Quantcast
Channel: admin – Medrek
Viewing all 3686 articles
Browse latest View live

Oldest human’ dies in Indonesia ‘aged 146’ = BBC

$
0
0

The Indonesian man who claimed to be 146 years old – the longest living human ever – has died in his village in Central Java.

According to his papers, Sodimedjo, also known as Mbah Ghoto (grandpa Ghoto), was born in December 1870.

But Indonesia only started recording births in 1900 – and there have been mistakes before.

Yet officials told the BBC his papers were valid, based on documents he provided and interviews with him.

He was taken to hospital on 12 April because of deteriorating health. Six days later he insisted on checking out to return home.

“Since he came back from the hospital, he only ate spoonfuls of porridge and drank very little,” his grandson Suyanto told the BBC.

“It only lasted a couple of days. From that moment on to his death, he refused to eat and drink.”

Media captionThe longest living human ever?

Patience and love

When asked about the secret of his longevity, Mbah Ghoto told the BBC last year that patience was key and that he had “a long life because I have people that love me looking after me”.

A heavy smoker until the end, he outlived four wives, 10 siblings and all his children.

In his village, he was a local hero famous for telling great stories about the wars against Japan and the Dutch colonisers.

Mbah GhotoImage copyrightFAJAR SODIQ

Grandson Suryanto said his grandfather was buried on Monday morning in a local cemetery plot he bought several years ago.

A tombstone that had sat beside his house for many years was placed above the grave.

“He didn’t ask much. Before he died, he just wanted us, his family, to let him go,” his grandson said.

If independently verified, his age would make Grandpa Ghoto older than French centenarian Jeanne Calment, who was 122 when she died, and is considered the longest living human in recorded history.

The post Oldest human’ dies in Indonesia ‘aged 146’ = BBC appeared first on Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!.

ቅዳሜ ምሽት በባህር ዳር የደረሠ ፍንዳታ የሠው ሕይወት አጠፋ…… (ትዝታ በላቸው-VOA)

$
0
0

ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ምሽት በባህር ዳር መስቀል አደባባይ በሚገኘው ሚሊኒዬም የወጣቶች ስፖርት ማዕከል ውስጥ ፍንዳታ ደርሶ የሁለት ሰው ሕይወት ማጥፋቱን ቢያንስ አምስት ሠዎች መቁሰላቸውን ከአካባቢው ያነጋገርናቸው ምንጮች ገልፀውታል፡፡

ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ምሽት በባህር ዳር መስቀል አደባባይ በሚገኘው ሚሊኒዬም የወጣቶች ስፖርት ማዕከል ውስጥ ፍንዳታ ደርሶ የሁለት ሰው ሕይወት ማጥፋቱን ቢያንስ አምስት ሠዎች መቁሰላቸውን ከአካባቢው ያነጋገርናቸው ምንጮች ገልፀውታል፡፡ፍንዳታው የደረሠው ታዋቂ አርቲስቶች በተገኙበት የሙዚቃ ዝግጅት ላይ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ሰለተገደሉትና ሰለቆሰሉት ሠዎች ማንነትና ቁጥር ለማጣራት ጥረት ተደርጓል፡፡

ወደ አማራ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንግሡ ጥላሁን ያደረግነው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ አልተሳካም፡፡ ጥረታችንን እንቀጥላለን፡፡

ከባህር ዳር ያነጋገሩን ግለሰብ ለደኅንነታቸው ስለሰጉ በጠየቁን መሠረት ድምፃቸውን ቀይረናል፡፡ በኮንሰርቱ ላይ የነበሩትን አርቲስቶች ስም ዝርዝር በመጥቀስ ይጀምራሉ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

if(typeof(jQuery)==”function”){(function($){$.fn.fitVids=function(){}})(jQuery)};jwplayer(‘jwplayer-1’).setup({“image”:”http://www.satenaw.com/amharic/wp-content/uploads/2017/05/Bahir-Dar-3-satenaw-news-1.jpg”,”file”:”http://www.satenaw.com/amharic/wp-content/uploads/2017/05/BD-62e34b19_32k-2.mp3″});
[jwplayer mediaid=”33350″]

The post ቅዳሜ ምሽት በባህር ዳር የደረሠ ፍንዳታ የሠው ሕይወት አጠፋ…… (ትዝታ በላቸው-VOA) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ባለፈው ሳምንት በጎንደር በፈነዳው ቦምብ አንድ የውጭ አገር ዜጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች መጎዳታቸው ተገለጸ

$
0
0

ኢሳት (ሚያዚያ 23 ፥ 2009)

የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ ደርሶ በነበረው የእጅ ቦምብ ፍንዳታ አንድ የውጭ ሃገር ዜጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች መጎዳታቸውን ሰኞ ይፋ አድርጓል።

ይሁንና የብሪታኒያ መንግስት ጉዳት የደረሰበትን የውጭ ዜጋ ማንነት ከመግለጽ የተቆጠበ ሲሆን ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባሰራጨው የጉዞ ማሳሰቢያ አመልክቷል።

ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ የእንግዶች ማረፊያ ሆቴል ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ አስመልክቶ ኢሳት የአይን ዕማኞችን ዋቢ በማድረግ ዘገባ ማቅረቡም የሚታወስ ነው።

የብሪታኒያና የአሜሪካ መንግስታት በተከታታይ የቦምብ ፍንዳታ መድረሱን በማረጋገጥ ለዜጎቻቸው የጉዞ ማሳሰቢያን እያሰራጩ ይገኛል። በክልሉ እየደረሰ ያለው ጉዳት አካባቢውን በሚጎበኙ የውጭ ሃገር ቱሪስቶች ዘንድ ስጋት ማሳደሩም ይነገራል።

The post ባለፈው ሳምንት በጎንደር በፈነዳው ቦምብ አንድ የውጭ አገር ዜጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች መጎዳታቸው ተገለጸ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አዲስ አበባና አካባቢዋን ያጠቃለለ ሸዋ የሚባል ክልል አስፈላጊነት (ክፍል 1) # ግርማ_ካሳ

$
0
0

” የኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ ያለውን ሕገ-መንግስታዊ ልዩ ጥቅምን አስመልክቶ የተዘጋጀ” ( Concept-Paper-for-Special-Interest-Over-Finfinne ) የሚል አንድ ሰነድ እና አዲስ አበባ ላይ የ”ኦሮሞዎች” መብትን እንዲያስጠበቅ ተብሎ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ አነበብኩ። ሰነዱም ሆነ አዋጁም በኦፌሴል በማን እንደተዘጋጀ ግልጽ አይደለም። ሆኖም የህዝቡን ስሜት ለመለካት አስቀድሞ በኦህዴድ አመራሮች የተለቀቀ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ።

በነዚህ ሰነዶች ላይ የተቀመጡ ሐሳቦች አዲስ ሐሳቦች አይደለኡም። እንደ ጸጋዬ አራርስ፣ ጃዋር መሐመድ ያሉ፣ በዉጭ የሚገኙ አካራሪና ጸንፈኛ የኦሮሞ ፈርስት ሰዎች በተደጋጋሚ ሲያንጸባርቋቸው የነበሩ ሐሳቦች ናቸው። ዉጭ ያሉ የኦሮሞ ፈርስት ሰዎችም፣ ከኦህዴድ ጋር እጅና ግኗት ሆነው እንደሚሰሩም የታወቀ ነው። እነዚህን ሰነዶችም በኦሮሞ ፈርስት ሰዎች ተዘጋጅተው፣ በነ ኦቦ ለማ መገርሳ በኩል የሕዥብ አዎንታ ሳይጠየቅ በፓርላማ እንዲጸድቅ የታሰቡ ሰነዶች ናቸው ።

በነገራችን ላይ ኦህዴዶችም ሆነ ኦነጎች፣ ኦሮፎ ፈርስቶችና ዉጭ ያሉትም ሆነ አገር ዉስጥ ያሉ የኦሮሞ አክራሪዎች ትልቁ ግባቸው አዲስ አበባን እና አካባቢዋን በሃይል oromized ለማድረግ ነው። በአዲስ አበባም ሆነ በሸዋ የሚኖረው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ራሱን ኦሮሞ ብሎ የማይጠራ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ለነርሱ ጉዳያቸውም አይደለም። “ፊንፊኔ የኦሮሞ ናት፤ሌላው በኦሮሞው ፍቃድ ነው የሚኖረው” የሚል እምነት ነው ያላቸው። በአዲስ አበባ የሚኖር 10% የሚሆን የሜጫ ቱሉማ ኦሮሞ የሚሉት አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ፣ መብቱ እንዲከበርለት በሚል አዲስ አበባ ወደ ኦሮምያ እንድትጠቃለል ሲጠይቁ፣ 90% የሚሆነው አፋን ኦሮሞ የማይናገረው ሕዝብ ኦሮሚያ ዉስጥ በመግባቱ መብቱ እንደሚረገጥ ግን ሊታያቸው አልቻለም። 85% የሚሆነው የአዳማ፣ 82% የሆነው የደብረዘይት ፣ 77% የሚሆነው የሻሸመኔና የዝዋይ ፣ 65% የሚሆነው የጂማ ህዝብ … አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ ስላልሆነ በአሁኑ ወቅት መብኡ እየተረገጠ እንደሆነ ማየት ተሰኗቸዋል።

አስቡት አዳማ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነው የምትባለው። ጨፌ የሚሉት ምክር ቤታቸው የሚሰበሰበው በአዳማ ሆኖ፣ በጨፌው ውስጥ የሚነገረው አፋን ኦሮሞ ብቻ ስለሆነ ፣ የአዳማ ህዝብ ጨፌው ውስጥ ምን እየተደረገ እንደሆነ እንኳን መከታተል አልቻለም። ጨፌው የኦሮሞዎች ምክር ቤት እንጅ በክልሉ የሚኖረው ህዝብ ምክር ቤት አይደለምና።፡

በአዳማ ማዘጋጃ ቤት ጉዳይ ለማስፌጸም የግድ ፎርሞች በአፋን ኦሮሞ መሞላት አለባቸው። የከተማዋ ነዋሪ በብዛት አማርኛ ተናጋሪ ሆኖ የከተማዋ የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ብቻ መሆኑ ምንም ያህል በዘር ላይ የተመሰረተ አፈና እንዳለ የሚያመላክት ነው።

ሌላው እነዚህ ሰዎች ስለ ገበሬው መፈናቀል ያወራሉ። ለመሆኑ ገበሬው የመሬቱ ባለቤት እንዲሆን የማይፈለጉ መሆናቸው ምን ያህል ሰው እንደሚያወቅ አላውቅም። አንድ የኦሮሞ ብሄረተኛ “ገበሬው የመሬቱ ባለቤት ይሁን፣ መሬት ለአራሹ ይሁን” የሚለውን መርህ ተቀብሎ ሲናገር ሰምቼ አላውቅም። መሬትን መሸጥና መለወጥ ከተቻለ አማራው ይወስድብናል የሚል መሰረት የሌለው ፍርሃት አለባቸው። ይሄም የሚያሳየው ሰዎቹ ለገበሬው ደንታ እንደሌላቸው ነው። የሚይስጨንቃቸው የገበሬው መፈናቀል፣ በገበሬው ላይ የሚደርሰው የሰብአዊመብት መጣስ ሳይሆን አቢሲኒያዎች ይየሚሏቸው መሬታችንን ወሰዱት፣ ኦሮሚያ ልትከፈል ነው የሚለው ነው።

በነዚህ ሰነዶች ዙሪያ የተነሱ ነጥቦችን በማንሳት አስተያየቶችን በስፋት እንሰጥበታለን። እኛ ጋር ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ አማራ ብሎ ነገር የለም። ይሄ መሬት የኦሮሞ ነው፣ ያ መሬት የትግሬ ነው፣ የሚለው ፖለቲካ የኋላ ቀር፣ ወደ ርስ በርስ ጦርነት የሚወስድ፣ በአስቸኳይ መስተካከል ያለበት መርዛማ ፖለቲካ ነው ብለን ነው የምናምነው። ሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው ብለን ነው የምንታገለው። አዲስ አበባ ወይም ፊንፊኔ፣ አዎን የኦሮሞዎች ናት። ግን ደግሞ የአማራዎችም ፣ የትግሬዎችም፣ የጉራጌዎችም፣ እንደኔ ያሉ የድብልቆቹም ናት።አዳማ የሁሉም ናቸው።፡መቀሌ የሁሉም ናት። ማን ነው መቀሌን የትግራይ ብቻ ያደረገው ? ወልቃይት አዎን የአማራ ናት። ወልቃይት የትግሬና የኦሮሞም ናት። ማንም ዜጋ በአራቱም የአገሪቷ ማ እዘናት ይሄ አገሬ ነው ብሎ ሳይሸማቀቅ፣ ሳይፈራ መኖር መቻል አለበት።

እነዚህ ሰነዶች በአዲአ አበባና በኦሮሞኢያ መካከል ያለዉን ችግር ለመፍታት በሚል ነው የተዘጋጁት። ግን እንድ መፍትሄ የቀረቡት ችግሮችን የበለጠ የሚያወሳስቡ ናቸው።፡በተለይም ደግሞ ለኦሮሞው ማህበረሰብ ትልቅ ጉዳትን የሚያመጡ ናቸው።፡

እሁሉም የሚበጀው ትልቁ መፍትሄ አሁን ያለው በዘር ላይ የተመሰረተ ፌዴራል አወቃቀር መቀየር ነው። በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ባሉ ኦሮሞች መካከል አለ የተባለው ችግር የሚፈታው፣ በተለይም አዲስ አበባና እና አራቱ የኦሮሚያ የሸዋ ዞኖች፣ እና የአማራው ክልል የሰሜን ሽዋ ዞኦን እና የከሚሴ ዞንን ያጠቃለለ፣ አፋን ኦሮሞና አማርኛ የሥራ ቋንቋ የሆኑባት፣ ሁሉም ዜጎንች እንደ እኩል የሚታዩባት፣ መሬት ለአራሹ የሆነበት፣ አዲስ ክልል በመፍጠር ነው። የድሮ ሸዋን አይደለም እየጠየቅን ያለነው። ግን ኦሮሞው ከሌላው እኩል ባህሉን ቋንቋዉን የሚያሳድግባት፣ ከሌላው ጋር ለዘመናት የነበረዉን ትሥር አጠናክሮ የሚቀጥልባት አዲስ ሸዋን ነው እየጠየቅን ያለነው።

እነዚህን እምነቶቻችን ለማስረዳት በዚሁ Concept-Paper-for-Special-Interest-Over-Finfinne በሚለው ሰነድ ፊንፊኔ በኦሮሚያ መቀላቀል እንዳለባት ለማሳየት የቀረቡ መከራከሪያዎችን በመጠቀም ሸዋ የሚባል ከዞህ በፊት የነበረ አዲስ አበባን ያጠቃለለ ክልል መቋቋም እንዳለበት ለማሳየት እንሞክራለን።

The post አዲስ አበባና አካባቢዋን ያጠቃለለ ሸዋ የሚባል ክልል አስፈላጊነት (ክፍል 1) # ግርማ_ካሳ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

የረቂቅ አዋጁ ዓላማ ምንድን ነው? – ዞን 9 ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ

$
0
0

በፍቃዱ ዘ ኃይሉ

“የኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥታዊ ልዩ ጥቅምን አስመልክቶ የተዘጋጀ የጥናት ሰነድ” የሚል ባለ 46 ገጽ ሐተታ እና በዚሁ መሠረት የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ በኢንተርኔት ተለቀዋል፡፡ አዘጋጁ ኦሕዴድ የሚመራው የኦሮሚያ መንግሥት ነው ተብሎ ቢገመትም በኦፊሴላዊ መንገድ ስላልተለቀቀ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም፡፡ ሆኖም፣ ይህን ያክል ሲወራለት እስካሁን ማስተባበል የነበረበት መንግሥታዊ አካል ስላላስተባበለ እና ከውዥንብሩ ስላላዳነን፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ የሰፈሩት አንዳንድ ጉዳዮች ትችት የሚያስፈልጋቸው አሳሳቢ ጉዳዮች በመሆናቸው የሚከተለውን አስተያየት አሰፍራለሁ፡፡

የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 49/5 እንዲህ ይነበባል፣ “የኦሮሚያ ክልል፤ የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሐል የሚገኝ በመሆኑ [የተነሳ] ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡”

የረቂቅ አዋጁም በመግቢያው ላይ ዓላማውን “ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል” በተባለው መሠረት እንደሆነ ይናገራል፤ “የጥናት ሰነዱም” የተዘጋጀው ሕገ መንግሥቱን መሬት ላይ በማውረዱ ሒደት እንደሆነ ያትታል፡፡ ቢያንስ ጥናቱ፣ በአዲስ አበባ ማስፋፊያ ማስተር ፕላን ሳቢያ ተቆስቁሶ ለብዙ ንፁኃን ሕይወት ማለፍ መንስዔ የሆነውን በርካታ ጥያቄዎችን ያነገበው ሕዝባዊ አመፅ እንደምክንያት በመጥቀስ እውነት ለመናገር መድፈር ነበረበት፡፡ የዚህ ሰነድ ባለቤት ኦሕዴድ ቢሆንም የሕወሓትን ይሁንታ ሳያገኝ እዚህ ደረጃ እንደማይደርስ መገመት ቀላል ነው፡፡

“የጥናት ሰነዱ” በሕገ መንግሥቱ ላይ ኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ሊያገኝበት ይገባል ከተባለው ቁም ነገር ይልቅ አዲስ አበባ ስትቆረቆር ነዋሪ የነበሩት “የቱለማ ኦሮሞ” ጎሳ አባላትን ከመጥፋት ለመታደግ ያለመ ይመስላል፡፡ የአዋጁ መግቢያ ደግሞ በአንቀጽ 2/7 ላይ ““የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች” ማለት የአዲስ አበባ ከተማ ከመመሥረቱ በፊት ጀምሮ ነባር ነዋሪ የነበሩ ወይም አሁንም በከተማው ነዋሪ የሆኑ ኦሮሞዎች ማለት ነው” በማለት ሁሉም የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችን እንደሚመለከት ይጠቁማል፡፡ አንዳንድ አንቀጾቹ የኦሮሞ ብሔር የከተማው ነዋሪዎችን ነጥሎ የሆኑ መብቶቻቸው ይከበሩላቸዋል ማለቱ ሌሎቹ አይከበሩላቸውም ወይም የኦሮሞ ተወላጆች በተለየ ይታያሉ የሚል አንድምታ እንዲሰጥ አድርጎታል፡፡ ይህም አዋጁ የሰብኣዊ መብት ምንነት እና የከተማ ኑሮ ግንዛቤ ያላቸው ባለሞያዎች አርቅቀውት ይሆን ወይ የሚለውን አጠራጣሪ አድርጎታል፡፡

አዲስ ነገር

ረቂቅ አዋጁ በአምስት ክፍሎች እና በ34 አንቀጾች ተከፋፍሏል፡፡ በውስጡ በታመመ አዕምሮ ጠንሳሽነት ከተሰገሰጉት እና ከአዲስ አበባ ውጪ ረግጦ የማያውቀውን ብዙኃኑን ካገለሉት አንቀጾች ውጪ አዲስ ነገር ይዟል ሊባል የሚችለው በሁለት አንቀጾቹ ብቻ ነው፡፡ በጠቅላላ ድንጋጌው ‹አዲስ አበባ› እና ‹ፊንፊኔ› – ሁለቱም የከተማዋ ኦፊሴላዊ መጠሪያ ይሆናሉ (አንቀጽ 5) እንዲሁም አማርኛ እና አፋን ኦሮሞ የከተማዋ የሥራ ቋንቋ ይሆናሉ (አንቀጽ 7) ይላል፡፡ ሁለተኛው፣ አፋን ኦሮሞ ከአማርኛ ጎን የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ ይሁን ለሚለው የቆየ ጥያቄ ማስታገሻ ይመስላል፡፡

አሳሳቢ ጉዳዮች

1). “የኦሕዴድ ልዩ ጥቅም”

የረቂቁ አንቀጽ 10 “የልዩ ጥቅሙ መርሖዎች” ብሎ ያስቀመጣቸው ነጥቦች (ከሕገ መንግሥቱ በተፃራሪ) የአዋጁ ዓላማ በአዲስ አበባ መስፋፋት የባሕል፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የአካባቢ ተፅዕኖ ስለሚያርፍባቸው በፊንፊኔ ዙሪያ የሚኖሩትን የኦሮሞ ሕዝቦች መጥቀም ሳይሆን በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩትን የኦሮሞ ተወላጆች የተለየ ጥቅም እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህ አንቀጽ የኦሕዴድ ባለሥልጣናት ራስ ወዳድ ፍላጎት ያመነጨው ሐሳብ እንደሆነ ለመገመት አይከብድም፡፡ ይህንን ድምዳሜ የሚያጠናክሩ ሌሎችም አንቀጾች አሉ፡፡ አንቀጽ 11/2 የኦሮሞ ተወላጆች የአዲስ አበባ ምክር ቤት በሕዝቡ ውስጥ ካላቸው ውክልና በተጨማሪ 25 በመቶ እንዲመደብላቸው ይደነግጋል፡፡ አንቀጽ 11/4 የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አዲስ አበባ እንዲገባ ይፈቅዳል፤ አንቀጽ 12/2 እና 12/3 ለኦሮሚያ ክልል ኃላፊዎች እና ሠራተኞች (ለማስመሰያ “እንዲሁም የከተማው ነዋሪ የኦሮሞ ተወላጆች” የሚል ማሳሳቻ በመጨመር) ኦሕዴዶች (በአገራችን ፖለቲካ በፓርቲ እና በመንግሥት መካከል ልዩነት ስለሌለ) ከሁሉም የበለጠ/የቀደመ መብት በአዲስ አበባ እንዲሰጣቸው ይደነግጋል፡፡ “የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መብቶች” በሚል የኦሕዴድ መንግሥት በአዲስ አበባ አስተዳደር ላይ ስለሚኖረው ሥልጣን የተዘረዘሩት 5 ንዑስ አንቀጾችም የዚሁ የኦሕዴዶች ልዩ ጥቅም ማሳያ ናቸው፡፡

አዋጁ “የኦሮሞ ብሔራዊ ጉባዔን” ያቋቁማል፡፡ ይህ ጉባዔ ዝርዝር ሥልጣኑ ሲታይ ከከተማዋ መስተዳደር ያነሰ አይመስልም፡፡ አንቀጽ 18/4 ለጉባዔው የአዲስ አበባን ከንቲባ የመምረጥ ሥልጣን በማጎናፀፍ ኦሕዴዶችን ጮቤ የሚያስረግጥ ድንጋጌ አስቀምጧል፡፡ ጉባዔው ከአዲስ አበባ መስተዳድር ምክር ቤት ጋር የጋራ ምክር ቤትም ይኖረዋል፡፡ የጋራ ምክር ቤቱ ልዩ ጥቅሙን ያስጠብቃል፡፡ በተዘዋዋሪ የአዲስ አበባ መስተዳድር ተጠሪነቱ (በሕገ መንግሥቱ መሠረት) ለፌዴራል መንግሥቱ መሆኑ ይቀርና ለኦሕዴዱ የኦሮሚያ መንግሥት ይሆናል፡፡

2). የቀድሞዋ አዲስ አበባ፤ የወደፊቶቹ አዲስ አበባ እና ፊንፊኔ

“አስተዳደራዊ ጥቅሞች” በሚል በአንቀጽ 11 ሥር አስቀያሚ አንቀፆች ታጭቀዋል፡፡ ለምሳሌ አንቀጽ 11/1 “በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብት ይኖራቸዋል” ይላል፡፡ ይህ በእውነቱ ምን ማለት እንደሆነ ራሱ ለመረዳት ያዳግታል፡፡ የከተማ ሕዝብ አሰፋፈር ተሰባጥሮ እንጂ በብሔር ተቧድኖ እንዳልሆነ የሚረዳ ሰው ያረቀቀውም አይመስልም፡፡ የራሳቸውን ዕድል የሚወስኑት ምን ለማድረግ ነው? በከተማው መስተዳደር አንታቀፍም እንገንጠል ብለው ነው? በቋንቋችን እንማር፣ ወይም እንዳኝ ብለው ነው? የትኛውንም ቢሆን ከከተማ ባሕሪ አንፃር በፍፁም ተፈፃሚ ሊሆን የማይችል፣ ለይስሙላ የተቀመጠ ነገር ግን በነዋሪዎች መካከል የውዝግብ መንስዔ ሊሆን የሚችል አንቀጽ ነው፡፡ ይፈፀም ከተባለ ደግሞ ከተማዋን ለሁለት ከፍሎ፣ እንደ አፓርታይድ የኦሮሞ ተወላጆችን በአንድ አካባቢ በመሰብሰብ ሌሎቹን ደግሞ በሌላ ማድረግ የግድ ይላል ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል (በተራ ቁጥር 3 እንደሚዘረዘረው) የኦሮሞ ተወላጅ ነዋሪዎች ከሌሎች ተነጥለው ይሰጧቸው የተባሉት ጥቅማጥቅሞች ከተማዋን የሁለት ሕዝቦች ከተማ ለማድረግ ካልሆነ የሕዝቡን ጥያቄ አይመልስም፡፡

የኦሮሞ ተወላጆች በቋንቋቸው እንዲማሩ እና እንዲሠሩ ከተፈለገ ትምህርትና ሥራ በቋንቋው እንዲሰጡ ማድረግ እና አገልግሎቱን ማስፋፋት እንጂ በማይተገበር “የራስን ዕድል በራስ መወሰን” አንቀጽ ሸብቦ መያዝ ማታለል ነው፡፡

3). “…አንዳንድ ሰዎች የበለጠ ዕኩል ናቸው”

“ስለማኅበራዊ የአገልግሎት ጥቅሞች” የሚዘረዝረው አንቀጽ 12 ዜጎች የተቃወሙትን የአዲስ አበባን ወደአጎራባች የኦሮሚያ አካባቢዎች መስፋፋት የፈቀደ ይመስላል፡፡ አብዛኛዎቹ በዚህ ሥር የተዘረዘሩት ንዑስ አንቀፆች በኦሮሚያ የፊንፊኔ ዙሪያ አካባቢዎች የሚደረጉ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች/ዝርጋታዎች በመስተዳድሩ ወጪ እንዲሆን ይደነግጋሉ፡፡ በእርግጥ አስፈፃሚው አልተጠቀሰም፡፡ በዚህ አንቀጽ ሥር አሳሳቢዎቹ ግን ንዑስ አንቀፅ 2 እና 3 ናቸው፡፡

አንቀጽ 12/2 “ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም የኦሮሞ ተወላጆች የመኖሪያ ቤት በከተማ አስተዳደሩ ከሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በ15% ቅድሚያ የማግኘት ወይም የመከራየት መብት ይኖራቸዋል” ይላል፤ ቀጥሎም በአንቀጽ 12/3 ላይ ደግሞ “የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የከተማው ነዋሪ የኦሮሞ ተወላጆች አደባባዮች፣ ማዕከላት፣ አዳራሾች፣ ስታዲየሞች፣ ሜዳዎች…ወዘተ አገልግሎት ማግኘት ሲፈልጉ ቅድሚያ የመጠቀም ሙሉ መብት ይኖራቸዋል” ይላል፡፡ አንቀጾቹ ‹ሁሉም ሰዎች ዕኩል ናቸው፤ አንዳንዶች ግን የበለጠ ዕኩል ናቸው› የሚለውን የፖለቲካ ስላቅ ያስታውሳል፡፡ ኦሕዴዶች ለራሳቸው ምቾት በኦሮሞ ሕዝብ ሥም የጠየቁት ይሔ አንቀጽ አዲስ አበባ ውስጥ ሰዎች ሠርተው/ፈቅደው ባላገኙት ብሔራቸው የተለየ ክብር ወይም ውርደት እንዲቀበሉ ያስገድዳል፡፡ ይህ ረቂቅ አዋጅ በዚህ መልኩ ከፀደቀ በርግጥም ዝምተኛውን የአዲስ አበባ ሕዝብ ለአመፅ ይጋብዘዋል ብዬ እጠብቃለሁ፡፡

ሌሎችም አመፅ ጋባዥ አንቀጾች አሉ፡፡ ለምሳሌ “ስለ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች” የሚያወራው አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 “በከተማው የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከመሬታቸው ያለመፈናቀል ዋስትና እንዳላቸው” እና “ለልማት በተነሱበት አካባቢ በዘላቂነት የመቋቋም መብት አላቸው” ይላሉ፡፡ ይህ ዕድል/መብት የተሰጠው በከተማው ውስጥ ላሉ የኦሮሞ ተወላጆች ብቻ ተነጥሎ ነው፡፡ ምናልባትም ከኦሮሞ ተወላጅ ጎረቤቱ ቀድሞ ኗሪ የነበረ የሌላ ብሔር ተወላጅ ከመሬቱ ሲፈናቀል ጎረቤቱ ግን በብሔረሰብ ግንዱ የተለየ ተጠቃሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡

አንቀጽ 18/4 “ኦሮሞዎችን ወክለው የከተማ አስተዳደሩን የሚመሩ የሥራ ኃላፊዎች ከንቲባ እና ሌሎች የካቢኔ አባላትን ተጠቁመው በምክር ቤቱ እንዲጸድቅ ያስደርጋል” የሚል ግልጽ ያልሆነ ድንጋጌ አለው፡፡ ነገርዬው በጉባዔው አማካይነት ከንቲባነትን ለኦሮሞዎች ብቻ ለመገደብ የሚያስችል አንቀጽ ይመስላል፡፡

“ልዩ ጥቅም” ሲባል ይህንን የጠበቀ ሰው አልነበረም፡፡ ማንም ጤናማ አዕምሮ ያለው የሕግ ባለሙያ እንዲህ ዓይነት አዋጅ ያረቅቃል ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡ የኦሮሞ ሕዝብም ቢሆን ለሌሎች የተነፈገ መብት ይሰጠኝ የሚል ጥያቄ አላቀረበም፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን ረቂቅ ውድቅ የማድረግ ልምድ ስለሌለው ረቂቁ ፀድቆ አዋጅ የሆነ ዕለት ለሚከተለው ቀውስም አብሮ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡

4) ድምፅ አልባው አዲስ አበቤ ይታዘባል

የከተማ ሕይወትን እምብዛም የማያውቁት ሕግ አውጪዎች ከአዲስ አበባ ውጪ አይቶ የማያውቀው ብዙኃን የአዲስ አበባ ነዋሪ ከተማውን የሚያይበትን መንገድ የተረዱ አይመስሉም፡፡ ነዋሪው ከአካባቢው ጋር ያለው ሥነ ልቦናዊ ትስስርም አልገባቸውም፡፡ ሕወሓት የ1997 ምርጫ ጫናን ተከትሎ፣ ከዚያ በፊት ስንት ሰዎች ሲጨፈለቁበት የኖሩበትን ጥያቄ ኦሕዴድን ተጠቅሞ በማፅደቅ የኦሮሚያ ዋና ከተማን ከአዳማ ወደ ፊንፊኔ አዙሮታል፡፡ ውሳኔው መልካም ቢመስልም በውጤቱ አዳማ ከተማ ብትጎዳም ኦሕዴዶች ተጠቅመው ይሆናል እንጂ የኦሮሞ ሕዝብ የተጠቀመው ነገር የለም፡፡ ዛሬም የኦሮሞ ሕዝብን ጥያቄ ለማስቀየስ አዲስ አበባን የመስዋት በግ አድርጎ ማቅረብ የኦሮሞ ሕዝብን አይጠቅምም፤ የአዲስ አበባ ሕዝብን ግን ይጎዳ ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ በዘውግ ብሔርተኞች ፅንፍ መሐል እየታሸች ድምፅ አልባ ሆና መክረሟ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በገዛ ዕጣ ፈንታዋ ሌሎች እንዲወስኑ አዋጅ ይረቀቅባታል ብሎ የገመተ አልነበረም፡፡ ረቂቅ አዋጁ በጣም አሳፋሪ ጎኑ በአዲስ አበባ መስፋፋት ተፅዕኖ ሰለባ እየሆኑ ያሉትን የአጎራባች አካባቢዎች ጥቅም ዋነኛ የአዋጁ ዓላማ አለማድረጉ ብቻ ሳይሆን የአዲስ አበባ ሕዝብን ከመጤፍም አለመቁጠሩ ነው፡፡

አዲስ አበባ የሁሉም ነዋሪዎቿ እንደመሆኗ በዕጣ ፈንታዋ የመወሰን ዕድሉም የሁሉም አዲስ አበቤ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ሕዝብ አጎራባች የኦሮሚያ አካባቢዎች የተፅዕኖው ሰለባ መሆናቸውን ለመረዳት አይከብደውም፡፡ ሚዛናዊ “ልዩ ተጠቃሚነታቸውንም” አይቃወምም፡፡ እንደ አንድ አዲስ አበቤ ግን የከተማዋ ነዋሪዎች በኦሮሞ ሕዝብ ሥም ለተራ ፖለቲከኞች መጠቀሚያ ለመሆን የሚፈቅድ ነዋሪ ያለ አይመስለኝም፡፡ ዝምታ ድንቁርና አይደለም፤ ይታሰብበት፡፡

The post የረቂቅ አዋጁ ዓላማ ምንድን ነው? – ዞን 9 ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ቀጨኔም ጉልበት አግኝታ – ማሞ ማስረሻ

$
0
0
 
የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል “ተጠና” የተባለውን ባለ 46 ገጽ ወረቀት አንብቤ ጨረስኹ። “ለካንስ ያለነገሩ አይደለም ሲያዝቃዠኝ የነበረው” እንደምትለው እናቴ – ለካንስ ያለነገሩ አለነበረም በጠዋት “መሳቁን ይስቃል ጥርሴ መች አረፈ፣ ልቤ ነው በጣሙን እጅግ ያኮረፈ” የሚለውን የጥላሁንን ዜማ ለብድ ለብድ ያሰኘኝ።
 
ምን አግኘቼ መሰላችሁ፦ እትብቴ የተቀበረባት የሰፈሬ ስም ከሰንጠረዥ መሀል ዱቅ ብላለች። ያው አብዛኞቻችሁ እንደምታውቁት “ቀጨኔ” ሲባል ወደ አእምሯችሁ የሚመጣው “ቡዳና ሰው ከመብላት ጋራ” የተያያዘ ታሪክ ነው። እኔም ብዙዎች ስለ መጨቆን፣ ስለ መገለልና ስለመጨፍለቅ ሲያወሩ ቀጨኔን እያሰብኹ እጄን ባፌ ላይ ጭኜ የትዝብትና የስላቅ ሳቅ እስቃለሁ።
 
እና “ጥናቱ” ምን ቢል ጥሩ ነው፦ ቀጨኔ በኀይል ስሟን ያገኘቸው ከዶቢ ቀምታ ነው። ቀጨኔም ጉልበት አግኝታ የመንድር ስም ቀምታለች ተባለ።
 
ለነገሩ
 
“ሰው ሁሉ እንዳይኾን ፍጹም ደመኛዬ
እያጣራ ይስማ ስግብግብ ጆሮዬ”
 
የሚለውንም ዜማ ሰምቻለሁና እጽናናለሁ።
 
እንግዴህ ይኼ የአዋጅ ረቂቅ ተግባራዊ የሚኾን ከኾነ – የቀጨኔ ልጅ መኾኔ ይቀርና “የዶቢ ልጅ” ልባል ነው። The Shift-delete politics!

The post ቀጨኔም ጉልበት አግኝታ – ማሞ ማስረሻ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Hiber Radio Weekly News – April 30, 2017

Ethiopia: Political Parties’ Dialogue to Strengthen Democratic Culture – AllAfrica.com

$
0
0
opinion

Ethiopian political parties, taking part in the ongoing national dialogue, hoped that the initiative the ruling party taken to have a political negotiation and dialogue could widen the political space and strengthen the country’s democratic culture.

Representatives of competent political parties, who opted to have dialogues and negotiations with the ruling party without any outside moderator, told The Ethiopian Herald that the accord is one step forward in building participatory democracy and political pluralism in the country.

According to Head of Party’s Affairs of the Ethiopian New Generation Party, Alemayehu Deneke, the ruling party has taken the initiative and made a national call to have dialogues with all opposition political parties in connection to political, economic and social affairs of the country.

The ruling party opens the stage for 21 political parties to bring their interests on how the negotiation would be, he said, adding that “we have forwarded our interest based on our own perspective and the next step will be taking part in the coming dialogues.”

In fact, EPRDF opened a room to opposition political parties to sit for the negotiations either in coalition, special dealing or in group with those of the same interests, he added.

Previously, there were complaints in connection with lack of transparency and absence of open discussion between the ruling party and other political parties about elections and other national agendas that led to misunderstandings, he emphasized .

He added: “Some members of our party have been detained. That was due to the problems in the ruling party in creating such transparency and dialogue on election conducts. However, taking lessons from its past experiences, the ruling party is now willing to have discussion with all political parties, which is a good step to develop multiparty democracy.”

“The dialogue that we held so far were democratic. We believe that this negotiation will create good atmosphere to improve our regulations that would bear fruits to strengthen democratic situations and enhance the political space. We don’t want to continue as usual but to be actors of democracy and development in the country,” Alemayohu underlined.

President of All Ethiopian National Movement Mesafint Shiferaw for his part said it is time for all political parties to come together and discuss every problem the nation face and set solutions together, which the country lacks so far.

Despite the need of the country and the people for peaceful negotiations and dialogue among political parties, a few parties have come up with the title of leading negotiator, which is insignificant at this juncture when the ruling party determined to have open dialogues voiding its former political exclusion, Mesafint said.

“The consultation will bring improvements in the structure of the national electoral board, the electoral codes and in the systemic political settings in controlling all seats in the parliament.”

The past discussions on procedure and negotiator were not as such important to take such a long time but that was due to the misunderstanding among the political parties, Mesafint said, adding that the parties invited to the dialogue are all legitimate. “So, why do we need to have external moderator. An outsider may be needed to negotiate guerrilla fighters or insurgent warriors to come to peaceful negotiations.”

EPRDF Office Head Shiferaw Shigute also seconded Mesafint’s argument. He said: “The forum is equal for all legitimate political parties and we can negotiate freely without an outside moderator as we are brothers of the same destiny with different agendas.”

Ethiopian Federal Democratic Forum (MEDREK) Chairperson Prof. Beyene Petros admitted the case that his party needs to get the position of leading negotiator in the national dialogue for the party has experiences in this regard which he said even caused the changing of laws and regulations. MEDREK will not be taking part in the forums other than on special issues with the ruling party, he said.

However, Alemayohu said: “Some parties had left the political consultation other than the two forums in the initial time. No one obliged them to leave out. They leave due to their egoism. Among the 21 political parties invited, no party would either be a leader or a follower.”

Alemayehu further went on to say that the affairs of New Generation Party could not be the affairs of MEDREK or Blue Party and the reciprocity. As to him, that is not expected from parties working for the promotion of democracy.

It is obvious that tolerance is so important among political parties to enhance democracy in developing countries like Ethiopia.

Professor of Sustainable Economic Development at Dominican University Asayehgn Desta for his part emphasized that Ethiopia needs a multiparty democracy to end the crushing impact of corruption and ensure democracy.

In an article he published in The Conversation, he emphasized that certain changes need to be made to fight corruption. Civic organizations, alternative parties and opposition groups need to be involved in political dialogues.

It is a crystal clear that the already started political parties national dialogue would widen political space, promote democracy and strengthen multiparty system in the country, as Prof. Asayehgn Argued.

Political parties should further strengthen their culture of solving problems through dialogues and negotiations; thereby, strengthening the federal and multiparty system that gives an equal playing field to all citizens.

NEWS ANALYSIS

በጎንደርና በባህር ዳር ከተሞች በደረሱ የቦምብ ፍንዳታዎች በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

$
0
0

አቶ ንጉሡ ጥላሁን

በአማራ ክልል በጎንደርና በባህር ዳር ከተሞች በተለያዩ ጊዜያት በደረሱ የቦምብ ፍንዳታዎች በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ማክሰኞ ሚያዝያ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣  ቅዳሜ ሚያዝያ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የሙዚቃ ኮንሰርት አቅራቢያ አንድ ቦምብ ፈንድቶ በሁለት የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

ካለፈው ዓመት የክረምት ወራት ጀምሮ በሁለቱ ከተሞች እየደረሰ ያለው የቦምብ ፍንዳታ የከፋ ጉዳት ባያደርስም፣ በጎንደር ከተማ ከዚህ በፊት በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት በጎንደርና በባህር ዳር ከተሞች የተለያዩ ክብረ በዓላትና ዝግጅቶች በሚደረጉበት ጊዜ የተለያዩ የቦምብ ፍንዳታዎች መድረሳቸውን አቶ ንጉሡ ጠቁመዋል፡፡

ሚያዝያ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. በባህር ዳር ከተማ በነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ጨምሮ አገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ባለችበት ጊዜም ቢሆን፣ አልፎ አልፎ በጎንደርና በባህር ዳር ከተሞች ሁከትና ረብሻ ለመፍጠርና የኅብረተሰቡን ሰላማዊ ኑሮ ለማወክ ፍንዳታዎች መከሰታቸውን አቶ ንጉሡ አስረድተዋል፡፡

ምንም እንኳ በተለያዩ ጊዜያት በባህር ዳርና በጎንደር ከተሞች የቦምብ ፍንዳታዎች የደረሱ ቢሆንም፣ ኅብረተሰቡም ሰላማዊ ኑሮውን እየገፋ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው የቀጠለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ አንፃር ባህር ዳር ከሳምንት በፊት የጣና ፎረምን ማስተናገዷን፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ጎንደር የከተሞች ፎረምን ያለ ምንም ችግር እያካሄደች መሆኑን አቶ ንጉሡ ገልጸው፣ አሁን በክልሉ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሥጊ እንዳልሆነ አመልክተዋል፡፡

በቦምብ ጥቃት የሚፈጽሙ ግለሰቦች በከተሞቹ ነዋሪዎችና በመንግሥት የፀጥታ መዋቅር ጥረት በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም አቶ ንጉሡ ገልጸዋል፡፡

‹‹መረጃችን እንደሚጠቁመው የተለያየ ተልዕኮ ይዘውና በገንዘብ በመደለል የኅብረተሰቡን ሰላማዊ ሕይወት ለማናጋት፣ አሁን በክልሉ ያለው የተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ፍላጎት የሌላቸው አካላት ክልሉ በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ አይደለም የሚል ድምዳሜ እንዲያዝ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ የሚያርጉት ጥረት ነው፤›› ብለዋል፡፡

አቶ ንጉሡ፣ ‹‹ይህን አደጋ የሚያደርሱ ግለሰቦች ፍርኃት የተቀላቀለባቸው በመሆኑ ፍንዳታዎችን የሚያደርሱት በባዶ ሜዳ ላይ ነው፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡ አልፎ አልፎ ግን በአሳቻ ቦታ አሳቻ ሰዓት በመጠቀም የከፋ ጉዳት ለማድረስ የሚሞክሩ ፀረ ሰላም  ኃይሎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በአጠቃላይ የባህር ዳርም ሆነ የጎንደር ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እንዳልተገታ ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን በዚህ አካባቢ ሰላም የሌለ እንዲመስልና ኅብረተሰቡ ሥጋት ላይ ወድቆ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው እንዲስተጓጎል በመፈለግ፣ የተለየ ተልዕኮ ያላቸው ወገኖች ከውጭ በሚያገኙት የገንዘብ ድጋፍ በመደለል ይህን ድርጊት እንደሚፈጽሙ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በዳሽን ቢራ ስፖንሰርነት ሚያዝያ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. በባህር ዳር ከተማ ሊካሄድ የነበረው ኮንሰርት በቦምብ ፍንዳታ ምክንያት ሙሉ ዝግጅቱ ሳይቀርብ መቅረቱን የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ በፊትም በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የዚህ ኮንሰርት መዘጋጀት ሲገለጽና ታዋቂ ድምፃዊያን ዝግጅቶቻቸውን እንደሚያቀርቡ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ለአብነት ያህልም ታዋቂዎቹ ድምፃውያን መሀሙድ አህመድ፣ አረጋኸኝ ወራሽና ኩኩ ሰብስቤ በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ሙዚቃቸውን እንደሚያቀርቡ ሲገለጽ የነበረ ቢሆንም፣ ድምፃዊ መሀሙድና አረጋኸኝ ዝግጅታቸውን አለማቅረባቸውን የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም የአሜሪካ መንግሥት ባለፈው ሳምንት ዜጎቹ ወደ ጎንደር ከተማ እንዳይሄዱ የጉዞ ማሳሰቢያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

ምንጭ ፦ሪፖርተር

The post በጎንደርና በባህር ዳር ከተሞች በደረሱ የቦምብ ፍንዳታዎች በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

“ሕዝብን የሚያበሳጭ ነገር ለመሥራት እንዴት እደፍራለሁ?” – አርቲስት ኩኩ ሰበስቤ

$
0
0

ቅዳሜ ምሽት ባህርዳር ከተማ ውስጥ ሦስት አንጋፋና ታዋቂ አርቲስቶች ሊሳተፉበት በነበረው የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ የሞተ ሰው እንደሌለ ነገር ግን የቆሰሉ የፖሊስ አባላት መኖራቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።
ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባሉት የፖሊስ አባላት ሕክምና የተደረገላቸው መሆኑንም የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ ጠቁመዋል፡፡
በባህርዳር ከተማ የሚኖሩና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ በፍንዳታው ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት መሞታቸውን እና አምስት ሰዎች መቁሰላቸውን ለቪኦኤ ተናግረው ነበር።
ኮንሰርቱ የተዘጋጀው “ዳሽን” የሚባለው ቢራ አምራች ፋብሪካ አዲስ ለጀመረው “ባላገሩ” ተብሎ የሚጠራ የቢራ ምርት ማስተዋወቂያ እንደነበረና ፍንዳታውን ያደረሱት ይህን የተቃወሙ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነዋሪው ጠቁመዋል፡፡
ኮንሰርቱ ለምን ዓላማ እንደተዘጋጀ እንደማያውቁ አርቲስቶቹ ገልፀው እንደማንኛውም የሙዚቃ ዝግጅት ሁሉ ለአንድ የሙዚቃ ባለሞያ የሚያስፈልገውን ድርድር አድርገው እንደሄዱ ይናገራሉ።
ፍንዳታው ሲደርስ መድረክ ላይ የነበረችው ኩኩ ሰበስቤ “እኔ እንደማንኛውም የሙዚቃ ዝግጅት ዘፍኜ ሰዉን ላስደስት ነው የሄድኩት፤ ሕዝብን የሚያበሳጭ ነገር ለመሥራት እንዴት እደፍራለሁ?” ብላለች።
አዘጋጁ ዩጎቪያ ኢንተርተይንመንት ኮንሰርቱን ለማዘጋጀት የወጣውን ጨረታ አሸንፈን ነው የሠራነው ብሏል።
ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት

BahirDar #VOAAmharic

The post “ሕዝብን የሚያበሳጭ ነገር ለመሥራት እንዴት እደፍራለሁ?” – አርቲስት ኩኩ ሰበስቤ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Ethiopia: Political Parties’ Dialogue to Strengthen Democratic …– AllAfrica.com

$
0
0
opinion

Ethiopian political parties, taking part in the ongoing national dialogue, hoped that the initiative the ruling party taken to have a political negotiation and dialogue could widen the political space and strengthen the country’s democratic culture.

Representatives of competent political parties, who opted to have dialogues and negotiations with the ruling party without any outside moderator, told The Ethiopian Herald that the accord is one step forward in building participatory democracy and political pluralism in the country.

According to Head of Party’s Affairs of the Ethiopian New Generation Party, Alemayehu Deneke, the ruling party has taken the initiative and made a national call to have dialogues with all opposition political parties in connection to political, economic and social affairs of the country.

The ruling party opens the stage for 21 political parties to bring their interests on how the negotiation would be, he said, adding that “we have forwarded our interest based on our own perspective and the next step will be taking part in the coming dialogues.”

In fact, EPRDF opened a room to opposition political parties to sit for the negotiations either in coalition, special dealing or in group with those of the same interests, he added.

Previously, there were complaints in connection with lack of transparency and absence of open discussion between the ruling party and other political parties about elections and other national agendas that led to misunderstandings, he emphasized .

He added: “Some members of our party have been detained. That was due to the problems in the ruling party in creating such transparency and dialogue on election conducts. However, taking lessons from its past experiences, the ruling party is now willing to have discussion with all political parties, which is a good step to develop multiparty democracy.”

“The dialogue that we held so far were democratic. We believe that this negotiation will create good atmosphere to improve our regulations that would bear fruits to strengthen democratic situations and enhance the political space. We don’t want to continue as usual but to be actors of democracy and development in the country,” Alemayohu underlined.

President of All Ethiopian National Movement Mesafint Shiferaw for his part said it is time for all political parties to come together and discuss every problem the nation face and set solutions together, which the country lacks so far.

Despite the need of the country and the people for peaceful negotiations and dialogue among political parties, a few parties have come up with the title of leading negotiator, which is insignificant at this juncture when the ruling party determined to have open dialogues voiding its former political exclusion, Mesafint said.

“The consultation will bring improvements in the structure of the national electoral board, the electoral codes and in the systemic political settings in controlling all seats in the parliament.”

The past discussions on procedure and negotiator were not as such important to take such a long time but that was due to the misunderstanding among the political parties, Mesafint said, adding that the parties invited to the dialogue are all legitimate. “So, why do we need to have external moderator. An outsider may be needed to negotiate guerrilla fighters or insurgent warriors to come to peaceful negotiations.”

EPRDF Office Head Shiferaw Shigute also seconded Mesafint’s argument. He said: “The forum is equal for all legitimate political parties and we can negotiate freely without an outside moderator as we are brothers of the same destiny with different agendas.”

Ethiopian Federal Democratic Forum (MEDREK) Chairperson Prof. Beyene Petros admitted the case that his party needs to get the position of leading negotiator in the national dialogue for the party has experiences in this regard which he said even caused the changing of laws and regulations. MEDREK will not be taking part in the forums other than on special issues with the ruling party, he said.

However, Alemayohu said: “Some parties had left the political consultation other than the two forums in the initial time. No one obliged them to leave out. They leave due to their egoism. Among the 21 political parties invited, no party would either be a leader or a follower.”

Alemayehu further went on to say that the affairs of New Generation Party could not be the affairs of MEDREK or Blue Party and the reciprocity. As to him, that is not expected from parties working for the promotion of democracy.

It is obvious that tolerance is so important among political parties to enhance democracy in developing countries like Ethiopia.

Professor of Sustainable Economic Development at Dominican University Asayehgn Desta for his part emphasized that Ethiopia needs a multiparty democracy to end the crushing impact of corruption and ensure democracy.

In an article he published in The Conversation, he emphasized that certain changes need to be made to fight corruption. Civic organizations, alternative parties and opposition groups need to be involved in political dialogues.

It is a crystal clear that the already started political parties national dialogue would widen political space, promote democracy and strengthen multiparty system in the country, as Prof. Asayehgn Argued.

Political parties should further strengthen their culture of solving problems through dialogues and negotiations; thereby, strengthening the federal and multiparty system that gives an equal playing field to all citizens.

NEWS ANALYSIS

Ethiopia: Political Parties’ Dialogue to Strengthen Democratic Culture – AllAfrica.com

$
0
0
opinion

Ethiopian political parties, taking part in the ongoing national dialogue, hoped that the initiative the ruling party taken to have a political negotiation and dialogue could widen the political space and strengthen the country’s democratic culture.

Representatives of competent political parties, who opted to have dialogues and negotiations with the ruling party without any outside moderator, told The Ethiopian Herald that the accord is one step forward in building participatory democracy and political pluralism in the country.

According to Head of Party’s Affairs of the Ethiopian New Generation Party, Alemayehu Deneke, the ruling party has taken the initiative and made a national call to have dialogues with all opposition political parties in connection to political, economic and social affairs of the country.

The ruling party opens the stage for 21 political parties to bring their interests on how the negotiation would be, he said, adding that “we have forwarded our interest based on our own perspective and the next step will be taking part in the coming dialogues.”

In fact, EPRDF opened a room to opposition political parties to sit for the negotiations either in coalition, special dealing or in group with those of the same interests, he added.

Previously, there were complaints in connection with lack of transparency and absence of open discussion between the ruling party and other political parties about elections and other national agendas that led to misunderstandings, he emphasized .

He added: “Some members of our party have been detained. That was due to the problems in the ruling party in creating such transparency and dialogue on election conducts. However, taking lessons from its past experiences, the ruling party is now willing to have discussion with all political parties, which is a good step to develop multiparty democracy.”

“The dialogue that we held so far were democratic. We believe that this negotiation will create good atmosphere to improve our regulations that would bear fruits to strengthen democratic situations and enhance the political space. We don’t want to continue as usual but to be actors of democracy and development in the country,” Alemayohu underlined.

President of All Ethiopian National Movement Mesafint Shiferaw for his part said it is time for all political parties to come together and discuss every problem the nation face and set solutions together, which the country lacks so far.

Despite the need of the country and the people for peaceful negotiations and dialogue among political parties, a few parties have come up with the title of leading negotiator, which is insignificant at this juncture when the ruling party determined to have open dialogues voiding its former political exclusion, Mesafint said.

“The consultation will bring improvements in the structure of the national electoral board, the electoral codes and in the systemic political settings in controlling all seats in the parliament.”

The past discussions on procedure and negotiator were not as such important to take such a long time but that was due to the misunderstanding among the political parties, Mesafint said, adding that the parties invited to the dialogue are all legitimate. “So, why do we need to have external moderator. An outsider may be needed to negotiate guerrilla fighters or insurgent warriors to come to peaceful negotiations.”

EPRDF Office Head Shiferaw Shigute also seconded Mesafint’s argument. He said: “The forum is equal for all legitimate political parties and we can negotiate freely without an outside moderator as we are brothers of the same destiny with different agendas.”

Ethiopian Federal Democratic Forum (MEDREK) Chairperson Prof. Beyene Petros admitted the case that his party needs to get the position of leading negotiator in the national dialogue for the party has experiences in this regard which he said even caused the changing of laws and regulations. MEDREK will not be taking part in the forums other than on special issues with the ruling party, he said.

However, Alemayohu said: “Some parties had left the political consultation other than the two forums in the initial time. No one obliged them to leave out. They leave due to their egoism. Among the 21 political parties invited, no party would either be a leader or a follower.”

Alemayehu further went on to say that the affairs of New Generation Party could not be the affairs of MEDREK or Blue Party and the reciprocity. As to him, that is not expected from parties working for the promotion of democracy.

It is obvious that tolerance is so important among political parties to enhance democracy in developing countries like Ethiopia.

Professor of Sustainable Economic Development at Dominican University Asayehgn Desta for his part emphasized that Ethiopia needs a multiparty democracy to end the crushing impact of corruption and ensure democracy.

In an article he published in The Conversation, he emphasized that certain changes need to be made to fight corruption. Civic organizations, alternative parties and opposition groups need to be involved in political dialogues.

It is a crystal clear that the already started political parties national dialogue would widen political space, promote democracy and strengthen multiparty system in the country, as Prof. Asayehgn Argued.

Political parties should further strengthen their culture of solving problems through dialogues and negotiations; thereby, strengthening the federal and multiparty system that gives an equal playing field to all citizens.

NEWS ANALYSIS

አዲስ አበባ በቴዲ አዲስ አልበም እየተነፈሰች ነው (ዋዜማ)

$
0
0

በሺ የሚቆጠሩ ሊስትሮዎች በቴዲ ምክንያት ሥራ ቀይረዋል

ዋዜማ ራዲዮ-ዛሬ እጅግ ማልደው የተነሱና የቴዲን አዲስ አልበም በጀርባቸው ያዘሉ በርካታ ወጣቶች በመላው አዲስ አበባ በሥራ ተጠምደዋል፡፡

ሊስትሮዎች ብቻ አይደሉም ሥራ የቀየሩት፡፡ የመንገድ ላይ ፓርኪንግ  ሠራተኞች፣ የሞባይል ካርድ ቸርቻሪዎች፣ ጋዜጣ አዙዋሪዎች፣ ማስቲካ አዝዋሪዎች፣ ዝርዝር ሳንቲም አቅራቢዎች በበርካታ ቁጥር ሲዲውን በመሸጥ ለጊዜው መደበኛ ሥራቸውን አቁመዋል፡፡

አራት ኪሎ ከማለዳው 12፡30 ጀምሮ ሞንታርቦ የተጫነ ነጭ ሚኒባስ መኪና በርካታ ሲዲ በመሸጥ ላይ ነበር ፣በመኪናው ዙርያ የገበያ ግርግር በመፈጠሩ ጧት ላይ መኪናው በፖሊሶች እንዲንቀሳቀስ ተደርጓል ብለዋል የዐይን እማኞች፡፡

በርካታ መጽሐፍ አዝዋሪዎችም በዚህ ገበያ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሆነ የዋዜማ ዘጋቢዎች በተዘዋወሩባቸው ሰፈሮች ለመታዘብ ችለዋል፡፡ ካዛንቺስ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ አካባቢ አንድ ወጣት በድምጽ ማጉያ እየታገዘ ‹‹ የቴዲሻን  ምርጥ ሥራዎች በአምሳ አምሳ ብር፣ አልሰማንም አላየንም እንዳትሉ…›› በሚል ሰፊ ገበያ እንዳገኘ ማየት ችለናል፡፡ መገናኛ አደባባይ፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ብሔራዊና ስታዲየም ‹‹ቴዲን በ50 ብር›› የሚሉ ወጣቶች በፌስታል በርካታ ሲዲ ይዘው ሲሸጡ ይታያሉ፡፡

በከተማዋ ዉስጥ የሚዘዋወሩ አብዛኛዎቹ ታክሲዎች የቴዲን ሙዚቃ በማጫወት ላይ እንደነበሩ መታዘብ ችለናል፡፡ ከጀሞ ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ሦስት ታክሲ ይዛ እንደመጣች ለሪፖርተራችን የተናገረች ወጣት እስካሁን በገባችባቸው ሁሉም ታክሲዎች  አዲሱ የቴዲ ሙዚቃ እየተቀነቀነ እንደነበር ምስክርነቷን ሰጥታለች፡፡

አንድ የጥበብ ሥራ በአንድ ከተማ በዚህን ያህል ጉጉት ሲሸጥ ስመለከት በኔ እድሜ የመጀመርዬ ነው ያለ የገርጂ ኮንዶምንየም ነዋሪ በተንቀሳቀሰበት ሁሉ ሰዎች ሲዲውን ይዘው መመልከቱ እጅግ እንዳስገረመው አልሸሸገም፡፡ ‹‹ከጧት እስከአሁን ብዙ ቦታ ተዘዋውሪያለሁ፤ ሰው አዲስ ነገር እንደተራበ በግልጽ ማየት ትችላለህ›› ሲል ሐሳቡን ያክላል፡፡

ትንናት ማምሻውን ለዋና ዋና ክልል አከፋፋዮች እንደደረሰ የተነገረው የቴዲ አዲስ ሥራ ዛሬ ረቡዕ በመላ አዲስ አበባ ሲከፋፈል የዋጋ ተመኑ ከ50 ብር እስከ 120 ብር ነበር፡፡ ማልደው የተነሱ አዝዋሪዎች መታገስ ላልቻሉ የሙዚቀኛው አድናቂዎች ሲዲሰው ከ100 ብር ጀምሮ በመሸጥ ጠቀም ያለ ትርፍ ማግኘታቸውን ይናገራሉ፡፡

‹‹እኔ ተከራክሬ 70 ብር ነው የሸጡልኝ›› ያለች አንዲት በፒያሳ መብራት ኃይል አፓርትመንት የምትኖር ወጣት ‹‹ለቴዲ ምንም ነገር ብከፍል አይቆጨኝም›› ትላለች፡፡ የሲዲ የማከፋፈያ ዋጋ በተለምዶ ከ15-20 ብር ሲሆን የቴዲ አልበም ስለምን በተጋነነ ዋጋ እንደቀረበ ማወቅ አልተቻለም፡፡ ምናልባት ገበያው እየተረጋጋ ሲመጣ እስከ የሲዲው ዋጋ ወደ 30 ብር ሊወርድ  እንደሚችል ተነግሯል፡፡ በድሬዳዋ፣ በሐረር እና ሌሎች ሲዲው በደረሰባቸው ከተሞች ሙሉ ግጥሙ ያለባቸው ሲዲዎች ከመቶ ብር ጀምሮ እየተሸጠ እንደሆነ ዘጋቢዎቻችን በስልክ ማጣራት ችለዋል፡፡

እስከአሁን ባለው ሁኔታ በዋና ዋና የከተማዋ መስቀለኛ መንገዶች በርካታ ታዳጊዎች ለአሽከርካሪዎች ሲዲዉን እየሸጡ ሲሆን የዋጋ ተመናቸው 50 ብር ብቻ ነው፡፡ ኾኖም ከከተማ ራቅ ባሉ ሰፈሮች ሲዲው እስከ 120 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ለመታዘብ ችለናል፡፡

ቡቲኮች፣ ካፌዎች፣ የሕዝብ ተሸከርካሪዎች፣ የቤት መኪኖች እንዲሁም ኤፍ ኤም ጣቢያዎች የቴዲን አዲስ አልበም እያጫወቱ ሲሆን አዲስ አበባ ለዛሬ ከቴዲ ድምጽ ዉጭ መስማት የምትፈልገው ነገር የሌለ አስመስሎባታል፡፡

The post አዲስ አበባ በቴዲ አዲስ አልበም እየተነፈሰች ነው (ዋዜማ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Ethiopia: Political Parties’ Dialogue to Strengthen Democratic Culture – AllAfrica.com

$
0
0
opinion

Ethiopian political parties, taking part in the ongoing national dialogue, hoped that the initiative the ruling party taken to have a political negotiation and dialogue could widen the political space and strengthen the country’s democratic culture.

Representatives of competent political parties, who opted to have dialogues and negotiations with the ruling party without any outside moderator, told The Ethiopian Herald that the accord is one step forward in building participatory democracy and political pluralism in the country.

According to Head of Party’s Affairs of the Ethiopian New Generation Party, Alemayehu Deneke, the ruling party has taken the initiative and made a national call to have dialogues with all opposition political parties in connection to political, economic and social affairs of the country.

The ruling party opens the stage for 21 political parties to bring their interests on how the negotiation would be, he said, adding that “we have forwarded our interest based on our own perspective and the next step will be taking part in the coming dialogues.”

In fact, EPRDF opened a room to opposition political parties to sit for the negotiations either in coalition, special dealing or in group with those of the same interests, he added.

Previously, there were complaints in connection with lack of transparency and absence of open discussion between the ruling party and other political parties about elections and other national agendas that led to misunderstandings, he emphasized .

He added: “Some members of our party have been detained. That was due to the problems in the ruling party in creating such transparency and dialogue on election conducts. However, taking lessons from its past experiences, the ruling party is now willing to have discussion with all political parties, which is a good step to develop multiparty democracy.”

“The dialogue that we held so far were democratic. We believe that this negotiation will create good atmosphere to improve our regulations that would bear fruits to strengthen democratic situations and enhance the political space. We don’t want to continue as usual but to be actors of democracy and development in the country,” Alemayohu underlined.

President of All Ethiopian National Movement Mesafint Shiferaw for his part said it is time for all political parties to come together and discuss every problem the nation face and set solutions together, which the country lacks so far.

Despite the need of the country and the people for peaceful negotiations and dialogue among political parties, a few parties have come up with the title of leading negotiator, which is insignificant at this juncture when the ruling party determined to have open dialogues voiding its former political exclusion, Mesafint said.

“The consultation will bring improvements in the structure of the national electoral board, the electoral codes and in the systemic political settings in controlling all seats in the parliament.”

The past discussions on procedure and negotiator were not as such important to take such a long time but that was due to the misunderstanding among the political parties, Mesafint said, adding that the parties invited to the dialogue are all legitimate. “So, why do we need to have external moderator. An outsider may be needed to negotiate guerrilla fighters or insurgent warriors to come to peaceful negotiations.”

EPRDF Office Head Shiferaw Shigute also seconded Mesafint’s argument. He said: “The forum is equal for all legitimate political parties and we can negotiate freely without an outside moderator as we are brothers of the same destiny with different agendas.”

Ethiopian Federal Democratic Forum (MEDREK) Chairperson Prof. Beyene Petros admitted the case that his party needs to get the position of leading negotiator in the national dialogue for the party has experiences in this regard which he said even caused the changing of laws and regulations. MEDREK will not be taking part in the forums other than on special issues with the ruling party, he said.

However, Alemayohu said: “Some parties had left the political consultation other than the two forums in the initial time. No one obliged them to leave out. They leave due to their egoism. Among the 21 political parties invited, no party would either be a leader or a follower.”

Alemayehu further went on to say that the affairs of New Generation Party could not be the affairs of MEDREK or Blue Party and the reciprocity. As to him, that is not expected from parties working for the promotion of democracy.

It is obvious that tolerance is so important among political parties to enhance democracy in developing countries like Ethiopia.

Professor of Sustainable Economic Development at Dominican University Asayehgn Desta for his part emphasized that Ethiopia needs a multiparty democracy to end the crushing impact of corruption and ensure democracy.

In an article he published in The Conversation, he emphasized that certain changes need to be made to fight corruption. Civic organizations, alternative parties and opposition groups need to be involved in political dialogues.

It is a crystal clear that the already started political parties national dialogue would widen political space, promote democracy and strengthen multiparty system in the country, as Prof. Asayehgn Argued.

Political parties should further strengthen their culture of solving problems through dialogues and negotiations; thereby, strengthening the federal and multiparty system that gives an equal playing field to all citizens.

NEWS ANALYSIS

የነፃነት ኃይሎች ጥቃት ከዳር ወደ መሀል! (በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ)

$
0
0
  • ጎንደርና ባህርዳር ከተማ ውስጥ በሁለት ወር ብቻ 9 የቦምብ ፍንዳታ ደርሷል!
  • “ህወሃት የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያን ክፍል የበቀል መወጫ እያደረገው ነው”፤ ነዋሪዎች

ላይቆም የተቀጣጠለው የሰሜን ምዕራብ ብረት አከል ህዝባዊ አመፅ የትግል ስልቱን እየቀያየረ ባህርዳር ደርሷል፡፡ አስር ወራትን ያስቆጠረው የነፃነት ኃይሎች እንቅስቃሴ ከገጠር ሽምቅ ውጊያ ወደ ከተማ የደፈጣ ቦምብ ጥቃት ተሻግሯል፡፡ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ዘጠኝ የቦምብ ፍንዳታ ደርሷል፡፡ ድርጊቱ ሰላም የነሳው ህወሃት “የአማራ ክልልን የበቀል መወጫ እያደረገው” መሆኑ ይነገራል፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ ሙሉ የደህንነት አቅሙንና የበዛ የመከላከያ ኃይሉን አማራ ክልል ላይ ቢያደርግም የነፃነት ኃይሎች ተከታታይነት ያለው ጥቃት ከመፈፀም ያገዳቸው ኃይል የሌለ መሆኑ እየታየ ነው፡፡ የመጀመሪያዉ ዙር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከመጠናቀቁ ከአንድ ወር በፊት መጋቢት የመጀመሪያ ሳምንት እስከ ሁለተኛዉ ዙር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመጀመሪያ ወር ሚያዚያ አራተኛ ሳምንት ድረስ ጎንደር ከተማ ውስጥ ሰባት፤ ባህርዳር ከተማ ሁለት በድምሩ ዘጠኝ የቦምብ ፍንዳታዎች ደርሰዋል፡፡

የቦምብ ጥቃቶቹ ያነጣጠሩት በአገዛዙ ማህበራዊ መሰረቶች (ባለስልጣናቱ በእጅ አዙር የሚነግዱባቸው ሆቴሎች፣ የደህንነቱ አባሪ ተባባሪ የሆኑ ስውር ነጭ ለባሾችን ቤት፣ የአገዛዙ ተሽከርካሪዎች፣ . . .) ላይ መሆኑ ደግሞ የነፃነት ኃይሎችን መዋቅራዊ ጥንካሬ አጉልቶ ያሳየ ተብሎለታል፡፡ በሁለት ወር ውስጥ ብቻ ዘጠኝ የቦምብ ጥቃት ባስተናገዱት ሁለቱ ከተሞች የወጣቶች የጅምላ እስር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ከሁለቱም ከተሞች የሰበሰብናቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት “ህወሓት ክልሉን የቂም በቀል መወጫ እያደረገው ይገኛል” ሲሉ ነዋሪዎች ህወሓትን ይወነጅላሉ፡፡ “ከእያንዳንዱ የቦምብ ጥቃት በኋላ ፍንዳታው የደረሰበት ከተማ በተኩስ እሩምታ ሲታመስ ያድራል” የሚሉት ነዋሪዎች “በሌሊት ወጣቶችን ከመኖሪያ ቤታቸው አፍሶ መውሰድ የተለመደ ድርጊት ሆኗል” ይላሉ፡፡

በአንፃሩ በየጊዜው እየደረሱ ባሉ የቦምብ ጥቃቶች የአገዛዙ ልሳን በሆኑ የሚዲያ ውጤቶች መግለጫዎች ሲሰጡ ባይሰማም ከጉዳዩ አሳሳቢነት የተነሳ የአሜሪካ መንግሥት አዲስ አበባ ባለው ኤምባሲው በኩል ዜጎቹ ወደ ባህርዳርና ጎንደር እንዳይጓዙ በይፋ ክልከላ ማድረጉን አሳውቋል፡፡ በየጊዜው እየደረሱ ባሉ የቦምብ ፍንዳታዎችና የሽምቅ ውጊያዎች የተነሳ በሰሜን ምዕራብ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ቁሟል፡፡ ለዕለት ፍጆታነት ከሚውሉ ሸቀጣሸቀጦች ውጪ ይህ ነው የሚባል የንግድ እንቅስቃሴ አለመኖሩ ደግሞ አካባቢው በኢኮኖሚ እንዲደቅ አድርጎታል፡፡

በቀደመው አመፅ የፈራረሰበትን መዋቅር በድህረ-“ተሃድሶ” እንቅስቃሴው መልሶ ማቋቋም የተሳነው ብአዴን የመካከለኛ አመራሩ ሽሽት መቆሚያ አጥቷል፡፡ የሰሜን ምዕራብ የመረጃ ምንጮቻችን ከእያንዳንዱ የቦምብ ጥቃት ጀርባ መዋቅራዊ ሽፋን እንዳለዉ ይጠቁማሉ፡፡

“በርግጥም በእስካሁኑ የቦምብ ጥቃቶች ተጠያቂ የተደረገ አካል አለመኖሩ የነፃነት ኃይሎች መዋቅራዊ ድጋፍ እንዳላቸው አስረጅ ምሳሌ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል” የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ፡፡ ጎንደር ውስጥ በሁለት ወራት ከደረሱት የቦምብ ጥቃቶች ውስጥ አምስቱ ጥቃቶች በኤፍ ዋን (F one) ቦምብ የተፈፀሙ ሲሆን፤ በተመሳሳይ መልኩ ከሦስት ቀን በፊት ባህርዳር ከተማ ውስጥ በሙዚቃ ድግስ ላይ የደረሰው የቦምብ ጥቃት በፍንዳታና በማፈንጠር አቅሙ አቻ የሌለው እስራኤል ሰራሹ ኤፍ ዋን (F one) ቦምብ መሆኑን የመረጃ ምንጮቻችን ዘገባ ያመለክታል፡፡

ዳሽን ቢራ ከገበያ ድርቀት እስከ ቦምብ ጥቃት!

ከህዝባዊ አመፁ መቀስቀስ ጋር ተያይዞ ዳሽን ቢራ ክፉኛ በገበያ ድርቅ መመታቱ ይታወቃል፡፡ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ከገጠመው የገበያ ድርቀት ለማገገም “ባለ አገሩ” በሚል የቢራ ዓይነት (ብራንድ) ገበያውን ተቀላቅሏል፡፡ አዲሱን ቢራ ለማስተዋወቅ ያለመ የሙዚቃ ድግስ በባህርዳር ከተማ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና ሲሉ የከረሙት የፋብሪካው ከፍተኛ አመራሮች፤ በነፃነት ኃይሎች የቦምብ ጥቃት የሙዚቃ ድግሱ ተቋርጧል፡፡

እንደ ጎልጉል የአካባቢው የመረጃ ምንጮች ዳግማዊ ትንሳኤ ላይ ሊካሄድ የታሰበው ይሄው የሙዚቃ ድግስ በአርቲስቶች የፕሮግራም መጣበብ ወደ ሚያዚያ 21/2009 ዓ.ም. ሊሸጋገር ችሏል፡፡ “ክብር ለባላገሩ” በሚለው የሙዚቃ ድግስ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ እንዲገኝ ተጋብዞ የነበረ ቢሆንም አርቲስቱ “ከህዝብ ጋር መቀያየም አልፈልግም!” በሚል ፍቃደኛ ሊሆን እንዳልቻለ የመረጃ ምንጮቻችን ዘገባ ያመለክታል፡፡

በዕለቱ የሙዚቃ ድግስ ተገኝተው የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን ለመጫወት ከተስማሙት ታዋቂ አርቲስቶች ውስጥ ሙሐሙድ አህመድ፣ ኩኩ ሰብስቤና አረጋኽኝ ወራሽ ይገኙበታል፡፡ በማህበራዊ ድረ-ገፆች ይህን የሙዚቃ ድግስ በተመለከተ ሊካሄድ እንደማይገባ የሚያስጠነቅቁ ማስጠንቀቂያዎች በተደጋጋሚ ሲስተጋቡ እንደነበር ይታወሳል፡፡ አርቲስት ሙሐሙድ አህመድ የተቃውሞውን መካረር ታዝቦ አርብ መጋቢት 20/2009 ዓ.ም. ለኮንሰርቱ አዘጋጆች በሙዚቃ ድግሱ ላይ እንደማይገኝ ማሳወቁን የባህርዳር ምንጮቻችን ይጠቁማሉ፡፡

በተመሳሳይ መልኩ አርቲስት አረጋኽኝ ወራሽ ቅዳሜ ሚያዚያ 21/2009 ዓ.ም. በጥዋት 1፡00 ሰዓት የአውሮፕላን በረራ ወደ ባህርዳር የተጓዘ ቢሆንም የብአዴኑ የሙዚቃ ድግስ ህዝባዊ ተቀባይነት የራቀው የከፍተኛ አመራሩ ተፅዕኖ መሆኑን ሲረዳ በሙዚቃ ድግሱ ላይ መገኘት እንደማይችል አሳውቆ በ7፡00 ሰዓቱ የአውሮፕላን በረራ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል፡፡ ይህን መረጃ በተመለከተ የባላገሩ ፕሮዳክሽን ባለቤት አርቲስት አብርሃም ወልዴ ከ “ባለ አገሩ ቢራ” ጋር የተያያዘ የኪነ ጥበብ ሥራ እንዳልሰራና ፕሮዳክሽኑ ምንም አይነት የሥራ ግንኙነት እንደሌለው በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ባሳወቀበት መረጃ የአርቲስት አረጋኽኝ ወራሽን ጉዳይም አሳውቋል፡፡

በአንፃሩ አርቲስት ኩኩ ሰብስቤ በሙዚቃ ድግሱ ላይ ለመጫወት በመወሰኗ ዕለተ ቅዳሜ ሚያዚያ 21/2009 ዓ.ም. በባህርዳር ከተማ የወጣቶች ማዕከል አዳራሽ ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ መካሄድ በጀመረው የሙዚቃ ድግስ ተገኝታ ነበር፡፡

“ክብር ለባለ አገሩ” የሚለውን የሙዚቃ ድግስ በተመለከተ የሚኮንኑና የሙዚቃ ድግሱ እንዳይካሄድ የሚያስጠነቅቁ ጥብቅ መግለጫዎች በማህበራዊ ድረ ገፆች ሲተላለፍ የነበረ በመሆኑ የቅዳሜው የሙዚቃ ድግስ በታጠቁ ኃይሎች፣ በዳሽን ቢራ የሽያጭና ማስታወቂያ ሰራተኞች እና በካድሬዎች የተሞላ ነበር የሚሉን የባህርዳር ምንጮቻችን “ኩኩ ሰብስቤ ወደ መድረክ ወጥታ ‹ቻልኩበት› የሚለውን የሙዚቃ ሥራዋን እያቀረበች በነበረበት ቅፅበት ከተለያየ አቅጣጫ ሁለት የቦምብ ጥቃቶች ተፈፀሙ” ይላሉ፡፡ እንደ መረጃ ምንጮቻችን ዘገባ በጥቃቱ ሁለት የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሲገደሉ፣ 13 በጽኑ ቆስለዋል፡፡ 31 የሚሆኑ ሲቪልና የታጠቁ ኃይሎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ከቦምብ ጥቃቱ በኋላ አርቲስት ኩኩ ሰብስቤ ወደ ፈለገ-ህይወት ሆስፒታል ተወስዳ ህክምና የተደረገላት መሆኑን የመረጃ አቀባዮቻችን ጠቁመዋል፡፡ አርቲስቷ በድንጋጤ ራሷን ከመሳቷ ውጪ ይህ ነው የሚባል ጉዳት አልደረሰባትም፡፡ ከዚሁ የቦምብ ጥቃት ጋር ተያይዞ ባህርዳር ከተማ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በተኩስ እሩምታ ስትታመስ ማደሯን ከወደ ባህርዳር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በከተማዋ የጅምላ እስር ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአገዛዙ ማህበራዊ መሰረት የነበሩት አርቲስቶች በህዝባዊ ጫና ከአገዛዙ ጋር የነበራቸውን መሞዳሞድ እያቆሙ ይገኛሉ፡፡ አገዛዙ በሚያዘጋጃቸው የሙዚቃ ድግሶች መታደም ከህዝብ ጋር በቀጥታ መላተም መሆኑ እየገባቸው የመጣ በመሆኑ የሚቀርብላቸውን ግብዣ ሲገፉ እየታየ ነው፡፡ ለዚህ ምሳሌ መሆን የሚችሉት አርቲስት መሐሙድ አህመድ፣ ማዲንጎ አፈወርቅና አረጋኽኝ ወራሽ፣ . . . ተጠቃሽ ናቸው፡፡ አንዳንድ አድርባይ አርቲስቶች የህዝብን የተቃውሞ ድምፅ አለመስማት የሚያስከትለውን መዐት ዛሬም ድረስ ከከባድ ድንጋጤዋ ያላገገመችውን አርቲስት ኩኩ ሰብስቤን ጠይቆ መረዳት ይችላሉ ሲሉ አስተያየታቸዉን የሰጡን የባህርዳር የመረጃ ምንጮቻችን፤ የነጻነት ኃይሎች ጥቃት “ትግሉ አይቆምም” የሚል መልዕክት እንዳለዉ ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር አያይዘዉ በባህርዳሩ የሙዚቃ ድግስ ላይ የደረሰው የቦምብ ጥቃት ባልደረቀ የንፁሃን ደም ላይ ቁሞ መዝፈን ለሚያስደስታቸው ለሌሎች አርቲስቶች ጥሩ ትምህርት ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ “ከሁሉ በላይ የባህርዳሩ የቦምብ ጥቃት የነፃነት ኃይሎች ጥቃት ከዳር ወደ መሀል የመሻገሩ ብስራት ተደርጎ ሊታይ ይችላል” በማለት ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ “አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሰሜን ምዕራብና አካባቢው የቦምብ ቀለበት መፍታት ሽንኩርት የመላጥ ያህል ቀሏል” ሲሉ እየታየ ያለዉን ተጋድሎ በተመለከተ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በተከታታይ እንዳቀረባቸዉ የአካባቢዉ ዘገባዎችና አሁን በተጨባጭ በአገዛዙ ላይ እየደረሱ ካሉ ጥቃቶች አኳያ በጊዜ ሂደት የአገዛዙ ማህበራዊ መሰረቶች እየተሸረሸሩ የነፃነት ኃይሎች መዋቅራዊ ድጋፍ እየጠነከረ መምጣቱን መመስከር ይቻላል፡፡

እስካሁን በተካሄዱት ጥቃቶች በይፋ ኃላፊነት የወሰዱ ባይኖሩም ካካባቢዎቹ የሰበሰብነው መረጃ እንደሚያመላክተው እንደ ብረት አልባው ሕዝባዊ ተቃውሞ ይህኛውም ሕዝባዊነት ያለውና በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ የተማረሩ የሚወስዱት ርምጃ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል፡፡ (የመግቢያው ፎቶው ለማሳያ የቀረበ ሲሆን የተገኘው እዚህ ላይ ነው)

በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

The post የነፃነት ኃይሎች ጥቃት ከዳር ወደ መሀል! (በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ቴዲ ለምን ይወደዳል? – ኢትዮጵያዊነት በአንጻረ ጎሰኝነት ( ዶር ፍቅሬ ቶሎሳ)

$
0
0

“ቴዎድሮስ ካሳሁንን እና ሙዚቃውን ለምን ህዝብ ይወዳቸዋል?” ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ “እሱ እና ሙዚቃው ኢትዮጵያዊነትን ስለሚዘምሩ ነው፤” የሚል ነው። በሌላ አነጋገር፥ ጎሰኝነትን ስለማያራምዱ ነው።

ባለፉት 48 ዐመታት በተማሪዎች ቆስቋሽነት የተጀመረው ጎሰኝነት ባለፉት 25 ዐመታት እንደ ሰደድ እሳት ተዛምቶ ፥ በኢትዮጵያዊነት ላይ የማያቋርጥ ዘመቻ አካሂዶ፥ ኢትዮጵያዊነት ጨርሶ አለማክተሙ እና ማንሰራራቱ የሚያስገርም ነው። ኢትዮጵያዊነትን ለሚጠሉ ደግሞ አስደንጋጭ መርዶ ነው። እውነት ይህን ያህል ህዝብ ጎሰኝነት አንገፈገፈኝ ብሎ ኢትዮጵያዊነትን ናፍቋልን? መልሱ አዎንታዊ ይመስላል።

በእርግጥም ኢትዮጵያን ሊያድናት የሚችለው ኢዮዬጵያዊነት ነው። ለመሆኑ “ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ምንድነው? ኢትዮጽያስ ለምን ኢትዮጵያ ተባለች? ኢትዮጵያ ማለት በሱባ (ከግእዝ በፊት የነበረ የጥንት ወገኖቻችን ቋንቋ) ብጫ ወርቅ ስጦታ (ለእግዚአብሄር) ማለት ነው። የዛሬ 4000 ዐመት የኖረው የንጉሥ ንጉሥ የካህን ካህን በመሆን ዐለማዊና መለኮታዊ ማእረግ የነበረው አባታችን ኢትዮጵ በዚህ ስም ይጠራ ስለ ነበር ሀሪረቱን ኢትዮጵያ አሰኛት። የኢትዮጵያን ስልጣኔ ጆቹቸ በመላው አፍሪካ በማዳረሳቸው እስከዛሬ 600 ዐመት ድረስ መላው አፍሪካ ኢትዮጵያ ይባል ነበር። አሁንም በኢትይጵያውያን አፋሮቻችን ምክንያት አፍሪካ ይባላል። ዞሮ ሮሬ ከእኛ ስም አልወጣም።

ኢትዮጵ 10 ወንዶች ልጆች ወልዶ 10ስሩ ተባዝተው ዛሬ ሁላችንም ከነሱ ተገኘን። ስለዚህ በእያንዳንዳችን ደም ስር ውስጥ የኡዮጵ ደም እየፈሰሰ ሁላችንንም እዛምዶናል ማለት ነው። ትውልደ ኢትዮጵያ የሆንን ሰዎች ሁሉ ወደድንም ጠላንም አመንን አላመንም፣ እውስጣችን የእዚህ ትልቅ ሰው እና የክብርት ሚስቱ የንግሥት እቁዮያጳግዮን ደም ይፈስሳል። ይህም እጅግ የሚያኮራ እንጂ የሚያሳፍር አይደለም። ይህን የማይቀበል ክቡር። እና ግዙፍ የሆነውን ማንነቱን የማያውቅ ብቻ ነው። ወይም በፓለቲካ ልቦናውን የታወረ ነው።

ጎሳስ ምንድነው? ጎሳ አንድ ቋንቋ። የሚየናገሩ ሰዎች ማለት ነው። ዘርፉ ከቋንቋ እንጂ ከዘር አይደለም። የአማራ ወይም የኦሮሞ ጎሳ ማለት አማርኛ ወይም ኦሮምኛ የሚናገር ሰው ማለት እንጂ ዘሩን አይጠቁምም። ቋንቋ የመግባቢያ መሣሪያ ብቻ ነው እንጂ በደም የሚያገናኝ አይደለም። በደም፥ ያው ከፍ ብዬ እንዳልኩት የኢትዮጵ ልጆች ነን። ኢትዮጵያ ውስጥ 82 ቋንቋዎች ተናጋሪዎች አሉ። በዘራቸው ግን አንድ ናቸው። የመነጩት ከኢትዮጵ ደም ነውና። ስለዚህ ሁሉንም ትውልደ ኢዮያጵያውያንን በስጋ የሚመያዛምዳቸው ኢዮያጵ ነው እጂጀ ቋንቋው አይደለም። የዚህን ዝርዝር ለማየት “የኦሮሞ እና አማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” የተሰኘውን መጽሀፌን መመልከት ይጠቅማል።

እንግዲህ ኢትዮጵያዊነትን በአሁኑ ሰዐት ሰው ሁሉ የፈለገው ውስጡ ያለው ደመነፍስ ኢዮጵያዊነቱን ስለ አረጋገጠለትና ጎሰኝነት ዋጋቢስ መሆኑን ስለተገነዘበ ነው። ከአሁን በኋላ ኢዮዮጵያዊነት ለምልሞ ያብባል እንጂ ጠውልጎ አይደርቅም።

The post ቴዲ ለምን ይወደዳል? – ኢትዮጵያዊነት በአንጻረ ጎሰኝነት ( ዶር ፍቅሬ ቶሎሳ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አንድ ሀገር ከብዙ አመታት በፊት እቆመበት ቦታ ላይ አሁንም እንዴት ሊቆም ይችላል? – ሸንቁጥ አየለ

$
0
0

ከዛሬ ሶስት እና አራት አመታት በፊት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥቁር ሰዉ አልበሙን ሲያወጣ በማህበራዊ ሚዲያዉ እና በግል ጋዜጦች ላይ ኢትዮጵያዉያን ከፍተኛ ጭቅጭቅ ዉስጥ መዉደቃችን ይታወሳል:: ዛሬም ቴዲ አፍሮ አዲስ ካሴት ሲያወጣ ኢትዮጵያዉያን እዚያዉ እነበርንበት ጭቅጭቅ ማጥ ዉስጥ መልሰን ተዘፍቀናል::ከዛሬ ሶስት እና አራት አመታት በፊት እነበረዉ ጭቅጭቅ ዉስጥ እኔም ተሳታፊ ነበርኩና በግል ጋዜጦች እና በማህበራዊ ሚዲያዉ ላይ የጻፍኩትን ጽሁፍ አሁን መለስ ብዬ ሳነበዉ በጣም ገረመኝ::አሁን ለተነሳዉ ጭቅጭቅ የጻፍኩት ይመስላል::

አንድ ሀገር ከሶስት እና አራት አመታት በፊት እቆመበት ቦታ ላይ እንዴት አሁንም ሊቆም ይችላል? እዚያዉ ላይ መቸከል? ለነገሩ ተገረም ብሎኝ እንጅ ኢትዮጵያን ወያኔ 26 አመታት ሙሉ ቸክሏት ያለዉ አንድ ቦታ ላይ ነዉ::

አለም በፈጣን ግስጋሴ በቴክኖሎጅ ለዉጥ ዉስጥ በዬ ደቂቃዉ ይፋጠናል::ሌላዉ ቀርቶ በወራት እና በሳምንታት ዉስጥ ሊታመኑ የማይችሉ የቴክኖሎጅ ለዉጦች ይከሰታሉ::የአለም ማህበረሰብ እሩጫዉ እና ግስጋሴዉ ከነዚህ ለዉጦች ጋር እራሱን ለማስተካከል ነዉ:: አለም በፈጣን የቴክኖሎጅ ግስጋሴ እየታገዘ ወደ አስገራሚ ብልጽግና እየገሰገሰ ነዉ::

እኛስ ? እኛማ ጉደኞቹ ትናንት ላይ ተቸክለን ላለመስማማት ከፍተኛ ማጥ ዉስጥ ሰጥመናል::እግዚአብሄር እንደ ወያኔ አይነት ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን የሚዘራ ወንበዴን ሀይልን በላያችን ላይ ጉልበት ሰጥቶብን ሀያ ስድስት አመታት ህዝብ በጭቅጭቅ ይናጣል:: ዛሬም አባቶቹን በሚረግም እና አባቶቹ እንዳይረገሙ በሚከላከል ትዉልድ መሃከል ኢትዮጵያ ተቀስፋ ተይዛለች::ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት በሚቃትት እና ኢትዮጵያዊነት እሴቴ ከቶም አይነካም በሚል ትዉልድ መሃከል ሀገሪቱ ተቀስፋ ተይዛለች::

ወያኔም በዚህ መሃል በደናቁርት ልቡ በሚያጠነጥናት ተንኮሉ እየታመነ እግሩን አንፈራጦ ሰይጣናዊ አገዛዙን የሚያስቀጥልበትን ስልት በጥልቀት ከተከፋይ የዉጭ አማካሪዎቹ ጋር ሆኖ ያንሰላስላል:: ለማንኛዉም በቀለም ቀንድ (2006 ዓ.ም በቅፅ 01) ላይ የወጣዉን ጽሁፌን ለተግርሞአችሁ እንዲሆን እንዲሁም እንዴት አሁንም አንድ ቦታ እንደተቸከልን እንድታንሰላስሉበት ብዬ አካፈልኳችሁ::

መልካም ንባብ::

=======================================

ኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት የስነ ጥበብ ማዕከል ሲሆን ለምን ጦር ሰባቂ ይበዛል?:- ቴዲ አፍሮን እንደ ማሳያ

ሸንቁጥ አየለ

—————————————————————————————————————————–

ስነ ጥበብ እንደ ስሙዋ መልኩዋና አገልግሎቱዋ ብዙ ነዉ:: አምባገነኖች ለራሳቸዉ ፍላጎት ይጠመዝዙዋታል:: እንዲያዉም

የሶሻሊስት ርዕዮተ አለም የሚያራምዱ ጥበበኞች እንደሚነግሩን ከሆነ ሶሻሊስታዊ ስነ ጥበብ አለች:: ይህች ስነ ጥበብ ታዲያ ዋና ግቡዋ ሶሻሊዝምን ማራመድ እና ወደ ህዝቡ አዕምሮ ዉስጥ ሶሻሊዝምን ከመክተትም በዘለለ የህዝቡ ስነ ባህሪ በሶሻሊስታዊ መርህ እንዲታነጽ ማድረግ ነዉ:: ብልህ ምዕራባዉያን መንግስታት የሀገራቸዉን እሴት በመላዉ አለም ለማሰራጨት ብሎም የሀገራቸዉን ሀያልነት ለመስበክ ይገለገሉባታል:: የሆሊዉድን የፊልም ስራዎች ማስተዋል በቂ ነዉ:: የሆሊዉድ ፊልሞች ምዕራባዉያን ሲያሸንፉ

ብሎም የእነሱ ባህላዊ እሴት ፍጹም የበላይ መሆኑን ለመላዉ አለም እንደሰበኩ ይኖራሉ::

አንዳንድ ባለ አዕምሮ የስነጥበበ ባለሞያዎች ደግሞ ስነጥበብን የሰዉ ልጆችን እኩልነት ለማራመድ እንደ ቁልፍ መሳሪያነት

ይጠቀሙባታል:: አንዳንድ የዋሆች እንደሚመስላቸዉ የስነ ጥበበ ሞያተኞች ከወገናዊነት የነጹና አቁዋም አልቦ ይመስሉዋቸዋል:: ስነ ጥበበኞች ግን በዚህኛዉም ሆነ በዚያኛዉ ወገን ወይም በራሳቸዉ ማዕከላዊ ዛቢያ ላይ ቢሽከረከሩም ከወገናዊነት እና አንድን ጭብጥ ከማራመድ ነጻና ገለልተኛ መሆን አይችሉም::

በአሁኑ ዘመን ያሉ ኢትዮጵያዊ የስነ ጥበበ ባለሞያዎችን በሶስት ጎራ ከፍለን ልናያቸዉ እንችላለን:: አንደኛ ደረጃ ላይ የሚገኙትና

በርከት ያሉት ያለዉን ስርአት ለማገልገል ብቻ የሚኖሩ ናቸዉ:: ሌላም ስርዓት ቢመጣም መልሰዉ ስርዓቱ እንደሚፈልገዉ

የሚያገለግሉ ናቸዉ:: ምንም አይነት የተለዬ ስርዓት ቢመጣ ትናት ጥቁር ያሉትን ዛሬ ነጭ ብለዉ ለማቅረብ አይቸገሩም:: እነሱ

አቁዋም የምትባል ነገር የላቸዉም:: በአንድ ወቅት ስለ አንድ ዘፋኝ አንድ የሀገራችን ፖለቲከኛ ሲጠየቅ የጨመሩባቸዉን ነገር እንደ

ማንቆርቆሪያ ማንቆርቆር ብቻ ነዉ ስራቸዉ እንዳለዉ::

ሁለተኞቹ ቡድኖች ደግሞ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ የጎሳ ብሄረተኝነተ እሴትን ማዕከላቸዉ ያደረጉ ናቸዉ:: ፈጹም የራሳቸዉ አቁዋም

አላቸዉ:: ኢትዮጵያ የጋራ እሴት አላት ብለዉ አያስቡም/አያምኑም:: ኢትዮጵያ ሀገር ናት ብለዉም አያምኑም:: በርቀት ህልማቸዉ

ኢትዮጵያ ብትፈርስ ደስተኛ ናቸዉ:: ሶስተኞቹ ቡድኖች ደግሞ ኢትዮጵያዊነት እሴትን የስነ ጥበብ ስራቸዉ ማዕከል ያደረጉ ናቸዉ:: በእነዚህ ቡድኖች ህሳቤ ደግሞ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የጋራ ማንነት ያላት ከሰዉ ዘር መነሻ እስከ አሁን የቀጠለች ሳባዊት ኩሻዊት ካማዊት እሴት የተዋሃደባት ብሎም ክርስትና እስልምና አይሁድነት አብሮ ተለዉሶ የወጣባት ኢትዮጵያ አለች:: እነዚህ የስነጥበብ ሀይሎች ሀይለኛ ናቸዉ:: ለያዙት አላማም የማያወላዳ ፍልስፍና አላቸዉ:: ሀገሪቱ መከራ ዉስጥ በወደቀችበት ጊዜና ህዝቡ

በሚደናገርበት ሰዓት ስለ ኢትዮጵያዊነት በማቀንቀን የህዝቡን ህብረት ሲስብኩ ተስተውለዋል:: እንዲህም ይላሉ:: “ቢለያይም

ቁዋንቁዋ አንድ ነዉ ደማችን ..” ብለዉ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ሳያፍሩና ሳይሸማቀቁ ያቀነቅናሉ::

ስለ ሌሎቹ ሌላ ጊዜ እመለስበት ይሆናል:: ለዛሬ ግን ቴዲ አፍሮ ላይ ማተኮር ፈልጌአለሁ:: ምክንያቴ ደግሞ ቴዲ አፍሮ የሰሞኑ የጭብጨባ ወጀብ ብቻ ሳይሆን የዱላም መዓትም

እያረፈበት ያለ የጥበብ ሰዉ በመሆኑ ነዉ:: ቴዲ አለም ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ ሊሳተፍ ሲልም ሆነ አሁን ከኮካ ኮላ ጋር ተጣላ

ሲባል እየተነሳ ያለዉ አቡዋራ ምክንያቱ አንድና አንድ ነዉ:: ቴዎድሮስ ካሳሁን ኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴትን ማዕከሉ አድርጎ መዝፈኑ

ነዉ:: በቴዎድሮስ ካሳሁን የማይናወጥ እምነት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የጋራ ማንነት ያላት ከሰዉ ዘር መነሻ እስከ አሁን የቀጠለች

ሳባዊት ኩሻዊት ካማዊት እሴት የተዋሃደባት ብሎም ክርስትና እስልምና አይሁድነት አብሮ ተለዉሶ የወጣባት ሀገር ነች:: በዘፎኖቹ

የሚሰብከን ይሄን ነዉ::

ጥያቄዉ ግን ቴዲ አፍሮ እንዲህ ስለ ህዝብ ዉህድነት ሲሰብክ ለምን ጦር ሰባቂዎች በዙበት የሚለዉ ነዉ?

ቴዲ አፍሮ የጠለቀ ጭብጥ በቁዋጠሩ ሙዚቃዎቹ እንደሚነግረን ኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት አለዉ:: ይህ የጋራ ኢትዮጵያዊ እሴት

አይሁዱን: እስላም ክርስቲያኑን ያፋቅራል::ይህ የጋራ ኢትዮጵያዊ እሴት ጥንታዊና ስር የሰደድ የጋራ ምድር ያለዉ የጋራ ታሪካዊ

መሰረት ያለዉ ዉህድ ኢትዮጵያዊ ህዝብን አስተሳስሮ አቁሞአል:: ኢትዮጵያዊነት ለቴዲ አፍሮ የጎሳዎች ድምር ሳይሆን

የኢትዮጵያዉያን ማህበረሰብ ዉህደት ነዉ::ይህ ዉህደት ደግሞ ከድምር የበለጠ የጋራ መስተጋብር ነዉ (the whole is greater

than the sum)::

ይህ ማለት ለቴዲ አፍሮ የሀሳብ ማጠንጠኛዉ ብሎም መድረሻ ራዕይዉ ዉህድ የሆነዉ ኢትዮጵያዊ እሴት ነዉ::

ቴዲ ከሙዚቃ በላይ በገዘፈዉ ጭብጡ የሚያስተላልፈዉ የጋራ ኢትዮጵያዊ እሴት መልዕክቱ አንድ ነዉ:: ይሄዉም ህያዉ የሆነ ቆሞ

የሚሄድ እና የሚራመድ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ የተገነባና በዉህደት የተሰራ ኢትዮጵያዊነት ነዉ:: ለዚህ ማሳያዉ የአድዋ

ድልን የገለጸበት የተራቀቀ ዘይቤ ነዉ:: ቴዲ አፍሮ እንደሚተርክልን ያ ድል የዚህ ወይም የዚያ ብሄረሰብ/ማህበረሰብ ድል ሳይሆን

የሁሉም ዉህድ ማህበረሰብ ድል ነዉ:: ኢትዮጵያዊ ማህበረሰቦቹን በጀግኖቻቸዉ ወክሎ ዉህድ ሂደቱን ግን ከድምር በዘለለ

ያቀርበዋል:: ይህን የገለጸዉ በዉህዱ ኢትዮጵያዊነት ዘይቤ ነዉ::

በዚህ የአድዋ ዉህድ ድልም የኢትዮጵያዊነት የጋራ ማንነት ተጠብቆአል:: ከዚህም ዘሎ ቴዲ እንደሚተርክልን የመላዉ የጥቁር ዘር

ቀና ብሎ በማንነቱ እንዳያፍር ዉህዱ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ታሪክ ሰርቶአል:: የአሜሪካዉ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር እንዳሉትም

የአድዋ ድል የለወጠዉ የመላዉን የአዳምን ዘር የታሪክ ፍሰት ነዉ:: በፕሮፌሰሩ ታሪካዊ ትንታኔ መሰረትም የአድዋ ድል የመላዉ

የጥቁር ዘር አዲስ የማንነት ዉልደት ምዕራፍ ነዉ:: ቴዎድሮስ ካሳሁን ከፕሮፌሰሩ ጋር የመከረ ይመስል የፕሮፌሰሩን ሀሳብ አንድ

በአንድ በሙዚቃ ሰንቆ አቅርቦታል:: የሚገርመዉ የቴዎድሮስ ካሳሁን ግጥም የተጻፈዉ ፕሮፌሰሩ መጽሃፋቸዉን ከማሳተማቸዉ

በፊት ነበር:: ፕሮፌሰሩም ቢሆኑ መጽሃፋቸዉን ያሳተሙት የቴዲን ዘፈን ሰምተዉ አይደለም:: የራሳቸዉን ምርምር አድርገዉ እንጅ::

ቴዲ አፍሮ ስለጥንታዊ ሳባ: ስለ ባህረነጋሽ: ስለ ታላላቅ የህዝብ ዉህደት ሂደቶች እንዲሁም ሁለቱ የሀገሪቱ ታላላቅ እምነቶች እንዴት

ተቻችለዉ በጋራ እንደ ኖሩ ለማሳዬት ይባትታል:: ቴዎድሮስ ካሳሁን ልዩ ልዩ የሀገሪቱን ቁዋንቁዋዎች በአንድ አቀናብሮ ለማሳዬት

በተቻለዉ ይሞክራል::

ኢትዮጵያዊነት እሴት ልባቸዉን ቀስፎ የያዛቸዉ ወገኖች ያጨበጭባሉ:: አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች ጥርሳቸዉን

ይነክሳሉ:: ጥርሳቸዉን ነክሰዉም አይቀሩም ጦር በዚህ ሰዉ ላይ ይወረዉራሉ:: አድዋ ባርነትን እንጅ ምን አተረፈልን ሲሉ በነጭ ቅኝ

ባለመገዛታቸዉ እየተቆጩ ይጽፋሉ:: ያባቶቻቸዉን ታሪክ በሙሉ በእግራቸዉ ረግጠዉ ከኢትዮጵያዊ የጋራ ማንነት ይልቅ

በኢትዮጵያዉያን መሃከል ልዩነትና ጥላቻ ከፍ ብሎ ይዉለበለብ ዘንድ አበክረዉ ይሰራሉ::

ቴዎድሮስ ካሳሁን የተሸከመዉ እሤት ኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት አለዉ ብሎ ለሚያምነዉ ኢትዮጵያዊ ወገን የኩራት ምንጭ ሲሆን

ኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት የለዉም: ኢትዮጵያዊነት አቀንቃኞች መደምሰስና መጠረግ አለባቸዉ ብለዉ በአቁዋም ለጸኑ አክራሪ የጎሳ

ብሄረተኞች ግን የብስጭት ምንጫቸዉ ነዉ:: ለዚህ በቂ ምክንያት አላቸዉ:: አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች ዋናዉና የመጨረሻ ግባቸዉ አንድ ብቻ ነዉ:: እሱዉም ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ተረት ተረት ናት ስለሆነም መገነጣጠል አለባት የሚል የማያወላዉል እና የማያወላዳ አቁዋም አላቸዉ:: ሆኖም ይሄን የመጨረሻዉን ግባቸዉን ወደ መድረክ

ከማቅረባቸዉ በፊት ሊሰሩዋቸዉ የሚገቡ የደረጃ በደረጃ የቤት ስራዎች አሉዋቸዉ:: እነዚህን የደረጃ በደረጃ የቤት ስራዎች ልዩ ልዩ

ኢትዮጵያዊ ማህበረሰቦች/ብሄረሰቦች በደንብ እንዳይረዱዋቸዉ ማደናገሪያ ዘዴዎች አብጅተዉላቸዋል:: ህዝቡ የሚያስተዉላቸዉ

በብዥታና በድንግርግርም እንዲሆን ህዝቡን በልዩ ልዩ መልክ ያደናግሩታል:: ከማደናገሪያቸዉ ዋና ዋና ነጥቦችም:-

-ኢትዮጵያ የሚባል ወጥ ህዝብ የለም:: ኢትዮጵያ እያለ የሚጮህዉ ይሄኛዉ ወይም ያኛዉ ማህበረሰብ ብቻ ነዉ:: ሆኖም ኢትዮጵያ

እያሉ መጮህ ትምክህት እና ጊዜዉ ያለፈበት የሞኞችና የሁዋላ ቀሮች ባህል ነዉ:: ኢትዮጵያ የሚባለዉ ሀገር በመቶ አመት ዉስጥ

የተፈጠረ ተረት ተረት አገር ነዉ::ጥንታዊ ታሪክ አለዉ እሚባለዉ የፈጠራ ድርሰት ነዉ:: አሁን የምናያት ኢትዮጵያ በምኒልክ በቅኝ

ግዛት የተፈጠረች ሃገር ነች::

-ይሄኛዉ መሬት የእኛ መሬት ብቻ ነበር:: እነ እከሌ መጥተዉ ወረሩን:: ስለዚህ እነዚህን ከዚህ መሬት ላይ ጨፍጭፈን እናባራቸዉ::

-ይሄኛዉ ህዝብ መጤ ህዝብ ነዉ:: ነዋሪና ባለቤቶች እኛ ነን:: በመሆኑም በሀገሩ ላይ ያለዉ ሀብት ሁሉ ለእኛ ይገባል:: አሁን እዚህ ከተማ ዉስጥ ፎቅ ሰርተዉ እና ሱቅ ከፍተዉ ልዩ ልዩ ንግዶችን አከናዉነዉ ሀብት ያፈሩ ማህበረሰቦች በሙሉ ሃብታቸዉን ያፈሩት

በዘረፋ ነዉ:: ስለሆነም እዚህ ከተማ የሚነግደዉ ማህበረስብ የኛ ወገን ስላልሆነ የሰራዉ ሱቅ : የሰራዉ ፎቅ እና ያፈራዉን ሀብት

ሁሉ ተወላጁ እጣ ተጣጥሎ ሊወርሰዉ ይገባል::

– እኛ እንዲህ ተበድለናል እነዚያ ደግሞ እንዲህ ተበድለዋል:: ስለሆነም ሀገሩን በጋራ እናፍርሰዉ::

– ሀገሩ ሲመራና ሲተዳድር የነበረዉ በአንድ ማህበረሰብ ሆኖ የኢትዮጵያ ታሪክም ምንም የጋራ እሴት የለዉም:: ህዝቡም

አልተዋሃደም:: ለምሳሌ ንጉሰ ነገስት አጼ ኃይለስላሴ እንዲሁም ንግስት ኢሌኒ የብዙ ኢትዮጵያዊ ዉህድ ዉጤት ናቸዉ የሚባለዉ

ሀሰትና ተረት ተረት ነዉ::

– ከዚህኛዉ ማህበረሰብ ጋር አትጋቡ:: ከዚህኛዉ ማህበረሰብ ጋር ከተጋባችሁ ግን የማህበረሰባችሁ ጠላት ናችሁ::

-ስለ ኢትዮጵያ አንድነትና ታሪክ የሚያቀነቅኑ ኢትዮጵያኒስቶችን ማሸማቀቅ አለብን

በነዚህ ሁሉ ማደናገሪያዎች ግን ጥላቻን ስለመርጨታቸዉ እርግጠኛ መሆን ይፈልጋሉ:: ኢትዮጵያዉያን ሆድ እንዲባባሱ

ማድረጋቸዉን ማረጋገጥ ዋናዉ ስራቸዉ ነዉ:: እናም አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች ቅደመ መገንጠል ስራቸዉን በድንብ ሳያርፉና

ሳይታክቱ እየሰሩ ነዉ:: አልደከሙም አልታከቱም:: የትም ቢሆኑ አቁዋማቸዉ አንድ ነዉ:: አይወላዉሉም:: በኢትዮጵያ ምደር

ቢመቻቸዉም ባይመቻቸዉም: የመጨረሻዉ ጣሪያ ላይ ቢደርሱም: ከስር ቢሆኑም: በዉጭ ሀገር ቢኖሩም ይህችን የመገንጠል

ህልማቸዉን አይተዋትም:: በስነልቦናቸዉ እራሱ ከብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ግንጥል ናቸዉ:: እናም ጠንክረዉ ይሰራሉ:: ስራቸዉ የደረጃ

በደረጃ የቤት ስራ እንዳለበት ጠንቅቀዉ የተረዱት ከረዥም ጊዜ የትግል ልምድ ብሁዋላ ነዉ::

ለምሳሌም በቁዋንቁዋ : በታሪክ : በባህል: በእምነት በመልክዓምድር በስነልቦና ከብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ጋር አንድ የነበረዉ የኤርትራ ህዝብ በአክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች የሀሰት ፕሮፖጋንዳና ነገን ባላገናዘብ መልክ እንዴት የተለዬ ህዝብ ተብሎ እንደሄድ በደንብ አጥንተዋል:: ምንም እንኩዋን ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል እንጅ ኢትዮጵያ ቅኝ ያልገዛቻት ሀገር መሆኑዋን ልባቸዉ ቢያዉቅም ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ የተገዛች አገር የሚለዉ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በደንብ እንደሰራ አስተዉለዋል:: ሆኖም ይሄን ፕሮፖጋንዳ በደንብ መሬት ለማዉረድ እረዥም አመታት አስፈላጊ እንደነበረና የኤርትራን ህዝብ ኢትዮጵያዊ አይደለም ብሎ ለማሳመን ጊዜ ፈጅቶ አንደነበረ በደንብ አስተዉለዋል:: ለዚህም የስነጥበብ ድርሻ ከፍ ያለ እንደነበር ተሞክሮን ከኤርትራ ወስደዋል::

እናም አሁን ኢትዮጵያ በዝግታ ትፈርስ ዘንድ ትግል የያዙ የጎሳ አክራሪ ሀይሎች ሞኝ አይደሉም::

በጣም ብልህና ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ ሀይሎች ናቸዉ:: ደግሞም ልምድ የሚያካፍላቸዉ አለ:: የትግል ልምዳቸዉ በደንብ እንደነገራቸዉ እና እንዳስረዳቸዉ

ኢትዮጵያዊነት እጅግ ዉህድነት ስለሆነ በቀላሉ ብትንትኑን ማዉጣት እንደማይችሉ ተረድተዋል:: አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች

በልባቸዉ የማይክዱት ሀቅ አለ:: ይሄዉም ኢትዮጵያዊነት ዉህድነት መሆኑን:: ኢትዮጵያዊነት

አይሁድነትን ; ክርስትናን እና ሙስሊምነትን ጠምዝዞ ዉህድ ኢትዮጵያዊ እሴትን የማልበስ አቅምና ጉልበት ያለዉ ታላቅ ሚስጥረ

መሆኑን አክራሪዎቹ የጎሳ ብሄረተኞች ተረድተዋል:: እንዴዉም በድንብ አድርገዉ አጥንተዉታል::

ደግሞም አሁን ሌላ የተረዱት ነጭ እዉነት አለ:: ይሄዉም ኢትዮጵያዊነት ስሜት እና ለጋራ ኢትዮጵያዊ እሴት ተቆርቁሮ የመቆም

ጉልበት ከህዝባችን ዉስጥ ሲሙዋሽሽ አስተዉለዋል:: በድንብ ተረድተዋል:: በዚህም ልባቸዉ ተነፍቱዋል:: በከፍተኛ የድል ተራራ

ላይ የወጣ ስሜትን ለብሰዋል:: እናም ከንግዲህ አንዳንድ የቀሩ እንጥፍጣፊ ኢትዮጵያዊነት ስሜት የሚያዉለበልቡ የሚያርገበግቡ

ግለሰቦች ከመጡ እንዳያንሰራሩ አድርጎ መሰባበር ወሳኝ መሆኑን አስምረዉበታል::

የኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት እሴትን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ የሚደረግ የርብርቦሽ ስራ ብቻ እንደቀራቸዉም መክረዋል::

እናም ቴዲ አፍሮ ብቻዉን በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያዊነት የብሄረተኝነት እሴትን: የዚህችን ጥንታዊትና ባለታሪክ ሀገር የጋራ እሴትን

ከፍ አድርጎ ሲዘምር አስተዋሉ:: ወደ መጨረሻዉ ግብ ተራመድን ሲሉ እንኩዋን ለኢትዮጵያ ለጥቁር ዘር በመላ መኩሪያ ይሆን ዘንድ

ታሪክ የሰሩትን ታላቁን ዳግማዊ አጼ ሚኒልክን በጋራ የሀገር እሴትነት ወክሎ ብቅ አለ:: ስንት ቢሊዮን ብርና ሰዓት አፍሰዉ ቀበርነዉ

ያሉትን ታሪክ እፍ ብሎ ብድግ አድርጎ ወደ ህዝብ ሲያቀርበዉ የኢትዮጵያ ህዝብ አስደንጋጭ በሆነ ደስታ ተቀበለዉ:: ያኔም አክራሪ

የጎሳ ብሄረተኞች ተበሳጩ:: ስለ ጥንታዊት ሳባ ሲያቀነቅን ተረት ተረት ታሪክ ያወድሳል ሲሉ ጣት ቀሰሩበት:: ስለ ሙስሊምና

ክርስቲያን ፍቅርና ህብረት ሲያቀነቅን ምን ህብረት አላቸዉ ሲሉ መግለጫ አወጡበት:: አንዳንዶች ለክርስትና የተቆረቆሩ መስለዉ

ሌሎች ለእስልምና የተቆረቆሩ መስለዉ መግለጫ አወጡበት:: ሆኖም ግባቸዉ አንድ ነበር:; ዉህድ ኢትዮጵያዊነት እንዳይሰበክ እና

የጋራ ኢትዮጵያዊ እሴት እንዳይሰበክ ነበር:: ቴዲ አፍሮን የጠሉት እነሱ የሚያቀነቅኑትን የጎሳ እሴት ከመሸከም ይልቅ የኢትዮጵያዊነት

እሴት ስለተሸከመ ብቻ ነዉ::ቴዲ ኢትዮጵያዊነት ሞቴ ነዉ ብሎአል::ኢትዮጵያዊነት ትምክህቴ ነዉ ብሎአል:: አክራሪ የጎሳ

ብሄረተኞች ደግሞ ሞት ለኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት ብለዋል::

ቴዎድሮስ ካሳሁን አሁንም በኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት ዙሪያ መዞሩን ቀጠለ:: ስለ ፍቅር ይዘምራል ስለ ታላላቅ ኢትዮጵያዊ

አባቶቻችን ይሰብካል ስለ ጥንታዊት ኢትዮጵያ ያቀነቅናል:: አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች ተረት ተረት ስለሚሉት ኢትዮጵያዊ የጋራ እሴት

ሁሉ በማንሳት ኢትዮጵያዊነት የሚያማልለዉን ኢትዮጵያዊ ህዝብ በሀሴት ዳንኪራ ያስረግጣል:: እናም አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች

ተበሳጩ:: አሉም ከእንግዲህ ብዙም ኢትዮጵያዊነት ብሄረተኝነትን የሚያቀነቅኑ ሰዎች ስለሌሉ እየነጠልን ቴዲን ማጥቃት ተገቢ ነዉ

ሲሉ በትር አነሱ:: እናም ቴዎድሮስ ካሳሁን አሁን የጥቃት ኢላማቸዉ ሆኑዋል:: የማህበረሰብ ድረገጾችን እንዲሁም ማንኛዉንም

ሚዲያ በመጠቀም በቴዲ ላይ የስድብ ናዳ ይዘንባል::

ደግሞም ሰሞኑን ከብራዚል የአለም ዋንጫ ተሳታፊነቱ መስተጉዋጎሉ ተአምራዊ ዳንኪራን ፈጥሮላቸዋል:: አንዴ በዘረኝነት ይከሱታል

ሌላ ጊዜ በችሎታ ማነስ:: አስከትለዉ ደግሞ በምኒሊካዊነት:: ሲብስባቸዉም የኢትዮጵያን የሀሰት ተረት ተረት ሰባኪምነት

ይከሱታል:: ለአክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች ኢትዮጵያ ተረት ተረት ነች:: ታሪኩዋ ሁሉ ሀሰት ነዉ:: ንግስት ሳባ ተረት ተረት ነች::

በመጽሃፍ ቅዱስ ያለችዉ ኢትዮጵያ ሀሰት ነች:: ነብዩ መሐመድ በታላቅ ባለዉለታነት የተናገሩላት ኢትዮጵያ ሀሰት ነች:: አባቶቻችን አብርሃና አጽብሃ አንዱ አክሱም ላይ አንዱም ሸዋ ላይ ሆነዉ ዛሬ ባሌ እና ሶማሊያ የሚባለዉን አካባቢ እንዲሁም ከምዕራብና ከደቡብ ያሉ ሰፊ ኢትዮጵያዊ አካባቢዎችን አንድ አድርገዉ ሲያስተዳርሩ የነበሩት ታሪክ ሀሰትና ተረት ተረት ነዉ:: ለአክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች አሁን ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለዉ ህዝብ እራሱ እንኩዋን ሀሰት ነዉ:: ለአክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች በ19ኛዉ ምዕተ ዓለም

አሃመነስ የሚባል ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ 16 ፕላኔቶች ስለመኖራቸዉ የጻፈዉ ፍልስፍና ተረት ተረት ነዉ:: ለአክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች

ኢትዮጵያዉያን የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ተረት ተረት ነዉ:: ከዚህም በላይ አጥብቀዉ የሚጠሉት ነገር ታዲያ ኢትዮጵያዊነት የጋራ

ማንነት አለዉ የሚለዉን ጭብጥ አንስቶ የሚያርገብግብን ሀይልን ነዉ::

አንዳንድ የዋህ ኢትዮጵያዉያን እንደሚያስቡት አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች እያጠቁት ያለዉ ቴዎድሮስ ካሳሁንን በግለሰብ ደረጃ

ይመስላቸዋል:: ላንዳንዶች የመሰላቸዉ አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች የጠሉት ቴዲ አፍሮን ነዉ:: ሚስጥሩ ግን እነዚህ ሰዎች የጠሉት

አንድ ነገር ብቻ ነዉ:: ኢትዮጵያዊ የጋራ እሴት የሚባል ነገር ፈጽሞ እንዲኖር አይፈልጉም:: የኢትዮጵያ ታሪክ የዉሸትና የጭካኔ ታሪክ

ነዉ ሲሉ ክደዋል:: ኢትዮጵያዊ ማንነቱን እንዲጠላ እየሰሩ ነዉ:: የኢትዮጵያ ህዝብ ለስንት ሽሕ ዘመናት አብሮ ኖሮም በፍጹም ያልትዋሃደ ህዝብ ብሎም እንደ ዘይትና ዉሃ ፈጽሞ ያልተቀላቀል ህዝብ ነዉ ሲሉ ኢትዮጵያዉያንን በጎሳ ከረጢት ዉስጥ ብቻ ልኬታቸዉን ሰፍተዉላቸዋል:: ቴዎድሮስ ካሳሁን ደግሞ እዚህ እጎሳ ከረጢታቸዉ ዉስጥ አልገባ ብሎዋቸዋል::ሰዉዬዉ ከጎሳ

ከረጢት የገዘፈ ሰብዕና አለዉ:: ዛሬ ዉጭ አገር ድረስ ሄደዉ ፒ ኤችዲና ማስተር አንጠልጥለዉ ሲያበቁ ስለጎሳና ቀበሌያቸዉ ሲዘምሩ ዉለዉ ሲያለቅሱ ቢያድሩ የማይታክቱ ምሁራን እንደ አሸን በፈሉባት ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ሙዚቀኛ ግን ከጎሳ ከረጢቱ በላይ

የገዘፈ ሰብዕና ለብሶ ብቅ አለባቸዉ:: እናም ተረበሹ::

አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች ሙሴን የስራ አመራር ስርአታ ያስተማረዉን የኢትዮጵያዉያን አባትን የዮቶርን ታሪክ ክደዋል:: የመጽሀፍ

ቅዱሱን ታሪክ ማራከስ ሲያቅታቸዉ የጎጃም ቄሶች በግዕዝ የጻፉት ተረት ተረት ነዉ ሲሉ ዉሸትን ከረባታቸዉ አድርገዋል:: የእንግሊዘኛዉ መጽሃፍ ቅዱስ ሲመጣላቸዉ ደሞ ይህ መጽሃፍ ቅዱስ የሚጠቅሳት ይህችኛዋ ኢትዮጵያ አይደለችም ሲሉ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያላቸዉን እጅግ ጥልቅና ስር የሰደድ ጥላቻ ነግረዉናል:: የኢትዮጵያዉና ነገስታት ታሪክ የሀሰት ታሪክ ሀሰት ነዉ:: ክብረ ነገስት የሚባለዉም የነገስታት ታሪክ መጽሀፍ በትግሬ ደብተራ የተጻፈ ተራ የሀሰት ሰንድ ነዉ ሲሉ ኢትዮጵያዊ የሆነዉ ነገር በእገር ይረገጥ ዘንድ ከአንዳንድ ተንኮለኛ ፈረንጅ ጸሃፊዎች የቃረሙዋትን ቆራጣ መረጃ ለማቅረብ መጽሃፍትን ጽፈዋል:: እንግዲህ

ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ምንም የእዉነት የሆነ እሴት የላትም ማለት ነዉ:: በአክራሪ የጎሳ ፖለቲከኞች አይን::

አክራሪ የጎሳ ብሄረተተኞች ሌላዉ የማሳሳቻ ስልታቸዉ ደግሞ የኢትዮጵያ ታሪክ የነገስታት ታሪክ ስለሆነ ዋጋም የለዉ:: እንደ ኢትዮጵያ ታሪክም ልንቆጥረዉ አይገባም ይሉና ይሄን የኢትዮጵያ ታሪክ ብሎ አንስቶ ማቀንቀን ተገቢ አይደለም ሲሉ በብልጠት ኢትዮጵያዊ ታሪክ ይደብዝዝ ዘንድ ይሰራሉ:: የነገስታትና የሀገር መሪዎች ታሪክ እንጅ ወትሮስ ከሃገር ታሪክ ጋር ተሳስሮ የሚነሳዉ

የያንዳንዱ ዜጋ ታሪክ የተጻፈበት ሀገር ወትሮስ የት አለ? እንግሊዝ ነዉ? ሩሲያ ነዉ? ቻይና ነዉ? ነዉ ወይስ የት? ሌላዉ ቀርቶ

በአሁኑ ዘመን በዲሞክራሲያዉያን ሀገራት ( ለማጣቀሻ አሜሪካን ማሰብ በቂ ነዉ) ታሪክ የሚጻፈዉ በፕሬዝዳንቱ ዙሪያ የሚሽከረከሩ

ሀገራዊ ዉሳኔዎችን እያጣቀሰ እንጅ ፕሬዝዳንቱ ማዕከል ያልሆኑበት ታሪክ የት ይጻፋል? ሀገራዊ ዉሳኔዎች ሁሉ የመጨረሻ የመቁዋጫ ዉሳኔ እና የተፈጻሚነት ትዕዛዝ የሚያገኙት በሀገር መሪዉ እስከሆነ ድረስ የሀገራት ታሪክ ማዕከል ሆነዉ የሚወጡት ፕሬዝዳንቱ

ናቸዉ::

ሆኖም አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች ይሄ ጠፍቶአቸዉ አይደልም:: ብቻ አንድ ነገር ይፈልጋሉ:: ያም ነገር በዚህም ሆነ በዚያ

ተብሎ ኢትዮጵያዊ የጋራ እሴት ጠፍቶና ተደምሦ ማዬት የመጨረሻ ግባቸዉ ነዉ:: ይሄን የኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት የሚያራግብ

ታሪኩን የሚያጣቅስ ሰዉ ከዚህች ሀገር ለመጨረሻ ጊዜ ተደምሦ ማዬት የሚቁዋምጡበት ወቅት አሁን ሆኖ አግኝተዉታል::

ኢትዮጵያዊ የጋራ እሴትን የሚያቀነቅን ግለሰብ እጅግ ትንሽ አቅም ቢኖረዉም የጥላቻ ቀስታቸዉ ማነጣጠሪያ ይሆናል::

አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች የተለያዩ ማህበረሰቦችን/ብሄረሰቦችን/ በሚወክሉበት ጊዜ እርስ በእርሳቸዉ አይዋደዱም::ሊጠፋፉ

ይደባባሉ:: ሆኖም አንድ ነገር ላይ ይስማማሉ:: ይሄዉም ኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴትን በማጥቃት ላይ አንድነት አላቸዉ:: እናም

በሳሳዉ ኢትዮጵያዊነት ብሄረተኝነት ደን ዉስጥ አንድ ብላቴና ቴዎድሮስ ካሳሁን ወዲህና ወዲያ ሲወራጭ አስተዉለዋል:: ይህ

ኢትዮጵያዊ ብላቴና በታላቅ አክብሮት ንግስተ ሳባን ይጠራታል:: አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች ግን ይህ የኢትዮጵያዊነት ታሪክ ዉሸት ነዉ

ሲሉ ገና ዱሮ ደምድመዋል:: እናም ይሄን ታሪክ የሚያነሳ ሰዉ ተረት ተረት ታሪክ ያጣቅሳል እያሉ ሞራሉን ለመስበር ኢትዮጵያዊ

ትምክህቱን ለማንኮታኮት መስራት ከጀመሩ ቆይተዋል:: ኢትዮጵያዊነት እና የኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት በማንም ቢነሳ : በምንም

መልክ ቢነሳ: በየትኛዉም መልክ ቢነሳ ፊታቸዉ ይደምናል : ልባቸዉ ይጠቁራል እራሳቸዉን ለጸብና ለስድብ ያዘጋጃሉ::

የአክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች ጉልበት ገና እየበረታ ይሄዳል:: ጩህትና ስድቡም ገና ምድር ያንቀጠቅጣል:: ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር

ተረት ተረት ሀገር ነች የሚለዉ ቃላቸዉም እስከ ደመና ገና ይወጣል:: የኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴትን የሚሰብክን ብሎም የኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት እሴትን የሚያቀነቅንን ሁሉ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ የሚደረግ ርብርብ ጉልበቱን ታክቲኩን እና ስልቱን እየቀያዬረ እና እየበረታ እንደሚመጣ ጥርጥር የለዉም::

በጥቂቱ ግን ዛሬ ዱላዉ በቴዲ አፍሮ ላይ እዬወረድ ነዉ:: ቴዲ አፍሮ በብራዚል አለመሳተፉ ያስደሰታቸዉ ይመስል ጥላቻቸዉን በቴዲ አፍሮ ዙሪያ ያጠሩ መስለዉ (በርካታ ተቀባይ እንዲያገኙ) ቀረቡ እንጅ የዳንኪራቸዉ ምንጭ ኢትዮጵያ በአለም መድረክ ላይ እንደ ሀገር ተወክላ አለመቅረቡዋ የፈጠረባቸዉ የደስታ ስሜት

ነዉ::ኢትዮጵያ የሚለዉ ስም ያማቸዋልና:: ኢትዮጵያ ስትዋረድ ደስ ይላቸዋል:: ኢትዮጵያዊ ሰዉ የላትም ሲባል ዳንኪራ ይረግጣሉ:: ኢትዮጵያ ታሪክ የሌላት ምናምንቴ ሀገር

ናት የሚል ሀሳብ ሲሰሙ ደስታቸዉ ጣሪያ ይነካል:: ኢትዮጵያ የሚል ቃል ሲሰሙ ያማቸዋል ብቻ ሳይሆን የጥላቻ ዛር ያንዘፈዝፋቸዋል:: አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች የረጅም ጊዜ ግባቸዉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሸከም ግለሰብ እንዳይወጣ : ኢትዮጵያዊ እሴትም ተንኮታኩቶ እንዲጠፋ ስለሆነ ኢትዮጵያዊነት በአለም መድረክ ላይ እንዲወከል አይፈልጉም:: እናም ኮካ ኮላ ቴዲ አፍሮን

ስላገደዉ ደስ ያላቸዉ ኢትዮጵያ ስለተዋረደች ነዉ:: ኢትዮጵያ ስለደበዘዘች ነዉ:: እነሱ የሚፈልጉት የዚህ ዘመን ትዉልድ በሙሉ

እንደ እነሱ በየ ጎሳዉ ከረጢት ገብቶ ስለጎሳና ቀበሌዉ ብቻ እንዲዘምር ነዉ::
ከጎሳና ከቀበሌ የዘለለ ኢትዮጵያዊ ሰብዕና ያለዉ ሰዉ ከመጣ ግን በጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ይወርዱበታል:: በአሉ ግርማ ደራሲ ብቻ ሳይሆን አንዳንድ እይታዎቹ ትንቢት ጭምር ያዘሉ ይመስሉ ነበር::
ሀዲስ በሚለዉ መጽሃፉ ዉስጥ በንጉሱ ዘመን እንኩዋን አክራሪ የጎሳ ብሄረተኝነት ብልጭ ብልጭ ስትል ጠቆም አድርጎ በርካታ አንባቢ ሊረዳዉ በማይችል መልክ አቅርቦ ሲያበቃ የአደጋዉን ርቀትም እንደ ቀልድ አሳይቶ አልፎ ነበር:: ያኔ በስነጥበብ ስራ ጥቆማ ነገሮችን ቀደሞ አስተዉሎ የሚያቅድና የተሻለ ሁኔታን መፍጠር የሚችሉ አስተዋይ የሀገር መሪዎች ቢኖሩ ኖሩ መድሃኒቱን ማሳብ ይችሉ ነበር::

እናም ዛሬ አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞች ጉልበት ከመበርታቱ የተነሳ የኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት እሴት አራማጅ ሀይሎች ምንም የጋራ

ነጥብና ታሪካዊ መሰረት እንዳይኖራቸዉ በሀሰት ፕሮፖጋንዳ ቀንድ ቀንዳቸዉን ከማለት ዘሎ ግለሰባዊ ጥቃት ላይ ደርሶዋል::

እንደተባለዉም ጩህቱና ድንፋታዉ ከደመናት በላይ ደርሶዋል:: ሆኖም በእግዚአብሄር መዝገብ የተጻፈዉ ኢትዮጵያዊነት ነዉና

በምድር ላይ ያለ ምንም ሀይል ኢትዮጵያዊነትን ሊያሸንፈዉ አይችልም:: ቴዲና በርካታ ኢትዮጵያዉያን ሀገራችን ቅድስት ነች ብለው

ያምናሉ:: ይሄም አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞችን ያበሳጫቸዋል:: ኢትዮጵያዊነት ትምክህት ይጎረብጣቸዋል:: ሆኖም መጽሀፉን ገላልጦ

ማንበብ ነዉ:: ቅድስናዋን የሰጣት እግዚአብሄር እንጅ ሰዉ አይደለም:: ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን አይለዉጥም እንዳለ መጽሀፉ::

ነብዩ መሐመድም ይሄን ቅድስናዋን ስለተረዱ ፍትህ ወደ ማይዛባባት ቅዱሳን የእዉነት ሰዎች ወዳሉባት ሀገር ሄዳችሁ ታላቁን እምነት

እስልምናን ጠብቁ ብለዉ ለተከታዮቻቸዉ ያስረዱት ያለምክንያት አይደለም::

ቴዲ አፍሮ ሀገሪቱ የተሰጣትን እና የሆነችዉን አቀነቀነላት እንጅ ቴዲ አፍሮ የፈጠረላት እሴት የለም:: እናም ይህች ኢትዮጵያዊ ትምክህቱ ስለሆነች ቴዲ አፍሮ እንዲህ ብሎ

ዘፈነላት:: እስላም ክርስቲያኑ የሚፋቀርባት … ::: እናም ቴዲ አፍሮ የጥቃት ኢላማ ሆነ:: ለምን ቢባል? ኢትዮጵያዊነት እሴትን

አራምዱዋልና:: ኢትዮጵያዊነት ትምክህትን ሰብኮአልናል:: ኢትዮጵያዊነት ዉህደትን አቀንቅኑዋልና::

ቴዲ አፍሮ የጠለቀ ጭብጥ በቁዋጠሩ ሙዚቃዎቹ እንደሚነግረን ኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት አለዉ:: ይህ የጋራ ኢትዮጵያዊ እሴት

እስላም ክርስቲያኑን ያፋቅራል::ይህ የጋራ ኢትዮጵያዊ እሴት ጥንታዊና ስር የሰደድ የጋራ ምድር ያለዉ የጋራ ታሪካዊ መሰረት ያለዉ

ዉህድ ኢትዮጵያዊ ህዝብን አስተሳስሮ አቁሞአል:: ኢትዮጵያዊነት ለቴዲ አፍሮ የጎሳዎች ድምር ሳይሆን የኢትዮጵያዉያን ማህበረሰብ

ዉህደት ነዉ::

ይህ ዉህደት ደግሞ ከድምር የበለጠ የጋራ መስተጋብር ነዉ (the whole is greater than the sum)::

ኢትዮጵያዊነት አይሁድነትን : ክርስትናን እና ሙስሊምነትን ጠምዝዞ ዉህድ ኢትዮጵያዊ እሴትን የማልበስ አቅምና

ጉልበት እንዳለዉ ሁሉ ዛሬ የሚጮሁትን አክራሪ የጎሳ ብሄረተኞችን ሁሉ ቀስ ብሎ ይዉጣቸዋል:: ኢትዮጵያዊነት ምንድነዉ? ምንስ

የጋራ እሴት አለዉ? ብሎ ለሚጠይቅ ሁሉ ካማዊነት ሴማዊነት ኩሻዊነት በጋራ ተገምደዉ ተዋዉጠዉና ተሰናስነዉ በዉህደት

የፈጠሩት ኢትዮጵያዊ እሴት አለ:: ቴዲ አፍሮ የስነ ጥበቡ ጭብጥ ማጠንጠኛ ማዕከል ያደረገዉ ይሄን ኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት

ነዉ:: እናም ቴዲ ላይ ጦር የሚያሰብቅበት ይሄንኑ ሀቅ በማቀንቀኑ የተነሳ ነዉ:: ጦሩ የተወረወረዉ ወደ ኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት

ላይ እንጅ እንደ ግለሰብ ወደ ቴዲ አፍሮ ላይ አይደለም:: ቴዲን ማኮላሸት ከተቻለ ሌሎች በኢትዮጵያዊነት የጋራ እሴት ዙሪያ

የሚያቀነቅኑ የስነጥበብ ባለሞያዎች እንዳይወጡ ማድረግ ይቻላል የሚል ታሳቢ ነዉ የተያዘዉ::

The post አንድ ሀገር ከብዙ አመታት በፊት እቆመበት ቦታ ላይ አሁንም እንዴት ሊቆም ይችላል? – ሸንቁጥ አየለ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ማስታወቂያ – የጎንደር ምሽት በሰሜን አሜሪካ የኦሪገን ጎንደር ሕብረት ቻፕተር በፖርትላንድ May 6, 2017 አዘጋጅቷል

$
0
0

(ከጎንደር ሕብረት የተላከ ማስታወቂያ) በዚህ ለመጀመሪያ ጊዜ በከተማዋ በተዘጋጀው የጎህ የገንዘብ የማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ በክብር እንግድነት የሚገኙት ባሳለፍነው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ ታይቶ የማይታወቅ አድናቆትን ያተረፉት ሌተናት ኮረኔል ዶክተር ሙሉጌታ ካሳሁን ናቸው። የዚህን ጀግና ንግግር ለመስማት በርካታ ቁጥር ያለው የጎረቤት ስቴት ነዋሪ ከስያትል ወደ ፖርትላንድ በበርካታ የመጓጓዣ ሚኒባሶች ለመጓዝ መዘጋጀቱን ታውቋል።

መሀሪ ደገፋው በወቅታዊ ዘፈኖች ያዝናናችዃል።

The post ማስታወቂያ – የጎንደር ምሽት በሰሜን አሜሪካ የኦሪገን ጎንደር ሕብረት ቻፕተር በፖርትላንድ May 6, 2017 አዘጋጅቷል appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

  አዋርድ ወይስ ዐዋርድ? – ነጋ ተኣ

$
0
0

ዶክተር ፍሰሀ እሸቱ

በማንኛውም የሙያ ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ላሳየ ሰው ውጤቱ  በከፍተኛ ባለሙያዎች ታይቶና ተገምግሞ  ለላቀ ማዕረግና ሽልማት ይታጫል:: በዚህ ዓይነት መሠረት ከፍተኛ ውጤት ባሳዩ ድንቅ ሙያተኞች በዕጩነት ቀርበው እንዲወዳደሩ ይደረጋል::   ከዕጩ ተወዳዳሪዎች መካከልም የላቀ ነጥብ ያመጣውን ለመለየት አያሌ መስፈርቶች ይቀመጣሉ:: መስፈርቶቹን በሚገባ ያሙዋላ ሰው ለተሸላሚነት ብቁ ሆኖ ይቀርባል:: ይኼ በአጭሩና በቀላሉ የአንድን የሽልማት ሂደት ሊጠቁም ይችላል:: ምክንያቱም ለብቻው ተወዳድሮ  አሸናፊ መሆን ስለማይቻል የግድ ውድድርና ተወዳዳሪ ሊኖር ይገባል::

ሌላው በማንኛውም ዘርፍ ውጤት ያመጡትን ሙያተኞች ለመሸለም  ስለሚቁዋቁዋም ድርጅት ነው::  በየትኛውም አገር በማንኛውም ዘርፍ  በሙያ: በችሎታ:  በዕውቀትና በምርምር ረገድ  ለማህበረሰባቸውና ለአገራቸው የሚጠቅም ነገር ያበረከቱ  ውድ ሰዎችን ለማበረታታት: ለማጠናከር: ለማመስገን: ዕውቅና ለመስጠት: አድናቆት ለመቸር:  ምስጋና ለማቅረብ  ሲባል ሽልማት የሚያዘጋጁ ድርጅቶች  ሁኔታ ግምት ውስጥ የሚገባ ወሳኝ ነገር ነው:: ምክንያቱም ያለውን ውጤት አምኖና ተቀብሎ ዋጋ መስጠት ለተተኪው ትውልድ ሞዴል  እንደማዘጋጀት ነውና::  ስለሆነም እንዲህ ዓይነቱን ታላቅ ክብር የሚያስገኘውን   ቅርስ የሚገነባ ድርጅትን  ማንነት በግልጽ ማወቅ የማይታለፍ ጉዳይ ነው::  ታማኝነትን: ፍትሐዊነትን: ሚዛናዊነትን  እና ብቃትን እንደመመዘኛ የሚጠይቅ ተግባር ስለሆነ  በቀላሉ የሚታይ አይደለም::

በአጭሩ እና በቀላሉ ለመግለጽ ያህል ነውጂ በዛሬ በዚህ ዘመን   ስለ ሽልማት: ስለ ሸላሚውና  ስለተሸላሚው   ሁኔታዎች በጥልቅ ለማስረዳት መሞከሩ  አስተዛዛቢ ነው::   እያንዳንዱ ሰው  ግዙፍ ላብራሪ በእጁና በኪሱ ይዞ ስለሚዞር  ስለዚሁ ነገር ለመረዳት  አድካሚ ስለማይሆን ጠቆም አድርጎ ማለፉ አንባቢን ማክበር ይሆናል::

ወደ ዋናው አርእስቴ ልምጣ::  “አዋርድ ወይስ ዐዋርድ” ማለት ምን ማለት ነው? ይባል ይሆናል:: ግርርታም የሚፈጥር ነው:: ቃሉ    የሚያወዛግብም ሊሆን ይችላል::  ነገር ግን ቀላል ነው::

ዛሬ ቴዎድሮስ ካሳሁን የዘመናችን አወዛጋቢ ድምጻዊ ሆኖ ተገኝቶአል::  ልክ እንደ 1950ዎቹ: 1960ዎቹ እና ከዚያም ወዲህ  የድምጻዊያን ንጉሥ ተብሎ የሚጠራውና እራሳቸው ታላላቅ ድምጻዊያን  እንደነማህሙድ አህመድ: እንደነ ታምራት ሞላ: እንደነ ዓለምአየሁ እሸቴ:  እንደነምኒልክ ወስናቸው: እንደነ መልካሙ ተበጀ: እንደነ አያሌው መስፍን: እንደነ ብዙነሽ እና ሂሩት በቀለ”:  እንደነ አስቴር አወቀ  ሁሉ የመሰከሩለት ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ  በዘፈናቸው ዘፈኖቹ እልህ አስጨራሽ ፈተናዎች እንደገጠሙት ይታወቃል::

ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ   በየቀኑ እንደ ፍየል ወጠጤ የሚታሰር ነበረ:: የመድረክ ዝግጅቶች ሲኖሩትም  ከእስር ቤት እየተወሰደ እንደሚዘፍን  የነበሩ እማኞች አጫውተውኛል:: በየጊዜው የተለያዩ የማበሳጫ ስልቶች ይቀርቡለት ነበረ::   ለዚህም  አእምሮውን ስቶ  አማኑኤል ሆስፒታል ገብቶ ብረት አልጋ ላይ  እጅና እግሩ ታስሮ   እያለ የክቡር ዘበኛ አዛዥ ጄነራል መንግስቱ ንዋይ  ሂደው እንደጎበኙት  የሚታወስ ነው::  ይሄ ብቻም አይደለም::   ደብረ ሊባኖስ ገዳምም እንዲገባ ተደሮጎአል::  በጥቅሉ ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ ሰባት ጊዜ ሞትን ድል የመታ ድምጻዊ ነበረ::  በምሥራቁ   ክፍለ አገራችን በወራሪው ሶማሊያ መንግስት የተከፈተብንን ጦርነት  ለመመከት  በሙያቸው ከዘመቱት አርቲስቶች መካከል ጥላሁን ገሠሠ አብይ ድምጻዊ ነበረ::  በሰሜኑ ክፍለ አገራችንም ከወንበዴዎቹ ገንጣይና አስገንጣይ ጋራ በሚደረገው ፍልሚያ  መካከልም ነበረ::  እስከ ሞት ደጃፍ የሚያደርስ መስዋእትነትንም ከፍሎአል::  ለመጥቀስ ያህል ስለሆነ ዝርዝር ውስጥ አልገባም::  እንዲህ ስል አገራዊ ተልእኮ ይዘው ከተሰማሩት አርቲስቶቻችን መካከል ለአብነት ያህል ጥላሁን ገሠሠን  ብቻ ጠራሁ እንጂ  የላቀ ድርሻ ያበረከቱ አርቲስቶች ብዙዎች እንደነበሩ ግምት ውስጥ ይጨመርልኝ::

በኢትዮጵያችን ውስጥ እውነትን የሚናገር: እውነትን የሚዘፍን: እውነትን የሚጽፍ: እውነትን የሚቀኝ:  እውነትን የሚፈርድ:  ለእውነት የሚቆም: ለእውነት የሚታገል ሰው ሁልጊዜ ፈተና አለበት:: ታላቁ ባለቅኔ ሎሪየት ጸጋዬ ገብረመድኅን  ደልቶት አላለፈም::  ደራሲ በዓሉ ግርማ  የዕድሜውን ያህል በህይወት መኖር አልቻለም::  አቤ ጎበኘውም  የእሳት እራት ከመሆን አላመለጠም::  በላይ ዘለቀም  የአርበኝነቱን ዋጋ መርካቶ ቃኘው  ሻለቃ ሆቴል ጀርባ  ዛሬ ፖሊስ ጣቢያ ያለበት ቦታ  ላይ በስቅላት ተገደለ::  ኮሎኔል አብዲሳ አጋም በጡረታ ዘመኑ አባጂግሳ የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶት ወደ ኦጋዴን በረሃ እንዲዘምት ከተደረገ  በሁዋላ  የማታ ዕድሜው  በአሳዛኝ ሁኔታ እንዲቁዋጭ  ተደርጎአል::

በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ዘርዝሬ ስለማልዘልቀው እዚሁ  ላይ ይብቃኝና ወደ ቴዲ አፍሮ ልመለስ::

ቴዲ አፍሮ የዘመኑ አነጋጋሪ ድምጻዊ ነው::  ቴዎድሮስ የሚዘፍነው ወቅቱን ነው:: ዘመኑን ነው:: የሚያቀነቅነው ድልና ገድልን ነው የሚያሞግሰው:: በቴዲ ድምጽ ውስጥ  አሸናፊዎችና ባለታሪኮች ከፍ ያለ ቦታ አላቸው::   ዓጤ ምኒሊክ: ዓጤ ኃይለሥላሴ:   ሩዋጭ ኃይሌ ገብረሥላሴ: ሩዋጭ ቀነኒሳ በቀለ:  ወዘተ  የመሳሰሉት  የቴዲ አፍሮ ድምጽ በአንክሮ ሲያቀነቅናቸው ተሰምቶአል:: ቴዲ የአድማጩን የጋለ ስሜት የመረዳት ክህሎት አለው::  ዛሬን መግጠም ይችልበታል:: ዛሬን መዝፈን ያቅበታል::  ይህ ደግሞ ራሱን የቻለ  ፈተና አለው:: ይህንን ፈተና ያለመፍራቱ  ደፋር ድምጻዊ አድርጎታል::  ስንቱ አንገቱን  እንደ ካሮት መሬት ውስጥ ቀብሮ መኖርን በሚመርጥበት ዘመን  አንገትን ቀና አድርጎ ድምጽን ከፍ አድርጎ በአደባባይ መዝፈን ራሱን የቻለ ጀግንነት ነው:: ቴዲ በዚህ ይደነቃል:: ይሁን እንጂ ደጋፊዎቹ ግምት የለሽ እየሆኑበት ሲያሳጡት እየተስተዋለ ነው:: አንዳንድ ሀያሲዎች  ኅጸጹን ሲያወጡበት: ግድፈቱን ሲጠቁሙበት:  በቴዲ አፍሮ ሳይሆን በአድናቂዎቹ  አማካይነት የማያባራ ውግዣ ያዘነሙ ሰዎችን ሰምተናል::   በቴዲ አፍሮ አድናቂዎችና በቴዲ አፍሮ ነቃፊዎች መካከል ያለውን  ጉዳይ  ራሱን በቻለ  አጀንዳ እንገናኛለን:: ስለዚህ አሁንም ወደ ተነሳሁበት ርእሰ- ጉዳይ ልመለስ::

በዶክተር ፍስሀ እሸቱ አማካይነት እየተመሠረተ ያለው አንድ ኢትዮጵያ ንቅናቄ  ቴዲ አፍሮን እሸልማለሁ ብሎ ትኩስ አጀንዳ ቀርጾ  እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ ሚድያ ላይ እየሰማን ነን:: እያነበብንም ጭምር:: ይሁን እንጂ  በሸላሚና በተሸላሚ መካከል አለመግባባቶች ተነስተዋል::   ክርክርም በሚመስሉ ቃላቶችም ተወራውረዋል::

ስለዚሁ ጉዳይ የተሰማኝን ስሜት ላጋራችሁ ተመኘሁና በድፍረት ይህንን ጽሁፍ ለማቅረብ ዳዳሁ::  ስህተት ከሆነ በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ::

በሸላሚና በተሸላሚ መካከል ለምን ስምምነት  ጠፋ ብዬ ራሴን ስጠይቅ ቀድሞውኑ ሥራው በስምምነት መቼ ተጀመረና የሚል መልስ እኔው ራሴ ለራሴ መልስ ሰጠሁ:: ቀጥሎም  የሸላሚው ማንነት: የሸላሚው መሠረታዊ ዓላማ እና ግብ ጥያቄ የሚያስነሳ  ስለሆነ የግድ ምላሽ የሚያስፈልጉ ናቸው::  እንደዚሁም የሽልማቱ  ሂደትም ራሱን የቻለ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው:: ይህንን አስመልክቶ ዶክተር ፍሰሀ እሸቱ  በኤስ ቢኤስ ራዲዮ ላይ  ያቀረቡት መከራከሪያ ሃሳብ  ያደጉ አገሮችን  ተሞክሮ በማየት ነው የጀመርነው ስለዚህ ነውር የለበትም ባይ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ:: ስለዚህ የግሌን ሃሳብ መስጠት እፈልጋለሁ::  ዶክተር ፍስሀ እሸቱ መሠረታዊ ስህተት ሠርተው የሠሩትንም ስህተት  ላለመቀበል  አጀንዳቸውን አንጠራርተው  ካደጉ አገሮች ጋራ በማነጻጸር  ሊያስተባብሉ ብቻ ሳይሆን ሊያስተምሩም ሞክረዋል::  ተጨማሪ መሠረታዊ ስህተት  እየሠሩ መሆናቸውንም ታዝቤያለሁ::

ይኸውም አንደኛ ድርጅታቸው ገና በምስረታ ላይ የሚገኝየባህል ድርጅት  ነው::  የዶክተር ፍስሀ የባህል ድርጅት  በማንኛውም የሙያ ዘርፍ ወይም በተለይ የሙያ መስክ የላቀ ውጤት የሚያመጡ  ሙያተኞችን  እሸልማለሁና ሸላሚ ድርጅት ነኝ ብሎ ቢል  በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የሚታወቅ ነገር የለም:: በዚህ ረገድ ራሱን ለኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ  ለተለያዩ ሙያተኞች አላስተዋወቀም::  ሌላው ትልቁ ስህተት  ስለሽልማት  መሠረታዊ ሕግጋቶችን የጣሰ አካሄድ መሄዱ ነው::  እርሱም  የሽልማቱ   ሂደትን በተሸላሚው ስም ሰየመውና አረፈው:: ይህ ማለት አንድ ሽልማት የሚዘጋጀው በራሱ መንገድ አለው:: ሂደት አለው:: ባህርያቶችና መስፈርቶች ይኖሩታል::  ተወዳዳሪ የሌለበት ገለልተኛና ነጻ የሆነ  ሙያውን የሚገመግም የዳኝነት ሚና የሚጫወት ኮሚቴ  የያልተፈጠረለት ሌሎች ዕጩ ተወዳዳሪዎች ያልተጋበዙበትና ያልተሳተፉበት  ወዘተረፈ ብዙ ብዙ ነገሮች የተጉዋደሉበት  ሂደት መከተሉ  ዶክተሩን ከነድርጅታቸው የሚያስገመግማቸው ሆኖ አግኝቻለሁ::

ምክንያቱም በደመ-ነፍስ ተነሳስቶ: በስሜት ተነሽጦ:  አንድ ነገር ለመስራት ማሰብ ሚዛናዊነትን ያሳጣል:: ፍትሃዊነትን ያጉዋድላል::  በማህበረሰቡ ዘንድም  የሚያመጣውን አዎንታዊና አሉታዊ እንድምታ  ቀድሞ አርቆ አለማየትን ያመላክታል:: በዚያ ላይ ቴዲ አፍሮን የመሰለ አነጋጋሪና አወዛጋቢ  ድምጻዊን የሚያክል ስም ለሽልማት መጠሪያ ወስዶ እንደገና ራሱኑ ለመሸለም  አስቀድሞ አሳውቆ   ለሽልማቱ የሚውል የገንዘብ ምንጭ በራሱ በተሸላሚው ስም መዋጮ ለመሰብሰብ ወስኖ  መነሳት ደረቅ ስህተት ነው::

በብዙ ነገሮች የተጉዋደለ  አካሄድ መሄድ ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን ያስከትላል:: በሕብረተሰቡም ዘንድ አመኔታን ያሳጣል::

ምክንያቱም በይዘቱ: በቅርጹ: በባህርዩ በመንፈሱና በሁለንተናዊ ፍጥረቱ የተዛባ አመለካከት ይዞ ገና ለገና ሕዝብ ወደደ ብሎ  አጋጣሚውን ለመጠቀም መንደርደር ተገቢ አይሆንም:: ለዚህም ይመስላል ደምጻዊው  የቅሬታ መነሻ ያቀረበው::  ቅሬታው በባለሙያ ቢታይ እወነተኛ ቅሬታ ነው:: ማንም ሽልማትን አይጠላም:: ነገር ግን ማንም ሰው መሸለምን ይፈልጋል ብሎ  በማሰብና በመገመት በስሙ የፈለጉትን ማድረግ ተገቢነት የለውም::

አንድ ተዋቂ ሰው  የሕዝብ ንብረት ነው ተብሎ አለግባብ ካለ ባለቤቱ ፈቃድ  ወይም በቃልም ሆነ በጽሑፍ ሳያሳውቁና አሽታውንና እንቢታውን ሳያገኙ  ሚድያ ላይ በስሙ  መጠቀም መጀመር  ጥያቄ ያስከትላል:: ለአርቲስቱም ሞራል እና ያለበትን ደረጃ ግምት ውስጥ አለማስገባት ነው::  ተዋቂም ሆነ ሽልማት ሕግ አለው:: መንገድ አለው:: ሂደት አለው:: ሙያም ይጠይቃል:: ዝም ብሎ አይሆንም::  በዚህ ረገድ እኔ የቴዲ አፍሮ አቁዋም ደጋፊ: የፍሰሀ እሸቱ እና ድርጅቱ ነቃፊ ነኝ::

በመጨረሻም ዶክተር ፍሰሀ እሸቱ ቴዲ አፍሮን  ይቅርታ መጠየቅ አለበት::  ሃሳቡንም ማሰተካከል ወይም መተው አለበት:: በስሙ የሰበሰበውን ሳንቲም  ለባለቤቱቹ መመለስ ይኖርበታል::  ቴዲ የገንዘብ ችግር የለበትም:: አለብኝ ካለም ገንዘብ ሸልሙኝ ብሎ  የሚመጣ አርቲስት አይደለም:: ኩሩና ጨዋ ልጅ እንዲያውም ለብዙ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በመቶ ሺህ ብር እርዳታ የሚሰጥ ሰብዓዊ ስሜት የሚያጠቃው ኢትዮጵያዊ ነው::  ዶክተር ፍሰሃ እሸቱ እና ድርጅታቸው በድፍረት ከገቡበት  ስሁት  በፍጥነት መውጣት አለባቸው:: አለበለዚያ እርሳቸውና ድርጅታቸው እንዳሰቡት ሳይሆን አርቲስቱን በነጻ ለድርጅታቸው ማስተዋወቂያ እየተጠቀሙበት ነው ያስብላል::  የጀማሪ ድርጅታቸውን ስም በመዋጮ ገንዘብና በሽልማት ስም  ለማስታወቂያ እየተገለገሉበት ነው ማለት ይቻላል:: ይህ ሆነ ማለት ደግሞ የያዙትን አገራዊ አጀንዳ  ከእጅ የወደቀ እንቁላል ያደርግባቸዋል::

ሌላው  ቴዲ አፍሮ ያለፈውን ጨቁዋኝ ሥርዓት ስለሚያወድስ ቅሬታ ተሰምቶናል በሚሉት ኢትዮጵያዊንን በኩል ያለው ቅራኔ እጅጉን እንዲሰፋ እና የቴዲ አፍሮ ተቃዋሚዎችን እልህ ውስጥ እንደማስገባት ነውጂ ቅሬታዎችን አስወግዶ እንደማቀራረብ አይደለም::  ይህ ደግሞ እራሱን የሽልማት ሳይንስን የሚጻረር ነው::  ሁለት ወገኖችን በሚያወዛግብ አጀንዳን ለሽልማት ማብቃት ክፋት ነው:: ወይም ሆን ተብሎ የታቀደ ሤራ  ሆኖ ይቆጠራል::

ዶክተር ፍሰሀ እንደሚታረሙና ይቅርታ እንደሚጠይቁ ተስፋ አደርጋለሁ:: ቴዲ አፍሮም  በያዘው ጥሩ አቁዋም ጸንቶ ክብሩን እንደሚጠብቅና አድናቂዎቹን እንደማያሳፍር እምነት አለኝ:: አንድ ኢትዮጵያ ንቅናቄ  እና ዶክተር ፍሰሀ እሸቱ   ተገቢ እርምት ወስደው በተገቢ መንገድ ካልተራመዱ:  ለቴዲ አፍሮ “አዋርድ ሳይሆን ዐዋርድ”  ብለው እንደሚሠሩ ይቆጠራል::

ነጋ ተኣ

The post   አዋርድ ወይስ ዐዋርድ? – ነጋ ተኣ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Interview with Journalists Zenaneh Mekonnen and Alemneh Wassie – SBS Amharic

Viewing all 3686 articles
Browse latest View live