንድ ፖስቱ እንዲህ ላለዉ የአፈና ዝግጅት ሲሰናዳ ይህ የሁለተኛዉ ግዜዉ መሆኑን የገለጹት ምንጭ ለአፈናዉ ተግባራዊነት ከፍተኛዉን ሚና በመጫወት የብሄራዊ መረጃ አመራሮችና ወታደራዊ ደህንነቶች የሚሳተፉበት ሲሆን ፖሊስ እና ልዩ ሐይል እስካሁን የደረሳቸዉ መመሪያ አለመኖሩን ጠቅሷል ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

The post ሰበር ጥብቅ መረጃ . . . .በተለይ በአማራዉ ክልልና በአዲስ አበባ አካባቢ ለምትገኙ. – በልኡል አለሜ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


ወረራውን በመመከት ለመልሶ ማጥቃት መዘጋጀት ያስፈልጋል ( ኮ/ል አለበል አማረ )

$
0
0

ኮ/ል አለበል አማረ

ህወሃት ” ጸረ- ሰላም ሃይሎችን ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ለ2010 ለልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠር” በሚል መፈክር ከሰኔ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ነሃሴ የሚዘልቅ በጎንደር ምድርና ህዝብ ላይ ሰፊ የወረራ አቕድ ማውጣቱንና ፈጻሚ ሃይሉንም እያዘጋጀ መሆኑን እየሰማን ነው። ህወሃት በዚህ የጥፋት የወረራ እቅድ አላማ አድርጎ የተነሳው፥ የጎንደርን አማራ በማንበርከክ የጀመረውን የተስፋፊነት አባዜ በማጠናከር ያሰባቸውን የአማራ መሬቶች ወደ ትግራይ ለማካለልና ለሱዳንም ሊሰጥ የተስማማውን መሬት ለመቸር፣እንዲሁም ጎንደር ላይ ተረባርቦ በሚያገኘው ድል ሌሎችንም ህዝቦች ለማንበርከክ ይረዳኛል በሚል ተስፋ የተዘጋጀ እቅድ መሆኑ ታውቋል።

ይህንን የጥፋት የወረራ እቅድ ለማስፈጸም ሁለት ክ/ጦሮች በዋነኛነት እና ከ5 ሌሎች ክ/ጦሮች የተውጣጣ ሃይል በተጨማሪነት እየተዘጋጀ ሲሆን ከፌደራ ፖሊስም የተወሰነ ሃይል መመደቡ ታውቋል፥ የአማራ ክልል የጸጥታ ሃይሎችን በጥርጣሬና በስጋት እንደተመለከቷቸውና ይህም ለህወሃትና ብአዴን አለመተማመን እንደሚያሰፋ ወሬወች እየተሰሙ ነው/ተጨማሪ ጥናት ያስፈልገዋል።እንደተሰማው፥ እቅዱ ሁሉንም የጎንደር አካባቢወች ሙሉ በሙሉ ከመቆጣጠርም በላይ ሰፊ የጦር መሳሪያ ዘርፋ እቅድም አብሮ ተካቷል።

የጸጥታ ሃይል አሰላለፍ ከመሃል ጎንደር፣ ከትግራይ፥ ከሱዳን እና ከሰቆጣ አቅጣጫ እንደሚንቀሳቀስ ታውቋል።

መላው አማራ ይህንን የትግሬ ህወሃት ወረራ ለማክሸፍና አጋጣሚውንም ለመጨረሻ ድል ለመጠቀም በሁሉም አቅሞቹ መረባረብ አለበት። እንደሚታወቀው ህውሃት እንዲህ አይነት ወረራ ሲያካሂድ መጀመሪያ የመገናኛ ዘዴወች ይቆራርጣል፥ እኛም ቀድምን ለዚህ መፍትሄወች ከማበጀታችንም በላይ ጠላት የሚጠቀምባቸውን የመገናኛ ዘዴወች ለማፈራረስ መዘጋጀት አለብን። ትግሬው ህወሃት ክረምቱን እየጠበቀ የሚያካሂደው ዘመቻ ሆን ብሎ ገበሬውን ከአዝመራው ለማለያየትና ለማደህየት መሆኑ ታውቆ የገበሬው አዝመራ እንዳይጎዳ የተቻለውን ጥረት እየተደረገ በአማራ ምድር የሚገኙ የትግሬ ወያኔ ንብረቶች ላይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀት። ይህ የትግሬ ወያኔ ወረራ ዛሬ በጎንደር አማራ ላይ ቢካሄድም ነገ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወገን ላይ የማይቀር በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለጸረ ወረራው ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማስተላለፍ፣ በተለይም አማራው ጉዳዩ የራሱ መሆኑን ተረድቶ በያለበት ተደራጅቶ በወንድም እህቶቹ ላይ የሚደርሰውን ግፍ በያለበት እየተመካከረ እንዲበቀል ማድረግና በአጠቃላይ የአካባቢውን ነባራዊና ህሌናዊ ሁኔታውችን በመዳሰስ ወረራውን በማክሸፍ የመልሶ ማጥቃት እቅድ እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል። ይህ የትግሬ ወያኔ ወረራ፥ አማራው ሃምሌ 5 የወልቃይት መላ አማራ ቀን ብሎ ሰይሞ ለማክበር በውጭም በውስጥም እየተንቀሳቀሰ ባለበትና የአማራ የፖለቲካ ድርጅቶች ውህደት ለመፈጸምና ቀጣዩን ትግል በብቃት ለመምራት እየተዘጋጁ ባሉበት ሁኔታ መከሰቱ ትግሉን ይበልጥ ለማጠናከር አመች ሁኔታ ይፈጥርልናል።

The post ወረራውን በመመከት ለመልሶ ማጥቃት መዘጋጀት ያስፈልጋል ( ኮ/ል አለበል አማረ ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Ethiopia’s emergency food aid to run out next month – BBC

$
0
0

Ethiopia will run out of emergency food aid for 7.8 million people affected by drought at the end of this month, the UN has warned.

Aid groups and the government are calling for help, but fear donor fatigue with other crises worldwide.

Famine has been declared in South Sudan, and there are warnings of famine in north-east Nigeria, Yemen and Somalia.

But Ethiopia is also struggling following successive failed rains.

The government, while better at coping with droughts than in previous years, still does not have the funds to cope by itself.

It allocated $381m (£300m) extra over the last two years, but is unable to sustain it for a third year.

It has left Ethiopia in a “dire situation”, according to John Aylieff of the World Food Programme, a UN agency.

“We’ve got food running out nationally at the end of June,” he told reporters on Friday.

“That means the 7.8 million people who are in need of humanitarian food assistance in Ethiopia will see that distribution cut abruptly at the end of June.”

His words were echoed by John Graham, of Save the Children

He told AFP news agency: “After [the food runs out], we don’t know what is going to happen. And without that basic food then you will have problem falling into severe malnutrition because people are not getting any food.

“These children become severely malnourished and that’s where you have a very dangerous situation.”

The post Ethiopia’s emergency food aid to run out next month – BBC appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.

የአርቲስቶቻችን የባዶ መሶብ ግብዣ – በ: ሀ. ህሩይ, ቶሮንቶ

$
0
0
በ:   ሀ. ህሩይ, ቶሮንቶ
  ሰኔ,2017
 ሰሞኑን በተወሰኑ አርቲስቶች የተዘጋጀውን ወደ ሀገር የመመለስ ጥሪ ወይም ውትወታ በቴሌቪዥን ስመለከት ስልችት ያለኝን የሰራዊት እና የሙሉዓለምን የቅብብሎሽ ማስታወቂያ በተደራጀ መልኩ እንደገና አየሁት።
መቼም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን የሚመለከት እና ሬዲዮኑን የሚሰማ አድማጭ የነዚህን አርቲስቶች   የሳሙና፣ የ ኦሞ፣ የቢራ፣ ፓስታ ፣የሎተሪ ፣የውሃ ፣የኤግዚቢሽን አረ ምኑ ቅጡ ተመሳሳይ አሰልቺ ማስታወቂያ ሲያዳመጥ እና ሲመልከት በብስጭት ቴሌቪዥኑን ያጠፋ ሬዲዮኑን የዘጋ ብዙ ሰው እንደሚኖር እገምታለሁ።
 ወይ ጉድ!  የሰራዊት እና የሙሉዓለም አልበቃ ብሎ እነ ሸዋእፈራው፣ አበበ ባልቻም ተጨምረው ጭራሽ አሁን ደግሞ በቡድን ተደራጅተው በወሬ ቅብብሎሽ  ያደንቁሩን?   እንዳውም ቁጥራቸው በዝቶ ስመለከት እንደተለመደው የብሔር ብሔረሰብ ልብስ ይለብሳሉ ብዬ ነበር።
የሚያሳዝነው ነገር ልክ ቀይ ምንጣፍ አንጥፈው ወይም በሀገራችን ባህል መሠረት ቄጤማ ወይም ሳር ጎዝጉዘው ይቀበሉ ከዛም ደግሞ በተገቢው መልኩ ያሚያቋቁሟቸው ይመስል ለመመለስ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ስይሟሉ  ናፍቃችሁናል ኑልን ማለታቸው ነው።
በፌስ ቡክ ለጥሪአቸው መልስ የሰጠችውን አንዲት  እህትን በጣም አድንቄአታለሁ። እውነትሽን ነው።  ከእነዚህ አስመሳዮች እና  ዝና ፈላጊዎች  የሚገኝ መፍትሄ የለም። ሀገር አላችሁ ብቻ ብሉ ተመለሱልን ማለት ለችግሩ መፍትሄ አይደለም። ከሱ በፊት የሚሰሩ እና መሟላት ያለባቸው በርካት ቅድመ ሁኔታዎችና  ጉዳዮች አሉ። አይደለም ከሳኡዲ አረቢያ ለመምጥት አዲስ አበባ ውስጥ ለመጓጓዝ እንኳን የአውቶቡስ ወይም የታክሲ ገንዘብ ያስፈልጋል። ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚጣ ሰው ደግሞ ማረፊያ እና ምግብ ሌላም ብዙ ነገር ያስፈልጋል።  ታዲያ አርቲስቶቻችን ይህንን ማሰብ እንዴት ተሳናቸው?
 ሀገራችን ለከፍተኛ ረሀብ በተጋለጠችበት ግዜ (በ1977ዓ.ም) ማይክል ጃክሰን እና ሌሎች ድንቅ ይዓለማችን ዘፋኞች የሌለን ምግብ እና ውሃ ብሉ ወይም ጠጡ ብለው ባዶ መሶብ እያሳዮ ወይም አቅርበው የተራበውን ህዝብ ብላ አላሉም ግብዣም አልጠሩትም። ምክንያቱም የሌለን ነገር መጋበዝ ፋይዳ እንደሌለው ያውቃሉና።
ያደረጉት ግን ምግብ የሌለው መሶብ ከፈትው ብሉልን ሳይሆን መሶቡን በምግብ ነው የሞሉት። ይህንን ለማድረግ እንዲርዳ ኮንሰርት አዘጋጅተው “We are the World” የሚለውን ዜማ በማዜም ወገኖቻችንን ከረሀብ ለመታደግ ገንዘብ ነው ያሰባሰቡት። ታዲያ እነ ሰራዊት ምነው ይሄንን ማሰብ ተሳናቸው? ወይስ የተለመደውን ማስታወቂያ የሚሰሩ መሰሏቸው ይሆን?
 ችግሩ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ ወይም ድራማ የሚሰራበት ሳይሆን ትክክልኛ እና አፋጣኝ መንግሥታዊ መፍትሄ የሚያስፈልገው ነው። በአረብ ሀገራት በተለይም በሳኡዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ችግር ከተፈጠረ ዓመታት አስቆጥሯል። በመንግሥት በኩል ግን ለችግሩ መሠረታዊ መፍትሄ  አልተሰጠም። ችግሩ ጉልቶ ሲመጣ ብቻ “ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ” ዓይነት መተራመስ ነው ያለው። ትርምሱም ቢሆን ከዜና ሽፋን ያለፈ ነው አያሰኝም።
 በየሀገሩ የሚገኙ የሀገራችን ኤምባሲዎች ዋና ሥራ የኢህአዴግን ፖለቲካዊ ማራመድ ነው። በውጭ  የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚፈለጉት ሀገራቸው ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ፣ የግንቦት 20 እና የህዋሀትን ልደት እንዲዘክሩ ብቻ ነው?
 ስለዚህ አርቲስቶቻችን መንግሥትን እንደመንግሥት ኃላፊነትቱን እንዲወጣ እና ዜጎቸን እንዲታደጋችው ንገሩት።ለጉዳዩ ምን እርምጃ እየወሰደ እንደሆን ጠይቁት።

The post የአርቲስቶቻችን የባዶ መሶብ ግብዣ – በ: ሀ. ህሩይ, ቶሮንቶ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ኢትዮጲያን  ለማዳን ማድርገ ያለብን ጉዳይ! (ከሙሉቀን ገበየው)

$
0
0

አገራችን ኢትዮጲያ  ወደ አስጊ መንገድ እየሄድች ነው። አብዛኞቻችን ይህ ሁኔታ ይሆናል ብለን አናስበው ይሆናል። አንዳንዶቻችን የተጋነነ አባባል አደርግን እንውስደዋላን። የተወሰነው ደግሞ በተለየ ሁኔታ  አገራችን በቅርቡ አስርት አመታት ከተከሰተው ታሪካችን በመንሳት ኢትዮጲያ በተሻለ መንገድ ላይ ናት ብለን እናስባለን። እውነታው ግን በኢትዮጲያ ታሪክ ታይቶ በማይታውቅ ደርጃ የመበታተንና አስከፊ የእርስ በርስ ጦርነት አሳት ወስጥ  ልንገባ የሚያስችል  እጣ ፈንታ የተዘረጋልን  መሆኑ ነው። ይህ ክፉ እጣን  ማስቀረት ይቻላል! ይሄ የአሁኑ ትውልድ  ማስጠንቀቂያወን ቸላ ያለው እንደሆነ የተፈራው በማይመልስ መልክ ሊፈጸም ይችላል።

አሁን አንገብጋቢ ሆኖ የሚፈታተነን ችግር የዲሞክራሲ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን፤  ሁላችንንም አቅፎ በኢትዮጲያ አገራችን የያዘን ምሰሶና ማገር እንዲበሰብስና  እንዲዝግ በላያችን ላይ ጊዜ ወስዶ እንዲደረመስ ስለ መደርጉ ነው። ሕወሓት (ወያኔ) የሚመራው አገዛዝ በሃሰትና የተጋነነ የውሸት ታሪክ፣ ቋንቋችንን፣ የባህል  እንዲሁም የሃይማኖታችንን ልዩነት እያጎላ  የዘራው የተንኮል ዘር ፤ በመካከላችን የጠላትነት ፣ የጥርጣሬ፣  የጥላቻና የመከፋፈል  እኩይ  ተግባር ፈጥሯል።

የጥቂቶች የሆነው የወያኔው ቡድን ያምነበትና ተግባር ላይ ያወለው አጥፊ  የአገዛዝ ስልት ዘርግቷል። የ አነስተኞች ወገን ሁኖ ብዙሃኑን ኢትዮጲያውያን ለመገዛት፤ ብዙሃኑን በመከፋፈልና በማዳከም፣ እንዳይደራጅ አድርጎ በ “ከፋፍለህ ግዛው” ዘዴው  ሰውሮ ይዞታል። ይህንንም ለማስፈጸም  የማጭበርበሪያ የፌድራል ክልል አበጅቷል። ‘ብሄር ብሄረሰቦችን’ የሚከፋፍል፣ የሚያራርቅ፣ የሚያጋጭ ፖሊሲ ነድፎ፤ እያጋጨ፣ ራሱ ፖሊስና ዳኛ ሆኖ ወያኔው ስልጣን ላይ ለዘመናት ፊጥ ብሏል። የቀደሙት አገዛዞች በመደብ ለይተው ህዝቡን ይግዙ እንጂ እንደ አሁኑ አገዛዝ እርስ በርስ ሊያጨራርስ በሚያስችል የተንኮል አገዛዝ አልተጠቀሙም። በዋናው የመደብ ልዩንት አገዛዝ ላይ አንዳንዴ የጎሳና ሃይማኖት ቅባቶች ተጠቀሙ እንጂ አንዱን ባንዱ የሚያስነሳ ፖሊሲ አልተጠቀሙም።

ወያኔ በ1983 በመሳርያ ሃይል ስልጣን ላይ ከተቀመጠ ጀምሮ በዚህ ከፋፍለህ ግዛው ዘዴው አውቆም ይሆን ሳየውቀው  በአገራችን ኢትዮጲያ ሁላችንንም ተሽክሞ የያዘነን ምሰሶ እየናደው መሆኑን ነው። የተለያዩ የጎሳ “መሪዎች” በወያኔው የፈጠራ ታሪክና ፕሮፓጋንዳ  ራሳቸውን ልዩ ጎሳ እንደሆኑ እንዲያስቡ አድርጎቸዋል። ጎሳ ለጎሳ እንዳይተማመን አድርጎ፤ በተለይ ወያኔው የአንድነት ጠበቃ ናቸው ብሎ የሚያስባቸውን  “አማራ” እና “ኦርቶዶክስ” ሃይማኖትን እንዲጠሉ ተድርገዋል። የወያኔው ሽንገላ ባንዳንዶች የጎሳ “መሪዎች” ላይ “የራስህን አገር መምስረት ትችላልህ” የሚል ቀቢጸ-ተስፋ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 39  አስፍሮ ፡ የግብዞቹን አይን አውሮ  የቅጠፈት አገዛዙን አንሰራፍቷል።

ወያኔው አስቀድሞ በያዘው እቅዱና ትልሙ ኢትዮጲያን በበላይነት እየገዛና እይዘረፈ፤ ክፉ ቀን ሲመጣ “የትግራይን ሪፐፕሊክ”  ከኢትዮፒያ በዘርፈው ንብረት መስርቶ፡ ሌሎችንም ጎሳዎች እንዲገንጠሉና መንግስት እንዲመስርቱ፤ ኢትዮጲያን እንዲያፈርሱ   አልሟል።

መራራው እውነት ግን ወያኔው በፈጠረላቸው ማንነትና የግዛት ወሰን የሚደርገ  ግንጠላና አዲስ አገር የሞህን ጉዳይ ከዩጎስላቪያና ሶማሌ በበለጠ ወደ ማያባራ የእርስ በርስ ጦርነትና ደም መፋሰሰ ያመራል።  “የትግራይ ሪፐፕልክም” የእሳቱ ቃጠሎ ይደርሳታል።  የ ምስራቅ አፍሪካንም  ያወካል።

ኢትዮጲያውያን ልንረዳው የሚገባን አንገብጋቢው ጥያቄ የዲሞክራሲ እጦት ብቻ ሳይሆን፤ ዋናው አገር የማዳን ጉዳይና ትልቅ የእርስ በርስ ደም መፋሰስ እልቂትን ማዳን ነው። እስኪ ላአንዳፍታ አገር ተገነጣጥሎ ያለውን እውነታ እንየው። ኦሮሚያ የምትባል አገር ወያኔ በሰፈርላት የድንበር ወሰን ብትገንጠልና አዲስ አገር ብትሆን  በሰሜን በኩል ከአማራው ጋ፣ በምስራቅና ደቡብ ምስራቅ  ከኢትዮጲውያን ሶማሌ ጋ፣ በምራብ ና ደቡብ ምራብ ከደቡብ ህዝቦች ጎሳ ጋ የማያባራ የድንበር ና የጎሳ ጦረነት ላይ ስትወድቅ አስቡት። አማራ የሚባል አገር ተመስርቶ በሰሜን ከ”ትግራይ ሪፐፕሊክ” ጋ፣ በደቡብ ከኦሮሚያ ጋ፤ በምስራቅ ከአፋር ጋ የማያባራ የግዛት ና ወሰን ጦረነት ሲከሰት። ደቡብ ኢትዮጲያ ውስጥ ያሉ ብዙሃን ጎሳዎች አገር እንሁን ብለው በድንበር ወሰን ምክንያት እርስ በርሳቸው ሲጨራረሱ ። ይህ ሁሉ ቢሆን ማንንም ሳይጠቅም መንግስት ከሌላት ሱማሌ የባሰ ጥፋት ይደርሳል።

ውድ እህትና ወንድሞች፤ እንድምናየው ኢትዮጲያችን ወደ አስፈሪ መንግድ እየትጓዘች ነው። አገዛዙን የምትደግፉ ወገኖች ሁሉ ይሄ ነገር ሊያሳስብቸሁ ይገባል። ለዚህ መፍቴው ይህንን አስከፊ እጣ ፈንታ የዘረጋብንን አስከፊ አገዛዝ መቃወም ነው።  ኢትዮጲያውያን በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ በዘር፣ በፖለቲካ አምለካክት፣ በትምህርት. በችሎታ፣ በጾታ ሳንለያይ በጋራ በመሆን የጋራ አገራችንን በማደን የወያኔን አገዛዝ ሞት ማፋጠን ይኖርብናል።

ወያኔው ለ 26 አመታት ካደነዘዘን የህልም እዣት ውስጥ መንቃት አለበን። ተደራጅተን በትብብር ካልሰራን፤ በወያኔው ገዳይ ወጥመድ ወስጥ ወድቀን ወደ ሚያስፈራው መራራ ቀን መቀርባችን ነው። አገራችንና የወደፊት እጣ ደርሻችንን የመወሰኑ ጉዳይ የራሳችን እንጂ ሌላ የውጭ ሃይል ይህን ለኛ ይሰራልናል ብለን መጠበቀም ተስፋ ማድርገም የለብነም። ሱማሌ ከ 1983 ጀምሮ ያለችበትን የእርስ በርስ እልቂትና የጦረነት አገር መሆኑዋን መርሳት የለበንም። አገራችንና ህዝባችንን ከዚህ መሰል እልቂት ማዳን አለበን።

አገራችንን ካዳንና የተደገሰልንን የእርስ በርስ እልቂት ማቆም ስንችል፤ ተመካክርን ሰላም የነገስባትን፣ ሁሉም ዜጋ በእኩለነት የሚታይበትን፤ ለትምህርት፣ ለስራ፣ ንግድና ሌላም ሌላ የፖለቲካ ተሳትፎንም ጨምሮ ሁላችንም እኩል እድል ያለን ዲሞክራሲያዊና ፍታሃዊ አገር እንገነባለን። የፌድራል መንግስት ማድርግ ቢያሻንም የክልል ወስኖች ለኢኮኖሚ እድገትና ህዝብን በሚያቀራርብ መልክ ይዘረጋል እንጂ እንደወያኔው አገዛዝ ልዩነታችንን የሚያጎላ የአኮኖሚ ችገር  ፈጣሪ መሆን አይገባውም።

ዋናው ሁሌም ማስታወስ የሚገባን ቁም ነገር ግን ተባብርን በመስራት ብቻ ነው አገራችንን ማዳን የምንችለው። ስለዚህም ወያኔውን በመቃወም ላይ ያላችሁ የፖልቲካ ሀይሎች ሁሉ እንዲሁም በወያኔው ጎራ ያላችሁ ወገን፤  አንድ ላይ በመሆን አገር የማዳን ግዴታችንን እንድንወጣና የተደቀነብንን ክፉ እጣ አስቀርተን በነጻነት ራስችንም ልጆቻችንም እንድንኖር ጥሪ አቀርባለሁ።

The post ኢትዮጲያን  ለማዳን ማድርገ ያለብን ጉዳይ! (ከሙሉቀን ገበየው) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

What Needs to be Done to Save Ethiopia? (by Muluken Gebeyew)

$
0
0

Our country, Ethiopia  is heading to great disaster. Many people haven’t realised what is the stake. Some may underestimate the risk. Few may even think Ethiopia is in its best stable state taking  in account of the recent decades event.  The truth is Ethiopia is at risk of disintegration and bloody civil war that has never seen in its history. This grave risk is preventable! If the current generation ignored this warning (tell tale signs), there is  high possibility that the irreversible event would happen.

The challenging issue we face today is not only a question of democracy, but  the fundamental structure that holds the nation together  have been intentionally made to rust. The TPLF (Tigray People’s Liberation Front)  led regime which has  saw seeds of animosity, suspicion, paranoia, hate, division among Ethiopians by magnifying and creating false history  using our  minor difference in   language, culture , history and religion.

The minority regime has believed and put in practice a fatal ruling system. As a minority to rule Ethiopians (majority) is by dividing, making it weak and disorganised thorough its “divide and rule ” policy. It has created a structure that facilitate this division in form of federal boundaries. It has formulated policies that  ferments  inflammatory  remarks, false history, exaggeration  and divisive acts among different ethnicities and religion to wage  division,  animosity  and war among ourselves. No former regimes organised such kind of system and structure which strongly disintegrate the fundamental structure that holds us together.  Previous regimes used mainly class oppression as means of ruling Ethiopians although some minor form of religious and ethnic oppressive means topped up on the main  class oppression.

Since TPLF assumed power through arms in 1991 ( 1983 Ethiopian calendar), it created pseudo federal states which are  based on language, ethnicity  to maximize the division among Ethiopians and rule as police and judge.  Unfortunately these  system goes beyond as ruling means, it is shaking the fundamental structure that holds the nation together. TPLF is knowing and unknowingly losing its grip on latter part.

Different ethnic group “leaders”  are fed with false history, propaganda  and given pseudo identity. They are encouraged to develop hate towards other groups, principally “Amara” and the “orthodox religion” which are thought by TPLF as unifying force of the nation . The wicked propaganda created  a false promise and identity that each ethnicity can form it own country. TPLF already put  Article 39 “the right up to secession” on the constitution. This created a delusional believe systems on those who are made blind by TPLF drama.

 

TPLF’s  long held plan of ruling Ethiopia as superior force has  enabled it to loot the resources from Ethiopia to build the “Republic of Tigray” which it will declare at some time in the future. When rainy days come, TPLF would use Article 39 or other means  to establish  the ” Republic of Tigray” leaving other nationalities to declare such facilitating  the disintegration of Ethiopia.

The  eventual truth  is if every nationalities declare independence according to the current boundary TPLF made for them; it would eventually led to civil war among these “independent” nations; a war worse than Yugoslavia  and Somalia as this artificial TPLF boundary is neither factual nor representative. Each nation and nationalities leaders which dreamed independence will be doomed to unending fire which also  burn “the Republic  of Tigray” and the whole East Africa.

Ethiopians have to understand that the current main problem is not only about democratic system, but the stake of the country to stay as Ethiopia or facing catastrophic civil war. Imagine the independent Oromia  fighting Amara in the north, Ethio-Somale in the east and south east, the Southern people in the west and south west. The Amhara fighting with “Republic of Tigray” in the north, Afar in the east, Oromia in the south; Other numerous  ethnicities in the Southern Ethiopia fighting for border among themselves leading to unending unimaginable  civil war worse than Somalia.

Dear sisters and brothers, Ethiopia is heading to great danger. Ethiopians including those who support the regime have to  think about this grave danger waiting for us. The root cause of such catastrophes is TPLF. As mentioned earlier, is not only matter of democracy; it is matter of saving our country, our children and future generation.

TPLF killed all peaceful opposition parties and voices back in Ethiopia  who attempted  to counter this danger through peaceful means. TPLF has chosen anti-democratic means to rule the country under iron fist using its divide and rule  policy. Even after 26 years of ruling, there is no shift in TPLF thinking and policy in regard to inclusive and democratic Ethiopian government.

 

TPLF which controls the whole power is endangering our dear country and people to such grave. It will never give up  or share  power through peaceful means. The only remedy against this oppressive regime is to do the opposite of its thinking, policy and action. Ethiopian people of different ethnicity, language, culture, ability, gender, education and political opinion should   work together in solidarity with aim to preserve our country and  freedom which eventually easily kill TPLF.

We have to wake up from the false dream and hypnosis we are given  for the last 26 years. Unless organised and work in solidarity, the struggle would be futile and  each day we come close to the grave danger. It is up to us to save our country and future, we should never expect and depend on foreign power to do it for us. Remember Somalia, a stateless country since 1991.

Once we save our country and prevent the civil war plotted for us, we can build and  live in peaceful country  in democratic system where every Ethiopian’s right is respected. We all will have equal opportunity to education, employment, business and power. Our difference in  language and culture that make us colourful would be used as our variety and strength instead of our division. We would organise federal system  in our country not based on our difference but in way that will facilitate and fasten economic development and people unity  for every resident in that region. The current federal system is structured for division among people in way that doesn’t favour uniform development among ethnicities and people.

Remember it is only unity and working together that can save our country! I call up on every political organizations that oppose TPLF  and even to the regime supporters to come to these reality, work together and guide our people to save our country from dooms day  and ensure our freedom for ourselves and children.

The post What Needs to be Done to Save Ethiopia? (by Muluken Gebeyew) appeared first on Satenaw: Ethiopian News|Breaking News: Your right to know!.

Viewing all 3686 articles
Browse latest View live