Quantcast
Channel: admin – Medrek
Viewing all 3686 articles
Browse latest View live

በኮንሶ አፈና፣ እስራቱና ዝርፊያው ተጠናክሮ ቀጥሏል

$
0
0

ዛሬ መስከረም 20/ 2009 ዓ.ም.
konso-people-4-satenaw-news1. በኮንሶ ካራት ሆስፒታል ሁለት ሰራተኞች — የሆስፒታሉ የሰው ኃይል ሃላፊና የፋናንስ ሃለፊ በመከላከያ ኃይል ከቢሮኣቸው ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ሆስፒታሉ ለህዝቡ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ መስተጓጎል ፈጥሯል፣ በቀጣይም በአገልግሎቱ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ህዝቡ ሥጋቱን እየገለጸ ነው፡፡

2. ከ600/ስድስት መቶ/ በላይ ታጣቂ ኃይል አባላት ከካራት ወደተለያዩ የኮንሶ ገጠር ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ በህዝቡ ላይ ችግር እየፈጠሩ ውጥረት ነግሷል፡፡ ሠራዊቱ የተንቀሳቀሱት ወደ- ናላያ ሰገን፣ ጃርሶ፣ ቡቶ፣ ዴራ፣ ዴበና፣ እና ቶካች ቀበሌዎች ነው፡፡

በሁሉም ቀበሌዎች ታጣቂዎች ቤት ለቤት እየገቡ አሰሳ ያካሄዱ ሲሆን በሁለት ቀበሌዎች በግለሰቦች ላይ እስራትና ዝርፊያ ተፈጽሟል፡፡ ታጣቂዎች በዴበና ቀበሌ ነዋሪ የሆኑትን ጡረተኛ መምህር ጋሬ ቦያ ቤት በመበርበር ያገኙትን 31 ሺህ/ 31 000 ብር/ በጥሬ ገንዘብ፣ 2 /ሁለት/ ጄሪካን የተነጎረ- በከፊል የተነጠረ ሁለት/2/ ቅቤና አራት/4/ ጄሪካን የተጣራ ማር ዘርፈዋል፡፡ ከላይኛው ቶካች መንደር አቶ ሮቢቾ ረጋሳ ታፍነው ተወስደዋል፤ የት እንደተወሰዱ አልታወቀም፡፡

3. ከቀኑ 10 ሰዓት – ት/ቤታቸው ውጤት እንዲቀበሉ ተጠርተው የሄዱ የአስረኛና አስራ ሁለተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በታጣቂ ሃይል ተከበው በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ታግተዋል፡፡ እስካሁን 11፡45 ሰዓት ድረስ አልተለቀቁም፡፡ ከነዚህ ውስጥ አምስት ተማሪዎች ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ የተወሰዱ ሲሆን የአስራ-ሁለተኛ ክፍል ፈተናን 612 ነጥብ በማምጣት በከፍተኛ ውጤት ያለፈው ተማሪ ተስፋዬ በደረሰበት አሰቃቂና ዘግናኝ ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበትና በአስጊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

ይህን መረጃ ያቀበለኝ ወዳጄ የተማሪ ተስፋዬ ድብደባ በወረታ ሁሉንም ትምህርት ‹ኤ› አምጥቶ- ውጤቱ ሲመጣ በህይወት ያልተገኘው (የተገደለውን) የ10ኛ ክፍል ተማሪ በለጠ ንብረቱን ያስታውሰናል ፣ በማለት በከፍተኛ ቁጭት ገልጾኣል፡፡ በማያያዝም ስለኮንሶ ህዝባዊ ትግል ‹‹ሁላችን ኢትዮጵያዊን በተባበረና በተቀናጀ ትግል በአንድነት ቆመን ይህን አምባገነን ሥርዓት እስካላስወገድን በተናጠል ያጠቁናል፣ የምንቀዳጀው የተናጠል ነጻነት ግን የለም፡፡ ስለዚህ በተናጠል ነጻ ላንወጣ በተናጠል ማለቅ የለብንምና ትግሉን ማስተባበርና ማቀናጀት አለብን›› በማለት የመተባበር ጉዳይ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በተባበረና በተቀናጀ ህዝባዊ ትግል ኢትዮጵያዊ ክብርና ነጻነታችን እናስመልሳለን፡፡


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በተቀሰቀሰ ግጭት 8 የጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ

$
0
0

ኢሳት (መስከረም 19 ፥ 2009)
tplf-and-tigray
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሰርቀሌ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በነዋሪዎችና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 8 የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን እማኞች ለኢሳት ገለጹ።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉት በስፍራው ወርቅ ለማውጣት በሚል በቅርቡ ከ1ሺ በላይ የትግራይ ተወላጆች መስፈራቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰ አለመግባባት መሆኑ ተነግሯል። በዚሁ ግጭት ከተገደሉት የጸጥታ ሃይሎች በተጨማሪ ከ20-30 የሚደርሱ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የቤኒሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ አመራሮች ለኢሳት ገልጸዋል።

የንቅናቄው ሊቀመንበር አቶ ዮሴፍ ሃሚድ ናስር በቅርቡ በአካባቢው ያለን የወርቅ ሃብት ለማልማት በሚል ከትግራይ ክልል የመጡ ወታደራዊ አመራሮችና ሌሎች አካላት በጊዛን ሸርቆሌ መስፈራቸውን ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል።

በአካባቢው ተካሄዷል ያሉትን ህገወጥ ወራራ ተከትሎ በነዋሪዎች ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱንና ሰፋሪዎችም ቦታውን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ረቡዕ ግጭት መቀስቀሱን ገልጸዋል።
በነዋሪዎችና የወርቅ ሃብት ያለበትን ይዘው በሚገኙ አካላት ዘንድ በተፈጠረው ግጭት በትንሹ ስምንት የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውንና አካባቢው በውጥረት ውስጥ መሆኑን የንቅናቄው ሃላፊ አስታውቀዋል።

በርካታ መምህራን ከቤታቸውና ከመንገድ እየተወሰዱ እየታሰሩ ነው። [ታደሰ ብሩ]

$
0
0

teachers-training-satenaw-newsበብዙዎች የመምህራን “ስልጠናዎች” ላይ ዝምታ ከቃላት በላይ ተቃውሞን ለማስተላለፍ ጠቅሟል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግን አላስችል ያላቸው መምህራን ካድሬዎቹን አሳፍረዋል። ”ለምን እንዲህ አደረጋችሁ”፤ “ምን አቅብጧችሁ ተናገራችሁ?” ማለት አይቻልም፤ የካድሬዎቹ ድፍረት ትዕግስት ያስጨርሳል። ክፋቱ በእነዚህ አዳራሾች ውስጥ የነበሩ ጆሮጠቢዎች ሪፓርት የሚያደርጉትን አግኝተዋል። በዚህም ምክንያት በርካታ መምህራን ከቤታቸውና ከመንገድ እየተወሰዱ እየታሰሩ ነው።

ተናገሩ ተብለው ተወትውተው ስለተናገሩ ታሰሩ !!! ያሳዝናል !!! ለዚህ ኢፍትሀዊነት ውሳኔ የምሰጠው ምላሽ ምንድነው?

ዘንድሮ ት/ቤቶች እንደተከፈቱ ወዲያውኑ የሕዝባዊ አሻጥር ሥራዎች መጀመር አለባቸው። በሥራ መለገም፤ የታዘዙትን ሳይሆን ያልታዘዙትን መፈፀም … ወዘተ ከቀን አንድ ጀምሮ ተግባራዊ ልናደርጋቸው ይገባሉ ብዬ አምናለሁ።

“የሕዝባዊ አሻጥር ተግባራት ለመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች” እና “የሕዝባዊ አሻጥር ተግባራት ለመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን” የሚሉ ሁለት አጫጭር መጣጥፎችን በፌስቡኬ ለጥፌዓለሁ። እነዚህ ለመነሻ ያህል የቀረቡ ናቸው። ዜጎች እኔ ከዘረዘርኳቸው የተሻሉ ተግባራት ሊኖራቸው ይችላል። እነዚህም ሆኑ ሌሎች ትምህርት እንደተጀመረ በሥራ ላይ ቢውሉ መልካም ነው እላለሁ።

ለኮሌጅና ዩኒቨርስቲ መምህራን የሚሆኑ ሌሎች ዝርዝሮችን ማዘጋጅት የሚያስፈልግ ከሆነም እናስብበት።

2009 የትምህት ዘመን የሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ የሕዝባዊ አሻጥር እና የአዝባዊ አመጽ – ማለትም የሁለገብ ትግል – ዘመን ይሆናል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

Tadesse Biru Kersmo

ሰበር_መረጃ !… የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ መምህሩ ስዩም ተሾመ በወያኔ ደህንነት ታፍኖ ተወሰደ

$
0
0

danielየአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ መምህሩ ስዩም ተሾመ በወያኔ ደህንነት ታፍኖ ተወሰደ! በቅርቡ የመምህራንን ስብሰባ ተከትሎ ስዩም ተሾመ ሰፊ ትንታኔ አቅርቦ ነበር! ለረጅም ጊዜ በዚሁ ማህበራዊ ሚድያ ላይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትንታኔ በመፃፍ እንዲሁም በሆርን አፌርስ ድህረ ገፅና በሌሎችም የማህበራዊ ሚድያ ገፆች ላይም ፅሁፎቹ በተከታታይ ይወጡ ነበር።

Daniel Feyssa Atew Qorcha

ሽግሽግ እናደርጋለን እድሜ ለማራዘምና ለማጭበርበር?? [ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ]

$
0
0

21 / 1 / 2009 መቀለ

woyane-satenaw-news-5የህዝብ ፍላጎትና የህወሐት የሽግሽግ እስትራተጂ ህዝብን አታልሎ ለመግዛትና የስልጣናቸው እድሜ ለማራዘም ነው እንጅ ከ15 አመት በፊት ከነበረው የመተካካት ፡የመሸጋሸግ የተሀድሶ እናደርጋለን ብለው የሀገራችን ሚዲያዎች በሞኖፖል ይዘው በመሬት የለለ ለወጥ አመጣን እያሉ ለ90 ሚልዮን ህዝባችን የማይታይ ፡የማይዳሰስ ፡ የማይጨበጥ ፡የህልም እንጀራ አብልተውናል ።

በዛን ጊዜ መሸጋሸግ ያሉን የተባላሹ ፡በሙሱና የበሰበሱ ጋንግሪናቸው ቆርጠው ማስወገድ ሳይሆን የበሰበሱ ተብሎው ወደ የህዝብ አይን ብሌን የገቡ ከማእከላይ ኮሚቴ ወደ አምምባሳደርነት ፡ ወደ ያረጁና ያፈጁ መሰብሰበያ የሆነው በጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ በአማካሪነት ሰብስቦ ማስቀመጥ ደበቁዋቸው ፡ አጃቢ፡ ዘበኛ፡ የነበሩ ተላላኪዎች በስቢል ሰርቢስ ሞቅሞቅ ሰሚናር የውሼት 1ኛ ዲግሪ ፡ 2ኛ ዲግሪ (ማስትሬት ) በማስያዝ ማእከላይ ኮሚቴ ፡ስራ አስፈጻሚ በማድረግ አሮጌዎች ፡ሽሪኮቻቸው ፡ዘር ዘራቸው ለፈጸሙት ሙሱናና ኪራይ ሰብሳቢነት ፡ ስልጣናቸው ተጠቅመው ለሚፈጹሙት ምዝበራ ።በህዝብ ሲጠየቁ ዘበኛ ሆነው ሊጠብቋቸው ታሳቢ በማድረግ ነበር የተመለመሉና 15 አመት ሙሉ አየሰሩት የመጡ ነው ።

መላው ህዝባችን በሚገባ መገንዘብ ያለበት እነዚህ ፍጡራን ለዝህቺ አገር በሳይንሳዊ መንገድ ልትመራ የሚፈልጉ ቢሆኑ ንሮ በጠቅላይ ምኒስቴር ቢሮ አማካሪ መሆን የነበራቸው ፡ የኢኮኖሚ፡ብቁ የፓለቲካ ሳይንስ ፡ የጤናና የተፈጥሮ ሀብት ፡ የህግ ፡ የታሪክ ፡የትምህርቲ ወዘተ ተማራማሪዎች መመደብ ነበረባቸው ። እስከአሁን ግን 90 ሚሊዮን የኢትዮጱያ ህዝብ እንደ መንጋ እንስሳ እኩል በመቁጠር አሁንም ማጭበርበሩ ተያይዘውታል ።

ሌላ የፈጸሙት የመሸጋሸግ ስልት ፡በክልል አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ደረጃ የተባላሹ ፡በህዝብ የተጠሉ ፡አቅማቸው የጨለጡ ፡ ወደ ፓርላማ ተመራጭ አድርገው ምርጫው 100% ወንበር ተቆጣጥረው እንዲያመቁና እንቅልፋቸው እንዲጨርሱ ተደርገዋል እየተደረጉም ናቸው ።ጥቂቶቹ ደግሞ አንባሳደር ተሽመው የሀገራችን ዶላር በቪአይቪ ለመስተላለፍ ተጠቅመውባቸዋል ።
ዝቅያሉ ባለስልጣናት በዞን በወረዳ ሆነው ዋናዎቹ የምዝበራ አቀባዮች ደግሞ ወረዳ ወደ ዞን እርከን ፡ዞን ወደ ክልል ቢሮና ኤፈርት ኩባኒያዎች ተመድበዋል ። በአጠቃላይ ባለፈው 15አመት በተደረገው ተሀድሶ ቡዙ ተነግሮለት ግን ለኢህአደግ ህወሀት በሀሳብ የሚቃወም ካልሆነ በስተቀር በእከከኝ ልከክህ የትግል ስልት ነው የተጓዙትና ሀገራችን የመዘበሩት።

ታድሰናል የኪራይ ሰብሳቢነት ፡ሙሱና ጠነቅ ፡የምልካም አስተዳደር ፍትህ ዲሞክራሲ እንቅፋት ናቸው ብለው ለይምሰል ያሰሩዋቸው ፡የቀጡዋቸው ተራ የቀበሌ የጎጥ አስተዳዳሪዎች ያለክፍያ ሲያሰርዋቸው የነበሩ ናቸው ። በዛ ተሀድሶ የዋና ገዥዎች ታማኞችና አቀባዮች በለፉት 15 አመታት የነበሩ በአሁኑ ጊዜ የሀገራችን ሀብት ተቆጣጥረው ዘመናዊ ዘንዶ ሆነዋል ። እንዳውም እነዚህ ዞንዶዎች በአሁኑ ጊዜ ፍጹም የማይገፉ በቤተሰብ በገጥ ተሳስረው የታጠቁ ሀይል ሆነዋል ።

ከዘንድሮ የ2009ዓ ም ተሀድሶና ሽግሽግስ ምንእንጠብቃለን ???????,,
የተከበራችሁ ወገኖቼ በእኔ እምነትና በሁሉም የኢትየጱያ ህዝቦች በተለይ ቀለም የቆጠሩ ፡የገጠርና የከተማ ነዋሪ ምራቃቸው ዋጥ ያደረጉ ሽማግሌ ወይ የሚገነዘቡ ፡ ሙሁራንና ተመራማሪዎች በዚሁ የዘንድሮ የማጭበርበር የታድሶ ሽግሽግ እቅዳቸው እምነት የላቸውም ። ይህም ከወዲሁ ባደረጉት ስብሰባ በዩንቨርሲቲዎች በአስተማሪዎች በመንግስት ሰራተኞች ተቀባይነት አጥተዋል ።

እነዚህ መሪዎች ራሳቸው ባመኑበት ያለፈው የ15 አመት ተሀድሶ አልሰራም በባሰው በስብሰናል ብለዋል ። በተለይ ደግሞ ሀይለማርያም ደሳለኝ ብቻቸው ሆኑ እንጅ ሀቁን በማውጣት የሀገራቸን የስርአታች ጠንቅ ሆነው ያሉ ኢህአደግና አጋሮቹ ፡እሱ የሚመራው መንግስት አመራር ስልጣናቸው ተጠቅመው የሀገራችን ሀብት ከመመዝበራቸው አልፈው ኪራይ ሰብሳቢነት ጸረ ዲሞክራሲ ጠባብነት እና ትምክህት ተስፋፍቶ አደጋላይ ወድቀናል ። የጠባብነትና የትምክህት የዘረኝነት በግንባር ቀደምትነት ተጠያቂዎች የህወሐትና የበአዴን መሪዎች ናቸው ቡለዋል ። ባዶ ንግግር ጥርስ የለለው አንበሳ ሆኖ ቀረ ።

ባለፈው ሳምንታት አራቱ ዓንኳር ፓርቲዎች ስራ አሰፈጻሚና ማእከላይ ኮሚቴ በስብሰባና በገምጋም ተጠምደው ሰንብተው ውጤቱ ደግሞ ፡ ሽግሽግ እናደርጋለን ብው ህወሐት፡ በአዴን ፡ዴሄደን ፡ኦሆዴድ ወስነው ወጥተዋል የስብሰባቸው ውጤት በሁሉም ሚዲያዎች ታውጀዋል ።በተለይ የህወሀት የገምጋም ውጤት እጅጉን አጭበርባሪና ተቀባይነት አለገኜም ። ምክንያቱም አዋጁ ካለፉት የ15አመት የተሀድሶ ዘመን የቃላት ለውጢም የለውም ።

የህወሐት አህአደግ ስርአት ሊታደስ ከሆነ ፣ አቅማቸው ሟጥጦው አጨረሱ ፡አገልግለታቸው ጨርሰው ሀሳብ የማመንጨት ይሁን የአማራር ድጋፍ አቅማቸው ፍጹም የጨረሱ በአመካሪነትበታሀድሶ ስብሰባቸው ከሚያሳትፉ አቅም ያላቸው ሁሉም አቀፍ ተመራማሪዎች ዜጎች ለምን አያሳትፉም ።
ለምን ከሁሉ ገለልተኛ የሆኑ ዜጎችና ይመለከተናል ወይ ያገባናል ለሚሉ ተሳታፊነት ለምን አይፈቅድም ? እነዚህ ፍጡራን ወደ ጎናቸው ሙሁራን ለማስጠጋት አይፈቅዱም ምክንያቱም ከጥንት ይዘውት የመጡ ባህሪ ነው ።

ይቀጥላል
ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ
21 /1 2009 ዓ ም

ህውሓት ሃያ አምስት አመት ሙሉ የሳበው ካርድ አልቆበታል [ናትናኤል አስመላሽ]

$
0
0

የህውሓት የመጨረሻ ካርድ !!!

TPLF (1)የቀሩት ሁለት ካርዶች ብቻ ናቸው። አንደኛው በትግሉ ጊዜ ሲጠቀምበት የነበረው አማራ እና ኦሮሞ ነው ጠላትህ የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ዓረና የአማራ የኦሮሞ ተላላኪ ነው ከአማራ እና ከኦሮሞ ጋር ሆኖ ሊያጠፋቹ ነው የሚል ነው። ህውሓት አሁን መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከትግራይ ህዝብ ሙሉ በሙሉ አመኔታ ተነግፈዋል(አጥታለች)፣ ይህ ብቻም አይደለም የህውሓት አባላት በህውሓት ላይ ተስፋ ቆርጠው አማራጭ ፓርቲ ፍለጋ ላይ ናቸው።
.
ህውሓት በየገጠሩ እና ከተማው አማራ እና ኦሮሞ ተባብረው ሊያጠፍዋቹ ነው ተነሱ ዓረናም ተባባሪ ነው በማለት ቀን ከለሊት እየቀሰቀሰች ነው። የዚህ ሁሉ ምንጭ የህውሓት የስልጣን ጥም እና የህውሓት መጨረሻችን ምን ይሆን ከሚል ፍራቻ ነው። ህውሓት ከትግራይ ውጭ ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ውስጥ ለውስጥ በማስፈራራት እና ተጠንቀቁ በማለት የስልጣን ማራዘምያ ዘዴም ከፍታለች። ለምሳሌ በሃረህ ለሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በተለይ የትግራይ መታወቅያ ያለባቸው በማስፈራራት ላይ ትገኛለች።
.
የህውሓት መጨረሻ ልክ የሳዳም እና የጋዳፊ መጨረሻ እንደሚሆን አጠያያቂ አይደለም !ይህንን የምታውቅ የትግራይ ወጣት ከህውሓት ቦሃላ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመተባባር በአንድነት እንደሚኖር አውቀህ በየከተማው እና በየገጠሩ ላለው የትግራይ ህዝብ በማስረዳት አዲስትዋን ኢትዮጲያ ለመገምባት ታሪካዊ ግዳጅህን ተወጣ። የትግራይ ህዝብ እንደ ማንኛው የኢትዮጲያ ህዝብ ከህውሓት በፊት የተፈጠረ ህዝብ ነው። የትግራይ ህዝብ ከህውሓት አልተጠቀመም አዎ የህውሃት ባለስልጣናት እና ቤተሰቦቻቸው ግን ከትግሉ ተጠቅመዋል፣ ስለሆነም ከህውሓት ቦሃላ የትግራይ ህዝብ እንደማንኛው ጭቁን ህዝብ ከህውሃት የጭቆና ቀንበር ወጥቶ አብሮ እንደሚኖር ምንም ጥርጥር የለውም ፣ ስለሆነም የትግራይ ወጣት ሆይ የትግራይ ህዝብ ከህውሓት ቦሃላ ከሁሉም ህዝቦች ጋር አብሮ እንደሚኖር በማወቅ በማስረዳት እና መከታ በመሆን ታሪካዊ ግዳጅህን ተወጣ።
.
ዓረና ትግራይ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ተላላኪዎች ሳይሆን የትግራይ ህዝብ አማራጭ ፓርቲ መሆኑን ታውቃለህ፣ የትግራይ ህዝብ ብቸኛ ጠላት ህውሓት ነው። አዎ ትናንትም ዛሬም ነገም የትግራይ ህዝብ ብቸኛው ጠላት ህውሓት ነው!!! የትግራይ ህዝብ ሆይ በከፈልከው ደም እና አጥንት ለዓረና የመታገል እና የማታገል መብት የምትሰጠው አንተ የትግራይ ህዝብ እንጂ ህውሓት አይደለም ! ህውሓት ሃያ አምስት አመት ሙሉ በስምህ ነግደዋል፣ዘርፈዋል፣ገድለዋል አሁን የትግራይ ህዝብ ልክ እንደ ሌላው ህዝብ ለውጥ ትፈልጋለህ፣ የለውጡ መሪ ደግሞ አንተ ነህ።
.
ህዝቦች በታሪክ ተጣልተው አያቁም አምባገነኖች ግን አዎ ህውሓቶች ግን አዎ።የትግራይ ህዝብ የወደፊት እጣ ከሌሎች ህዝቦች እንጂ ከህውሓት ጋር አለመሆኑን የተገነዘብከው የህውሓት ካድሬም በርታ፣ ጊዜው አሁን ነው ዓረና ማለት ሰላም ፍቅር አንድነት መከባበር ማለት ነው። የትግራይን ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ከሚያፋቅር ዓረና ጎን ተሰልፈህ የትግራይን ህዝብ መከራ ስደት ወዘተን ለማስቆም ታገል።የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ከትግራይ ህዝብ የወጡ የህውሓት አምባገነኖች እንጂ ከትግራይ ህዝቦች ጋር ለአመታት የኖሩ የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች አይደሉም።አዎ “ትናንትም ዛሬም ነገም ” የትግራይ ህዝብ ብቸኛው ጠላት ህውሓት ነው!!!

በአዲስ አበባ “አቧሬ” አካባቢ ሁለት ሺህ ሕጋዊ ቤቶች ይፈርሳሉ [ዋዜማ ራዲዮ]

$
0
0

abware-area-satenaw-newsዋዜማ ራዲዮ- በየካ ክፍለ ከተማ ሚስስ ሳንፎርድ ትምህርት ቤት አካባቢ የሚገኙ ሁለት ሺሕ የሚጠጉ ቤቶች በቅርብ ወራት ዉስጥ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሰፋፊ የግለሰብ ይዞታዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የቀበሌ ቤቶች ናቸው፡፡ እንዲፈርሱ የዉሳኔ ሐሳብ የተሰጠባቸው የአቧሬ ሰፈሮች ሕገወጥ በመሆናቸው ሳይሆን ቦታው ለመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች በእጅጉ በመፈለጉ ነው፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች ባሳለፍነው ሳምንት በጽሑፍ የተላለፈላቸው መመሪያ እንደሚያስረዳው አቧሬና አካባቢውን በአስቸኳይ ለማልማት አቅጣጫ በመያዙ በወረዳ 6 (በቀድሞ አጠራር ቀበሌ 09) ዙርያ የሚገኙ የግል ይዞታዎችና የቀበሌ ቤቶች ቁጥርና ስፋት በዝርዝር አጥንተው በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲያቀርቡ በማዕከል ኃላፊዎች ታዘዋል፡፡

በአንጻሩ የቤቶቹን መፍረስ ዉሳኔ በጥርጣሬ የሚመለከቱ በክፍለከተማ በተለያየ ኃላፊነት ደረጃ እየሰሩ የሚገኙ የዋዜማ ምንጮች በቅርብ ወራት ዉስጥ ምንም አይነት የቤት ማፍረስ ሥራ እንደማይከናወን ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ይህም የሚሆነው ቤቶችን ለልማት ሲባል የማፍረስ ተግባር ለተቃውሞ እንቅስቃሴ በር ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት በካቢኔው ዘንድ በመኖሩ ነው፡፡

አገሪቱ ወደለየለት ብጥብጥ እንድታመራ የሚሹ አክራሪ ኃይሎች በዋና ከተማዋ አመጽ ለመቀስቀስ አጀንዳ አጥተዋል፤ እኛ ቤቶችን ለልማት ስናፈርስ እነርሱ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ሊጠቀሙበት ይችላሉ የሚል ስጋት በከንቲባው ዋና የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ተወልደ ገብረጻዲቅ ሲንጸባረቅ በተደጋጋሚ ሰምቻለሁ ይላል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የይዞታ ጽሕፈት ቤት ዉስጥ በኦፊሰርነት የሚያገለግል ወጣት የድርጅት አባል፡፡

ቤት የማፍረስ ተግባር ዘንድሮ የማይታሰብ ነው የሚሉት ወገኖች እንደ ተጨማሪ ማስረጃ የሚያቀርቡት በ2008 መጨረሻ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀርሳ፣ ኮንቶማና ማንጎ ሰፈሮች ዉስጥ ሕገወጥ ሰፋሪዎችን ለማንሳት በተደረገው ሙከራ የወረዳ አንድ ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ የነዋሪዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ ዉጥረት መንገሱን በማስታወስ ነው፡፡ በወቅቱ በነዋሪውና በፀጥታ ኃይሎች መሐል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከንቲባው አቶ ድሪባ ኩማ ሕገወጦችን የማፍረስ ጉዳይ ለድርድር አይቀርብም የሚል መግለጫ ቢሰጡም በዚያው ሰሞን እንዲፈርሱ ቀነ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩ ሰፈሮች ለጊዜው እንዲታለፉ ለክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና ማደስ ኃላፊዎች የቃል ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር፡፡

እንደ ምሳሌም የቀርሳና ኮንቱማ ሰፈሮችን የሚያዋስነውና በርካታ ሕገወጥ ሰፋሪዎች ይገኙበታል የሚባለውን የአቃቂ ቃሊቲ መንደር ለማፍረስ ግብረኃይል ተደራጅቶ፣ ቀን ተቆርጦ፣ ልዩ የፖሊስ ኃይል ተመድቦ፣ ዶዘሮች ወደ አካባቢው እንዲቀርቡ ከተደረገ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት የማፍረስ ሂደቱ ድንገት እንዲታጠፍ ሆኗል ይላሉ የወረዳው ባልደረቦች፡፡

የዋዜማ ዘጋቢ ያናገራቸውና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንድ የአራዳ ክፍለ ከተማ ሰራተኛ ዉሳኔው የታጠፈው ዜጎችን በክረምት ማፈናቀል አግባብ እንዳልሆነ በካቢኔው አቅጣጫ በመያዙ ነው ሲሉ ሌሎች በመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤት የሚሰሩ ኦፊሰሮች ደግሞ በተቃራኒው እንዲያውም ሕገወጥ ቤቶች እንዲፈርሱ የሚመረጠው በክረምት ወቅት ነው፡፡ ይህም በበጋ ቤቶችን ማፍረስ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ሊያርቃቸው ስለሚችል ነው ሲሉ ተጻራሪ ሐሳቦችን ያቀርባሉ፡፡

በኦሮሚያ መንግሥትን ለሰፊ ሕዝባዊ ተቃውሞ የዳረገው የተቀናጀ ማስተር ፕላን ለጊዜው እንዲታጠፈ ከተደረገ በኋላ አዲስ አበባ የተናጥል የከተማ መሪ ፕላን ለማዘጋጀት ተገዳለች፡፡ ኾኖም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እስከዛሬም በይፋ አላጸደቀችውም፡፡ የሕዝብ ዉይይት ተደርጎ በአስቸኳይ ይፀድቃል የተባለው መሪ ፕላን ከዛሬ ነገ እየተባለ ለወራት ሲንከባለል ቆይቷል፡፡ ያም ኾኖም አስሩም ክፍለ ከተሞች በአሁኑ ሰዓት የመሬት ጉዳዮችን እየፈጸሙ ያሉት ያልጸደቀውን የከተማዋን መሪ ፕላን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ባይፀድቅም እየሰራንበት ነው፤ በሱ መስራት ከጀመርን ዓመት አልፎናል ይላል ለዋዜማ ሐሳቡን የገለጸ አንድ የአራዳ ክፍለ ከተማ የመሬት ባለሞያ፡፡

በአዲሱ መሪ ፕላን የከተማዋ 30 በመቶ ለአረንጓዴ ልማት የሚፈለግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለአረንጓዴ ቦታ የተከለሉ ሥፋራዎች ዉስጥ እየኖሩ ያሉ ዜጎች በሂደት እንዲነሱ እንደሚደረግ የከተማዋ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡ ኾኖም ቁጥራቸው በርካታ ከመሆኑ ጋር ምትክ ቦታ ለመስጠት አስተዳደሩ ፈተና እንደሚገጥመው ከወዲሁ ተሰግቷል፡፡

ባለፉት ዓመታት የከተማዋን አብዛኛዎቹን የቆረቆዙ መንደሮች በመልሶ ማልማት ለማልማት በተደረጉ እንቅስቃሴዎች በሰንጋ ተራና አካባቢው 14 ሄክታር መሬት ለፋይናንስ ተቋማትና ለ40/60 የቤት ልማት ፕሮጀክት የተላለፈ ሲሆን በልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ 16 ሄክታር መሬት ደግሞ ለ20/80 ቤቶች ልማት ማከናወኛ የተሰጠ ነው፡፡ በተለይ በልደታ ክፍለ ከተማ የልደታና አካባቢው መልሶ ማልማት ፕሮጀክት በመስተዳደሩም ሆነ በፌዴራል ደረጃ በስኬታማነቱ በተደጋጋሚ የሚወደስ ፕሮጀክት ነው፡፡ የግልና የመንግሥት ባንኮች ሕንጻዎችን፣ ፀሜክስ ኢንተርናሽናል እያስገነባው እንዳለው አይነት ባለ ኮከብ ሆቴል ፕሮጀክቶችን፣ ፍሊንስቶን ያስገነባውን ዘመናዊ የገበያ ማዕከል (ሞል) ተግባራዊ ማድረግ የተቻለው በዚህ እንደ ሞዴል በሚወሰድ የመልሶ ማልመት ሥራ እንደሆነ በኃላፊዎች በተደጋጋሚ ይገለጻል፡፡

ይህ የልደታ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት የኮንዶሚንየም ነዋሪዎች ከመሀል ከተማ ርቀው እንዳይሰፍሩ፣ በመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች መሐል መራራቅ እንዳይኖር ያደረገ ልማት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ አማካሪ አቶ አባይ ፀሐዬ በተደጋጋሚ ሲያሞካሹት ይሰማል፡፡ ኾኖም ተመሳሳይ የመልሶ ማልማት ስኬት ሊደገም አልቻለም፡፡ ብዙዎቹ በመልሶ ማልማት ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ዜጎች ከነባር ይዞታቸው ተፈናቅለው በከተማዋ ጫፍ በሚገኙና መሠረተ ልማት ባልዳሰሳቸው ሥፍራዎች እንዲሰፍሩ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በቅርቡ የመፍረስ አደጋ የተጋረጠበት አቧሬ ሰፈር ከአንድ ሺ ካሬም የሚልቁ ሰፋፊ ይዞታዎች የሚገኙበት ሲሆን የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ዋና መቀመጫም የሚገኘው በዚህ ወረዳ ነው፡፡ በመልሶ ማልማት ምክንያት የሚነሱ ዜጎች ይዞታቸው ምንም ያህል ሰፋፊ ቢሆን እንኳ በመኖርያ ቤት እስከተመዘገበ ድረስ በምትክነት የሚሰጣቸው የካሬ ስፋት ከ500 ሜትር ስኩዌር ካሬ በላይ እንዳይሆን መመሪያው ያዛል፡፡ ኾኖም ተነሺዎቹ ይዞታቸውን በግላቸው የማልማት ፍላጎት ካላቸውና የፋይናንስ አቅም በራሳቸው መፍጠር ከቻሉ መሪ ፕላኑ በሚያዘው መሠረት በአካባቢው ዘጠኝ ፎቅና ከዚያ በላይ የመገንባት መብት ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ ግን ለብዙ የከተማዋ ጎስቋላ ነዋሪዎች የሚታሰብ ጉዳይ አይሆንም፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት ዉስጥ በልማት ስም ከፈረሱ የአዲስ አበባ ከተሞች መሐል አሜሪካን ግቢ ተጠቃሽ ነው፡፡ በአካባቢው ለ30 አመታት ነዋሪ የነበሩ ዜጎች የይዞታ ባለቤትነትን ከማረጋገጥና ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ዉዝግብ ዛሬም ሙሉ በሙሉ ምላሽ አላገኘም፡፡ ኾኖም ከአካባቢው የተነሱ ሱቆች ራሳቸውን በቡድን እያደራጁ ቁራሽ መሬቶች እየተሰጣቸው ቆይቷል፡፡

ከነዚህ አካባቢዎች በተጨማሪ አዲስ ከተማ፣ ጎጃም በረንዳ፣ ቁጭራ ሰፈር፣ ጣሊያን ሰፈርና ገዳም ሰፈር በመልሶ ማልማት የሚፈርሱና እየፈረሱ ያሉ አካባቢዎች ናቸው፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዉስጥ የሚካተተው የመስቀል አደባባይ ኢሲኤ ጀርባ 4 ሄክታር መሬት፣ አራዳ ክፍለ ከተማ ዉስጥ የሚካተተው የ አራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ 24 ሄክታር መሬት በመልሶ ማልማት ተነስቷል፡፡ የባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ በሊዝና በምሪት ለባለሀብቶችና ለድርጅቶች የተላለፈ ሲሆን ቦታ ከወሰዱ ድርጅቶች መሐል የብአዴን ጽሕፈት ቤት ግንባታ፣ ሁለት የግል ሆስፒታሎች ግንባታ፣ የዳሽን ባንክ ቅርንጫፍ ቢሮ ግንባታ፣ የሂልኮ ኮምፒውተር ኮሌጅ ግንባታ በአመዛኙ ተጠናቋል፡፡

የባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ እየተከናወኑ ካሉ ፕሮጀክቶች ትልቁ በአምባሳደር ልብስ ስፌት ባለቤት በአቶ ሰኢድ መሐመድ ብርሃን እየለማ ያለው ቦታ ሲሆን ከአርበኞች ግንብ ሕንጻ ጎን ከፓርላመው ባሻገር የሚገኝ 3ሺ ካሬ ቦታ ነው፡፡ አገልግሎቱም ባለ 4 ፎቅ ሰፊ የገበያ ማዕከል ግንባታ ነው፡፡ ይህ ግንባታ ረዥም ዓመታትን የወሰደ ቢሆንም እስካሁንም አልተገባደደም፡፡ የባሻ ወልዴ ችሎት መልሶ ማልማት ቦታዎች በተፈለገው ፍጥነት አለመሄዳቸው ብቻም ሳይሆን ብዙዎቹ ቦታዎች ከፈረሱ አመታት ቢያስቆጥሩም አሁንም አለመልማታቸው የነዋሪዎች መነጋገሪያ ሆነዋል፡፡ በመሪ ፕላኑ መሰረት አካባቢው ለቤተመንግሥትና ፓርላማ ቅርብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከ4 ፎቅ በላይ መገንባትን አይፈቅድም፡፡

ተመሳሳይ ሰፊ የመልሶ ማልማት ሥራ ካከናወኑ ክፍለ ከተሞች መሐል የቂርቂስ ክፍለ ከተማ ተጠቃሽ ሲሆን ለአፍሪካ ሕብረት አዲሱ ሕንጻ ግንባታና ለኢሲኤ (የቀድሞው አፍሪካ አንድነት ድርጅት የመጀመርያ መሰብሰቢያ አዳራሽ) ማስፋፊያና ፓርክ ሲባል ኢስጢፋኖስ ጀርባ የነበሩ በርካታ ነዋሪዎችን ከቀያቸው ለማፈናቀል ተገዷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ካዛንቺስና አካባቢዋ በርካታ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ መከናወን የቻለውም ቦታው ለመልሶ ማልማት በመዋሉ ነው፡፡

አሁን ተመሳሳይ ሰፋፊ የሆቴል ፕሮጀክቶች ይካሄዱበታል ተብሎ የሚገመተውና የካዛንቺስ 2 መልሶ ማልማት ዘመቻ በሚል የሚታወቀውን የልማት ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ራዲሰን ብሎ ማዶ፣ ኢንተርኮንቲነንሰታል ሆቴል ፊትለፊት፣ ኦራኤል ቤተክርስቲያን ተሻግሮ የሚገኙ ሰፈሮች ሙሉ በሙሉ እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጂ ቦታዎቹ ከጸዱ ዘለግ ያለ ጊዜ ቢያስቆጥሩም የፈረሱት ቦታዎች እስከአሁንም ለአልሚዎች አልተላለፉም፡፡

በከተማዋ ነዋሪዎች እንደ ተደጋጋሚ ቅሬታ የሚነሳውም ይኸው ጉዳይ ነው፡፡ ድሀን በልማት ስም አፈናቅሎ መተው፣ ወቅቱን ያገናዘበ ተገቢ ካሳን አለመስጠት፣ የማኅበራዊ ምስቅልቅል የሚፈጥሩ አሰፋፈሮችን መከተል የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለረዥም አመታት ያማረረ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የፈረሱ ቦታዎች ለአመታት ያለምንም አገልግሎት ተጥረው እንዲቀመጡ መሆናቸው ግርትን የሚፈጥር ጉዳይ ነው፡፡ ይህም አንድም በመስተዳደሩ ድክመት ቦታዎቹን ለአልሚዎች በጊዜ ያለማስተላለፍ ችግር ጋር የሚያያዝ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አልሚዎች ቦታዎቹን አጥረው ይዞታቸውን ካስከበሩ በኋላ ለዓመታት ግንባታ ለማከናወን ሳይፈቅዱ መቆየታቸው ነው፡፡

ይዞታዎች ለአልሚዎች ሲተላለፉ የግንባታ መጀመርያ ጊዜና ማጠናቀቂያ ጊዜ በዉል ተለይተው፣ የሊዝ ዉል ፈርመው የሚገቡበት አሰራር ቢኖርም ይህ ሁኔታ ለሁሉም ዜጎች በእኩል የሚሰራ አልሆነም፡፡

በዚህ ረገድ በከተማዋ የአስተዳደር እርከን በሁሉም ደረጃ ከኤህአዴግ አባላት ሳይቀር ሰፊ ትችትና ትዝብትን የሚያስተናግዱት በሳኡዲያዊው ባለሀብት ሼክ መሀመድ አላሙዲ የተያዙ ሰፋፊ የከተማዋ ይዞታዎች ናቸው፡፡ በተለይም ከካዛንቺስ ኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ጎን ተቆፍሮ የሚገኘው ቦታ መለስተኛ ኩሬ ፈጥሮ ለአካባቢው የጤና ጠንቅ እስከመሆን የደረሰ ሲሆን በኢንተርኮንቴኔንታል ሆቴል የሚያርፉ እንግዶች መስኮቶቻቸውን ለመክፈት እስከመቸገር መድረሳቸው ይነገራል፡፡ የሸራተን ማስፋፊያ በሚል ለጎልፍ ክለብና ልዩ ልዩ መዝናኛዎች የታጠረውና በተለምዶ ፖሊስ ጋራዥ የሚባለው ሰፊ ቦታ ማጅራት መቺዎችና ኪስ አውላቂቆች መሸሸጊያ እየሆነ እንደመጣ ነዋሪዎች ብቻም ሳይሆን የከተማዋ ፖሊስ ጽሕፈት ቤትም የሚያነሳው ጉዳይ ሆኗል፡፡ የፒያሳው ግዙፍ የመንታ ሕንጻዎች ፕሮጀክት በዲዛይን ለውጥና በሌሎች ጥቃቅን ሰበቦች የተነሳ ይህ ነው የሚባል ግንባታ ሳይካሄድበት ለ18 ዓመታት ታጥሮ መቀመጡም የከተማዋ ነዋሪ በአስተዳደሩ ላይ እምነት እንዲያጣ ካደረጉት አበይት ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡

“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” “አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” የህወሃት ነፍጠኞች

$
0
0

በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

slide15-e1466825122855ሰዎችን እንደ እህል በዘር ጆንያ እየሠፈረ በፈለገበት ሣጥን ውስጥ ማስገባት ዓላማው የሆነው የትግራይ ሕዝብ ነጻአውጪ ግምባር (ህወሃት)፤ በኦሮሞ ተቃውሞ #oromoprotest እና በአማራ ተጋድሎ #amhararesistance የተነሳው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ዕንቅልፍ ስለነሳው በተለይም ደግሞ የሁለቱ በኅብረት መቆም ኅልውናው ላይ አደጋ ስለጣለበት ሶማሊና አፋር ክልል መንጎዳጎድ ጀምሯል፡፡

ለኢትዮጵያ ቅንጣት ታህል ደንታ የሌለው ህወሃት የኦጋዴንን ሕዝብ እንዴት እንደፈጀ፣ ሴቶችን (ህጻናትንና ወንዶች ልጆችን ጨምሮ) እንደደፈረ፣ ለመከራና ለስቃይ እንደዳረገ የተረሳ መስሎት ሰሞኑን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ቅኝቱንም ሆነ ዜማውን የሶማሊ አድርጎታል፡፡ የህወሃትን ግፍ እንኳንስ የክልሉ ነዋሪዎች ሊረሱት ስዊድናውያኑ ማርቲን ሺብዬና ዩሃን ፐርሸን እስከ ሞት የሚረሱት አይደለም፡፡

“ዝም የተባለው ዳርፉር” በመባል ከዳርፉር እልቂት ጋር በእኩልነት የሚጠቀሰው የኦጋዴን ሰቆቃ ፈጻሚዎች ጨካኞቹ ህወሃቶችና ተባባሪዎቻቸውን ድርጊት ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ዳጎስ ያለ መረጃና ማስረጃ የያዙበት ነው፡፡

የኦጋዴን ጉዳይ የመለስ ራስምታት መሆኑን ጠቅሶ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በቦታው ስለተፈጸመው ግፍ መግለጫአውጥቶ ነበር፤

“… ለወራት ያህል በመለስ ታማኞች ትዕዛዝ ሰጪነት የተከበቡት ኦጋዴኖች በረሃብ ተጠበሱ። ችግሩ ሲጠናባቸው ሽማግሌ በመላክ “በረሃብ ማለቃችን ነው። እኛ ንፁሃን ዜጎች ነን። ህፃናት እየተጎዱ፣ ከብቶቻችን እያለቁ ነው’’ በማለት ከከበባው ለመውጣት ጥያቄ ቢያቀርቡም ትእዛዝ ከተላለፈላቸው የጦር አዛዦች ያገኙት መልስ ጥይት ነበር። በተፈጥሯቸው አንድ ቦታ ተወስነው መኖር የማይችሉ አርብቶ አደሮች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ተከልክለው ለአራትና አምስት ዓመታት እንዴት ኖሩ? ምን ያህልስ ሰብዓዊ ቀውስ ደረሰ? ከአመታት የስቃይ ኑሮ በኋላ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ደርሶ በኦጋዴን የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሄደ። ንፁሃን ጉድጓድ ተምሶ በጅምላ እንዲቀበሩ ተደረገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መለስ ስለ ኦጋዴን ሲነሳ ያማቸው ጀመር። ከዋናው የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የሰላም ስምምነት አድርጌያለሁ ቢሉም አካባቢውን ገለልተኛ ወገኖች ገብተው እንዲመለከቱት ፈቅደው አያውቁም። ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች (ማርቲን ሺብዬና ዩሃን ፐርሸን) ላይ የተወሰደው ርምጃም የዚሁ ‹ምስጢር ይወጣብኛል› ፍርሃቻ አካል ስለመሆኑ ጥርጥር የለንም … ” (የመግለጫው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)

ከሶስት ወር በፊት “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ግራሃም ፔብልስ በኦጋዴን የሚካሄደውን የሚዘገንን ግፍ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም አውጥቶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ June 25, 2016 አትመነው ነበር፡፡ የሰሞኑ የህወሃት የማስመሰያ “የፍቅር እሽሩሩ” ፈጽሞ የማይረሳ እንደሆነና የኦጋዴን ወገናችን መከራ የእኛም በመሆኑ እንደሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከህወሃት ቀንበር ነጻ መውታት ያለበትና ፍትህ ማግኘት የሚገባው መሆኑን ለማሳየት እንዳል ደግመን አትመነዋል! “በጭራሽ አንረሳውም!!”


 “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”

“አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” የህወሃት ነፍጠኞች

ogaden 4የኢትዮጵያን ሕዝብ በነጻ አውጪ ስም እስካሁን በግፍ እየገዛ ያለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሥልጣን በኃይል ከመያዙ በፊት ሲፈጽም የነበረውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ ሥልጣን ከያዘም በኋላ ላለፉት 25 ዓመታት ቀጥሎበታል፡፡ ህወሃት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ግፍ ያልተፈጸመበት አካባቢ የለም የሚለው አባባል የተጋነነ አይደለም፡፡

“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ግራሃም ፔብልስ በኦጋዴን የሚካሄደውን የሚዘገንን ግፍ ሰኔ 15፤ 2008ዓም (June 22, 2016) ዩትዩብ ላይ ለቋል፡፡ (ዘጋቢ ፊልሙ እዚህ ላይ ይገኛል)

“በዛፍ ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰቅለውኝ ነበር፤ በርካታ ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ አወረዱኝ፤ … ከዚያም ካሁን በኋላogaden 1 የምንልሽን ታደርጊያለሽ አለበለዚያ እንገድልሻለን አሉኝ” የግፍ ዶፍ የወረደባት አናብ ከተናገረችው፡፡

የሚዲና የዕርዳታ ሥራዎችን የሚያካሂዱ ሁሉ ወደ ኦጋዴን እንዳይገቡ በህወሃት ትዕዛዝ ተደርጎባቸው ባለበት ባሁኑ ወቅት በኦጋዴን የሚካሄደው ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፤ እስር፣ እንግልት፣ ወከባ፣ … በድብቅ ቀጥሏል ይላል ጋዜጠኛ ግራሃም፡፡

ዘጋቢ ፊልሙን ለመሥራት መረጃው የተሰበሰበው ከሚሊታሪው የኮበለሉና ሌሎች ለህይወታቸው ያልሳሱ ደፋሮች በሰጡት ምስክርነት ነው፡፡ በተለይም ከኢትዮጵያ ኮብለለው በቅርቡ ኬኒያ ልትዘጋው ወደ ወሰነችው የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ የሚገኙ ሦስት ሴቶች የህወሃት ሠራዊት ስላደረሰባቸው መከራ፣ ሥቃይና አስገድዶ መድፈር ተግባራት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ሚሪያም

ወደ ዳዳብ በግንቦት 2006ዓም የመጣችው ሚሪያም ለሁለት ዓመት ተኩል እንዴት እንደተሰቃየች፣ አስገድዶ መድፈርና ድብደባ እንዴት እንደተፈጸመባት ትናግራለች፤

“እንደ ማሰቃያ ይሆን ዘንድ እስኪደክመኝ ድረስ ሬሣ አቅፌ እንድቆም ተደርጌአለሁ፤ ከዚያም ሚጥሚጣ የሞላበት ላስቲክ በራሴ ላይ አስረውብኛል፤ ገመዱን ሲያስሩት አጥብቀው ከአንገቴ ጋር በማሰራቸው ራሴን ስቼ ወድቄ ነበር፡፡ ከዚያ ለብዙ ሆነ እየተፈራረቁ አስገድደው ደፈሩኝ …”ogaden 10

“ኦጋዴን በሚገኘው እስርቤት 1097 የምንሆን ነበርን፤ ቁጥሩን በትክክል አውቀዋለሁ ምክንያቱም በየቀኑ ማለዳ ላይ እያሰለፉ ከቆጠሩን በኋላ በቡድን በቡድን እያደረጉ ይከፋፍሉን ነበር፤ …

“(የተያዝን ጊዜ) እህቴን ጉሮሮዋን አንቀው መረጃ አምጪ አሏት፤ ምንም እንደማታውቅ ብትነግራቸውም አልሰሟትም፤ ከሌሎቻችን ጋር ተቀላቅላ እንድትቀመጥ አደረጓት ከዚያም ሁላችን እያየን አራት ቤቶቻችን አቃጠሏቸው፤ ቤቱን እያቃጠሉ እህቴን ከመካከል ነጥለው ግምባሯ ላይ በጥይት መቷት፤ እህቴን እስከሞት ስትደማ አየኋት፤ ከእርሷ አጠገብ ሌላ ሴት ልጅ በድብደባ ብዛት ሞታ ነበር፤ ከዚያም እኔን ሬሣ ባለበት ጉድጓድ ውስጥ ጣሉኝ፤ በዚያ ጉድጓድ ውስጥ አራት ቀንና አራት ምሽት አሳለፍኩ፤ ጥፋተኛ መሆኔን እንድናዘዝ ምርመራ ይካሄድብኝ ነበር፤ አለበለዚያ መጨረሻዬ እንደ ሬሣው እንደሚሆን ይነግሩኝ ነበር፤ እኔም ምንም የምናዘዘው የለኝም የምታርዱኝ ከሆነ እረዱኝ አልኳቸው፤ (ጉድጓድ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ) ከሬሣው መካከል አንዱ ጉሮሮው ታርዶ፤ አንገቱም በዱልዱም ነገር ተቆርጦ ጭንቅላቱ እዚያው የቀረው አካሉ ጎን ነበር፤…”

አናብ

በመስከረም 2007ዓም ወደ ዳዳብ ካምፕ የመጣቸው አናብ ደግሞ “የኢትዮጵያ ሠራዊት በጅምላ ከገደሉ በኋላ በጅምላ የሚቀብሩበትን ቦታ በመደበቅ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ አንዳንዶቹ መቼም አይገኙም፤ አንዳንዶቹ ግን በቁሻሻ ጉድጓዶች ውስጥ ተገኝተዋል” ትላለች፡፡

በእርሷ ላይ የደረሰውን በተመለከተ ስትናገር አናብ እንዲህ ትላለች፤ “ወደ እስር ቤት ተወስጄ በሽቦ ታነቅሁኝ፤ ይህ ዓይነቱን ተግባር በተደጋጋሚ ሲፈጽሙ ቆይተው በኋላ እስርቤት ተዉኝ፤ በተያዝኩ ጊዜ ከፊት፥ ከኋላና ጭኔ ላይ በጎማ ጠፍር ገርፈውናል፤ ከእኔ ጋር የተያዙ አምስት ልጃገረዶች ነበሩ፤ ከተያዙት ውስጥ ትልቋ 19ዓመቷ አካባቢ ነበር፤ ትንሽዋ ደግሞ ወደ 15ዓመት አካባቢ ነበረች፤ በተያዝንበት ወቅት ልጆቹን ክፉኛ ሲደበድቧቸውና በሰደፍ ሲመቷቸው አይቻለሁ፤ ልብሳቸውንም ቀዳድደውባቸው ብጣቂ እራፊ አድርገው ተመልሰዋል፤ ይህንን በየጊዜው የሚያደርጉት ተግባር ነው፤ …Ogaden 11

“መረጃ እንድንሰጣቸው በየጊዜው ይመረምሩን ነበር፤ ሴቶችን ‘አስገድደን እንደፍራችኋለን’ እያሉ ያስፈራራሉ፤ ‘አንደፈርም’ ብለው አሻፈረን የሚሉትን ደግሞ ያንቋቸዋል፤ ሴቶቹ ራሳቸውን ስተው ባሉበት ወቅት እንኳን ይደፍሯቸዋል … እኔ የታሰርኩበት ትንሽ ክፍል ውስጥ ሰባት ሴቶች ነበሩ፤ ከዚያ ክፍል ነጻ የተለቀቀ የለም ማለት ይቻላል፤ ከእኛ በፊት እዚያ ክፍል የነበሩት ታርደዋል፤ ሌሎቹም በረሃብ እንዲሞቱ ተደርገዋል፤ ሬሣቸውንም በየጉድጓዱ ወርውረውታል፤ እኛ የነበርንበት ክፍል ሬሣ ነበር፤ የክፍሉን ሁኔታ ማንም ሊገምት የሚችል አይደልም (መግለጽ አይቻልም)፤ በክፍሉ የነበረው ሬሣ ባብዛኛው የወጣት ወንዶች ነው፤ እስከ አራት ቀናት ሬሣው በክፍሉ እንዲቆይ ይደረጋል፤ ከዚያ አውጥተው በየቦታው፤ በየመንገዱ ይወረውሩታል፤ …”

ፋጡማ

እንደ ሚሪያም በግንቦት 2006 ዓም ወደ ዳዳብ የመጣችው ፋጡማ “ወታደሮቹ እናንተ የኦጋዴንን ሰዎች እናጠፋችኋለን፤ ምንም ዓይነት ነዋሪ እዚህ አካባቢ አንፈልግም፤ እንጨርሳችኋለን” ይሉናል፡፡ “እስርቤት ሳለሁ አንቀውኝ ነበር፤ በሳንጃም ወግተውኛል፤ በየጊዜው መላ አካላቴን ደብድበውኛል፤ ጭንቅላቴን በኤሌትሪክ ጠብሰውታል፤ የማያደርጉት ዓይነት ስቃይ የለም …” በማለት ምሬት እና ሰቆቃ በተሞላበት ድምጽ ምስክርነቷን ስትሰጥ ትደመጣለች፡፡ ኦብነግ በአካባቢው እንዳለ እና ሠራዊቱ አንድ መቀመጫ ቦታ እንደሌለው፤ በተገኘው አጋጣሚ ወደ ሰፈር እንደሚመጡ እና የሚፈልጉትን እንደሚያገኙ ፋጡማ ትናገራለች፡፡Ogaden 12

ህወሃት በበረሃ በነበረበት ጊዜ ተጋዳላዮቹ በየምሽቱና በየሌሊቱ ወደ መንደራቸውና ሰፈራቸው በሚመጡበት ጊዜ የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ምግብና መጠጥ እያሲያዙ፤ ስንቅ እንየቋጠሩ ይልኩ ነበር በሙስና ወንጀለኛ ሆነው ታስረው የተፈቱት አቶ ስዬ አብርሃ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ እንዲያውም የራሳቸውን እናት ጠቅሰው ብዙዎችን ይመግቡ እንደነበርና ለበርካታ ተጋዳላዮች “እናት” እንደነበሩ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በህወሃት አዛዥነት ወደ ሥፍራው የተላከው ሠራዊት አስገድዶ መድፈር አንዱ የጥቃት መሣሪያው ነው፡፡ በወታደራዊ ሠፈሮች ውስጥ ሴቶች ለወሲብ መገልገያ ሆነዋል፤ ከሚደርስባቸው ሰቆቃ በተጨማሪ በተደጋጋሚ በበርካታዎች ይደፈራሉ በሚለው የግራሃም የቪዲዮ ዘገባ ላይ የስቃይ እንባ የምታፈሰውን ሚሪያም “በተደጋጋሚ ተደፍሬአለሁ፤ ድርጊቱ መደበኛ እየሆነ ከመምጣቱ የተነሳ ተቀበልነው” ስትል ያሳያል፡፡ “ብዙዎች በጣም አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፤ አንዳንዶችም የሚጥል በሽታ ይዟቸዋል ሌሎችም እውር ሆነዋል፤ እኔም ራሴ ከደረሰብኝ ስቃይና ድብደባ የተነሳ አሁን እየተሻለኝ ቢሆንም የጡንቻ መኮማተርና የሚጥል በሽታ ይዞኛል፡፡”

የኦጋዴን ጭፍጨፋ መሃንዲሱና ጀማሪው ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ያስፈነጠረው መለስ ነው፡፡ የሙት ውርስ እንጠብቃለን የሚሉት አወዳሾቹም በሙት መንፈስ እየተመሩ ግፉን ቀጥለውበታል፡፡Ogaden 13

የኢትዮጵያን ስም ይዞ በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የዘመተው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሠራዊት ኦጋዴን በደረሰበት ጊዜ የፈጸመውን እማኞቹ በግልጽ ያስረዳሉ፡፡ “የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ይሁኑ ወይም ልዩ ፖሊስ እኔ አላውቅም” የምትለው ፋጡማ ሰፈሮቻቸው በወራሪው ሠራዊት ከተከበበ በኋላ ከብቶቻቸው፤ ግመሎቻቸው፤ … በአጠቃላይ ንብረታቸው እንደተዘረፈ ትናገራለች፡፡ ከሁለቱ ሴቶች ጋር በመስማማትም ወንዶች እየተነጠሉ እንደተገደሉ ታስረዳለች፡፡ በተለይ የተማሩ የሚባሉ የኦጋዴን ወጣቶችን እየለዩ እንደገደሉ የሟች ቤተሰብ የሆኑት እነዚህ እህቶች በቃለምልልሱ ላይ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ሁልጊዜ የሚባሉትም “አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” መሆኑን ግፍ፤ እልህና ሲቃ በሞላው ድምጽ ይናገራሉ፡፡ ዘጋቢ ፊልሙ ላይ በተሰጠው መረጃ መሠረት ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ግዢው ህወሃት በልዩ ሁኔታ ያሰለጠናቸው በትምህርት ያልታነጹ፤ ወታደራዊ ዲሲፒሊን የሌላቸውና ከወሮበላ የማይተናነስ ባህርይ ያላቸው ጨካኝ ፓራሚሊታሪዎች እንደሆኑ ያስረዳል፡፡

ህወሃትንና ሹሞቹን በዚህ የኦጋዴን ዘር ማጥፋትና በሰብዓዊ ዘር ላይ በሚፈጸም ወንጀል ማስከሰስ፤ ለፍርድ ማቅረብ የኦጋዴን ወገኖችንና የመላ ኢትዮጵያ ልጆችን ትብብር ይጠይቃል፡፡ ስቃይ፣ መከራ፣ ሰቆቃ፣ … ካላስተባበረን ሌላ ምን ሊያስተባብረን ይችላል? ሰዎች ደስታን እንደመሰላቸው ሊተረጉሙት ይችላሉ፤ ግፍ ግን ቋንቋውና ስሜቱ አንድ ዓይነት ነው – እስከ አጥንት ይዘልቃል፤ መቅኔን ይቆጠቁጣል፡፡

Ogaden 15ከአዘጋጆቹ፤ ምንም እንኳን በጋዜጠኛነት ተግባር ላይ የምንገኝ ቢሆንም የእነዚህ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን መከራና ስቃይ ያመናል፤ ያስለቅሰናል፡፡ ከአንዲት እናት የተወለድን ሰብዓዊ ፍጡር እንደመሆናችን የሴቶች ስቃይ ከምንም በላይ ልባችንን ያሳምማል፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊ ይህንን ስቃይ ማቅረብ ሌላውን ዜና የመዘገብ ያህል ቀላል አይደለም፡፡ ድርጊቱ አሁን የተፈጸመ ያህል እየተሰማቸው አሁንም ትኩስ እንባ እያፈሰሱ ስቃያቸውን የገለጹት እህቶቻችን ህመም የማያመውና የማያስለቅሰው ህወሃትና በድንቁርና ጭለማ ውስጥ የገቡት ጀሌዎቹ ናቸው፡፡ ህወሃት ይህንን ዓይነቱን ግፍ ሲደርግ ኖሯል፤ አሁንም እያደረገ ነው፤ ኢትዮጵያ ግን አሁንም ከእናንተ የኦጋዴን ግፉአን ጋር ታለቅሳለች፡፡

 


የማለዳ ወግ … ልጆቿን ያጣችው ቢሸፍቱም አለቀሰች ! [ነቢዩ ሲራክ]

$
0
0

* ተቃውሞን በጠመንጃ ለመግታት አይቻላችሁም
* መግደል ይቁም !

_91490985_mediaitem91490984ከረፋድ ጀምሮ የታዬ ፣ የተሰማው ሁሉ ሰቅጠጭ ግፍ ለማመን ያስቸገረኝ ግን የሆነ እውነት ነው … ለማመን ከቸገረኝ ካልኩት በተከታታይ ከደረሰኝ መረጃ እንዲህ የሚል ይገኝበታል ” …በዓሉ ከተጀመረበት ከጠዋት ጀምሮ የተቃዋሞ ድምጽ ነበር ፣ ፓሊስ አካባቢውን ከበበ ፣ ህዝብና ፖሊስ ገጠሙ ፣ አስለቃሽ ጭስ ወደኋላም ጥይት መተኮስ ጀመረ ፣ ህዝቡ ጭስና ጥይቱን ሲሸሽ በጥይት የተመታው ተመታ ፣ የሸሸው በግምት እስከ 10 ሜትር ድንጋያማ ገደል ውስጥ ከመውደቅ አላመለጠም …” በቦታው የነበሩ የአይን እማኝ ካካፈሉኝ መረጃ ቅንጫቢው ነው ????

j6መንግሥት ላለፉት በርካታ አመታትና በተለይም በተከታታይ ወራት የህዝብን ድምጽ ለማፈንና ለማክሸፍ በወሰደው እርምጃ የታሰረ ፣ የቆሰለ ፣ የተሰደደውን ሳንቆጥር በሽህ የሚቆጠር የንጹሃን ዜጎች ነፍስ ተቀጥፏል ፣ ይህ ሁሉ እየሆነ ለእልቂቱ የሚሰጠው ስም ” የአሸባሪዎች ” ሴራ የሚል ነው ፣ ዳሩ ግን በከባቢው እያሸበረ ያለው ጠመንጃ የታጠቀ የመንግስት ኃይል እንጅ ጣት የሚቀሰርባች አሸባሪዎች በከበቢው የሉም !

ከሁሉም የሚያሳዝነው እንዲህ እየገደሉ እስከ መቸ ሊገዙ እንደሚፈልጉ አለማወቃቸው ነው ! ከሁሉም የሚያሳዝነው የሚገድሉት ንጹህ ዜጋ ሚኒሶታ ሆኖ የተቃውሞውን መረጃ የሚያቀብለው የፖለቲካ ተንታኙ ጆሃር መሀመድ ጦር አድርጎ መገመታቸውና ማስነገራቸው ነው ፣ ከሁሉም የሚያስገርመው ከብርሃን ፍጥነት መረጃው እውነትን እያሳዬ መዋሸት መቅጠፋቸው ነው ! ከሁሉም የሚያሳዝነው ” የአስተዳደር በደል ፈጽመዋል ” እየተባለ የበደሉት ፣ ተቃወመ ብለው እያሳደዱ ያሳሰሩ የገደሉት በክበር ከስልጣን ገለል ሲደረጉ በእነሱ ጫማ እየተረገጠ የከረመው ግንባር ግንባሩን እየተባለ ሲገደል ማየት እጅግ ያማል ???? ጥይት ተቃውሞን አይገተውምና ዜጋው በመላ ሀገሪቱ በሚባል ሰፊ ይዞታ ተቃውሞውን እያጋጋለው መገኘቱ የሚያሳየው እውነታ በኃይል ድምጽን ማፈን አለማስቻሉን ግን ገዥዎች መማር አልቻሉም !

_91491843_mediaitem91491086የንጹህ ዜጋን ዲሞክራሲያዊ የመብት ጥያቄ በጠመንጃ መመከት የመንግስትን ጭፍን አንባገነንነት ከማሳየትና ተቃውሞን ከማጎልበት ባለፈ ፋይዳ የለውም ! ዛሬ የቢሸፍቱ ተራ ሆኖ ቢሸፍቱ ልጆቿ በግፍ ተገድለው አልቅሳለች ፣ ትግሉን ግን ጭፍጨፋው እንደማያስቆመው ሳስብ በክፉ አንባገነን መሪዎቿ ሰርክ የምታነባዋ ሀገረ ኢትዮጵያ ታሰዝነኛለች ፣ እኛም ልጆችዋ እናሳዝናለን ???? ደሩ ግን የዚህ ሁሉ ንጹህ ደም ዋጋ የትንሳኤው ቀን ያቀርበው እንደሁ እንጅ አያርቀውም ! ፈጣሪ ሁሉንም ያያል ! ይፈርዳልም !

እጅግ በጣም ያሳዝናል ፣ ልብ ይሰብራል ???? በቢሸፍቱ ላለቁት ወገኖቸ የተሰማኝ ሃዘን ጥልቅ ነው ፣ የሞቱትን ነፍስ ይማር ????

ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 22 ቀን 2009 ዓም

ቪዲዮ… ዛሬ በሻሸመኔ ህዝቡ ለተቃውሞ ወጥቶ በአደባባይና በየቀበሌው ከታጣቂ ኃይል ጋር ተፋጦ ይገኛል

$
0
0

ሁን ባለው ቁጥር ከ295 በላይ ሰዎች በቢሾፍቱ ተረሽነዋል፡፡ 120 አስክሬኖች ወደ ቢሾፍቱ ሆስፒታል ሲሄዱ 175 የሚሆኑት አስክሬኖች ወደ አዲስ አበባ ተጭነዋል፤ወደ ቢሾፍቱ ሀይቅ ውስጥ ከአስለቃሽ ጪስ እና ከጥይት ሸሽቶ የሰጠመ ህዝብ ቁጥር ብዛት ግን ገና አልታወቀም፡፡

በሻሸመኔ ህዝቡ ለተቃውሞ ወጥቶ በአደባባይና በየቀበሌው ከታጣቂ ኃይል ጋር ተፋጦ ይገኛል፤፤

በደብረዘይት በኢሬቻ በዓል ላይ የተፈጸመውን ወታደራዊ እርምጃ ተከትሎ በሻሸመኔ ህዝቡ ለተቃውሞ ወጥቶ በአደባባይና በየቀበሌው ከታጣቂ ኃይል ጋር ተፋጦ ይገኛል፤፤ ወጣቶች ወገኖቻችን ደም ፈሶ አይቀርም፣ የእኛም ደም ነው የፈሰሰው፡፡ ክብራችን፣ መብታችንና ነጻነታችን እስከሚመለስ ትግሉ ይቀጥላል፡፡

በተመሳሳይ የአጄ ከተማና አካባቢቀው ነዋሪዎች ለኢሬቻ በዓል በሄዱ ወገኖቻቸው ላይ በደረሰው አሰቃቂ ወንጀል ለመቃወም አደባባይ ወጥቶ በከተማ መስተዳድር ግቢ የተሰቀለውን ባንዲራ አውርደው ኮከብ ጠሌለበትን የኢትዮጵያ ሰንደቅና የኦነግ ዓርማ በቦታው ሰቅለዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ታጣቂ ኃይሉና ነዋሪው ከፍተኛ ትንቅንቅ ውስጥ ናቸው፡፡

በሻሸመኔ ህዝቡ ለተቃውሞ ወጥቶ በአደባባይና በየቀበሌው ከታጣቂ ኃይል ጋር ተፋጦ ይገኛል

ጅብ በማያውቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፍሉኝ አለ [ገብረመድህን አርአያ]

$
0
0

gebremedhin-arayaኢትዮሚዲያ በ26/09/2016 ከግደይ ዘርአፅዮን ጋር ያካሄደውን ቃለ ምልልስ አንብቤዋለሁ። ግደይ ዘርአፅዮንን የማውቀው ገና ትግሉ ሳይጀመር በፊት ነው። ግደይ በጥሩ ቤተሰብ ያደገ ግለሰብ ነው። ትገሉ ሳይጀመር በመስከረም 1967 አዲስ አባባ ውስጥ ማገበትን መሰረቱ። የመሰረቱትም አረጋዊ በርሄ፣ ገደይ ዘርአፅዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ዘርኡ ገሰሰ፣ ሃይሉ መንገሻና አስፍሃ ሃጎስ ናቸው። ከዚያ በኋላ እነ መለስና ስብሃት ወዘተ. ተቀላቀሉ። ግደይ ስለእኔ፤ ገብረመድህን፤ መስራች አልነበረም ብሎ ነው የተናገረው። ያለው ትክክል ነው፤ እኔ የማገበት – ተሓህት መስራች አልነበርኩም። ማገበት እንደተመሰረተ በተራ አባልነት ተመልምዬ ከማገበት ጀመሮ ትግሉን ለማጠናከር ስንቀሳቀስ የነበርኩ ተራ አባል ነበርኩኝ እንጂ መስራች አይደለሁም። ስለ ተሓህት – ህወሓት ማንነትን ግን ከግደይ ዘርአፅዮን ያላነሰ እውቀት አለኝ። ልክ እንደ እኔ፣ በወቅቱ የነበርው ታጋይ የህወሓትን እኩይ ሥራ ያውቃል። የህወሓት አመራር ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ዘረኛ፣ የአማራውን ዘር ለማጥፋት የተነሳ ወዘተ መሆኑን አስምሮበት ያለፈ ታጋይ ነው።

በትግርኛ አንድ ተረት አለ። እሱም “መባእያ እንዳ አባገሪማ ዝበለእስ ባእሉ ይለፋለፍ” ይባላል። ይህ ማለት፣ የአባ ገሪማ መባእ፣ የሰረቀ ሌባ ራሱ ይናዘዛል እንደማለት ነው።

ግደይ ዘርአፅዮን ትልቅ ትኩረት የሰጠው ከኢሳት ሰብአዊ መብት ተሟጋች ESAT Human Rights, May 13, 2016 –May 15, 2016 ባካሄድኩት በሁለት ክፈል ኢሳት ባስተላለፈው ቃለ ምልልስ፣ ስለ 06 ሓለዋ ወያኔ ሁኔታ ነበር። 06 ሓለዋ ወያኔ የገዳይ ማእከል ነው። በዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ እኔ ገብረመድህን አርአያ፣ የነበሩ ሓለዋ ወያኔ ብዛት ከመሬት በታች ሁለት ሜትር ተቆፍሮ፣ ነፋስ መግቢያ የሌለው ማጎሪያ ውስጥ ስለተገደሉት፣ ትግሬና አመራ መሆናቸውን በዝርዝር የገለጽኩበት ቃለ ምልልስ ነው። ግደይ ዘርአፅዮን ከኢቲዮ ሚዲያ ጋር ባካሄደው ቃለ ምልልስና በጽሁፍም የተዘረጋው ባጣም አንዶታል፣ ክንክኖታልም። በዚህም ምክንያት ይመስላል ብዙ ስድቦችን አውርዶብኛል። ግደይ የተናደደበት ዋናው ምክንያት፣ ምስጢራችንን በዝርዝር አውጥቶ አጋለጠን ብሎ ነው። ይህም ይመስላል ወደ ተራ ስድብና ውሸት የከተተው። የትግራይን ሕዝብ አጸያፊ ስድብ ተሳደበ ብሎም ወንጅሎኛል። እኔ ማን ሆኜ ነው የትግራይን ወላጆችና ወንድሞቼን የምሰድበው? ሃቅ ነው ካለስ፣ የተሳደብኩትን ስድብስ ለምን አልተናገረም? ግደይና ግብረአበሮቹ የህወሓት አመራር የትግራይ ሕዝብ ፊውዳል፣ ሸዋዊ አማራ ትግሬ፣ ፀረ-ህወሓት ወዘተ እያላችሁ የገደላችሁት አንተና ጓደኞችህ አልነበራችሁም ?እኔ የነበሩትን፣ 06 ሓለዋ ወያነ፣ በነሱ ውስጥም ስንት የሰው ፍጡር፣ አማራና ትግሬ – አማራው በዝቶ የተገደለበት – ቦታዎች መሆናቸውን ነው በትክክል የገለጽኩት። ቅንጣት ውሸት አልጨመርኩበትም። ግደይ ከፈጸመው ውንጀል ነፃ የሚወጣ መስሎታል። እውነት በውሸትና በማስመሰል አትጣጠፍም።

ግደይ ዘርአፅዮን ሲናገር፣ 06 ሓለዋ ወያኔ ከመሬት በታች ሁለት ሜትር መሆኑን በቃሉ አምኖበታል። ማመኑ ጥሩ ነው። ነገር ግን ዋሻም እንጠቀማለን ያለው ውሸት ነው። ይህንንም የምናደርገው የጦር ቀጠና ስለሆነ ነው ብሏል። ይህም ትክክል አይደለም። የህወሓት አመራር ሰውን ነፋስ በማይገባበት ጉድጓድ ውስጥ እያሸጉ የስንት ንጹሃን ኢትዮጵያዊያኖችን፣ ህፃን፣ ሽማግሌ፣ ወጣት፣ ወንድ፣ ሴት፣ እርጉዞችን ጭምር አጥፍተዋል፣ ግድለዋል። ሲፈጸም የነበረውንም ቶርቸር አንተ ራስህ፣ ግደይ ዘርአፅዮን፣ ቡምበትና ሱር ሓለዋ ወያኔ የፈጸምከውን ዘግናኝ ግድያ አምነህ መቀበል ይኖርብሃል። ኢትዮጵያን ለችግር ይዳረጋችኋት አንተና አረጋዊ በርሄ ናችሁ። በአማራው ላይ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሰማራችሁት አንተና ጓደኞችህ መሆናቸውን አምነህ ተቀበል።

ስለምርኮኛዎችም ተናግረሃል። መናገርህ ጥሩ ነው። የነበሩት ምርኮኞች ከሻእቢያ የመጡ ናቸው እንጂ ተሓህት -ህወሓት የማረካቸው አልነበሩም። አሻግራችሁ ወደየመጡበት ሸኙአቸው እየተባለ ተሓህት – ህወሓት እየተቀበላችሁ ትገድሏቸው ነበር። ይህንንም ሁሉም የድርጅቱ ታጋይ በወቅቱ የሚያውቀው ሃቅ ነበር። ግደይ፤ ታጋቅዮች በአይናቸው ያዩትን እና የተናገሩትን ሃቅ በአንተ በኩል በዚያ ወቅት የፈጸምከውን ላንሳልህ፡፡ 300 (ሶስት መቶ) ከሻእቢያ በህዳር 1971 የተላኩትን ምርኮኞች ምን ፈረድክባቸው? በጥይት ተረሽነው እንዲገደሉ አደርግሃቸው። ለዚህም በውጭ ሃገር የሚኖሩ በርካታ የቀድሞ ታጋዮች የዓይን ምስክሮች አሉ። የተረሸኑትም ሌላ ሃጢያት ሳይኖራቸው አማራ በመሆናቸው ብቻ ነው።

እናንተ የህወሓት አመራሮች የፈጸማችሁት ስንት ከባድ ወንጀል ተሸፋፍኖ እያለ፣ ይፋ ከሆነ የሚገጥማችሁ እስራት ብሎም ግድያ ይጠብቀናል በሚል ፍርሃቻ አካላችሁ ስለተወረረ፣ ከዚያ ለመላቀቅ ጥፋታችሁን ለሕዝብ ተናዛችሁ ይቅርታ ብትጠይቁ ይሻላችሁ ነበር። ግደይ፣ እኔ ፖሊት ቢሮ ስለነበርኩኝ የምናገረው ሁሉ ተአማኒነት አለው ብለህ ታስባለህ፣ ግን ስተሳስተሃል። ህወሓት ለምርኮኞች ብዙ እንክብካቤ ሲያደርግ እንደ ነበርም ተናግረሃል። የተናገርከው ግን ሙልጭ ያለ ውሸት ነው። ህወሓት የዚህ ዓይነት ባህሪ የለውም።

ግደይ ሲናገርም ገብረመድህን የትግራይ ሕዝብ አማራን ይጠላል ይላል ብሏላ። እኔ የምናገረውን አውቃለሁ። ግደይ የዘነጋው ነገር ግን አለ። ተሓህት – ህወሕት ገና ከጅምሩ በየቦታው እየተንቀሳቀሰ አማራ የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ነው እያላችሁ ስትሰብኩ እንደነበር የማይካድ ሃቅ ነው። ለዚህም የትግራይ ሕዝብ የሰጣችሁን መልስ አትዘነጋውም። ላስታውስህና፣ የትግራይ ሕዝብ ያለው አማራ ጠላታችን አይደለም፣ ወንድማችን፣ ደማችን፣ አጥንታችን፣ ኢትዮጵያዊ እንጂ ነው ያለው። ለትግራይ ሕዝብ የውሸት ስም እየሰጣችሁ፣ ትግራዋይ ሸዋዊ ብላችሁ፣ በምክንያት ስንት ሺዎች የትግራይን ሕዝብ ገድላችኋል፣ ንበርቱን ዘርፋችኋል።

በየካቲት 1968፣ ተሓህት – ህወሓት፣ ፕሮግራሙን ሲያሰራጭ የትግራይ ሕዝብ አንቀበልም በማለቱ በተከታታይ እያሳደዳችሁ በመግደል ወንጀል ፈጽማችሁበታል። በሓለዋ ወያኔ 06 እያሰራችሁ ፍዳውን አሳይታችሁታል። ፈዳያን አጥፍቶ ጠፊ አሰማርታችሁ የከተማውን ሕዝብ እየገደላችሁ ደሙ በየፒያሳው መጠጥ ቤት እንዲፈስ አድርጋችኋል። ይህንን የፈጸማችሁት ደግሞ፣ አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርአፅዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሥዩም መስፍን እና መለስ ዜናዊ ናችሁ። ምስክሬ የትግራይ ሕዝብ ነው።

ይህንን ሁሉ ግፍ ሲያስፈጽም የነበርረው ግደይ ዘርአፅዮን ለትግራይ ሕዝብ ተቆርቋሪ መስሎ የትግራይን ሕዝብ ሰደበ የሚለኝ፣ ስሰድብ የተቀረጸ የድምጽ ምስክርነት ካለው ያቅርብ። ኢሳትም ይህን ብለህ ነበር ብሎ በማለት ለሕዝብ ያጋልጠኝ። የትግራይን ሕዝብ የጨፈጨፈ ግደይ እንጂ እኔ አይደለሁም። ግደይ ዘርአፅዮን በኢሳት ላይ ባለው ጥላቻ ኢሳትን ውሽታም እያለ በሰው ሕዝብ ያሰድባል ማለቱ በጣም አስገራሚ ነው። ኢሳት ሕዝብን የሚሳደቡ ማሰባሰቢያ የመገናኛ ብዙሃን አይደለም። ግደይ ኢሳት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቆመ ሚዲያ መሆኑም አልተረዳውም። ኢሳትን መስደብና ማንቋሸሽ የኢትዮጵያን ሕዝብ መስደብና ማንቋሸሽ ነው። አሁንም እንደዱሮው በሕዝብ ላይ ያለው ንቀት አልለቀቀውም።

ግደይ ዘርአፅዮን ስለወልቃይት ሲናገር እንዲህ ብሏል፣ “ትግሉን ስንጀምር ትግራይ የሚባለው ያኔ የትግራይ ጠቅላይ ግዛት የነበረው ከአለወሃ መለስና ወልቃይት ያለው ትግርኛ ተናጋሪ የሚኖርበትን ያጠቃለለ ነው” ይላል። (ሰረዙ የኔ ነው)። እንዲህ ብሎ መናገሩ ከእውነት የራቀ ነው። ያልነበረውን ነበረ ማለት ያልተላቀቀውና ያደገበት የህወሓት መርህ ነው።

ግደይና ጓደኞቹ በረሃ ከመውጣታቸው በጣም ቀደም ብሎ፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ስቲት ሁመራ፣ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት፣ በተከዜ ወንዝ ድንበርነት አማራ መሆናቸው በታሪክ የተረጋገጠ ነው። አለወሃ መለስ ወልዲያ፣ ራያና ቆቦ፣ አፍላደራ ወዘተ በወሎ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ መሆናቸው ታሪክ ያረጋግጣል። ግደይ ዘርአፅዮን የወልቃይት አማራን በሁለት ከፍሎታል። ትግርኛ ተናጋሪ ወልቃይትና አማራ ተናጋሪ ወልቃይት በማለት ሰንጥቆታል። በታሪክም ሆን በአፈ ታሪክ ይህ አይነቱ አነጋገር ተሰምቶም አያውቅም። የወልቃይት ሕዝብ አማራ እንጂ ትግሬ አይደለም። ግደይ ስለሬፈረንደምም ለመዘባረቅ ሞክሯል። ጠገዴ አንተና የወያኔ መሪዎች በጉልበት ነጥቃችሁ ዘሩን እያጠፋችሁት እያለ፣ አንተ በምትቀባጥረው አይነት ሳይሆን ነገ ሕዝቡ በፈለገውና በመረጠው ዘዴ ማንነቱን ያስከብራል፣ መሬቱንም ወደቀድሞው ይዞታው ያስመልሳል።

ግደይ ይህን ሃሳብ ያነሳው የወልቃይት ሕዝብ ለጥቃት ከፋፍሎ እየሰጠው ነው። የአንድን አውራጃ ሕዝብ ለሁለት ከፍሎ ትግርኛ ተናጋሪና አማርኛ ተናጋሪ ብሎ ሕዝብ ላማጋጨትና አለመተማመን እና ጥርጣሬን ለመፍጠር አልሞ የተነሳ ነው። ይህ ደግሞ ወያኔ አሁን የሚጠቀምበት ዘዴ ነው። ታዲያ ግደይና ወያኔ ምን ልዩነት አላቸው? በታህሳስ 1972፣ ህወሓት መሬት ለመውረር በተነሳበት ጊዜ የህወሓት ፖሊት ቢሮ እየተመራ በሕዝቡ ላይ ጦርነት አወጀ። የግል ንብረታቸው በሕወሓት ተወረሰ፣ ተዘረፈ። በዚህም የተነሳ በርካቶች ለስደት ተዳረጉ። በሺዎች የሚቆጠሩም ወደ 06 ሓለዋ ወያነ እየተጋዙ ተገደሉ። የዚህ ሁሉ እልቂትና ዘር ማጥፋት ዋናው ተዋናይ ግደይ ዘርአፅዮን ነበር። አሁንም በአማራው የሚካሄደው የዘር ማጥፋት እንደቀጠለ ነው። የመሬት ወረራ በተጀመረበት ወቅት ግደይ ዘርአፅዮን የመጀመሪውያው ፖሊት ቢሮ ም/ሊቀመንበር ነበር። የሓለዋ ወያኔ እስር ቤቶች ሁለት ሜትር ወደ መሬት ጠልቀው እንዲሠሩ ትእዛዙን ያስተላለፈ መሪ ነበር። በትእዛዙም መሠረት ተፈጸመ። ነፋስ መግቢያ የሌለው፣ እርጥብ እንጨት “ዓየ” ተብሎ የሚታወቅ ዛፍ እየተቆራረጠ በማቃጠል ጪስ እየተለቀቀ የአማርውና የትግሬው ሕዝብ በአየር እጦት እየታፈነ አልቋል። የዚህም ፈላስፋግደይ ዘርአፅዮን ነበር።

ገደይ ወልቃይት ስንገባ ሕዝቡ አልተቃወመንም ብሏል። ይህ አነጋገር ቅንጣት ያህልም ሃቅነት የለውም። የወልቃይት ጠለምት ጠገዴ ሕዝብ ወራሪ መጣብን ብሎ እልህ አስጨራሽ በሆነ መልክ መሳሪያ አንስተው ፀረ ወያኔ ትግል ማቀጣጠላቸው በጋሃድ ይታወቃል። ከፋኝ የሚባለውና ህወሓትን ያስጭነቀው ፀረ-ወያኔ ድርጅት የተፈጠረውም በዚያ ጊዜ ነበር።

ግደይ ዘርአፅዮን የፖሊት ቢሮ አባል ሆኜ እንኳን ስለ 06 ብዙም የማላውቀው ነገር አለ ብሏል። ታዲያ የህወሓት ፖሊት ቢሮ ም/ሊቀመንበር ሆኖ ሳለ ድርጅቱን በሞግዚትነት ነበር የሚያስተዳድረው? (ይቀጥላል)

የመሪዎቹ ስም ዝርዝርና ገበናቸው ቀጥሎ ይቀርባል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

ገብረመድህን አርአያ

02 ኦክቶበር 2016

ቶክሱ ከመጀመሩ በፊት ሁሉንም ጋዜጠኞች ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ ከተደረገ በኃላ የቶክስ ድምፅ ና የህዝቦች ዋይታ ና ጮኸት በርቀት ይሰማ ነበር

$
0
0

_91490985_mediaitem91490984የጀርመን ሬድዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ ስለተከሰተው ነገር ሲናገር ትናንት ማታ የነበረውን እና ዛሬ ጧት ከግርግሩ በፊት የነበረው ሰላም ተቃውሞ የነበረ እንደነበርና ነገር ግን ግርግሩና ቶክሱ ከመጀመሩ በፊት ሁሉንም ጋዜጠኞች ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ መደረጉንና ጋዜጠኞቹ ከመሄዳቸው ወዳው የቶክስ ድምፅ ና የህዝቦች ዋይታ ና ጮኸት በርቀት ይሰማ እንደነበርና ቡሀላም ብዙ ቁስለኞችና አስክሬኖችን ማየታቸውን ገልጿል ። ለመሆኑ መጀመሪያ ጋዜጠኞችን በሙሉ ለምን ከዚያ እንዲወጡ ተደረገ? መጀመሪያ ግርግሩ ከመጀመሩ በፊት ከባድ መሳሪያዎች ና የፀጥታ ሀይሎች ለምን በተጠንቀቅቆሙ? ታንኩን የሚነዱት ወታደረችስ ለምን ፊታቸውን መሸፈን አስፈለገ? በደህናው ቀን ሲበሩ የነበሩትስ አምቡላንሶች ከግርግሩ በፊትና ቡሀላ ድራሻቸው ጠፋ ? ግርግሩን ጥቂት ሰዎች ጀመሩት ከተባለ ለምን አጠቃላይ ህዝብ ላይ አስለቃሽ ጭስ መልቀቅ አስፈለገ? እንዳጠቃላይ ይህ ጭፍጨፋ የተደረገው ቀድሞ በታቀደና ስልታዊ በሆነ መልኩ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየና ከላይ የተለቀቀው ጭስ ሆን ተብሎ ህዝቡ እንዲተራመስ በማድረግ ታጥቆ ለቆመው እና ህዝብን እንዲጨፈጭፍ ለታዘዘው አጋዚ ሰራዊት በር ምክንያትና ሽፋን መስጫ መሆኑንና አሁን በተግባር ተፈፃሚ እንዲሆን የተደረገ መሆኑን ያመላክታል ።

metereyes

የኢሬቻ በዓል በማክበር ላይ በነበሩ የኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ ለማውገዝ የግድ ኦሮሞ መሆን አይጠበቅም፡

$
0
0

14441153_10211019936320300_5131783730980288408_n

ያሳዝናል፤ ያናድዳል፡፡ ለነጻነት በሚደረግ ትግል የንጹሐን ዜጎች ሞት የሚጠበቅ ቢሆንም ባዶ ቄጠማን በእጃቸው ይዘው ከአምላካቸው ለአገራቸው ሰላም ሲለምኑ በነበሩ ሰዎች ላይ ይህን ዓይነት መቅሰፍት ሲወርድ በምን ቃል መግለጽ ይቻላል?
በዚህች አገር ላይ በዓልን በፌሽታና በደስታ እንዲያከብሩ የተፈቀደላቸው ከተከዜ ማዶ ያሉ ሰዎች ብቻ መሆናቸውን በግልጽ እያየን ነው፡፡
ለሞቱ ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁ፤ በአካባቢው ያላችሁ የአማራ ተወላጆች ከተጎዱ የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጎን በመቆም አጋርነታችን የምናሳይበት ከዚህ ጊዜ በላይ የለም፡፡
ትግላችን መራር ቢሆንም ማሸነፋችን ግን ጥርጥር የለውም!!

#OromoProtest;

 

metereyes

በዛሬው የኢሬቻ በዓል በተፈጠረው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠር ህይወት መጥፋቱን ኦፌኮ አስታወቀ

$
0
0

ጽዮን ግርማ/ VOA

በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ኃይቅ ሊከበር በዝግጅት ላይ የነበረውና ከኦሮሞ ክብረ በዓሎች አንዱ የሆነው እሬቻ በዓል ተስተጓጉሏል፤ በግጭትና በትርምሱ ወቅት ብዙ ሕይወት መጥፋቱና በአካልም7 ላይ ብዙ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡

በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ኃይቅ ሊከበር በዝግጅት ላይ የነበረውና ከኦሮሞ ክብረ በዓሎች አንዱ የሆነው እሬቻ በዓል ተስተጓጉሏል፤ በግጭትና በትርምሱ ወቅት ብዙ ሕይወት መጥፋቱና በአካልም ላይ ብዙ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡የመንግሥት ባወጣው መግለጫ ለበዓሉ መስተጓጎልና ለሕይወት መጥፋት “ሁከት ፈጣሪ ኃይሎች” ያላቸውን ወንጅሏል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ – ኦፌኮ በሰጠው መግለጫ መንግሥትን የተቃወሙ ባላቸው ወጣቶችና በመንግሥት ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በዓሉ ተቋርጦ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታውቋል።

ፓርቲያቸው አጠናቅሮታል ያሉትን መረጃ መሠረት ያደረጉት የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል “በሕይወት ላይ ጉዳት የደረሰው በተኩስ፣ በአስለቃሽ ጭስ እና በመረጋገጥ ነው” ብለዋል፡፡

የቆሰሉ ብዙ ሰዎች አሁንም ሆስፒታል እንደሚገኙ አክለው የተናገሩት ዶ/ር መረራ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመልክተዋል።

በሌላ በኩል የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ቦታው እንደነበሩና የዐይን እማኝ መሆናቸውን የገለፁ ሰዎች “ግጭቱ የተጀመረው በበዓሉ መክፈቻ ላይ ንግግር ሊያደርጉ በነበሩ ሰዎች ላይ እና ሊሰቀል በነበረ ባንዲራ ላይ ተቃውሞ በመነሳቱ ነው” ብለዋል፡፡

ግጭቱ ከተፈጠረ በኋላም ብዙ ሰው በተኩስ፣ በአስለቃሽ ጭስ፣ በመረጋገጥ እና ገደል ውስጥ ገብቶ ብዙ ሕይወት መጥፋቱን ገልፀዋል።

የተጎዱ ሰዎችን በተመለከተ እስካሁን ይህ ነው የተባለ ትክክለኛ ቁጥር ማግኘት ባይቻልም ዐይተናል ያሉ ሰዎች ተጎጂዎች 25 በሚሆኑ መኪኖች መወሰዳቸውን ጠቁመዋል፡፡

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽ/ቤት በሰጠው መግለጫ “የእሬቻ በዓልን ባህላዊ አከባበር ጠብቆ ለማክበር የኦሮሞ ህዝብ አባገዳዎችና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ያደረጉት ሰፊ ዝግጅት አስቀድመው የተዘጋጁ ባላቸው ኃይሎች ሁከትና ግርግር ተስተጓጉሏል” ብሏል፡፡

ስለጠፋው ሕይወት መንግሥት የተሰማውን ኀዘን የገለፀው የፅ/ቤቱ መግለጫ ሕይወት የጠፋውም “ሁከት ፈጣሪዎቹ ባስነሱት ሁከት በተፈጠረ ግርግር ተገጋግጠው ነው” ብሏል።

“ሁከት ፈጣሪ” ስላላቸው ወገኖች ማንነትና በሕይወትና በአካል ላይ ስለደረሰው ጉዳት ፅ/ቤቱ ዝርዝር መግለጫ አልሰጠም፡፡

ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ —

if(typeof(jQuery)==”function”){(function($){$.fn.fitVids=function(){}})(jQuery)};jwplayer(‘jwplayer-1’).setup({“file”:”http://www.satenaw.com/amharic/wp-content/uploads/2016/10/b822ef5e-1636-4745-b2fb-477ad1362835_hq.mp3″});

በሕዝብ አቆጣጠር አሁን ሁሉም ነገር አበቃ

$
0
0

ዛሬ ጨለሞ ዋለ። ዛሬ አገር ማቅ ለበሰች። ዛሬ የሆነውን ማመን ይከብዳል። ቄጤማና ቅጠል ይዘው የወጡ ሰላማዊ ዜጎች በጅምላ ተረሸኑ። “Down! Down! Woyane … Down! Down TPL! …” በማለት ቁጣውን የገለጸ ሕዝብ እገዛሃለሁ በሚለው የትግራይ ህዝብ ተገንጣይ ቡድን (በህወሃት) ተጨፈጨፈ። ከአየርና ከምድር ጭስና ጥይት የተረጨበት ህዝብ፣ የሚገባበት ጠፍቶት የውሃ ራት ሆነ። ሞተ። ቆሰለ። በውሃ ተበላ።

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት የሚባለው የወንበዴው ቡድን መሪ መለስ ሞት በድንገት እንደ ቡሽ ክዳን አፈናጥሮ ሲወስደው ጥቁር ለበሶ ሳግ እየተናነቀው ዜና ያወጀው ተመስገን በየነ፣ ዛሬ ነጭ በነጭ ለብሶ አኻዝ ባይጠቅስም የሰው ህይወት ማለፉን የተናገረው “ሰፊውና የተከበረው የኦሮሞ ህዝብ” በማለት ነበር።

temesgen1 temesgen-beyeneተመስገን ከጌታቸው የተላከለትን ሰዎች “በመረጋገጥ” ሞታቸውን ሲተፋ ቢያመሽም ህወሃትና ወኪሎቻቸው የዘነጉት ነገር ቢኖር የኢሬቻ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ዛሬ አይደለም፤ እስካሁን በተደረገው የበዓሉ አከባበርም ሁከት ሲነሳና ሰዎች በመረጋገት ሲሞቱ አልተሰማም፡፡

ብዙዎች እንዳሉትና፣ በማህበራዊ ገጾች እንደታየው ከኖረው ሃዘን ጋር ተዳምሮ የዛሬው ሃዘን በሕዝብ አቆጣጠር ሁሉም ነገር መጠናቀቁን ነው፡፡

የማህበራዊ ድረ ገጾች ምስል አስደግፈው እንዳሰራጩት ዜናና የውጭ መገናኛዎች እንዳሉት ቢሾፍቱ የኢሬቻን በአል ለማክበር የተሰባሰቡት ዜጎች ብዛት እስከ አራት ሚሊዮን ተገምቷል። ቢቢሲ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሲል ሌሎች ከዚያም ያስበልጡታል።

እንግዲህ እዚህ ህዝብ መሃል ነበር መርዝ የተተኮሰው። ጭስ የተተኮሰው። ህዝብ አየር አጥቶ እንዲታፈን የተፈረደው። ከዚያም በላይ ከባድ መሳሪያ ሲተኮስ የተቀረጹት ፊልሞች አረጋግጠዋል። ታንክ ሲጠቀሙም በምስል ተይዟል። በአየር ላይም ሄሊኮፕተር ተባባሪ ነበር።

ይህ ሁሉ የመሳሪያ አይነት የተሰለፈው ለወገን መሆኑ አገርን በድፍን አሳዝኗል። በዚህ ሁሉ ዝግጅት በተካሄደ የጅምላ ጭፍጨፋ ንጹሃን ዜጎች ሞቱ። ዜናው ከተሰማበት ደቂቃ ጀምሮ የሚወጡት መረጃዎች አስደንጋጭ ናቸው። ለጎልጉል መረጃ የሰጡ እንዳሉት “ሕዝብ ሲቃወም ዝም ቢሉ ምን ችግር ነበረው? ሲቃወም ውሎ ሲመሽ ወደቤቱ ይሄዳል!” እኚህ ሰው እንዳሉት በዓሉ በሚካሄድበት ስፍራ ህወሃትን የሚያሰጋው ነገር የለም። ቀድሞውኑ ህዝቡ ተከቦ ነበር። የተከበበና ከመንገድ ጀምሮ ተልብጦ ሲፈተሸ የዋል ህዝብ ምንም አደጋ ሊያስከትል እንደማይችል የታወቀ ነው። “ሲጀመር ፍርሃቻ የያዘው ህወሃት ህዝብ ሲሰበሰብ ስለሚታመም ከበሽታው በመነጨ ምላጭ ስቦ ህዝብን ረሸነ። ጨፈጨፈ። አቆሰለ። ይህ የማይሽር ጠባሳ በየትኛውም ጊዜ ሙሉ ዋጋ ያስከፍላል። ይቅርታ የለውም። አሁን የይቅርታን ገመድ በጠሷት። አለቀ። ካሁን በኋላ …”

እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች፣ ጎረምሶች … በያይነቱ በህወሃት መጨፍጭፋቸውን ህዝቡን አገንፍሎታል። በስፋት እንደሚባለው “አሁን ጊዜው ወያኔን በምትችለው ሁሉ ታገለው። ቦታ አትምረጥ፣ ጊዜ አትምረጥ … ወዘተ” የሚሉ ናቸው። የጅምላ ጭፍጨፋውን ተከተሎ አምቦ ህዝብ ቁጣውን አሰምቷል። በይፋ ባይነገርም እዚያም የህወሃት አንጋቾች ነፍስ አጥፍተዋል። ህዝቡም ንብረት አውድሟል። በሌላ በኩል ከቢሾፍቱ ወደደቡብ የሚወስደው መንገድ በበርካታ ቦታዎች ተዘግቷል፡፡

በጥልቀት መታደስ እያለ ሲፎክር የነበረው ህወሃት አመራሮችን ቀይሬአለሁ ብሎን ነበር፡፡ በመለስ ትዕዛዝ የአዲስ አበባ ንጹሃንን የጨፈጨፈው ወንጀለኛውን ወርቅነህ ገበየሁን የኦሮሞ ህዝብ መሪ አድርጎ ከሾመ በኋላ የዛሬውን ዓይነት ጭፍጨፋ በማድረግ ወርቅነህ ለራሱና ለለማ መገርሣ “ሹመት ያዳብር” የሚያሰኝ ታማኝነቱን አሳይቷል፡፡

ህወሃት ጠርንፎ የያዛት አገራችን ጉዳይ አሳሳቢ ከሚባልበት ደረጃ አልፏል፡፡ በርካታ በሰላማዊ ትግል የሚያምኑ ሰላማዊ ሰዎች በዛሬው ዕለት ጠአቅጣጫ ለውጥ ሲያደርጉና ሲያሰሙ ማድመጥ የወንበዴው ቡድን ህወሃት ጉዳይ በሕዝብ አቆጣጠር ሁሉም ነገር ያበቃለት መሆኑን ያመላከተ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ጥቂት የሕዝብ አስተያየቶችን ከዚህ በታች አቅርበናል፤

#IrreechaMassacre

በርካቶች ኢሬቻ ሊያከብሩ ወደ ሆራ ሲሄዱ እንዲህ እያሉ ነበር …
“Nuti shororkessa miti, wayyaaneen shororkessadha”
“እኛ አሸባሪዎች አይደለንም፤ አሸባሪው ወያኔ ነው”
ዋሹ?

Ye Kebede Yetnayet And here is the evidence . A highly trained government commando covering his face as a terrorist. Also a heavily armored “Zilla” (a heavily armored technical vehicle recently assembled at Beshoftu Armament industry of METEC). The picture says it all- the killing was planned well in advance.

Mahlet Fantahun

የኢሬቻን በአል እያከበሩ የነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰው ነገር እጅግ አሰቃቂ ነው። ለወትሮው ደብረዘይት/ቢሾፍቱ ከተማ ኢሬቻ በሚከበርበት ቀን፤ ወደ ሆራ በሚሄድ እና በሚመለስ ሰው ይጨናነቅ ነበር። ዛሬ ግን ከግማሽ ቀን በላይ አልቆየም። ወታደሮቹም ከየመንገዱ ያገኙትን እየደበደቡ ሲሰበስቡ ነበር። መንገዶቹ ጭር ብለዋል። ቢሾፍቱ ሆስፒታል በጣም በርካታ ህዝብ ተሰባስቧል። ግቢው ለቅሶ ቤት ነው የሚመስለው። እራሳቸውን ጥለው እያለቅሱ ወደ ሆስፒታሉ የሚሄዱ እናቶችን ማየት ይረብሻል። የሬሳ ሳጥን ይዘው የሞተባቸውን ቤተሰብ ሬሳ ለመውሰድ ሆስፒታሉ በር ላይ የሚጠብቁም አሉ።
★★★
እረፋድ ላይ ወደ ሆራ የሚሄዱና የሚመለሱ ወጣቶች እየጨፈሩ በድፍረት በሚያሰሙት ሰላማዊ ተቃውሞ ተደስቼ እና አድንቄያቸው ሳልጨርስ ነው ይህ አሳዛኝ ክስተት የተፈጠረው።

Addis Assefa Gonfa That is what I’M feeling…It did not have to be this way though…where is civilization?…where is common sense in all this? I don’t know why so many has to be sacrificed? So many has to be distracted? But now it looks the only way is out of this is fire with fire blood with blood…the barbaric way…the way they opted for…the only way they know….and I guess the end will be tragedy of an immense proportions… As a people Oromo in the past one year has walked the high walk with all the sacrifice to avert this … but it all fell on deaf ears… so let the *** begin

Kebede Degefu Nothing to say but I am outraged saddened no hope for political practices will work in that part of the world

Shovels must be changed to weapons, axes must be used the war they have started overhead must be reversed by all means

Bira’anuu Kabadaa Absolutely, everything has a limit! Our wish for peace and our resilience towards injustice in the name of peace fall on deaf ears and eyes! We can not go on like this everyday, our people being massacred and our heart broken.

Natnael Mekonnen

የነሱ አሸንዳ ያለምንም ኮሽታ ይከበራል እነሱን የሚደግልፍ ሰልፍም እንደዛው ሌላው ህዝብ ግን እንደ ቅጠል ይረግፋል

አንድ ዶክተር ከቢሾፍቱ እንደተናገሩት

«ለ41 አመታት ያህል በህክምና ሙያ ውስጥ አገልግያለሁ፤ በኢትዮ―ኤርትራ ጦርነት ላይም በሃኪምነት አገልግያለሁ። በአንድ ቀን ይሄን ያህል ግድያ ሳይ ግን ይህ የመጀመሪያዬ ነው።»

Abel Wabella የምወድሽ  tplf-on-mourning-joke

We have a unique regime. They kill civilians & the call it stampede and will declare mourning days

Tsedale Lemma

Every yr, millions of #Oromo gather to celebrate #Irreecha, non have died of ‘Stampede’ until today. Heartbreaking!! #Irreechamassacre

BefeQadu Z. Hailu

People peacefully protested they don’t want cadres speak in #Irrecha and police shot teargas on them, blamed stampede.

BefeQadu Z. Hailu  

#Qilinto prison caught in fire and inmates run to survive. Warders shot them and gov in #Ethiopia said people died in stampede.

Dawit T.

Too much to comprehend, too much to justify, too much to theorize, and too much to forgive. Ain’t too less to act upon it! #IrrechaMascara

Tsegaye Ararssa feeling determined.

Unfortunately, it has become increasingly more and more obvious that there is little likelihood for political end to this carnage. Regrettably, only military solutions are availing themselves. It has become abundantly clear that the matter now is going to be settled on the streets and jungles of Oromia, not on the corridors of the political class in Addis or on the diplomatic corridors of the regime’s foreign patrons. This must be the limit of politics, national and international.


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

<!–

–>


ትናንት #ደባርቅ ላይ በአጋዚ የተገደለው ወጣ #ሰለሞን_ገብሬ (በቅፅል ስሙ አለፋው)

$
0
0

1tከአክሱም ዩኒበርሲቲ የተመረቀው ወንድማችን ህወሃት በአማራ ህዝብ ላይ በከፈተው የጥፋት ዘመቻ ሰለባ ሆነ።

ደባርቅ ላይ አንድ ሰው ለመያዝ 7 ከባድ መሳሪያ ይዘው ከተማዋን ሲያሸብሩ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።
ደባርቅ በመከላከያ ሰራዊት ተወራለች

#AmharaResistance

በቢሻፍቱ ህይወታቸው በግፍና በጭካኔ ካለፈት መቶዋች መካክል የሚከሉት እህቶቻችን ይገኙበታል [ግርማ ካሳ]

$
0
0


si2ኢሬቻ በኦሮሞዋች ባህል የምስጋና ቀን ነው። ሰው የተሰበሰበው ቄጤማ ይዞ ዋቆ የሚሉትን አምላካቸውን ለማመስገን ነበር። ግን እዚያ ነፍሰ ገዳይ አጋንንት ጠበቃቸው። ደርግ ስልጣን ሲይዝ አምስት አመቴ ነበር። በደርግ ጊዜ ያደኩኝ ነኝ ማለት ይቻላል። በአንድ ቀን ብዙ ሰው ሲገደል ሰምቼም አይቼም አላውቅም። ይኸው ከአምስት መቶ በላይ ሰው ወያኔዋች በአንድ ቀን ጨረሱ።

ግን አንድ ጥያቄ አለኝ። እስከመቼ ነው ደም እንደዚህ የሚፈሰው ? ትላንት አወዳይ፣ ነቀምቴ፣ አምባ ጊየርጊስ፣ ባህር ዳር በግፍና በጭካኔ ወገኖቻችን ተገደሉ። ዛሬ በሚሰቀጥጥ ሁኔታ ወገኖቻችን በቢሻቱ ታረዱ። እንደከዚህ በፊቶቹ አዝነን የምንረሳው ይሆን ? ነገ ደግሞ ለየትኛዋ ከተማ እናለቅስ ይሆን ? ግድያው ይቀጥላል እንጁ አይቆምም። ሰዎቹ ያለ ምንም ጥርጥር ደም በማፍሰስ የሚደሰቱ ናቸው። ታዱያ እስከመቼ ነው ደመችን እየፈሰሰ የምንቀጥለው ? መቼ ነው የምንነቃው ? መቼ ነው በዘር ተከፋፍለን በተናጥል የምንመታው ? ለምንድን ነው ትግሉን በጋራ ማቀናጀት ያልቻልነው ? እነዚህ ሰይጣን ቀራጮችን አንድ ነገር ካለደረግናቸው 2009 በአስከፊ ሁኔታ የደም አመት ነው የምትሄነው።

 ነፍሳቸውን ይማር
si1ሌላዋ የዛሬ ሟች ደግሞ ይህች ገና ካገባች መንፈቅ ያልሞላት አዲሷ ሙሽራ ሲፈን ለገሰ ናት።
“ካገባች እንኳን ስድስት ወር ያልሞላት እህቴ ሲፈን ለገሰ ዛሬ ከጎኔ ተለየች። በቢሾፍቱ ሌሎች የቀመሱትን የሞት ፅዋ እሷም ተጋራች:: ሃዘኔ መራር ነው ሲፎኮ ምንም የምናገርበትም አደበት የለኝም። ፈጣሪ ነፍስሽን በገነት ያኑረው!” Ambo Gara Galgala የተባለው ወንድሟ ነው ይህን ያለው።
በዚህ መሪር የሀዘን ጊዜ ለቤተሰቦቿ መጽናናትን ይሰጣቸው ዘንድ ልባዊ ጸሎታችን ነው።
እባክህ ይቅር በለን!!!
u7ከሟቾቹ መካከል ይህች ከሚሣሱላት እናቷ ጋር የቆመችው ወጣት ትገኝበታለች።
“ምን ልበል? ምን ላድርግ እህቴ!? ተቃጠልኩልሽ! ተንገበገብኩልሽ እህቴ!! ገና ነበር እኮ ጊዤሽ! እንዴት ልሁን?! ምን ልሁን ሰላምዬ?!! ኢሀዲግ ቀማኝ እህቴን !!!”
(እህቷ ዲና አለማዬሁ (Dina Coffee Alemayehu ናት እንዲህ ያለችው። እናቷስ እንዴት ሆነው ይሆን?)
በዚህ ከባድ የፈተናና የሀዘን ወቅት እግዚአብሔር መጽናናቱን ይሰጣቸው ዘንድ ልባዊ ጸሎታችን ነው።

አቤቱ በዚህ የአረመኔዎች ስለምን ፈጠርኸኝ?

በቢሾፍቱ እልቂት በሙሽርነቷ ሕይወቷ የወደፊት ራዕይዋ በአጭሩ የተቀጨባት ሲፈን ለገሠ አጠገቧ የቆመው ወንድሟ ከሁለት ወር በፊት በአጋዚ ተገድሏል አሉ

u2

ማምሻውን ያለውን ሁኔታ ለማየት ወደ ኢሬቻ በአል ሚከበርበት ሆራ ሃይቅ ሄደን ነበር። ሆስፒታል ከተወሰዱ ሬሳዎች ውስጥ የተገኙ ጥቂት ፎቶግራፎችን ሃይቁ አካባቢ ያለ ዛፍ ላይ ተለጥፈዋል። ጉድጓዶቹም ይዘግንናሉ፤ ከ6 እና 7 ሜትር በላይ ይሆናሉ። እንደሰማነው በሰአቱ ጉድጓዶቹ በሰው ተሞልተው ነበር። አሰቃቂ ነው። አሁን ሰአት ድረስ የቀረ ሬሳ ሚፈልጉ አሉ።

u3
#IrreechaMassacre #Irreechaa #Oromoprotests

የቢሾፍቱው እልቂት የህወሓት መቀበሪያ ጉድጓድ ቁፋሮ ነው!!! [ከአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ ]

$
0
0

መስከረም 22 ቀን 2009 ዓ.ም.
ከአርበኞች ግንቦት 7
Ginbot 7ዛሬ መስከረም 22 ቀን 2009 ዓም ዓመታዊ ባህላዊ የእሬቻ በዓል ለማክበር በሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ ቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ከተማ የሚገኝ ሀይቅ ዳር ተሰባስቦ ነበር። በበዓሉ ትውፊት መሠረት ለፈጣሪ ምሥጋና ለማቅረብ ብዙዎች ቄጠማ፣ ለምለም ሳርና አበባዎችን ይዘው ነበር። ሕዝቡ አጋጣሚውን በመጠቀም የህወሓት አገዛዝ በክልሉና በመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚያደሰውን በደል ለመቃወም የተቃውሞ ድምጾችን አሰማ፤ የተቃውሞ ምልክቶችን አሳየ።
ሕዝባዊ ተቃውሞ ባጋጠመው ጊዜ ሁሉ የሚሸበረው የህወሓት አገዛዝ ለሰላማዊ ተቃውሞ የሰጠው ምላሽ እንደተለመደው ጥይት ነበር። ሕዝብ በማንኛውም ቦታ ተቃውሞ የማቅረብ መብት አለው። በየትኛውም ዓለም ሕዝባዊ በዓላት ዓይነተኛ የተቃውሞ ማቅረቢያ ቦታዎች ናቸው። ተቃውሞው የቀረበበት ድባድ በጣም ሰላማዊየነበረ በመሆኑ የተለየ ጥበቃ ሊሰጠው ሲገባ የአገዛዙ ምላሽ ግን ከተለመደው የባሰ ሆነ። በታንኮች ላይ ከተጠመዱ መትረሶች ተኩሰው በርካታ ሰው መፍጀታቸው አልበቃ ሲላቸው በሄሊኮፕሮች ላይ በተጠመዱ መትረሶች ሕዝቡን ፈጁ። የሞተውና የቆሰው ሕዝብ ብዛት ምን ያህል እንደሆነ መናገር ለጊዜው አይቻልም፤ ያም ሆኖ ግን ሟቶች በመቶዎች ቁስለኞች ደግሞ በሺዎች ነው የሚቆጠሩት።


ዛሬ መስከረም 22 ቀን 2009 ዓም የአየር ኃይል፣ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ፓሊስ ሠራዊትና የአጋዚ ክፍለ ጦር አባላት የፈፀሙት እጅግ አሳፋሪ ፋሽስታዊ ተግባር ለዘመናት የማይሽር ቁስል ፈጥሯል። “ነፃነታችንን እንፈልጋለን። የኦህዴድ ቅጥረኝነት ይብቃ፤ አማራን፣ ትግሬን፣ ጉራጌን፣ ኮንሶን፣ … ኢትዮጵያውያንን በሞላ እንወዳለን! አንጣላላችሁም!” ማለታቸው ነው በጥይት ያስፈጃቸው። ይህ ዋጋ የሚያስከፍል ግፍ ነው። ዋጋ የሚስከፍል መሆኑ ደግሞ እያየን ነው፤ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ በመላው ኦሮሚያ እንደገና እየተቀሰቀሰ ነው። አሁን ኦሮሚያ ብቻውን አይደለም፤ የአማራ ወገኑ ከጎኑ አለለት፤ ኮንሶው፣ ሲዳማው፣ ጉራጌው፣ አፋሩ፣ ሶማሌው፣ ትግሬው … የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ይነሳል። የቢሾፍቱው እልቂት የህወሓት መቀበሪያ ጉድጓድ ቁፋሮ ነው።


አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዛሬ መስከረም 22 ቀን 2009 ዓም በቢሾፍቱው እልቂት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ለሰማዕታቱ ቤተሰቦች እየገለፀ መጽናናትን ይመኛል፤ እንደዚሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም የተሰማውን ጥልቅ ስሜት ይገልፃል። አርበኞች ግንቦት 7 ከነገ ጀምሮ ያሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት የሐዘን ቀናት እንዲሆኑ ያሳስባል።
ለሰማዕታትና ቁስለኛ ወገኖቻችን የሐዘን መግለጫዎችን መስጠት ችግሩን አይፈታውም፤ ይልቁንም የሞቱለትና የቆሰሉበት ዓላማ ከግብ ለማድረስ ጠንክረን መታገል ይኖርብናል። የህወሓት አገዛዝን በቢሾፍቱ በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ለመቅበር ሁላችንም ተባብረን መነሳት የሚኖርብን ወቅት ላይ እንገኛለን።


ስለሆነም የተለየ ጥሪ ወይም የተለየ አመራር ሳትጠብቅ በሥርዓቱ የተማረርክ ሁሉ ከወዳጆችህ ጋር እየተቧደንክ ተነስ ! በየአካባቢው የሚገኘውን የአገዛዙን ወዋቅር እያፈረስክ የራስህን ጊዜዓዊ የሕዝብ አስተዳደር መስርት። አገራዊ ዓላማ ይኑርህ ትኩረት ግን በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ይሁን። ሁሉም አካባቢውን ከህወሓት አገዛዝ ነፃ ያውጣ!


አንድነት ኃይል ነው !
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

Ethiopia: 52 Die as Police Crackdown on Protest Spawns Stampede – Democracy Now!

$
0
0

Reporter Says Trump Used C-Word Slur in 1980s After Critical Story

H05 reporter called c word trump

Elsewhere, a former Philadelphia Inquirer reporter alleged on Saturday that Donald Trump once called her the C-word in the 1980s. Jennifer Lin says Trump used the slur to her boss after she wrote a story about Trump’s business dealings in Atlantic City in 1988. Lin’s former editor, Craig Stock, confirmed the story.

ሕዝባዊው አመጽ በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቀጣጠለ

$
0
0

cars

meki-768x432cars

ትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ትናንት በቢሾፍቱ የ እሬቻን በዓል ለማክበር በወጡ ንጹሃን ላይ በሂሊኮፕተር እና በመትረየስ የታጀበ የዘር ማጥፋት ከፈጸመ በኋላ በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ አመጹ እንደገና ተቀጣጠለ::

መረጃዎች እንደጠቆሙት በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቃውሞው ተቀጣጥሏል::

በተለያዩ ከተሞች በተነሱት በነዚሁ ሕዝባዊ አመጾች የመንግስት መኪኖች ሲነዱ ታይተዋል::
በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን እያሰማ ሲሆን በመንግስት ንብረቶች ላይ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይም ይገኛል::

በተለይ የሕወሃት ንብረት የሆነው ሰላም ባስ በሃረርጌ ጥቃት እንደተፈጸመበት የደረሰን መረጃ ያመልከታል::

በቄለ ወለጋ ጂማ ሆሮ ወረዳ ኑኑ ከተማ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ተቅስቅሶ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እንደሆኑ ሲታወቅ በባሌ ሮቤ ደግሞ ሁሉ ነገር መዘጋጋቱ ተሰምቷል::

በደምቢ ቦሎ ኢንተርኔት በጠቅላላ መቆረጡ ሲታወቅ ተቃውሞውም እንደበረታ ምንጮች ገልጸዋል:: በአምቦም እንዲሁ ተመሳሳይ ተቃውሞዎች ዳግም እንደተቀሰቀሰ የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ::

Viewing all 3686 articles
Browse latest View live