Quantcast
Channel: admin – Medrek
Viewing all 3686 articles
Browse latest View live

የእግዚአብሔር መልእክት በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል (ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም)

$
0
0

ግንቦት/2009

ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም)

‹‹ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደአለላ ብትሆን እንደአመዳይ ትጸዳለች እንደደምም ብትቀላ እንደባዘቶ ትጠራለች፤ እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እንቢ ብትሉ ግን ብታምጹም ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናገሮአልና፡፡›› ኢሳ. 1/18.
በእግዚአብሔር ለሚያምን ሰው፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜም፣ ለዘለዓለም ሙሉና የማይወዳደሩት ኃይል እንዳለው ለሚያምን ሰው፣ ለእግዚአብሔር ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም አሁን መሆኑን ለሚያምን ሰው ‹‹ኑና እንዋቀስ›› (በእንግሊዝኛው “come now let us reason together) ማለት ለእግዚአብሔር ምን ያህል መውረድ እንደሆነ መገንዘብ የሚዳግት አይመስለኝም፤ የእንግሊዝኛው ትንሽ ሻል ያለ መስሎ ‹‹ኑና እንከራከር›› የሚል ቢሆንም ከመጨረሻው የላይኛው ዳኛ ጋር መከራከር የሚችለው ማን ነው? እግዚአብሔር ነው፤ ትልቁ ነገር እሱ ፈቀደ፤ ‹‹እንዋቀስ›› አለ!
መዋቀስ ዓላማ አለው፤ ለመግባባት ነው፤ ለመስማማት ነው፤ ለፍቅር ነው፤ ለሰላም ነው፤ ለመረዳዳት ነው፤ እንደመለስ ዜናዊ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ማለት ሲቻለው፤ ኑና እንዋቀስ የሚል ኃያል አምላክ ለእኛ ምን ያስተምረናል?
የእግዚአብሔር ቃል ኑና እንማከር በማለት አልቆመም፤ እሺ ብትሉ፣ ለእኔም ብትታዘዙ፣ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እንቢ ብትሉ ግን ብታምጹም ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና፡፡
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ትሕትናንና መወያየትን፣ መወቃቀስና መስማማትን ለማስተማር በነቢዩ በኢሳይያስ በኩል መልእክቱን አስተላለፈ፤ ዛሬ ይህ መልእክት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ይመስለኛል፤ ዛሬ ይህ የእግዚአብሔር መልእክት ለወያኔ ይመስለኛል፤ ዛሬ ይህ መልእክት ለወያኔና ለአጋሮቻቸው ይመስለኛል፡፡
በኢሳይያስ በኩል የመጣው መልእክት ግልጽ ነው፤ ምርጫው ‹‹የምድርን በረከት መብላት›› ወይም በሰይፍ መበላት ነው፡፡
የምድር በረከትን በሙሉ ሁሉ በጄ ሁሉ በደጄ ላለ ጥጋብ ላይ ነውና ይበልጥ አይታየውም፤ በዕብሪት ላበጠም ስለሰይፍ ቢወራ አያስፈራውም፡፡
እግዚአብሔር ‹‹እንዋቀስ›› ካለ እኛ፣ ገዢዎቻችንም ለሰላም ሲሉ ለፍቅር ሲሉ፣ ለልጆቸው ሲሉ፣ ለአገር ሲሉ ‹‹እንዋቀስ›› ቢሉ ያስከብራቸዋል እንጂ አያዋርዳቸውም፤ ታሪካቸውን ያሳምርላቸዋል እንጂ አያጎድፍባቸውም፤ መንፈሳዊ ወኔ ያላቸው፣ ልበ-ሙሉ ጀግኖች ያደርጋቸዋል እንጂ ፈሪ አያደርጋቸውም፤ አርቀው የሚያስተውሉ ብልሆች ያደርጋቸዋል እንጂ ጊዜያዊ ጮሌነት አይሆንባቸውም፡፡-

መስፍን ወልደ ማርያም

The post የእግዚአብሔር መልእክት በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል (ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


ሰሞኑን ገበያ ላይ የሚውለውን የቴዎድሮስ ካሳሁንን አልበም (የዘፈን ጥራዝ) በተመለከተ ጥብቅ መልዕክት! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

$
0
0

እንደምታውቁት በዚህ ዘመን የሥነኪን (በዘልማድ የሥነጥበብና የኪነጥበብ) ሥራዎች ገበያ ሆን ተብሎ የሕገወጦች ሲሳይ እንዲሆን በማድረግ ጉልበት እውቀት ገንዘባቸውን አፍስሰው የደከሙት ከያኔያንና አሳታሚዎች ከገበያ ውጭ እንዲሆኑ ከስረው እንዲጠፉ ሲደረግ የመኖሩ ነገር የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሥነኪን በሀገራችን በሁሉም ጎን እየኮሰመነች፣ እየጎሰቆለች፣ እየጫጨች፣ እየተዳከመች መሆኗ በግልጽ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡

ዘርፉ ያቀፋቸው የሥነኪን ማኅበረሰብ በተለያየ ጊዜ “መብታችን ይከበር! ፣ ሠርተን መብላት አልቻልንም፣ በአደባባይ እየተዘረፍን ባዷችንን ስንቀር መንግሥት በዝምታ ሊመለከተን አይገባም! ፣ መንግሥት የሥራ ደኅንነት ዋስትናችንን የማስከበር ግዴታውን በመወጣት ከችግራችን ይታደገን!….” እያሉ የሚያሰሙት የመረረ የብሶት ጩኸታቸው አይሎ በሚመጣበት ወቅት ይሄንን ብሶት ለማስተንፈስ ያህል ለዚያው ሰሞን የይስሙላ የዘመቻ እርምጃዎች ይወሰዱና ወዲያውኑ ነገሮች ወደነበሩበት ቦታ እንዲመለሱ በማድረግ አገዛዙ በሀገራችን ሥነኪንና በባለሞያዎቿ ጢባጢቦ ሲጫወት መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ይሄን የተገነዘቡ የዘርፉ ባለሙያዎች “እኛ የምንፈልገው ከስንት ጊዜ አንድ ጊዜ የሚወሰድ የዘመቻ እርምጃ ሳይሆን በጸጥታ ኃይሉ እይታ ሕገወጥ ድርጊቱ እንደሌሎች የወንጀል ተግባሮች ሁሉ ትኩረት ተሰጥቶት ዘወትር በሕገ ወጥ ድርጊትነቱ እየታየ የሚተላለፉ ዜጎች ሲገኙ በሕግ ተጠያቂ የሚሆኑበት ሁኔታ እንዲኖር ነው፡፡ ሕጉ ተፈጻሚነት ያግኝ! የጸጥታ አስከባሪ (የፖሊስ) አባላት ይህ ድርጊት በአደባባይ በዓይናቸው ስር ሲፈጸም በዝምታ አይመልከቱ! ሕገወጥ ቅጅ ሲሸጡ ሲያጋጥሟቸው ስርቆት የሚፈጽሙ ግለሰቦች ሲያጋጥሟቸው በሕግ ተጠያቂ እንደሚያደርጓቸው ሁሉ እነኝህንም ተጠያቂ ያድርጉ!” እያሉ ቢጮሁም አገዛዙ ሆን ብሎ የሚያደረገው ውንብድና በመሆኑ ሰሚ አላገኙም፡፡

የዘርፉ ባለሙያዎች ጉዳያችን ብለው በቀጥታና በቅርበት ሲከታተሉት የነበረው ጎንደር በፋሲል ሙዚቃ ቤት እጅ ከፍንጅ ተይዞ የነበረውን በርካታ ሚሊዮን (አእላፋት) ገንዘብ ይንቀሳቀስበት የነበረ የሕገ ወጥ ቅጂ ተግባር አገዛዙ ፈጽሞ ባልተጠበቀና እጅግ በሚገርም ሁኔታ ያለአንዳች የተጠያቂነትና የኃላፊነት ስሜት ዓይን ባወጣ ነውረኛ ተግባር ፍትሕ በአደባባይ ተደፍልቃ ፍትሕ ሳይሰጥ ጉዳዩ እንዲዘጋ በማድረጉ ይህ ሕገወጥ ተግባር እንዲቀጥል ያለውን ፍላጎት በሚገባ ያረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡

አዲስ አበባ ውስጥ ካሉት ሕገወጥ ቅጅ ከሚሠሩት ግለሰቦች ውስጥ አገዛዙ ያደራጃቸው እንዳሉም ይነገራል፡፡ ይህ የወንበዴ ቡድን ከዚህም የከፉ በርካታ የውንብድናና የክህደት ተግባሮችን በዚህች ሀገርና ሕዝብ ላይ ሲፈጽም ኖሯልና፣ በግልጽ እየተየ ያለውም ግልጽ ጉዳይ የሚያሳየው ይሄንኑ በመሆኑ “ይሄንን አያደርግም!” ለማለት ይከብዳል፡፡

ለመሆኑ ወያኔ ሥነኪን እንድትጠፋ እንድትከስም ይሄንን የውንብድና ተግባር የሚፈጽመው ለምንድነው? መባሉ አይቀርምና ወያኔ ይሄንን የውንብድና ተግባር በሥነኪን ላይ የሚፈጽምበት ምክንያት ሥነኪን ማለትም ሙዚቃ (ዘፈን)፣ ተውኔት (ቲያትር)፣ ሥዕልና ቅርፃቅርፅ፣ ሥነ ግጥምና ሌሎች የድርሰት ሥራዎች በተፈጥሯቸው የሕዝብ ጠበቆች ናቸው፡፡ ወገኝተኝነታቸው ለሕዝብ ለተበዳይ ለተገፋ ነው፡፡ ብሶት የመተንፈሻ፣ ቅሬታ የማሰሚያ፣ የማስተማሪያ፣ የማንቂያ፣ የመቀስቀሻ መንገዶች ናቸው፡፡ ይሄ ሲባል ግን አንባገነኖን ሥነኪንን እንድታገለግላቸው አድርገዋት አያውቁም ወይም አያደጓትም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ተገዳ ያለፈቃዷ እጇን ጠምዝዘው በመሆኑ እንድታገለግላቸው የሚያደርጓት ወዳና ፈቅዳ እንዳደረገችው ሁሉ የእነሱም አገልጋይ እንደሆነች ልንቆጥራት አንችልም፡፡

ሥነ ኪን የተፈጠረችበት ዓላማና ግቧ ግን “ለሕዝብ፣ ለእውነት ጥብቅና ቆሞ በመታገል የሕዝብን ሁለንተናዊ ሕይዎት፣ የሀገርን ሁኔታ ምቹና ሰላማዊ ማድረግ!” የሚለው ነው፡፡ የሥነኪን ተፈጥሮ ይሄ መሆኑና በከያኔያን የሥነኪን ሥራዎችም ይሄ መንጸባረቁ ነው ወያኔን ያልተመቸውና የሀገራችንን ሥነኪን ደብዛዋን ለማጥፋት ከገባ ጊዜ ጀምሮ በሸፍጠኛ ተንኮሉ እያዳከመ ወደ መቃብሯ ሲገፋት የቆየበት ምክንያት፡፡

በታሪክ እንደምታስታውሱት ፋሺስት ጣሊያን ሊመሠርተው ለፈለገው ቅኝ አገዛዝ “ትልቅ እንቅፋት ሆነውብኛል!” በማለት አዝማሪዎችን ልቅም አድርጎ ነበር የፈጃቸው፡፡ በሥራዎቻቸው ሕዝቡ አሻፈረኝ እንዲል፣ አርበኞችን እንዲቀላቀልና እንዲደግፍ፣ ባንዶች እንዲያፍሩ እንዲሸማቀቁ፣ ሕዝብ ባንድነትን እንዲጸየፈው ወዘተረፈ. በየሠርጉ፣ በየማኅበሩ፣ በየገበያው፣ በየበዓላት መከወኛ ሥፍራዎች፣ በየመጠጥ ቤቱ ወዘተረፈ. እየዞሩ ሞያዊ ግዴታቸውን በመወጣታቸው ነበር ጣሊያን እንቅፋቴ ብሎ የፈጃቸው፡፡ ጊዜ ይገድበናል እንጅ በብዙ መልኩ አገላብጠን ብናየው ዛሬም ወያኔ እያደረገ ያለው ፋሽስት ከወሰደው እርምጃ የከፋ እንጅ ያነሰ አይደለም፡፡

ሕዝቡ ቢነቃና ቢተባበር ግን ኦሪጅናል (ንጥር) የሥነኪን ሥራ ኅትመቶችን ገዝቶ በመጠቀም ብቻ ወያኔ በሀገር ጥበብ ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት በጣም አነስተኛ እንዲሆን በማድረግ የሀገርን ጥበብ ከመጥፋት ታድገን እድገት እንድታሳይ ማድረግ ይቻላል፡፡ ጥበብ ተጠባቢዋን ማሳደር ማስተዳደር የማትችልበት ደረጃ ላይ በመድረሷ ተረካቢ ባለሞያ ከያኔያንን እያጣች እውቀቷም እየተረሳ እየጠፋና እየደከመ ነውና፡፡ በመሆኑም ለሽዎች ዓመታት ሲበስል፣ ሲዘመን፣ ሲጠበብ፣ ሲዳብር የመጣው የዚህች ሀገር ጥበብ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል!” በሚለው ጠባብና ደንቆሮ አገዛዝ እንዳልነበረ ሆኖ ከመጥፋቱና ሀገሪቱ ሥልጣኔዋን፣ ጥንታዊነቷን፣ ማንነቷን፣ ታሪኳን፣ እሴቶቿን የሚያሳይላትን፣ የሚያረጋግጥላትን ጥበብ አጥታ የራሷ ጥበብ ያልነበራትና የሌላት አዲስ ተመሥራች መሐይም ሀገር መስላ ከመታየቷ በፊት ሕዝብ ይሄንን የበሰለና ኃላፊነት የተሞላበት ግንዛቤ ሊይዝ በሚችልበት ጉዳይ ላይ መረባረብ ይጠበቅብናል፡፡

ሰሞኑን የቴዎድሮስ ካሳሁን የዘፈን ሥራ ገበያ ላይ ይውላል፡፡ ከላይ ከገለጽኩላቹህ ምክንያት በተጨማሪ የዚህን ከያኔ ኦሪጅናል (ንጥር) ቅጂ ለመግዛት የምንገደድበት ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ልጁ ሥነኪን ለሀገሩና ለሕዝቡ የጫነችበትን ሞያዊ ግዴታ ለመወጣት ጥረት በማድረጉ ከጨለማው አበጋዞች ወይም ከጥፋት ኃይሎች ምን ያህል ፈተና እንዲደርስበት እንደተደረገና እየተደረገም እንዳለ በሚገባ የምታውቁት እውነት ነው፡፡ እንዲያው ሌላ ሌላውን ትተን ቀላሉንና እንዲያጣ የተደረገውን ጥቅም ብቻ እንኳን ብናይ በተለያየ ጊዜ ከሁለት የንግድ ድርጅቶች ብቻ ከሃያ ሚሊዮን (አእላፋት) ብር በላይ የሥራ ውል እንዲሰረዝበት ተደርጎ ከፍተኛ ጥቅም አጥቷል፣ ተመሳሳይ ሥራዎችንም የማግኘት ዕድል እንዳያገኝ ተደርጓል፡፡ ለእኛ ለሕዝብ ሲል፣ ለሀገር ሲል፣ ለማንነት ሲል፣ ለታሪክ ሲል ነው ቴዲ ይሄንን ዋጋ ለመክፈል የተገደደው፡፡ ይህ የእሱ ዕዳ በከባዱ ስላለብን ኦሪጅናል (ንጥር) ቅጂውን መገብየታችን በጥቂቱም ቢሆን ያጣውን ጥቅም ሊያካክስለት ይችላልና ይሄንን በማድረግ ዕዳችንን እንድንወጣ አደራየ ጥብቅ ነው፡፡

በተረፈ ሌላው ላሳስባቹህ የምፈልገው ጥብቅ ጉዳይ ቢኖር “ኢትዮጵያ” በለሚለው የቴዲ አዲስ ዜማው ላይ ከአንዳንድ አካላት ሲሰነዘር የሰማሁትን ትችት ምናልባት በሌሎችም ሥራዎች “ዓየን!” የሚል ትችት ልትሰሙ ብትችሉ ለእነኝህ ትችቶች ፈጽሞ ጆሮ እንዳትሰጡ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ በግልጽ መናገር የምፈልገው ጉዳይ ቢኖር የዘፈን አቀናባሪዎች በተለይ ዋና ዋናዎቹ የቴዲን ዘፈኖች እንዳያቀናብሩለት በአገዛዙ ከባድ ጫና ሲደረግባቸው ነው የቆየው፡፡

ቴዲ አማራጭ ቢያጣ የውጪ ባለሙያዎችን ለመጠቀም የሞከረበት አጋጣሚም ነበር፡፡ በዋጋቸው አይቀመሴነትና ለእኛ ዘፈኖች ቃናና ቅኝት ባዳ የመሆናቸው ችግሮች አሰናከሉት እንጅ፡፡ በዚህ ምክንያት ቴዲ አዳዲስ አቀናባሪዎችን ለመጠቀም የተገደደበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በመሆኑ ያለው ሁኔታ እንዲህ አስቸጋሪና የተወሳሰበ በሆነበት ሁኔታ “ቅንብሩ እንዲህ ሆነ፣ ዜማው ምንትስ አለ…” እያሉ መተቸት ልጁ የገጠመውን ፈተና አለማገናዘብ በመሆኑ ከዚህም የተነሣ ትችቱ በፍጹም አግባብነት የሌለው በመሆኑ ማየት መስማትና ማገናዘብ ለተሳናቸው ተችዎች ትችን ጆሮ ሳትሰጡ የቴዲን ዘፈኖች መኮምኮም ብቻ ነው ያለባቹህ እላለሁ፡፡

ደናቁርቱ ተችዎች “ትናንትን ናፋቂዎች ናቹህ!” ቢሏቹህ “አዎ! ትናንትን ናፋቂ የሆነው ታሪክ ያለን ወይም ባለታሪክ ሕዝብ ስለሆንን ነው፡፡ ትናንትን የማይናፍቅ ወይም ለትናንት ክብርና አክብሮት የማይሰጥ ባንዳና ታሪክ የሌለው ማንዘራሽ ብቻ ነው!” በሏቸው አመሰግናለሁ!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

The post ሰሞኑን ገበያ ላይ የሚውለውን የቴዎድሮስ ካሳሁንን አልበም (የዘፈን ጥራዝ) በተመለከተ ጥብቅ መልዕክት! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ኢትዮጵያ የተያዘችባቸው ካንሰሮች – ያየያየ ይልማ

$
0
0

በአለም የጤና ድርጅት ፍቺ መሰረት ካንሰር ፤ በዛ ያሉ ጤናማ ያልሆኑ የሴሎች እድገት ሲሆን ፤ (Cancer is a group of diseases involving abnormal cell growth with the potential to invade or spread to other parts of the body.) ይህም ጤናማ ያልሆነ የሴሎች መባዛት ሌላውን እና ጤናማ የሆነውን የሰውን አካል የመበከል አቅምና አዝማሚያ ሲኖረው ነው ካንሰር የሚሰኘው፡፡ ታዲያ ይህ አለምን እና ህዝቦቿን እያስጨነቀ ያለ በሽታ ፤ ኢትዮጵያዊያን እንደ ግለሰብ በህዝቧ ላይ የተከሰተውን የበሽታውን መኖር ለመዘርዘር ሳይሆን ኢትዮጵያም እንደሃገር በዛ ያሉ ካንሰርን የሚሳዩ ምልክቶችን ማሳየት በመጀመሯ ፤ ኢትዮጵያን ካንሰር እንዳጠቃት ምልክቶቹን በማየት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ኢትዮጵያ የዘረኝነትን ስብከት እና ከልክ በላይ የተራገበ ብሄርተኝነትን እንድታራምድ፣ ህዝቦቿ ይህንን ቁንፅል አመለካከት አሜን ብለው እንዲቀበሉ ከህገ መንግስት ሰነድ እስከ የየግለሰብ መታወቂያ ድረስ አንድ አገር ያደረጓት ብልቶቿ ተፈልቅቀው እንዲለዩ፣ የተደረገባት አዲስ አገር ከሆነች እነሆ ሃያ አመት አለፈ፡፡ ይህ አላስፈላጊ የኋልዮሽ ሽምጥ መጋለብ ከተጀመረ ግዜ ጀምሮ አስገራሚ ብዙ እባጮች ኢትዮጵያ ላይ እና ኢትዮጵዊያን ላይ ታይቷል፡፡ እነኚህ እንደ ሃገር ኢትዮጵያ ላይ በገሃድ የሚታዩት ፣ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊ፣ እና ማህበረሰባዊ መስተጋብሮችን የሚያካልሉ እና በዋነኝነት በአመለካከት ላይ የሚገለፁ፣ አገራዊ ቀውስን ፍንትው አድርገው የሚያሳዩቱ፣ እባጭና ጉድፎች ናቸው አንድ በአንድ ተደማምረው፣ በሂደት አገሪቷን እንደ ሰው እያቆሰሉ፣ ቁስሏንም እያሸተቱና እያመረቀዙ፣ ብለውም እያበሰበሱ፣ አካሏን ሙት የሚደርጉት፡፡

ኢትዮጵያ በዚህ ካንሰር በመያዟ ምክንያት በአገሪቷ ላይ የሚታየው የጎጥ ፖለቲካ፣ በመንግስት ዘር በትኖ ለቃሚነት ፋና የሚመራው አርቲፊሻል ገፅታ የተላበሰው የሃገር ኢኮኖሚ እና ዘግናኝ በሚባል ደረጃ እንዲቀጥል ተደርጎ ያለው ኢፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ዋነኛ እውነታዎቹ የሆኑለት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ህፀፆችን፣ ለጊዜው ወደ ጎን ትቼ ማተኮር የምፈልገው በሌላኛው የካንሰር ምልክት እና የዚህ ፅሁፍ መነሻ ፤ ሙስና ላይ ይሆናል፡፡

ይህ አጭር ፅሁፍም፣  የአገሪቱ አንድ ክፍል በሆነችው አዲስ አበባ ፣ እየተደረገ ባለ በአንድ ተጨባጭ  እውነት ላይ የሚመሰረት ይሆናል፡፡ ለዚህ ፅሁፍ እንዲሆን የሚቀርበው እውነት መነሻው ኢትዮጵን እንደ ካንሰር ጤናማ ያልሆኑ ብክለቶች ፣ እዚም እዛም እየታዩ እንደ ሃገር ከፍተኛ አደጋ የደቀኑባትን እጅግ በጣም የበዙ ችግሮች በዚህ አችር ፅሁፍ ለመዳሰስ አይሞክርም፡፡

ነገር ግን በታሪካችን በየትኛውም ወቅት ቢሆን አይተን የማናውቀውን የንዋይ ፍቅርን ፤ ምስጋና ለወያኔ ይግባና ፣ ሁለንተናዊ የሆነ የአንድ ዜጋ ዝቅጠት (በእኩይ ስራ የሚያተርፉትን ብቻ)፣ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ላይ (ከመዲናዋ አዲስ አበባ ምሳሌ) አንድ አነስተኛ መንደር ላይ እየተከሰተ ያለን እውነት በማጋለጥ ፣ በአንፃሩ ደግሞ ከፍ ያሉት የሙስና አሻጥሮች እና የዚህ ሁሉ ሸፍጥ ጣጣው እንዴት ህዝቡን ፣ ብሎም ኢትዮጵን እንደ አገር ምን በደል እያደረሰባት እንዳለ በጥቂቱ ለማሳየት እና የዜግነት ሞራላዊ ግዴታን ለመወጣት፣ ብሎም እነኚህን ክፋቶች ለመታገል ማወቁ የመጀመሪ መፍትሄ ይሆናል በሚል ቅንነት ላይ በመመስረት ነው፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለጋራ መኖሪያነት ከተሰሩና እጅግ ብዙ ህዝብ ከሚኖርባቸው ሰፈሮች ውስጥ ፣ በቄራ አካባቢ የሚገኙትን ሁለቱን ትልልቅ የጋራ መኖሪ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን የሚመለከት ይሆናል የሙስና ሚና እንዴት የእንዳንዱን በነዚህ የጋራ መኖሪ ቤቶች ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ህይወት እንዴት እንደለያየው ያሳያል፡፡ እነኚህ በቄራ አካባቢ ያሉት የኮንዶሚኒየም ሰፈሮች የየራሳቸው መለያ ስያሜ አላቸው፤ አንደኛው ጎተራ ኮንዶሚኒየም፣ ሌላኛው ደግሞ መብራት ሃይል ኮንዶሚኒየም ተብለው ይጠራሉ፡፡ በመካከላቸው ያለው ቄራ ሲሆን ከቄራ ሁለቱም አንድ የታክሲ ፌርማታ ርቀት ላይ አንዳቸው ከሌላኛው ተቀምጠው የሚገኙ እና ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአዲስ አበባ ህዝብ የሚኖርባቸው፣ የደመቁ የጋራ መኖሪዎች ናቸው፡፡

የጎተራ ኮንዶሚኒየም

በጎተራ ኮንዶሚኒየም ከሰማንያ በመቶ በላይ የቤት ባለቤቶች ትግሬዎች ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ ከመከላከያ ሰራዊት አንስቶ በተለያዩ የመንግስት ስራ ላይ ቀድመው ተሰማርተው የነበሩ ሰዎች ተመርጠው የቤት ባለቤት የሆኑበት አስገራሚ የጋራ መኖሪ ግቢ ነው፡፡ ተከራዮቹ ግን ከሁሉም የማህበረሰብ የተውጣጡ እና እጅግ ዳጎስ ያለ ገቢ ያላቸው ንጥጥ ከተሜዎች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ አለበለዚያ ፣ የወር ደሞዝን በአንድ ገበታ አገልግሎት ለሚያስከፍሉ አገልግሎት ሰጪዎች ማን እየከፈለ ሊችለው ነው፣ ምንም ሳይመስላቸው ዩሴን ቦልትን (የወቅቱ የኢትዮጵ መቶብር ቅጥል ስም ነው፡፡) ጎተራ ላይ ከሚበትኑቱ የወያኔ ግት መጣጮች በስተቀር፡፡

ታዲያ በዚህ አስገራሚ ስፍራ እንደ ቀድሞዋ ሃያል አገር እንግሊዝ፣ በጎተራ ኮንዶሚኒየምም ፀሃይ አትጠልቅም፡፡ ከሱፐር ማርኬት እስከ ክሊኒክና ሆስፒታል፣ ከበርገርና ፒዛ ቤት እስከ ቁርጥና ጥብስ ቤቶች፣ ከፀጉር ቤት እስከ ባንክ ቤት ፣ አንድ ከተማ ውስጥ ተበታትኖ የሚገኝ አገልግሎት ሁሉ፣ በጎተራ ኮንዶሚኒየም በሚያስገርም የምርጫ ብዛት ተቸምችሞ በአንድ ስፍራ ይገኛል፡፡

የባለስልጣን፡ የኮንትራክተር እና የዌኔ ግት መጣጮች ያስቀመጧቸው እንስቶች፣ ከመኖሪያው እኩል መሸታ ቤቶች የሚገኝበት ጎተራ ኮንዶሚኒየም ሁለቱ አስከፊ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዋነኛ ችግሮች አይመለከታቸውም፣ ነዋሪዎቹ አዲስ አበባ ውስጥ እየኖሩ ይህንን የአዲስ አበባ ህዝብን ችግር መኖሩንም የረሱ ሰዎች በብዛት ለማግኘት ጎተራ ኮንዶሚኒየም ተወዳዳሪ የሌለው ስፍራ ነው፡፡ ይህ እንዴት እንደሆነ ስጠይቅ ያገኘሁት ምላሽ በጥቅልሉ ይህ ነው፡፡ በዋነኝነት የትግሬ ቤት ባለቤቶች የሚገኙበት ጠንካራ የጋራ መኖሪያ ኮሚቴ ስላለው ነው፡፡

የመብራ ሃይል ኮንዶሚኒየም

ውሃና መብራ እስከ ጭራሹንም ጠፍቶ እንደማያውቅ ስሰማማ ማመን ነው ያቃተኝ፤ ምክንያቴ ደግሞ በአንድ የታክሲ ፌርማታ ያክል የሚርቀው መብራ ሃይል ኮንዶሚኒየም ላይ ያለውን የውሃና የመብራ ችግር በመኖርም ጭምር ስለማውቀው ነበር፡፡ መብራት መሰረታዊ ነገር በመሆኑ ለምን እንደዚህ ኑሮን በሚያቃውስ መንገድ የአዲስ አበባ መብራት ሃይል እንደሚያቋርጠው የሁላችንም እንቆቅልሽ ስለሆነ የመብራት ሃይል ኮንዶሚኒየም (ከጎተራ ኮንዶሚኒየም በስተቀር) ብቻውን ተነጥሎ ስለዚህ መብራት ችግር ማውራቱ ይቅርና ስለ አስገራሚው የመብራ ሃይል ኮንዶሚኒየም ችግር ላመልክት፡፡

መብራት ሃይል ኮንዶሚኒየም ውሃ ይቋረጣል ሳይሆን፣ የሚመጣበት ለሊት እንደ አመት በአል የመዘከር ያክል ነው ጥቂት ነው፡፡ ቀን ውሃ መጥቶ ሳይቋረጥ ለተወሰኑ ሰአታት እንኳን ከቆየ፣ ነዋሪው ልክ እንደ ተአምር ስለውሃ መምጣት በስልክ እየተጯጯኸ ሲደዋወል፣ ከስራው አቋርጦ እየመጣ ሲተራመስ ማየት የማይቀር ነው፤ ምክንያቱም ይህ ክስተት ሁል ጊዜ የሚታይ ስላልሆነ፡፡ የመብራት ሃይል ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች፣ በሳምንት አንድ ግፋ ቢል ሁለት ቀን ለአንድ ሰአት ያክል፣ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰአት ላይ በምፅዋት የሚለቀቅ ውሃን ተጠቅሞ የሚኖር ፣ በከፍተኛ የቧንቧ ውሃ ችግር እጅግ ለአመታ እየተሰቃየ ያለ የአዲስ አበባ ህዝብ ነው፡፡ እረ ለመሆኑ ለምንድን ነው በኮሚቴዎች አማካኝነት ይህ ቸግር ለሚመለከተው አካል እንዲታወቅ ተደርጎ መፍትሄ የማይበጅለት ብዬ ስጠይቅ፣ ዋነኛው ችግር ታዲያ ይኸው አይደል እንዴ! በብዙ ሺህ ከሚቆጠረው ከህዝቡ ችግር የሚያተርፉ፣ ከስቃዩ እና ከምሬቱ ደስታ የሚጠጡ የዘቀጡ የመንግስት አላፊዎች አይደሉ እንዴ ይህ እንዲሆን ጠንክረው እየሰሩ ያሉት ብለው አፍረጥርጠው አስገራሚውን የጋራ መኖሪ ቤቶችን በውሃ ችግር የሚፈጠር አስገራሚ የሙስና ቢዝነስ ነገሩኝ፡፡

ውሃው እንዲለቀቅላቸው ነዋሪዎች ተሰብስበው ቁጥር ስፍር ለሌለው ጊዜ ከታች እስከላይ ለሚመለከተው ሁሉ ለአራ አመታ አቤት ቢሉ መፍትሄ ሳይበጅለት የኖረው የኮንዶሚኒየሙ ነዋሪ፣ ከቤት ኪራዩ ቀጥሎ የሚያወጣው ከፍተኛው ገንዘብ ለግዢ ውሃ በመሆኑ እና፣ ይህንን የግዢ ውሃ ገቢ የሚካፈሉት የመንግስት ሃላፊዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡ የመብራት ሃል ኮንዶሚኒየምን ከብበው ያሉ ነባር የቄራ መደበኛ መኖሪያ ቤቶች አሉ፤ ከእነዚህ ቤቶች የተመረጡት ውሃቸው ሳይቋረጥ እንዲፈስ የውሃ ልማት ሙሰኛች ይህንን ሁኔታ እንዳለ እንዲቀጥል ያደርጋሉ፤ እጅግ ግዙፉን የኮንዶሚኒየም ግቢን ያጥለቀለቁ፣ በዚሁ የሸፍጥ ስራ የጭነት መኪኖች ሳይቀር የገዙ ውሃ ቀጂዎች፣ በመብራት ሃይል ኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ እንደ አሸን ፈስሰው፡ ውሃ እንዲቀዳለት የሚፈልግ ሰው ከአንድ እስከ አስር ጀሪካን የውሃ ግዢ ትእዛዝ በስልክ እየተቀበሉ፡ እነሱው ከተከራዩትና ከውሃ ልማት አላፊዎች ጋር ጥቅም በሚካፈሉባቸው ቤቶች ሞልተው ከሚያከማቿቸው ባለ ሰላሳ ሊትር ጀረኪናዎች እንደ ትእዛዙ ልክ አንድ ጀሪካን በሰላሳ ብር እየቸበቸቡ፡ ምስኪኑን የኮንዶሚኒየም ነዋሪ ህዝብን ኑሮ አስከፊ እንዳደረጉት ይኸው እስከዛሬዋ እለት ድረስ በግፍ ይኖራሉ፡፡

ይህ ኢትዮጵያን እንደ አገር ከያዛት የዝቅጠት ካንሰር ማሳያ ምልክቶች አንዱና እጅግ ታናሹ እንጂ ፈፅሞ ትልቁ አይደለም፡፡ በቀጣይ የኢምፔርያል ሆቴልን በሚመለከት ተመሳሳይ እውነታን እናያለን፡፡ ሰላም!!!

ያየያየ ይልማ

The post ኢትዮጵያ የተያዘችባቸው ካንሰሮች – ያየያየ ይልማ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ሕወሓቶችና የአጋር ድርጅት አመራሮች እየተናከሱ ነው (ተንሳኤ ራዲኦ)

$
0
0

በአባይጸሃዬ የሚመራው የፖሊሲ ምርምር ማዕከል ያቀረበውን ጥናት ሃይለማሪያም ደሳለኝ ውድቅ ማደረጉ በመካከላቸው ያለው ክፍፍልና አለመግባባት የደረሰበትን ጡዘት ደረጃ ያመለክታል ተብሎአል።
የህወሃት ቁንጮ የነበረው መለስ ዘናዊ በሞት ከተለየ ወዲህ በህዝባዊ ወያኔ ሃሪነት ትግራይና በአባል ድርጅቶቹ አመራሮች
መካከል አለመግባባትና ክፍፍል መንገሱ ላለፉት አራት አመታት ውስጥ ለውስጥ ሲናፈስ ከቆየ በኋላ ሃይለማሪያም ደሳለኝ
ሰሞኑን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሎአል።

የህወሃት ጠቅላይ ሚንስቴር ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኘው ሃይለማሪያም ደሳለኝ ትናንት ሚያዚያ 12 ቀን 2009 ዓመተምህረት ለመንግሥትና ለፓርቲ ጋዜጠኞች በሰጠው
መግለጫ እንደተናገረው በኢህአደግ አባል ድርጅቶች መካከል ያለው አለመግባባት በህወሃትና በብአዴን መካከል ብቻ ሳይሆን በህወሃትና በኦህዴድ እንዲሁም በህወሃትና በደኢዴድ
መካከልም ነው።
ሃይለማሪያም በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫው በተለይ በብአዴንና በህወሃት አመራሮች መካከል ያለው አለመግባባት አሁን የተፈጠረ ሳይሆን ገና ድርጅቶቹ በመሳሪያ ትግል ላይ ከነበሩበት
ጊዜ ጀምሮ የነበረ እንደሆነ ተናግሮአል። ሆኖም በመሳሪያ ትግሉ ወቅት ያልነበረውና ህወሃት የአዲስ አበባን ቤተመንግሥት ከተቆጣጠረ ቦኋላ የተፈጠረው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች
ዲሞክራሲያዊ ድርጅትም ሆነ ህወሃት ወደ አዲስ አበባ በመገስገስ ላይ በነበረበት የመጨረሻው ትግል ወቅት የተመሠረተው የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ ከመቸ
ጀምሮ ከህወሃት አመራር ጋር መላተም እንደጀመሩና አደባባይ ላይ የወጣው አለመግባባት መንስኤው ምን እንደሆነ ከመናገር ተቆጥቦአል።
አንዳንድ ለአገዛዙ ቅርበት ያላቸው የውስጥ ምንጮች እንደሚናገሩት በህወሃትና በአባል ድርጅቶቹ አመራሮች መካከል ለተነሳው አለመግባባት ዋናው ምክንያት የህወሃት አመራሮች
በአብዛኛው የተቆጣጠሩት ቁልፍ የመንግስት ሥልጣን ቦታዎችና ከአቅማቸው በላይ በዘረፋ ያካበቱት ሃብት ጉዳይ ነው።
ህወሃቶች በደም መስዋዕትነት አገኘን በሚሉት የመንግሥት ሥልጣንና በስልጣን ዘመናቸው ባካበቱት ሃብት ጉዳይ ላይ ከማንም ጋር መደራደር አይፈልጉም የሚሉ ምንጮች በዚህም
የተነሳ ቀደም ሲል ለግልጥቅማቸው ሲሉ የተጠጉዋቸው የሌሎች ድርጅቶች አመራሮች እንወክለዋለን ከሚሉት ህዝብ በየዕለቱ ከሚደርስባቸው ተቃውሞና ማሸማቀቅ ለመላቀቅ ሲሉ
እንዳንድ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ማንሳት በመጀመራቸው በመካከላቸው ያለው ልዩነትና አለመግባባት እየተባባሰ እንደሄደ ይገልጻሉ።
በተለይ የመለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በህወሃት አመራሮች ምርጫ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ወደ ጠቅላይ ሚንስትርነት ሥልጣን ከመጣ ወዲህ በመሳሪያ ትግል ወቅት ከፍተኛ
መስዋዕትነት የከፈሉትን የብአዴንን አመራሮችንና እወክለዋለሁ በሚለው ህዝብ ብዛት ወደ ከፍተኛው ሥልጣን እርከን መምጣት እንደነበረበት እየዋለ እያደረ ግንዛቤ እያገኘ
የመጣውን የኦህዴድ አመራሮችን በህወሃት ላይ ቂም እንዲቋጥሩ አድርጎአቸዋል የሚሉ አሉ።
የህወሃትን የበላይነት እንደቀድሞው ላለመቀበል በኢህአደግ አባል ድርጅቶች መካከል እያደገ የመጣው ልዩነት አደባባይ መውጣት መጀመሩን ከሚጠቁሙ ምልክቶች አንዱ በሆነው
በትናንትናው የሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በራሱ በሃይለማሪያም ጠቅላይ ሚንስትር መ/ቤት ሥር የሚገኘውና በአባይ ጸሃይ የሚመራው የኢትዮጵያ ፖሊሲ ምርምር
ማዕከል ያወጣው የጥናት ሪፖርት ውድቅ መደረጉ ነው። በአባ ጸሃይ ዳይሬክተርነት የሚመራው የምርምር ማዕከል በዚህ ሪፖርቱ ሥራ አስፈጻሚው አካል ከህግ በላይ እየሆነ መምጣቱ
በአገሪቱ ውስጥ እየተባባሰ ለመጣው የፖለቲካ ችግር ምክንያት መሆኑን በግልጽ ቋንቋ አስቀምጦአል። ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ምንስትሩ መሆኑ የሚነገርለት የፖሊሲ ምርምር ማዕከል
ለአንድ አመት ያህል አካሂጄዋለሁ በማለት ያቀረበውን የጥናት ሪፖርት ሃይለማሪያም ደሳለኝ አደባባይ ላይ ወጥቶ ስለ ሪፖርቱ የማውቀው ነገር የለም ማለቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።
አባይ ጸሃይ ሃይለማሪያም ደሳለኝን ካነገሱ የህወሃት መሪዎች አንዱ ሆኖ ሳለ የርሱን ሪፖርት ለማጥላላት አይዞህ ያለው ሌላ የህወሃት አንጃ መኖሩን የሚየመለክት እንደሆነ የፖለቲካ
ተንታኞች ይናገራሉ።
Source: Tensae Radio

The post ሕወሓቶችና የአጋር ድርጅት አመራሮች እየተናከሱ ነው (ተንሳኤ ራዲኦ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

አቶ ለማ ተናገሩ ግን ….- #ግርማ_ካሳ

$
0
0

“ስለ አዲሱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት፣ አቶ ለማ መገርሳ አንዳንድ ነገር እሰማለሁ። እስቲ ፕሬዘዳንቱ ተናገሩ ፣ ወይም አደረጓቸው የተባሉትን አንድ ሁእት ሶስት ነጥቦችን ጀባ በሉን..” ብዬ ነበር። አንድ የቪዲዮ ክሊፕ አገኘሁ። አቶ ለማ ለኢንቬርስተሮች ያደረጉትን ንግግር የያዘ ።

“ፍትህን ነው መጀመሪያ ማስፈን ያለብን። ፍትህን ለማስፈን ሕግን ነው ማስከበር ያለብን። በፕሮፖጋንዳና በጎድ ፋዘርስ (በዝምድና) እዚያም እዚህ ሰዉን በመያዝ የሚሰራ ነገር አያዋጣም። ለአንድ ሰሞን ሊያዋጣ ይችላል።” ሲሉ አቶ ለማ ይየተናገሩት ነገር አስደስቶኛል። ሌላ ምንም ነገር አያስፈልግም፤ የአገሪቷቷ ትልቁና ዋናው ችግር ይሄ የፍትህ መታጣት፣ አገራችን ሕግ ያለባት ሳይሆን ሕገ አራዊት የሰፈነባት መሆኗ ነው።

የኦሮሚያው ፕሬዘዳንት ንግግር ያደረጉት ለኢንቨርስተሮች ነው። በአማርኛ። ይሄም ያለ ምክንያት አይደለም። አማርኛ የኢትዮጵያ የፌዴራል ቋንቋ ብቻ ሳይሆን፣ የአማራው ክልል፣ የደቡብ ክልል፣ የጋምቤላ ክልል፣ የቤነሻንጉል ክልል፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ቋንቋ ነው። በኦሮሚያ ባሉ ትላልቅ ከተሞች (አዳማ፣ ጂማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሻሸመኔ ፣ አሰላ…..) የሚኖረው ህዝብ በስፋት የሚናገረው አማርኛ ነው። በጂማ 65%፣ በአዳማ 85%፣ በአሰላ፣ በቢሽፍቱ ….አብዛኛው ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ ነው። የአርሲ ዞን 21%፣ የምስራቅ ሸዋ ዞን 34%፣ የሰሜን ሸዋ ዞን 20%፣ የሰሜን ምእራብ ሸዋ ዞን 15%፣ የምስራቅ ወለጋ ዞን 15%፣ የሁሉ ጉርዱ ዞን 20%፣ የቡራዩ ዞን 45% ነዋሪ ኦሮምኛ አንደኛ ቋንቋቸው አይደለም።

ሆኖም በኦሮሚያ የሰፈነው ጸረ-አማርኛና አፋን ኦሮሞ ብቻ ፖሊሲ ብዙ ወገኖችን ያገለለ ብቻ ሳይሆን ያራቀም በመሆኑ፣ የንግድ፣ የቱሪዝም፣ የኢንቨሥትመንት እንቅስቃሴዎች ብዙ አይታዮም። በአዲስ አበባ እና አዳማ አካባቢ ካልሆነ በር ብዙ የኦሮሚያ ከተሞች እየወደቁ ነው። ሰው ነቀምቴን አልፎ አሶሳ ነው ኢንቨስት የሚያደርገው። መቱ፣ ደደር፣ ደምብቢ ዶሎ ፣ ሮቢ፣ ጊምቢ ..ዘመድ ለመጠየቅ ካልሆነ ለሌላ ጉዳይ ማንም አይሄድም። በአዲስ አበባ ድሬዳዋ መስመር ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች በፊት በባቡር እንቅስቃሴ፣ ንግድ ስለነበረ፣ ብዙ ይጠቀሙ ነበር። ገበሬዎች ያመረቱትን ፍራፍሬዎች እየሸጡ ብዙ ይጠቀሙ ነበር። አሁን ግን ያም ራሱ ደርቋል።

አቶ ለማ መገርሳ ” “ኢንቨስተሮችን ማበረታታ አለብን” ሲሉ ኢንቨርስተሮች በኦሮሚያ ኢንቨስት እንዲያደረጉ በርግጥ ፍላጎት ካላቸው ፣ በአማርኛ ጥሪ ማቅረባቸው ጥሩ ጅማሬ ቢሆንም፣ የኦሮሚያ መንግስት ዘር ሳይለይ በክልሉ ላሉ ሁሉም ነዋሪዎች መቆሙን በተግባር ማረጋገግጥ አለበት። በዚህ ረገድ ሊወስዳቸው የሚገባ መሰረታዊ ተግባራት ያሉ ይመስለኛል፡ ሁለቱን ልጥቀስ

1) አማርኛ ከኦሮሞኛ ጋር የክልሉ የሥራ ቋንቋ መሆን አለበት። የክልሉ የሥራ ቋንቋ ኦሮምኛ ብቻ እንዲሆን አለማድረግ ጸረ-ዲሞክራሲያዊ ፣ ጸረ-ሕዝብ፣ ዘረኝነት የተላበሰ አግላይ ከመሆኑም ባሻገር ፣ እንኳን ኢንቨስተርችን ሊስብ እንደዉም የበለጠ የሚያርቅ ነው። የኦሮሞ ማህበረሰብን ራሱ በኢኮኖሚ የሚያደቅ፣ ኦሮሞ የጠቀመ የሚመስል ግን ኦሮሞውን ራሱ የሚጎዳ ነው። ይሄ በኦሮሚያ ክልል ያለው ለ15 አመታት የተዘረጋው ጸረ-አማርኛ ፖሊሲ ምን ውጤት አመጣ? ለድሃው ኦሮሞ ምን ጠቀመው ?

(እዚህ ጋር አንድ ነገር አንርሳ፣ አፋን ኦሮሞ የክልሉ የስራ ቋንቋ መሆኑ ይቀጥላል። አምርኛማ አብሮ ይጨመር ነው እያልን ያለነው።፡አማርኛ የስራ ቋንቋቋ በመሆኑ የኦሮሞዉን መብትንና ጥቅም አምስት ሳንቲም አይቀንስም። ኦሮምኛ የማይናገረው ዜጋን መብት ግን ያረጋግጣል። ሌላው ማህበረሰብ መብሩ ተረግጦ እንዲኖር ፍላጎት ከሌለ በስተቀር አማርኛ የሥራ ቋንቋ መሆኑን ማንም ሊቃወም አይገባም)

2) በኦሮሚያ ሕግ መንግስት በአንቀጽ 8፣ የኦሮሚያ ባለቤት ኦሮሞው እንደሆነ ነው የሚደነግገው። ያ ማለት ሻሸመኔ ተወልዶ ያደገ አንድ ሰው “ኦሮሞ ነኝ” ካላላ፣ ከርሱ ይልቅ፣ ስለሻሸመኔ የሚያገባው፣ ከሻሸመኔ የትናየት እዚያ ማዶ ነጆና፣ አወዳይ ተወልዶ ያደገ፣ ከሻሸመኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላው፣ ሻሸመኔ የት እንዳለችም የማያወቅ፣ ግን ራሱን ኦሮሞ ብሎ የሚጠራ ሰው ነው።

ይሄ አይነት አንድን ክልል ለአንድ ዘር ሰጥቶ በዚያ የሚኖሩ ከዚያ ዘር አይደሉም የሚባሉትን ዜጎችን እንደ መጤ ወይንም እንግዳ የመቁጠር ፖለቲካ የአፓርታይድ ዘረኛና የኋላ ቀር ፖለቲካ ነው።

አቶ ለማ መገርሳ ይሄን አንቀጽ በማስተካከል ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ሳትሆን ኦሮሞዉን ጨመሮ፣ የነዋሪዎቿ ሁሉ እንደሆነች ማረጋገጥ አለባቸው። አለበለዚያ ራሳችቸውን ኦሮሞ ብለው የማይጠሩ ዜጎች፣ “ነገ አገራችሁ አይደለም፣ ኦሮሞ አይደላችሁምና ቅድሚያ ለኦሮሞ ነው፤ ለቃችችሁ ውጡ” እንደማይባሉ የሚያረጋግጥላቸው የሕግ ዋስትና አይኖራቸውም። አንደኛ ላለፊኡት 25 አመታት ያየነው ይሄንኑ ነው። ኦሮሞ ስላልሆኑ ብዙ ወገኖች ከኦሮሚያ በሃይልና በጭካኔ ተፈናቅለዋል። የዘር ማጽዳት ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል።፡ሁለተኛ “Ethiopians out of Oromia” ማን እንዳለ ሁላችንም የምናወቀው ነው። ጃዋር መሐመድ። ይህ ሰው ብዙ ተከታዮች አሉት። በርሱ ፖለቲካ የሰከሩ ። እነዚህ የጃዋር ተከታዮች በጣም አደገኞች ናቸው።

በመሆኑም አቶ ለማ ፍቅርን፣ መተማመንን፣ አንድነትን ማስፈን አለባቸው። ወደ ትክክለኛው የኦሮሞ ባህል መመለስ እንደሚገባ ማስተማር አለባቸው። የኦሮሞ ባህል የጉዲፈቻ ባህል ነው። ሌላውን እንደራሱ አድርጎ የመቁጠር ባህል። ኦሮሞው ሌላው ማህበረሰብ በኦሮሚያ ዉስጥ ከኦሮሞው እኩል መሆን አለበት። አቶ ለማ ያንንን ማረጋገጥ አለባቸው።

The post አቶ ለማ ተናገሩ ግን ….- #ግርማ_ካሳ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

ኢሕአዴግ ያንዣበቡበትን ብዥታዎች አጥርቶ ወደ ጤንነት መመለሱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ

$
0
0
  •  በብሔራዊ ድርጅቶች አመራሮች መካከል ጥርጣሬ ተከስቶ እንደነበር ይፋ አድርገዋል
  • መጠራጠሩ ቀጥሏል የሚል መረጃ ካለ በቀጣይ እንደሚገመገም ጠቁመዋል

ገዥው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) አንዣበውበት የነበሩ ውስጣዊ መደናገሮችን በማጥራት ወደ ጤናማነት መመለሱን፣ የግንባሩ ሊቀመንበርና የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚያዝያ 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ፣ ኢሕአዴግን በፈጠሩት ብሔራዊ ድርጅቶች አመራሮች መካከል በዓይነቱ ሰፋ ያለ ‹‹መጠራጠር›› ተከስቶ እንደነበር በግልጽ ይፋ አድርገዋል፡፡ በግንባሩ ውስጥ የአማራ ብሔር የወከለው ፓርቲ ብአዴን ከወር በፊት ባሳተመው መጽሔቱ፣ እህት ድርጅቱ የሆነው የትግራይ ብሔርን በሚወክለው ሕወሓት ላይ መጠራጠር ውስጥ ገብቶ እንደበር ይፋ አድርጎ ነበር፡፡ ይህንን መሠረት አድርጎ ኢሕአዴግ አሁን ጤነኛ እንደሆነ ጋዜጠኞች ጥያቄያቸውን ለአቶ ኃይለ ማርያም አቅርበዋል፡፡ ‹‹የነበሩ ብዥታዎች በአብዛኛው የተቀረፉ በመሆናቸው አሁን ድርጅቱ (ኢሕአዴግ) እጅግ ጤናማ ነው፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ብአዴን በሕወሓት ላይ ተፈጥሮበት ስለበረው መጠራጠር በልሳን መጽሔቱ መግለጹ ተገቢ መሆኑን የተናገሩት አቶ ኃይለ ማርያም፣ ብዥታውና ጥርጣሬው ተከስቶ የነበረው ግን በሁለቱ ድርጅቶች አመራሮች መካከል ብቻ እንዳልነበር በዝርዝር አመላክተዋል፡፡

‹‹በብሔራዊ ድርጅቶቹ አመራሮች መካከል ተፈጥሮ የነበረው መጠራጠር ደረጃው የተለያየ ቢሆንም በኦሕዴድና በሕወሓት፣ በኦሕዴድና በብአዴን፣ እንዲሁም በደኢሕዴና በብአዴን መካከልም የተፈጠረ ነው፤›› ብለዋል፡፡

በብሔራዊ ድርጅቶቹ መካከል ተከስቶ የነበረው መጠራጠርና ብዥታ አንዳንዱ በመለስተኛ እውነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ያስረዱት አቶ ኃይለ ማርያም፣ አንዳንዶቹ መነሻቸው ጥርጣሬ አንዳንዶቹ ደግሞ ምንም ‹‹እውነት ላይ ያልተመሠረቱ›› እንደነበሩ አስረድተዋል፡፡

በአመራሮች መካከል መጠራጠሮች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ፣ ተመሳሳይ ሁኔታዎች ከዚህ ቀደምም በትጥቅ ትግሉ ወቅት ጭምር ፓርቲውን ገጥመውት ያውቅ እንደበር ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን መሰል ችግሮች ሲከሰቱ የሚፈቱበት ግልጽ የአሠራር ባህልን የታጠቀ በመሆኑ በቀላሉ እንደሚፈቱ ገልጸዋል፡፡

ልክ ከዚህ በፊት በተፈቱበት መንገድ ግልጽ ውይይት በማድረግ የተፈታና መተማመንን የተፈጠረ በመሆኑ፣ በአስተማማኝ ሁኔታ ፓርቲው ወደ ጥንካሬው መመለሱን ጠቁመዋል፡፡

በቅርቡ በኢሕአዴግ ምክር ቤት በተደረገ ግምገማ በድርጅቶች አመራሮች መካከል ያለው ግንኙነት በእጅጉ መሻሻሉን ማረጋገጥ እንደተቻለ ጠቁመዋል፡፡ ‹‹አሁንም መጠራጠሩ ቀጥሏል የሚል ካለና በመረጃ ላይ የተመሠረተ ከሆነ ጥሩ ነው፡፡ እኛም በቀጣይነት እንገመግመዋለን፡፡ በእኛ በኩል ግን ክፍተቶችን በመዝጋት አብሮ መሥራት ይቻላል የሚል መተማመን ላይ በመድረስ ከመቼውም በላይ አንድነታችን ተጠናክሮ እንዲወጣ አድርገናል፤›› ብለዋል፡፡

የመቀልበስ አደጋ

በቅርቡ በአገሪቱ ተከስቶ የነበረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት መሠረታዊ ምክንያቶች የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ ሥልጣንን ለግል ጥቅም ማዋል፣ ሥራ አጥነት፣ ለሕዝብ ጥያቄዎች በአፋጣኝ መፍትሔ አለመስጠት የመሳሰሉት መሆናቸውን ኢሕአዴግ በማዕከላዊ ኮሚቴው እንዲሁም በምክር ቤቱ መለየቱ ይታወሳል፡፡ በመፍትሔነትም ‹‹በጥልቀት መታደስን›› በማስቀመጥ በየደረጃው እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው የሰሞኑ ቆይታም በጥልቀት የመታደሱ እንቅስቃሴ ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ ተከስቶ የነበረው ሥጋት በጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄው መፈታቱን መንግሥት እየገለጸ መሆኑን መሠረት በማድረግ፣ ሥጋቶቹ ተመልሰው ሊያገረሹ ወይም የተገኘው መረጋጋት እንደማይቀለበስ እርግጠኛ መሆን ይቻል እንደሆነ ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡

‹‹በአገሪቱ ተከስተው የነበሩ ሥጋቶች በጥልቅ ተሃድሶው መቀልበሳቸው እርግጥ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ማንኛውም የፖለቲካ ሒደት አስተማማኝ መሆኑ የሚለየው በሕዝቡ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በመረዳት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

‹‹መቀልበሳቸውን የምናረጋግጠው ከሕዝባችን አመለካከት እንጂ ረብሻውን ከሚፈጥሩ ጥቂት ኃይሎች ተነስተን አይደለም፡፡ በዚህ ግምገማችን እናምናለን፣ ምክንያቱም ሕዝባዊ መንግሥት እንደ መሆናችን መጠን መነሻችንም መድረሻችንም ሕዝቡ ነው፤›› ብለዋል፡፡

አሁን የተገኘው ሰላም የማይቀለበስ ደረጃ ላይ ቢሆንም አጠናክሮ ወደፊት መቀጠል እንደሚያስፈልግ ፓርቲው መገምገሙን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ምክንያቱም እኛ ካበላሸነው ሊበላሽ ይችላል፤›› ብለዋል፡፡

አስፈጻሚው አሁንም ችግሮች አሉበት መባሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በተሃድሶ እንቅስቃሴው ከፍተኛ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑንና እንዲሁም በአገሪቱ ተፈጥረው የነበሩ ሥጋቶች በተሃድሶው መቀልበሳቸውን ቢገልጹም፣ በመንግሥት የምርምር ተቋም የቀረበው ሪፖርት ግን ይህንን አያረጋግጥም፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ እንዲሆን ተደርጎ ከሦስት ዓመት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል በመጋቢት ወር ይፋ ያደረገው የጥናት ውጤት ይህንኑ ያረጋግጣል፡፡

‹‹መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንፃር የሕዝብ ተሳትፎ ማነቆዎች፣ መንስዔዎችና የመፍትሔ ሐሳቦች›› በሚል ርዕስ ለአንድ ዓመት ሲያጠና የቆየውን ሪፖርት አቅርቧል፡፡

በዚህ ጥናት ውስጥ ግኝት ሆነው የቀረቡት በተፅዕኖ ሥር የመውደቅ ጉዳይ ነው፡፡ በተፅዕኖ ሥር ወደቁ ከሚላቸው መካከል ደግሞ መንግሥትን የመቆጣጠር ኃላፊነት የተጣለባቸው ምክር ቤቶች ናቸው፡፡ ‹‹ዜጎች በግላቸውም ሆነ በማኅበር ተደራጅተው ወይም ባላቸው ኃላፊነት በሚመለከታቸው ጉዳይ ሲሳተፉና ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ ከአስፈጻሚው አካል በሚደርስባቸው ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ ጥቃት፣ አድሎዓዊነት፣ ወዘተ ከፍተኛ እንደሆነ ጥናቱ ይጠቁማል፡፡

ሦስቱ የመንግሥት አካላት ተናበው አለመሥራት፣ በአስፈጻሚ አካላትና በአፈ ጉባዔዎች ዘንድ የሥልጣን ግጭት መኖሩ፣ ተግባብቶ በቅንጅት አለመሥራት፣ በቋሚ ኮሚቴዎች ያለመስማማትና በቅንጅት ያለመሥራት፣ ወዘተ በጥናቱ ተጠቅሰዋል፡፡

ጥናቱ ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓባይ ጸሐዬ፣ አስፈጻሚው በሁሉ ነገር ላይ የበላይ መሆን እንደሚፈልግ ተናግረዋል፡፡

ለምክር ቤት የሚቀርበው ሕግ፣ ሹመት፣ ሪፖርት፣ በጀት የሚፈጸመው በጥድፊያ ነው ያሉት አቶ ዓባይ፣ በሰዓታት ውስጥ አስፈጻሚው እንዲፀድቅ እንደሚፈልግና ሕዝቡም በዚህ የተነሳ ለውጥ አይመጣም ብሎ እንደሚያምን ተናግረዋል፡፡

ይህንን ክፍተት ድርጅታዊ አሠራርም የሚገታው እንደማይመስላቸው የተናገሩት አቶ አቶ ዓባይ፣ ‹‹በድርጅታዊ አሠራር ችግሩን ለመቅረፍ መጀመሪያ ኢሕአዴግ መስተካከል አለበት፤›› ማለታቸውን ሪፖርተር መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆነው የኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ባቀረበው በዚህ ጥናት ላይ በሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ሪፖርቱን እንደማያውቁት ተናግረዋል፡፡

‹‹የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል አቀረበ የተባለው ሪፖርት እኔ ጋ የደረሰ አይደለም፡፡ ስለዚህ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ የለኝም፤›› ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከፓርላማ ክትትልና ቁጥጥር ጋር የጥናት ማዕከሉ አቀረበ ስለተባለው ሰምተው ኃላፊዎቹን እንዳነጋገሯቸው ገልጸዋል፡፡

‹‹ጠይቄያቸው ነበር የፌዴራል ፓርላማን የሚመለከት አይደለም ነው ያሉኝ፡፡ ስለዚህ የተሳሳተ መረጃ ነው የተላለፈው፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በማግሥቱ ሐሙስ ሚያዝያ 12 ቀን 2009 ዓ.ም. የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የምርመራ ሪፖርት ፓርላማው ያደመጠ ሲሆን፣ በዚሁ ዕለት የተገኙት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሩ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያቀረበው ሪፖርት ለብዙ ጉዳዮች መልስ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

‹‹በኢትዮጵያ እየተፈጠረ ያለው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ክትትልና ቁጥጥር (Check and Balance) እንዲረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነ፣ ተጠያቂነት ለማስፈን የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚገታ ግዙፍ ችግር እንደሌለ፣ አስፈጻሚው እዚህም እዚያም ጣልቃ እየገባ ተፅዕኖ እየፈጠረ፣ አልጠየቅም ብሏል፣ አስቸግሯል ብለው ለሚረዱ አንዳንድ ወገኖች ምላሽ የሚሰጥ ሪፖርት ነው፤›› ብለዋል፡፡

የክልሎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና ሥጋቶች

በፌዴራላዊ ሥርዓት አወቃቀር መሠረት ክልሎች ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ የማስተዳደር መብት እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ በኢትዮጵያም በሕግ የተረጋገጠ ነው፡፡ ነገር ግን በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት በኢትዮጵያ አንድ ወጥ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የመንደፍና ተግባራዊነቱን የመከታተል ኃላፊነት የተሰጠው ለፌዴራል መንግሥት መሆኑ ይጠቀሳል፡፡ የሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ የመጨረሻ ግብ ተደርጎ የሚቆጠረውም በኢትዮጵያ አንድ ወጥ የኢኮኖሚና ፖለቲካ ማኅበረሰብ መፍጠር ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ክልሎች ያላቸውን ሉዓላዊ መብት በመጠቀም ግዙፍ ኢኮኖሚያዊ ፕሮጀክቶችን “Public Private Partnership” (የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የጋራ ኢንቨስትመንት) ሞዴል ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል፡፡

ይህ ሞዴልና በክልሎቹ የተጀመሩት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ከፌዴራል መንግሥት ዕቅዶች ማለትም ከአጠቃላይ የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ ከዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ፕሮራሞች ጋር ምን ያህል እንደሚጣጣሙ ሪፖርተር ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር፡፡

ክልሎች የጀመሩት ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን ለማቋቋም እንጂ፣ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የጋራ ኢንቨስትመንት (Public Private Partnership) ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም ብለዋል፡፡

የጋራ ኢንቨስትመንቱ በሕግ መመራት እንዳለበት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌዴራል መንግሥት የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የጋራ ትብብር ፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ እያረቀቀ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

‹‹በሕግና በሥርዓት የሚመራ አገር ነው፣ ስለዚህም ምንም ዓይነት ሥጋት የግል ባለሀብቶች ላይ ሊያድር አይገባም፡፡ ይኼንን ላረጋግጣላችሁ እፈልጋለሁ፤›› ሲሉ በዚህ የክልሎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ፍርኃት ያደረባቸው የኢንቨስትመንት ፈቃዳቸውን ከፌዴራል መንግሥት ያወጡ ባለሀብቶች እንዳይሠጉ አሳስበዋል፡፡

‹‹በቀጣይ ግን የተባለው ነገር ምን እንደሆነ የምናየው ይሆናል፤›› ሲሉ አቶ ኃይለ ማርያም ተናግረዋል፡፡

በዚህ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የጋራ ትብብር የኢኮኖሚ ማዕቀፍ ሥራ የጀመሩ ክልሎች መካከል የኦሮሚያ ክልልና የአማራ ክልል ናቸው፡፡ የኦሮሚያ ክልል በተጠቀሰው የኢኮኖሚ ማዕቀፍ እስካሁን ወደ ሰባት ቢሊዮን ብር በሚጠጋ የኢንቨስትመንት ካፒታል ሁለት ኩባንያዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ ከእነዚህም መካከል ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት ለተባለው ኩባንያ የአንድ ቢሊዮን ብር የአክሲዮን ሽያጭ ሲያካሂድ፣ በተመሳሳይ ኬኛ ቤቨሬጅስ ለባለው 5.7 ቢሊዮን ብር ለሚያወጣው የመጠጥ ኢንዲስትሪ 1.2 ቢሊዮን ብር አክሲዮን ሸጧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የክልሎች የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ ማዕቀፍን በተመለከተ በገለጹ በማግሥቱ ደግሞ፣ የአማራ ክልላዊ መንግሥት በተጠቀሰው የኢኮኖሚ ማዕቀፍ ካቀዳቸው 22 ኩባንያዎች ውስጥ የመጀመሪያው የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡

የአማራ ክልል በተጠቀሰው ማዕቀፍ ይፋ ያደረገው ዓባይ የኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማኅበር የተባለ ሲሆን፣ ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 22 ታላላቅ ኢንዲስትሪዎችን ለመገንባት ዕቅድ ይዟል፡፡

ዜና- ሪፖርተር

 

The post ኢሕአዴግ ያንዣበቡበትን ብዥታዎች አጥርቶ ወደ ጤንነት መመለሱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Calling your attention regarding Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus (Amhara Professionals Union)

$
0
0

 who is one of the finalists for the assignment of WHO Director General. Dr. Ghebreyesus is an individual suspected of a crime against Humanity in his home country.

Dear Sir/Madam,
The Amhara Professionals Union (APU) presents you objective facts about Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus proving that he is unfit to be one of the finalists for the appointment of WHO Director General, let alone to win and assume the role in few months.
Amharas are one of the most populous ethnic groups in Ethiopia comprising over one third of population. The Amhara Professionals Union (APU), which is a non-profit advocacy group for the causes related with the Amhara, is a Washington D.C. based Civic organization comprised of Medical Doctors, Scientists, Lawyers and other Professionals of Amhara descent all over the world organized to defend the rights and interests of the Amhara people against the heinous crimes the current TPLF/EPRDF led regime has been committing for over twenty five years. APU believes that not only is Dr. Ghebreyesus a very poor choice for the job, he is also an embarrassment to the core values of WHO.
One of the core principles in the constitution of WHO reads: “Informed opinion and active co-operation on the part of the public are of the utmost importance in the improvement of the health of the people”. We at the APU share the following statement about Dr. Ghebreyesus’s candidacy and have attached a paper that exhibits the candidate’s overall record at the helm of the Ministry of Health and Foreign Affairs of Ethiopia in more than a decade.
If we were to consider only our Ethiopian or African background, we, members of the Amhara Professionals Union (APU), could have simply supported the candidacy of Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus for WHO’s Director General position. However, we believe that WHO, as an International organization with extended reach throughout the world, should be led by someone who has a proven record of accomplishment of serving human beings without prejudice and shows respect to all human kind irrespective of their ethnic background or religion. As APU, we evaluate individuals based on their competence and past track records regardless of their ethnic, religious or regional background. Dr. Ghebreyesus should be judged based on his role as Minister of Ethiopian Federal Ministry of Health (FMOH), Minister of Foreign Affairs and as a politburo member of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), a political party that is the most powerful within the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) led government of Ethiopia.
Human Rights Watch and many other National and International Organizations have widely criticized TPLF/ EPRDF led government for crimes against Humanity and atrocities towards the Ethiopian people. The attached document provides objective evidences why APU believes Dr. Ghebreyesus lacks the competence, impartiality, accountability and transparency that we feel are required for a position of this magnitude. The document highlights the following:

•    The candidate has failed to be transparent by forcing the Ethiopian Ministry of Health to not report and cover up a Cholera epidemic throughout his tenure by simply renaming a deadly epidemic as an Acute Watery Diarrhea (AWD) even after the diagnosis of Vibrio Cholerae was confirmed. His priority in deciding so was to conceal the impact a public admission of Cholera epidemic might have on Tourism and image of his Party rather than protecting the international community and attempting to reach out to the affected areas. Such a sad error due to lack of judgment resulted in a nationwide epidemic.

•    The candidate has treated his own citizens differently based on their ethnicity contrary to WHO’s goal of building a better, healthier future for all people throughout the world. While WHO strives to better the lives of underserved and marginalized communities, Dr. Ghebreyesus who descends from Tigre ethnic group disfavored the “Amhara Regional State” through poor health care. For instance, disproportionately high mortality coupled with selective application of contraceptives use has led to a selective reduction of the growth rate of the Amhara people. Such disparities were created and gaps increased across all measures of health in his leadership tenure. Of particular importance is the unexplained 2.5 million decrease in the Amhara population under his healthcare leadership. The Amharas were victimized and punished due to their ethnic background.

We understand that accountability, integrity, transparency and honesty are among WHO’s core ethical principles. Sadly, Dr. Ghebreyesus has failed to meet all these standards while he assumed his role in the aforementioned posts. Therefore, we at the APU, believe that it would be a travesty of justice if WHO awards its highest position to a person who violated WHO’s core principles and whose deliberate actions and inactions have claimed the lives of millions of Amhara people as well as other Ethiopians.

We urge WHO members to look at the attached review of the data that have been published by the Ethiopian FMOH, and learn how Dr. Ghebreyesus and his associates systematically discriminated against the Amhara people in Ethiopia while preferentially treating others with a high level of open partiality. We at the APU thank you in advance for the attention you give to the attached document entitled “International Organizations Leadership Recruitment Policies:  the Failed Experiment of Dr. Tedros A. Ghebreyesus Candidacy for WHO Director General position”.

If you have any questions or need further explanations, please do not hesitate to contact us at any time.

Sincerely,

Amhara Professionals Union (APU)
Washington D.C., USA

The post Calling your attention regarding Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus (Amhara Professionals Union) appeared first on Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!.

ፎረም 65፦ የቴዲ አፍሮ ሚና

$
0
0

ባለፈው ሳምንት ቴዲ አፍሮ የለቀቀው “ኢትዮጵያ” የተሰኘው ነጠላ ዜማ በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ትኩረት ስቦ ሲያወያይና ሲያወዘግበን ቆይቷል። በፍረም 65 የቴዲ አፍሮን ሚና በሚምለከት ከአቶ ግርማ ጉተማ እና ከአቶ ግርማ ካሳ ጋር አጭር ውይይት እናደርጋ…

ፎረም 65፦ የቴዲ አፍሮ ሚና

 

 

The post ፎረም 65፦ የቴዲ አፍሮ ሚና appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ!! 87ኛ ዓመት

$
0
0

መግባቢያ!

የሀገረ-ኢትዮጵያ የእውቀት አደባባይ በአስፈሪ ዝምታ ተውጧል። ምሁራኖቻችን ከህዝባዊ ተዋፅኦ አፈግፍገዋል። የአደባባይ ምሁራን ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት በመናመን ላይ ባሉ ብርቅዬ የዱር እንሰሳት መመሰል ከጀመረ ዓመታት አልፈዋል። ቁጥራቸው የበዛ ምሁራን አገዛዙ በፈጠረው የጥቅመኝነት ፖለቲካ ጥላ ስር መጠለል ምርጫቸው ሆኗል። ጥቂት የማይባሉት ደግሞ የባዕድ አገር ስደትን መርጠዋል። ሕዝባዊ መድረኮቻችንን ፋይዳ ቢስ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮችና በተዛቡ የታሪክ ትርክቶች፤ በዘውጋዊ አጥርና አገራዊ ከፍታን መፍጠር በማይችሉ ሙግቶች ተውጠዋል። ዕድሮችና የመረዳጃ ማህበራት ሳይቀር ዘውጋዊ ቅርጽ (አጥር) ሰርተዋል።

አገሪቱ ለገባችበት የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ቅርቃርና ለማህበራዊ ችግሮቻችን መፍትሔ ይሰጣሉ ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው የፖለቲካ ልሂቃን አገሪቱን ለአራት አስር ዓመታት ክፉኛ የናጣትን “የብሔር ጥያቄ” በማንገብ ወደ ማንነት ቅርጫታቸው በመጠቃለላቸው፤ የአገራዊ ችግር ባህሩን በማሻገር ወደ አርነት ከፍታ የሚያወጡን ሙሴዎች መምጫ ጊዜን እንደ ምፅአት ቀን የማይታወቅ አድርጐታል። በአናቱም አገዛዙ ከቀን ወደ ቀን አምባገነናዊ አገዛዝን በምልዐት መተግበር በመጀመሩ የጓዳ እንጂ የአደባባይ ፖለቲከኞችና ሕዝባዊ ተቆርቋሪነት ያደረባቸው ምሁራን ከፖለቲካ አፀዱ ተመናምነዋል። “አለን” የሚሉን ፖለቲከኞች የጓዳ ገመናቸውን መሸፈን አቅቷቸው በየአደባባዩ መዘላለፍ የሰርክ ተግባራቸው ሆኗል።

በርግጥ ለዘር ያህል የሚሆኑ ጥቂት የአደባባይ ምሁራን አሉ። ከትላትን እስከ ዛሬ መሰረታዊ ግባቸውን ያልሳቱ፤ የዚህችን አገር የውድቀትና የስኬት ታሪኮች መርምረው የደረሱበትን ድምዳሜ ካለ ፍርሃት ወደ አገሪቱ የእውቀት አደባባይ የሚያወጡ፤ የዘመን ዕንቁዎች አሉ። ክፋቱ ከጠመዝማዛው የኢትዮጵያ ታሪክ ቋጠሮ እና ከብዝሃነታችን አኳያ የጥቂት ለዛውም በጣት በሚቆጠሩ የአደባባይ ምሁራን ተሳትፎ ብቻ አገዛዙ ያነበረውን የሴራ ፖለቲካ ሰንሰለት ለመበጣጠስ አለመቻሉ ነው።

የምሁራኑ ከአደባባይ መራቅና አገዛዙ በተጠና መንገድ የፈጠረው አገራዊ ድብርት በጋራ ተጋምደው ወደ ቁልቁለት መንገድ ያንደረድሩን ጀምረዋል። እንደ አገርም ከፍታው ርቆናል። ያም ሆኖ የአገዛዙን ቅጥፈትና የለየለት አምባገነንነት ካለ ፍርሃት የሚተቹ ምሁራን ለዘር ያህል አሉ። በዚህ ፅሁፍ “ለሥልጣን እውነትን የመናገር” ግዴታን በበቂ ሁኔታ እየተወጣ ስላለው ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በጥቂቱ እናነሳለን። የመስፍንን ትሩፋቶችና አካዳሚያዊ ተዋፅኦዎች በአንድ ፅሁፍ ማብራራት የሚቻል አይደለም። ግና ስለመስፍን የአደባባይ ምሁርነት አብዝተን እናወራለን። እውነታውንም ለትውልድ እናካፍላለን። የወደደ የመስፍንን የትውልድ ዋርካነት አስተውሎ ይጠለል፤ ያልወደደም ከመስፍን ፅናትንና ብርታትን ይማር!!

መስፍን ትልቁ ሰው!

በኤሌክትሮኒክስና በህትመት ሚዲያው (መፅሐፍትን ሳንረሳ) ስለ ግለሰቦች የሚናገሩና የሚጻፉ ፅሁፎች እንደተናጋሪው ወይም እንደ ፀሐፊው የዕድሜ ደረጃ፣ የግል ቀረቤታ፣ አመለካከት ወዘተ የተነሳ “አንተ” ወይም “አንቱ” ሊባል ይችላል። የዚህ ፅሁፍ  አዘጋጅ  ለፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም ካለው ቅርበት፣ ፍቅር፣ አድናቆትና ከበሬታ የተነሳ “አንተ” እያለ ለመጥራት ወዷል፤ ማዕረጉንም በአገር በቀሉ “የኔታ” ተክቶታል። (እንደ እውነቱ ከሆነ የዕውቀት አባት “አንተ” ሲባል፣ ከጥልቅ ከበሬታ ጋር መሆኑን ልብ ይሏል።)

ከግላዊ ጥቅም በዘለለ በርከት ያሉ አካዳሚያዊ የምርምር ሥራዎችን የሰራ፣ አገራዊ ፋይዳ ባላቸው ሕዝባዊ ተዋፅኦዎች የራሱን አሻራ ማሳረፍ የቻለና፣ የሰው ልጆች ሰብዓዊ መብት እንዲከበር አብላጫ የዕድሜ ዘመኑን ያሳለፈ፣ ዛሬም በእርጅና ዘመኑ የሚያምንበት ሃሳብ በአደባባይ የሚናገር (የሚፅፍ) ብርቱ ሰው የኔታ መስፍን ወ/ማርያም!

የእኔን ዘመን አምላጭ ትውልድ ሳይጠየፍና ሳይንቅ ምሁራዊና አባታዊ ተግሳፁን “በአስተዋይ ገላማጭነት” ወደ ትውልዱ ማድረስ የቻለው ይህ የዘመን ዕንቁ ያመነበትን ነገር በአደባባይ በመናገር ወደር የሌለው ኢትዮጵያዊ የአደባባይ ምሁር ነው። የመስፍንን ትጋትና አይደክሜነት ያስተዋሉ የዘመን ተጋሪዎቹም ሆኑ ተከታዮቹ በአንድ ድምፅ “የማይዳፈን ጩኽት፤ የማይከሽፍ ተስፋ ባለቤት” ይሉታል።

ዲያቆን፣ ጂኦግራፈር፣ ፈላስፋ፣ ሕዝባዊ ታሪክ ፀሃፊ፣ ገጣሚ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ . . . የሆነው የኔታ መስፍን ከአስራ ስድስት በላይ የምርምር መፅሐፍቶችን በማሳተም፤ በድርቅ ፣ ረሃብና መልከዓ ምድር ዙሪያ የሚያጠነጥኑ በርከት ያሉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በአለም አቀፍ ጆርናሎችና ዩኒቨርሲቲዎች በማቅረብ፣ ባለፉት አምስት አስርታት ውስጥ ለረዥም ጊዜያት በተለያዩ ጋዜጦችና መፅሄቶች በአምደኝነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በማህበራዊ ድረገጽ (ፌስቡክ) ጭምር በመሳተፍ አገራዊ እሴትን በሚጨምሩ ፅሁፎቹ ያደፈውን ለማንፃት፣ የጎበጠውን ለማቃናት፤ የተናደውን ለመካብ፤ . . . በአያሌው የደከመ፤ የነፃው ፕሬስ ግብዓተ መሬት ከመከናወኑ በፊት የነፃው ፕሬስን በአግባቡ በመጠቀም እንዲሁም የማህበራዊ ድረገጽ የቴክኖሎጂ በረከትን ለአገራዊ ግንባታ በማዋልና አገዛዙን በሃሳብ በመሞገት ከዕድሜ ዘመኑ አኳያ የእርሱን ያህል የታገለና የደከመ የአደባባይ ምሁር መኖሩ ያጠራጥራል።

የፊታችን ሰኞ ሚያዚያ 16 ቀን 2009 ዓም 87 ዓመት የልደት በዓሉን የሚያከብረው ሞጋቹ ምሁር፣ ብዙዎች ሊገፉትና ሊወጡት የማይቻል የሚመስለውን የህይወት ውጣ ውረድ አሳልፏል። ከትላንት እስከ ዛሬ በማይጣረሱ መሰረታዊ ግቦቹና ከብረት በምናነጽረው ሥነ-ምግባሩ ለዜጐች ሰብዓዊ መብት መከበር፣ እኩልነት፣ ፍትህና ዘላቂ ሰላም በአይበገሬነት መታገል ችሏል። መስፍን ኢትዮጵያዊ ወገኖቹን በዘውግ መነፅር ሳይሆን በዜግነት ማዕቀፍ የሚመለከት የመርህ ሰው ነው።

የኔታ መስፍን የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪውን በምስራቁ (ህንድ)ና በምዕራቡ (አሜሪካ) አለም እንደ መስራቱ የታሪክ አተያዩና አረዳዱን ከፃፋቸው መፅሃፍት አኳያ ስንመረምር ሰውዬው አንዳችም የውጭው አለም ተፅዕኖ የሌለበት፤ ነጮቹ በቀደዱለት ቦይ ለመፍሰስ የማይዳዳው ምሁር እንደሆነ እንረዳለን። አድርባይነትና ወላዋይነት ከመስፍን ስብዕና ጋር ተዛምዶ እንደሌላቸው እና ሰውየው ለእውነት የሚሰጠውን ዋጋ ለማሳየት “ባህል፣ ሥልጣንና አገዛዝ በኢትዮጵያ” እንዲሁም “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” በተሰኙት መፅሃፍቶቹ ይዘት (በይበልጥ) መረዳት ይቻላል።

የመስፍን የአካዳሚ ስራዎች በድርቅ፣ ረሃብ፣ የመሬት አስተዳደር፣ ካርታ ሥራ፣ . . .  ወዘተ ዙሪያ የሚያተኩሩ የበሰሉ ሥራዎች ናቸው። በነገራችን ላይ በአገሪቱ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጂኦግራፊ መማሪያና አጋዥ መፅሐፍቶች የመስፍንን የምርምር ሥራዎች ቀዳሚ ማጣቀሻ ያደረጉ ናቸው። መስፍን ከአካዳሚያ ሚናው በተጨማሪ በአገራዊ ጉዳዮች የሚያተኩሩ በምርምር የተደገፉ ሥራዎችንም የ(ሚ)ሰራ የአደባባይ ምሁር ነው። “አደጋ ያንዣበበት የአፍሪቃ ቀንድ ስጋት” በሚለው መፅሃፉ ስለ ሽብርተኝነትና የርስ በርስ ጦርነት ያነሳቸው ጭብጦች አለም አቀፋዊ ተሞክሮ ያላቸው ተጨባጭ ስጋቶች ሆነው እናገኛቸዋለን።

የኔታ መስፍን በመፅሃፍቶቹ የሚያነሳቸው ጉዳዮች ትላንትን መነሻ ያደረጉ፣ ዛሬን በቅጡ የፈተሹና ለነገ መውጫ ጫፎችን የሚጠቁሙ የምርምር ስራዎች ናቸው። ከልክ በላይ የተወጠረው የዘውግ ፖለቲካ እንደ አገር የሚያስከትለውን ችግር፣ የመሬት ፖሊሲውን ክሹፍነት፣ የህወሓትን የጠቅላይ ዝግ አምባገነናዊ አገዛዝና በትግራይ ህዝብ ስም መነገዱ ለትግራዋያን የሚያመጣውን የነገ ዕዳ . . . ወዘተ የተመለከቱ ጉዳዮች በየጊዜው ባሳተማቸው መፅሃፍቶቹ የተነበያቸው በስጋት ያስቀመጣቸው ችግሮች ሲቀርቡና (ሲደርሱ) እንጂ ሲርቁን አላየንም።

በኦሮሚያና በአማራ ክልል በተነሱት ተደጋጋሚ ህዝባዊ አመፆች ህወሓት በሁለቱ ክልል ህዝብ ላይ መንግስታዊ ፍጅት ሲፈፅም፣ ድርጊቱን ኮንኖ ተቃውሞ ያሰማ (አገር ቤት ያለ) የአደባባይ ምሁር አልታየም፤ ከየኔታ መስፍን ወ/ማርያም በስተቀር!! “የወያኔ አገዛዝና የኢትዮጵያ ወደፊት” በሚል ርዕስ በመስከረም 2ዐዐ9 ዓም በማህበራዊ ድረ-ገፆች ለውይይት ያቀረበው 22 ገጽ ፅሁፍ የያዘውን ጭብጥና አገራዊ ፋይዳ ስናስተውል የሰውየውን ብርቱነትና ልበ ሙሉነት እንድንረዳ ተጨማሪ ዕድል ይሰጠናል።

በርግጥ የመስፍንን አካዳሚያዊ ሥራዎችና ሕዝባዊ ተዋፅኦ እንዲሁም በህወሓት አገዛዝ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከብዙ ውጣ ውረድና እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ በመስፍን ፕሬዝዳንትነት የተመራውን ኢሰመጉ (የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ) ለማቋቋም የከፈለውን መስዋዕትነት፤ እንዲሁም ባለፉት ሁለት አገዛዞች እንደ ምሁር የተጫወተውን ሚና በዚህች ፅሁፍ ማብራራት የሚቻል አይደለም። ይልቁንስ መስፍን ላመነበት ነገር መሰጠቱንና የጉልበተኞችን ሥልጣን በብዕሩና በአንደበቱ በመሞገቱ የደረሰበትን ፈተና ለማሳያነት ያህል በአዲስ ንዑስ ርዕስ እናያለን።

እውነትና እውቀት ብዙ ዋጋ ያስከፍላሉ!

የኔታ መስፍን በብዕሩና በአንደበቱ አገዛዙን በመሞገቱ ዛቻና ግሳፄው ከገዢው ኃይል ብቻ አልመጣበትም፤ የአገዛዙን መቀጠል አብዝተው ይመኙ ከነበሩት አቡነ ጳውሎስ ጭምር ዘለፋ ደርሶበት ነበር።

“. . .  በጣም የሚያስከፋ ፣ የሚዘገንንና የሚያስለቅስ የሥልጣን መባለግ አለ። አንድ ጊዜ አንድ ጓደኛዬ ሊቀ ጳጳሱ ሊያነጋግሩህ ይፈልጋሉ አለኝና አብረን ሄደን። እጅ ነስተን ተሳልመን ቁጭ አልን።  . .  . ብፁህ አባታችን ግሳፄ ጀመሩ . . . ‹ብዙ ትናገራለህ፣ ምን እንደምትናገር፤ ለማን እንደምትናገር ማሰብ አለብህ!› በማለት ተራ ለፍላፊ አስመሰሉኝ። እሳቸው ሲናገሩ ቦግ ብለው ይታዩኝ የነበሩት መስቀሎች እያነሱብኝ። ሄደው በመጨረሻም ጠፉብኝ ። በሃሳቤ አንድ የማውቀውና ግን ለሰው ነግሬው የማላውቀው ነገር ትዝ አለኝ። ሲቃ ያዘኝ ጥርሴን ብነክስ፣ ሰውነቴን ባፈራግጥ በዓይኔ ላይ ባንዴ የተከመረው የእንባ ጎርፍ ሊታገድ አልቻለም። መነፅሬን አውልቄ በመሃረቤ ዓይኖቼን ይዤ ተንሰቀሰቅኩ። የሚደንቀው ነገር አብሮኝ የነበረው ጓደኞዬ ከእኔው ጋር አለቀሰ። እስከ ዛሬ እሱ ያለቀሰበት ምክንያት አይገባኝም። ብፁዕ አባታችን ደንግጠው ዝም አሉ፤ ምናልባትም በተግሳፅ የሚያለቅስ ሞልቃቃ የሚል ሃሳብ አድሮባቸው ይሆናል።

“ለማንኛውም እንደ ምንም ራሴን ተቆጣጥሬ የማውቀውን ሁሉ ለእርሳቸው እንደመሰላቸው እንደማልናገር ለማስረዳት አንድ የሚዘገንን ታሪክ ነገርኳቸው። አንዲት የቸገራት ሴት የአስራ ስድስት ዓመት ልጇን አስከትላ አንድ ሚኒስተር ዘንድ ለደጅ ጥናት ትሄዳለች። ችግሯን ስትናገር ታለቅሳለች። ሚኒስትሩ ልጅቱን ወደ ፀሃፊዋ ጋር ይልክና ሴትዬዋን ለብቻዋ ያናግራል። ችግሯ በቀላሉ እንደሚፈታ ይገልፅላትና . . . ግን ልጅሽ ድንግል ከሆነች ፍቀጂልኝና ይላታል። ይህ ደግሞ ምናልባት ወደ መጨረሻው የሚጠጋ የሥልጣን ብልግና ነው። የብፁህ አባታችንን መስቀል ሳልሳለም፤ እሳቸውም ያሰቡት ሳይሳካላቸው እንባዬን እየጠረግሁ ወጣሁ . . .” (መስፍን ወ/ማርያም – ኢትዮጵያ ከየት ወዴት? ገጽ 59)

ይህ ከላይ የሰፈረው ምስል ከሳች ትረካ መሰፍን ያነገበውን የእውቀትና የእውነት ዋጋ ለሕዝብ በማድረሱ ካጋጠሙት ልብ የሚነኩና ቅስም ሰባሪ ኩነቶች አንዱ ነው። ግና መሰፍን እንዲህ ባለ ውረፋ፣ ለዚያውም ራሳቸውን  ከእግዚአብሔር በላይ ለቄሳር ያስገዙ ተብለው በአደባባይ ለሚተቹ አካላት በቀላሉ እጅ የሚሰጥ ሰው አልነበረም። ለባለ ብረቶቹም እንደዛው።

ዛሬ ላይ አገዛዙ በንፅፅር ለአንድ በአነስተኛና ጥቃቅን ለተደራጀ ማህበር ከሚሰጠው ድጋፍ እጅግ ባነሰ “የበጀት ድጋፍ” ለሚንቀሳቀሰው፤ በአናቱም የበጎ አድራጐት ድርጅትና ማህበራት ሕግ (አዋጅ ቁጥር 621/2001) የሚሉት እግረ-ሙቅ ህግ እያሽመደመደ ላለው የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በአሁኑ አጠራር የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) መመስረት፤ በምስረታ ወቅት የሁሉም ዜጐች አበርክቶ እንዲኖር በተለይም ከፆታ እኩልነትና የወጣቶችን ተሳትፎ ከማሳደግ አኳያ የከፈለው መስዋዕትነት እጅግ የላቀ ነው።

ከምስረታው በኋላ ደግሞ በሽግግር መንግስት ምስረታው ወቅት በአራቱም የኢትዮጵያ አቅጣጫዎች፤ በተለይም በደቡብ ምዕራብና በምስራቅ ኢትዮጵያ በአማራ ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ ጭፍጨፋዎችንና የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን ከነፃው ፕሬስ አባላት፣ ከወቅቱ ምሁራንና ከአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጋር በመሆን አገዛዙ ይፈፀም የነበረውን ድርጊት እንዲያቆምና ተጠያቂ እንዲሆን በአደባባይ መሞገት ችሏል። ጉዳዩንም በወቅቱ ለመለስ በግንባር በመቅረብ አስረድቷል። በርግጥ ከእያንዳንዱ ጭፍጨፋ ጀርባ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር እጅ ነበረበት። መስፍንና አገዛዙ ሆድና ጀርባ መሆን የጀመሩትም ከዚያ ግዜ ጀምሮ ነበር።

ለመስፍን ተሟጋችነትና ህዝባዊ ወገንተኝነት፣ አለም አቀፍ ተቋማትና ሚዲያዎች በየጊዜው ዕውቅና ችረውታል። የአውሮፓ ህብረት በአለም አቀፍ ደረጃ ለሰብዓዊ መብት ጠበቃዎች በየጊዜው “Sakharov Prize” በሚል ለሚሰጠው ከፍተኛ ሽልማት እ.ኤ.አ በ2006 ለሽልማት ታጭቶ ነበር። አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂውማን ራይትስ ዎች ኢትዮጵያን የተመለከቱ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን መረጃ የሚያገኙት ከየኔታ መስፍን ነበር።

ለዕውቀት አድባሩ መስፍን የአደባባይ ምሁርነትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋችነት የአገር ውስጥ ዩኒቨርስቲዎች የዕውቅና ሽልማት ለመስጠት ባይደፍሩም ከምዕራቡ አለም ዩኒቨርስቲዎች የክብር ዶክትሬትን ጨምሮ የተለዩ የዕውቅና ሽልማቶችን አግኝቷል። ከረፈደም ቢሆን ባሳለፍነው ወር የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) የኔታ መስፍን ወ/ማርያም ኢትዮጵያ ውስጥ ለዜጐች ሰብዓዊ መብት መከበር ለከፈለው ውድ ዋጋ ዕውቅና በመስጠት ሽልማት አበርክቶለትል። እስከዛሬ ድረስ የፃፋቸውን መፅሃፍትና የሰራቸውን የምርምር ስራዎች እንዲሁም በምዕራቡ አለም ውድ ዋጋ ሊያወጡ የሚችሉ ቤቱ ዉስጥ የነበሩ ሁለት የገብረ ክርስቶስ ደስታ ዝነኛ የስዕል ሥራዎችን ለሰመጉ የሃዋሳ ቤተ መፃህፍት በስጦታ አበርክቷል።

የዘመን ዕንቁው የኔታ መስፍን ወ/ማርያም የኢሰመጉ ፕሬዚዳንት በነበረበት ወቅት በበደኖ፣ በአርባጉጉ፣ በወተርሉ፣ . . . በአማራ ላይ የደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተከታትሎ በማስረጃ አስደግፎ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማጋለጥ በቀዳሚነት የተጋ ሰው ነው። በአንፃሩ ዛሬ ላይ አንድም ረብ ያለው ተግባር ማከናወን ያልጀመሩና ፖለቲካዊ መብቃት ላይ ያልደረሱ የአዲሱ አማራ ብሔርተኝነት አቀንቃኞች መስፍን በየጊዜው የሚያነሳቸውን ሃሳቦች እየተከተሉ ብርቱውን ታጋይ በሚያሳዝን መልኩ በስድብ ሊያቃልሉት ሲሞክሩ መታየቱ አሳዛኝ ክስተት ነው። ነገሩ ከባዶነት በላይ ነዉ። በታወቀ “ምክንያት” በኦሮሞና በትግራይ አክራሪ የዘወግ ብሔርተኞች ዘንድ መስፍን እንደማይወደድ ግልፅ ነው። ይህም መሰረታዊ መነሾ እርሱ ለዘውግ ፖለቲካ ጽዩፍ በመሆኑ ለግራ ቀኙ ኃይል በሚሰጣቸው ግልፅ አስተያየቶች “ተሰደብን” የሚሉ፤ ዝናን እንጅ ትችትን መሸከም የማይችሉ የመንደር ፖለቲከኞች በመሆናቸው ነው። የሟች እህት ወንድሞቻቸዉን አስከሬን ፌስቡክ ላይ በመለጠፍ “አብዮተኛ” የሆኑ የሚመስላቸዉ ከብሄር ፖለቲካ አንቀልባ ላይ መውረድ የተሳናቸዉ ስሁት “ፖለቲከኞች” ከመስፍን ምልከታ እጅግ ቢለያዩ የሚገርም አይደለም።ገራሚዉ ነገር ስድብ የጡት ቋንቋቸዉ መሆኑ ነዉ።

የኔታ መሰፍን በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነት ጎዳና የቻለውን ያህል ከታገለ በኋላ ራሱን በይፋ ወደ ተቃውሞ ፖለቲካ ጐራ በመቀላቀሉ የደረሰበትን እንግልትና የእስር መከራ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተል ሰው የሚያውቀው ጉዳይ ነው። የሰላማዊ ትግል ጀምበር ጨርሳ በጠለቀችባት ኢትዮጵያ፤ መስፍን ከፓርቲ ፖለቲካ ትግል ርቆ እንኳ ዛሬም ድረስ ተቃውሞውን በሰላ ሂስ፣ በምሁራዊ አንደበት ከመግሰጽ አልተቆጠበም። ከፖለቲካው ባሻገር የማህበረ – ባህል ጉዟችን የከተተንን ቅርቃር በአደባባይ የሚተቸው መስፍን ለአምስት አስርት ዓመታት በብቸኝነት በአደባባይ ሐሳቡን መግለጽ የቻለ የአደባባይ ምሁም አድርጎታል።

በመጨረሻም

አብዛኛዎቹ የቅድመ አብዮት (1966) እና የድህረ-አብዮት (ያ) ትውልድ አባላት ዛሬም ድረስ የገዛ ፍላጎታቸውን ማሸነፍ ባልቻሉበት የትንቅንቅ ዘመን፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ኑሯቸውን በብህትወትና መሰል የአኗኗር ዘይቤ ጊዜያቸውን በሚገፉበት ወቅት፤ አይበገሬው መስፍን ወልደ ማርያም በ87 ዓመቱ ለእውነትና ለዕውቀት እንደቆመ በማስመስከሩ፣ የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ! የሚሉ ገላጭ ሃረጋት የእርሱን ዋጋ የሚያስረግጡ ይመስላል። ረጅም እድሜ እንዲኖር ያደረገውም ለእውነትና ለዕውቀት በመትጋቱ ይመስለኛል። በአምላክ ቸርነት ገናም ይኖራል።

ፎቶ: ከአርአያ ጌታቸው ፌስቡክ የተወሰደ

ይህ ትውልድ ከየኔታ መስፍን ወ/ማርያም የአቋም አዕማዶች ጋር ተስማማም አልተስማማም፤ ከእርሱ ጠንካራ ስብዕና ብዙ የሚቀዱ ልምዶች እንዳሉ ግን ማወቅ ግድ ይለዋል። በልዩነት ውስጥ እንኳ ለእውነትና ለእውቀት የሚያሳየው ትጋት የሚወደድ ነው። እውነት እንነጋገር ከተባለ፤ የትኛው የአገሪቱ ምሁር ይሆን በ87 ዓመቱ ሀሳቡን የሚገልፅበት ነፃ ፕሬስ ቢያጣ በማህበራዊ ሚዲያ ሃሳቡን በነፃነት የሚያጋራ? በርግጥም የኔታ መስፍን ወ/ማርያም የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ ነው! ያስተዋለ ወደ ዋርካው ይጠጋ። የእውቀት ግቡ ነፃነት ነውና!!!

ፕሮፍ እንኳን ተወልድክ! አንተ የመርህ ሰው፣ የህገ-ኅልዮት አማኝ ነህና አከብርሃለሁ። ተምሬብሃለሁ። ገናም እማርብሃለሁ።

ይህ ነው የዘመኔ ዕንቁ!! የኔታ መስፍን!! የቅኔ ጌታ!! የዕውቀት ገበታ!!

ሙሉአለም ገ.መድህን

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

ጠቅላይ ሚኒስትራችንን በዚህች ትንሽ አጋጣሚ ዕንወቅ – ነፃነት ዘለቀ

$
0
0

እንደአካሄድ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የማያውቅ ወይም ለማወቅ የማይጓጓ ዜጋ መኖር የለበትም፡፡ ምክንያቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ማለት ከእያንዳንዱ ዜጋ ልብ ውስጥ መጥፋት የሌለበት የሁሉም አለኝታና ከአባትና እናት የማይተናነስ ቦታ ያለው ነውና፡፡ አንድ ዕድለኛ ቤተሰብ ውስጥ እናትና አባት ይኖራሉ፡፡ አንዱ ቢጎድል ከሁለት አንዱ ይኖሩና ክፍተቱን በተቻለ መጠን ለመሙላት ይሞክራሉ፡፡ ሁለቱም ከጎደሉ ግን በተለይ ልጆች ትንንሽ ከሆኑ ብዙ ችግር ይፈጠራል፡፡ በተጨማሪም የወላጆች መኖር ብቻውን ምንም ማለት የማይሆንበት አጋጣሚ መኖሩንም መዘንጋት አይገባም፡፡ በዋል ፈሰስ የሆኑ አባትና እናት ያጋጥሙና መንጋው የሚበተንበት ወይም ዘምቦለል የሚሆንበት ሁኔታ ቢፈጠር ችግሩ የቤተሰባቸውን አውራ(ዎች) በሞትና በመሰል መጥፎ አጋጣሚዎች ከተነጠቁ ወገኖች ባልተናነሰ የሚገዝፍ መሆኑ አይካድም፡፡ ቤተሰብና ሀገር ደግሞ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ቤተሰባዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ የማይወጣ አባውራ ሀገር ቀርቶ የቅሬ(ዕድር) ሊቀ መንበርም መሆን አይችልም፡፡ ሌባ ከላይ ከታዬ ከታችም ሌባ ነበርና ቤተሰቡም እንዲሁ ጠፍቷል ማለት ይቻላል፡፡ …

የኛ ችግርም እንደዚሁ ነው – በላይኛው አንቀጽ መጨረሻ አካባቢ እንደተገለጸው ዓይነት፡፡ ሲጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር የለንም፡፡ ሲቀጥል አለ የሚባለው ጠቅላይ ሞንስተርም ለአቅመ አሻንጉሊትነትም ያልደረሰ በጌኛ ፈረስነት ሕወሓትን ለማገልገል የተጎለተ መሆኑ ወያኔ በቆራጣ ጅራቱ ሊሸፍነው የማይችለው አገር የሚያውቀው ፌዝ ነው፡፡ ወያኔ ትግሬ በእንደራሴ አገር መግዛትን ከጥንትም ያውቅበታልና ይህን ጉልቻ አስቀምጦ እየተጫወተብን ነው፡፡ (በል ብሎኝ ቲቪ ሳይ ይህን “ጠ.ሚኒስትር” እመለከትና በሣቅ ፍርስ እላለሁ፡፡ “እርሱስ ያምንበት ይሆን?” ብዬም መልስ የማላገኝለትን ጥያቄ ራሴኑ እጠይቃለሁ፡፡ ሆ! ምን ዓይነት ለዛቢስ ቲያትራዊ ቀልድ ነው እባካችሁን ወያኔዎች በዓለም ሕዝብ ፊት እየተወኑ ያሉት፡፡ የሚገርመው ይህን ቲያትራቸውን እያዬ የሚዝናና “ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ” መኖሩ፡፡)

አነሳሴ ጉልቻውን ለምን እንደተጎለተ መግለጽ አይደለም፡፡ የሰማሁትን የዚህን ሰው ነውር ለመናገር እንጂ፡፡ ያገራችን ድንጋይ ራስ ባለሥልጣናት የማይሠሩት ወንጀልና ሙስና የለም፡፡ ባይሞስኑ ኖሮ ለምሣሌ ቀደም ባለ አንድ ወቅት ይሄው የክርስቶስ ልጅ ነኝ ባዩ የሁለት ጌቶች ባሪያ ደቡብ አፍሪካ ሄዶ በአንድ ጊዜ ግብይት አሥር ሺህ ዶላር የሚያወጣ ሸቀጥ በአንድ ሱፐርማርኬት እንደገዛ ባልተገለጸ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ደሞዝ ይህ ግዢ የሚታሰብ አይደለምና፡፡ እኛ እርቃናችንን እንሄዳለን እነሱ በወርቅ በተሞላ በርሜል ውስጥ ይዋኛሉ፡፡ ዕንቆቅልሽ፡፡ ግድያውንና ስቃዩን በተውልን ኧረ! የወርቁስ ነገር እዬዬም ሲዳላ ነው፡፡

ይህን ምሥጢር ከሰማሁ ብዙ ጊዜየ ነው፡፡ ግን የነገረኝ ሰው ጠቅልሎ ውጪ እስኪወጣ ምሥጢሩን መጠበቅ ነበረብኝ፡፡ የሰማሁት ነገር ከሙስና ጋር የተያያዘ ነው፡፡

የማውቀው ሀብታም አዋሳ ውስጥ አንድ ቢዝነስ ሊጀምር ለሚመለከተው ኃላፊ ቢሮ ያመለክታል፡፡ ጊዜው ራቅ ይላል፡፡ የዚያ ቢሮ ኃላፊ ደግሞ የአሁኑ ውዝፍ ጠቅላይ ሚኒስትር የያኔው የተጠቀሰው ቢሮ ባለሥልጣን ደሳለኝ ማነው ኃይለማርያም ደሳለኝ ነበር፡፡ ያ ስሙንና ሥራውን አሁንና እዚህ የማልገልጸው ወዳጄ በዚህ ጉልቻ ሰውዬ የተጠየቀው ጉቦ ግን የጉልቻውን ሰውዬ ቁጥርን ያለማወቅ ደደብነት በግልጽ የሚናገር ነበር፡፡ “ለዚህ ጉዳይ (ለፈገግታ ያህል ‹ዳ›ን እንደርሱው ብታነቡልኝ ደስ ይለኛል) 500 ሺህ ብር ካልሰጠህ አይፈጸምልህም፡፡ ለኔ ብቻ ሣይሆን ለብዙ ሰው ስለሚከፋፈል – በኔ አማርኛ – ‹ከዚህ በታች አያዋጣንም፡፡›…” ብሎ ነበር ቅስሙን ሰብሮ ከቢሮው ያስወጣው – የኛ ፕሮቴስታንት ‹የኢየሱስ ልጅ›፡፡ ሃይማኖት እንዲህ መቀለጃና ማጭበርበሪያ ይሁን? ለነገሩ ዛሬ ጊዜ ሃይማኖት እንጂ ሃይማኖተኛ የት አለ? ምሎ የነገረኝ በመሆኑ ስለእውነትነቱ ሃሳብ አይግባችሁ፡፡ ከዚህም በላይ አለና የሙስና ነገር በኛ ሀገር የእጅ ሰላምታን ያህል በጣም ቀላልና የማይታፈርበትም ነው፡፡ የሚያሳፍረውና የሚያሸማቅቀውስ አለመሞሰን ነው፡፡ ሙስና እግር አውጥቶ እንደልቡ የሚሄድበትና የሚንቀባረርበት ብቸኛዋ የዓለም ሀገር ኢትዮጵያ ለመሆኗ ጥርጥር አይግባችሁ፡፡

የኛ ጠቅላይ ሚኒስትር – ለላግጣም ቢሆን – ይሄን መሰሉ ነው፡፡ እንደኔ አፈራችሁ?

በመሠረቱ ሕወሓት ጋር ለመሥራት ቆሻሻ ስብዕና አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን የማይደራደሩበት ቅድመ ሁኔታም ነው፡፡ ንጹሕ ሆነህ ቆሻሻ ጋር ዝምድና አይኖርህምና ወያኔ ጋር ለመሥራት ወይም ከነሱ ጋር አንዳች ኅብረት ለመፍጠር በግድ ሞሳኝና በምግባርህ የበሸቀጥህ መሆን አለብህ፡፡ የወረደ ስብዕና ከሌለህና አእምሮህን በአግባቡ ልጠቀም የምትል ከሆነ ከዚህ ወራዳ ድርጅት በልጅ ልጆቼ አገላለጽ በአፋጣኝ ‹መፋታት‹ አለብህ፡፡ ጨለማና ብርሃን የጋራ ነገር የላቸውም፡፡ በዘመነ ክርፋትና ጥምባት አልባብ አልባብ እየሸተትህ ልሂድ ብትል አትችልም፡፡ አብረህ ጠምብተህ መጓዝ ብቸኛ አማራጭህ ነው፡፡ ልንገልጸው ቃላት የሚያጥሩን የሙስና አዘቅት ውስጥ ተዘፍቀን እንገኛለን፡፡

ኃይሌ ለውሸትም ቢሆን ጠቅላይ ሚኒስትሬ ሆኖ ሳየው የሀገሬን ማርጀትና መበስበስ እረዳለሁ፡፡ እንዲህ ያለ ሙሰኛና ጉቦኛ ብቃትን ተጎናጽፎና ምሉዕነትን ተላብሶ ከ100 ሚሊዮኑ ሕዝብ “በመመረጥ” ጠቅላይ ሚኒስትሬ ሲሆን መታዘብ ምን ያህል በኩራት እንደሚያስፈነድቅ እናንተም ይታያችሁ፡፡ የአለመታደላችን ዙሪያጥምጥምነትና ጥልቀት እጅግ ያስደነግጣል፡፡

ሙሰኝነት – እርግጥ ነው- የዚህች ምድር አንዱ መገለጫ መሆኑን አላጣሁትም፡፡ ግን ግን ዓይነት ዓይነት አለው፡፡ የጣሊያንም፣ የጃፓንም… መሪዎችና ባለሥልጣናትም እንደሚሞስኑ ይነገራል፡፡ የነሱ ሙስና ግን መልክ አለው፡፡ ከታላላቅ ተቋማትና ከካምፓኒዎች ሊያውም በእጅ አዙርና የሀገርን ጥቅም በማይነካ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንጂ ከግለሰብ ዜጋ ተደራድረው ክብራቸውንና የኃላፊነታቸውን ወንበር አዋርደው አይደለም – አሁንም እርግጥ ነው ያም ትልቅ ስህተትና ዋጋም የሚከፍሉበት ነው፡፡ የኛዎቹ ግን እስከዚህን የወረደ ደረጃ ድረስ  ቅሌታሞች ናቸው – የግለሰብን አጥንት የሚግጡ ጅቦች፡፡

የአንድ ባለሥልጣን የሥልጣን መወጣጫ እርካብ መጠናትና እንዲህ ያሉ ልክስክሶች ተነቅረው የሚተፉበት አሠራር ካልተፈጠረ ሀገራችን እንደደማችና ሕዝቧም እንደተዋረደ እንደተጎሳቆለም ይኖራሉ፡፡ ስለሀገራችን የሙስና ጡዘትና ዐይን አውጣነት ብመለስበት ደስ ይለኛል (እንዴ፣ ምንም ነገር ካለሙስና አይፈጸምም እኮ! ባለኝ ግንዛቤ ተፈጥሯዊ ሞት ብቻ ናት ካለ ሙስና የምትገኝ)፡፡ ብቻ ለአሁኑ ሰላም፡፡

መሰነባበቻ፡-

  • በቅርብ አንድ ብዕር መንጠፉ ተሰማ – የአቶ አሰፋ ጫቦን ነፍስ ይማር፡፡ ከርሱም በፊት ሁለት ስመጥር ዜጎችን በማይቀረው ሞት አጥተናል – ጄ. ጃጋማና ፕሮፌ. ዮሐንስ፡፡ ሞት እንኳን ነፍስ ዐውቆ እንዲህ ከየብሔረሰቡ ሲወስድ ማደጊያቸው ላይ ቁልቋልና ቅንጭብት የበቀለባቸው ወያኔዎች ግን በዚያቺው ትግራይንና ትግሬን በማስቀደሙና ሌሎችን በማውደሙ ጠባብ የአስተሳሰብ ጉድባ ውስጥ እንደተሰነቀሩ አሉ፡፡ ሲያሳዝኑ!
  • ቴዲ አፍሮ ላይ ብትር መብዛቱ ተሰማ – ጥሩ ሀገራዊ ሥራ እንኳንስ የዐድዋውን ቴዎድሮስ ፀጋየንና መሰል የወያኔ ቡችሎችን ይቅርና ሆድ አደሮችንም ያበሳጫልና ቴዲ አፍሮ ታድለሃል፤በርታ፡፡ ከነጋበት ጅብ ፈጣሪ እንዲታደግህ ላንተም እጸልያለሁ፡፡
  • ከ4000 ጥይቶች የተረፉ ታላቅ ሰው በሕይወት መኖራቸው ተሰማ – እሰይ! እንኳንም ከ4000 የደርግ ጥይት ተረፉልን፡፡ ተዓምር ዱሮም አልነበረም አይባልም፡፡ ግን ማን ቆጥሮት ይሆን? ደርግ የጥይት ሀብታም ነበር ማለት ነው!
  • ወያኔ አማራውን ለማጥፋት ልዩ የጤና ፖሊሲ ዘርግቶ እንደነበር ተሰማ – ወያኔ ምን አጠፋ? የታወጀበትን የዕልቂት ዐዋጅ ተባብሮ ከማክሸፍ ይልቅ እርስ በርሱ እየተከፋፈለ የሚናቆር ሕዝብ ከተገኘ ያ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለመጥፋት ፈቃደኛ የሆነ ሕዝብ የልቡ እንዲደርስ አቅም በቻለ መጠን መተባበር ክፋት የለውምና ለዓላማቸው ስኬት አንድም ቀን ተሳስተው የማያውቁት ወያኔዎች አላጠፉም፡፡
  • የወያኔዎች ምሥጢር በቀድሞ ባልደረቦቹ እየተዘከዘከ መሆኑ ተሰማ – ይዘክዘካ! ማን ምን ያመጣል? የወያኔ ምሥጢር ዱሮውንስ ከማን ተደብቆ ያውቃል? ችግሩ እኮ የምሥጢራቸው አለመታወቅ ሣይሆን ቀን ከሌት ተግተው እንደመሥራቸው ጠላቶቻቸውን ለመበታተንና ኅብረት ለማሳጣት የሚያደርጉት ጥረት ፍሬያማ ሆኖ መቀጠሉ ነው፡፡
  • ይብቃኝ – ስንቱን “ተሰማ” ጠቅሼ እዘልቀዋለሁ?

 

 

The post ጠቅላይ ሚኒስትራችንን በዚህች ትንሽ አጋጣሚ ዕንወቅ – ነፃነት ዘለቀ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Remembering Assefa Chabo – SBS Amharic

የህብር ሬዲዮ  ሚያዚያ 15 ቀን 2009 ፕሮግራም

$
0
0

ለክርስትና ዕምነት ተከታይ አድማጮቻችን ዕንኳን ለዳግማይ ትንሳዔ በዓል  አደረሳችሁ

<… የኢትዮጵያው አገዛዝ የራሱን ወንጀል ለመሸፈን ያቋቋመው የሰብዓዊ ከሚሽን ያቀረበው ሪፖርትበየትኛውም ሕጋዊ መድረክ ዛሬም ዕድል ተገኝቶ ወይም ነገ በፍትሕ አደባባይ ቢቀርብ ተቀባይት የሌለው ነው።ሪፖርቱ ዋናውን ተጠያቂ አካል ነጻ ለማድረግና ወንጀሉን በማይመለከታቸው ላይ ለመለጠፍ ከተጠያቂነትለማምለጥ ያደረጉት ቢሆንም ገዳዮችና አስገዳዮች ሆነው ራሳቸው አቀረብነው የሚሉት ሪፖርት ማንምየሚቀበለው አይደለም …> አቶ ያሬድ ሀይለማሪያም መቀመጫውን በቤልየም ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ዳይሬክተርስለ ሕወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት አስመልክቶ ከህብር ጋር ካደረገው ቆይታ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሚባለው ራሳቸው ገዳይ ራሳቸው አጣሪ ራሳቸው ዳኛ የሆኑበትን ሂደት ኮሚሽኑየራሱ የስርዓቱ አፈ ቀላጤ እንጂ ለሰብዓዊ መብት ያልቆመ በመሆኑ የትኛውም ዓለም አቀፍ ተቋም ይህን ሪፖርትአልተቀበለውም። በሪፖርቱ ሆን ብለው የሟቾችን ቁጥር ቀንሰዋል ለምሳሌ በኦሮሚያና በአማራ የተገደሉትንብቻ ብንወስድ እነሱ ካቀረቡት 669 ቁጥር ጋር አይገኛኝም በኦሮሚያ ብቻ 1072 ንጹሃን ተገለዋል በአማራከአራት መቶ በላይ ተገለዋል። ሪፖርቱ የራሳቸውን ግድያ ለመሸፈን የሞከሩበት ዋናዎቹ ተጠያቂዎች የአገሪቱንስልጣን የተቆታጠሩትን ሕወሓቶች ከተጠያቂነት ለማዳን የሞከሩበት ነገር ግን በየትኛውም ቦታ ተቀባይነትየሌለው ነው…> በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲና በቨርጂኒያ ሊን የህግ መምህር የሆነው ሔኖክ ጋቢሳ ስለ የሕወሓት/ኢህአዴግ የሰብዓዊ መብትኮሚሽንን አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

አርቲስት ቴዲ አፍሮ እና ስመጥር የሙያ አጋሮቹ ለኢትዪጵያ እና ለህዝቧእየከፈሉት ተጋድሎ  ሲቃኝ(ልዩጥንቅር)

ከአቶ አያሌው መንገሻ የቀድሞው የአማራ ክልል የደህነት ክፍል ሀላፊ ስለ ደህነት /ቤቱ የአፈና መዋቅር፣የደህነቱ /ቤትበተቃዋሚዎች ውስጥ ሰርጎ ስለሚገባበት፣የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የሕወሓት አባላት በዋና ወና የደህነቱ ሀላፊነቶችና ምስጢርለመጠበቅ በአፈናና በግድያ የሚሰማራው ቡድን 99 በመቶ በእነሱ ቁጥጥር ስር ስለመሆኑ፣የስርኣቱ ደጋፊ የትግራይ ባለሀብቶችበጎንደርና በባህር ዳር ጨምሮ የንግድ ቤቶቻቸውንና ህንጻዎቻቸውን ጭምር ለደህነቱ የጭካኔ ማሰቃያነት ስለሚፈቅዱበትሁኔታ አብራርተዋል (ክፍል ሁለት ቃለ መጠይቅን ያዳምጡት)

 

ዜናዎቻችን

የሕወሓት ግድያን ሕጋዊ ለማድረግ የሞከረው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንሪፖርት በዓለም አቀፍ መድረክ ተቀባይነት አጣ

ሪፖርቱ በሕግ ፊት ተቀባይነት የለውም ተባለ

ሰሞኑን በአሜሪካ ሎሳንጀለስ ከተማ ውስጥ በፓሊስ የተገደለው ኢትዪጵያዊወጣት አሟሟት ታላቅ መደናገጥ ፈጠረ

የወጣቱ አስክሬን በክብር ለማስቀበር የማህበረሰቡ ድጋፍ ተጠየቀ

የታዋቂው ፖለቲከኛ ጸሐፊና የህግ ባለሙያ አቶ አሰፋ ጫቦ አስከሬንን ወደአገር ቤት ሊሸኝ ነው

የአማራ ምሁራን በዘር ማጥፋት ጭምር የተሳተፉትን የዶ/ ቴዎድሮስአድሃኖምን ለዓለም የጤና ድርጅት መሪነት ብቃት የሌላቸው መሆኑን ጠቅሶተቃወመ

የቴዲ አፍሮ አልበም  ለዳግማ ተንሳይ ያልወጣበት ምክንያት ተገለጸ

በጎንደር የሚከበረው የከተሞች ቀን ከወዲሁ ተቃውሞ ገጠመው ጎንደር ሐዘንላይ ነች ለጭፈራ ጊዜ የለም የተቃውሞው ጥሪ

ኤርትራ የተመድ የጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላት የቻይናን ጣልቃ ገብነትንተማጸነች

 

 

 

ኤርትራዊያን ስደተኞች በሆላንድ ውስጥ የጠሩ አመታዊ ስብስባንባለስልጣናት እንዳይገኙ ያገደችው ሆላንድ ብርቱ ትችት ገጠማት

አርከበ እቁባይ ኢህአዲግ የሚያስተዳድራቸው። የንግድ ተቋማት ብቁ እናከሙስና የጸዱ ናቸው ሲሉ ለአለም ተወካዪች ተናገሩ

ቴሌ ኮምንኬሽን የማይነጥፍ ላም በመሆኑ ለውጭ ባለሀብቶችአይሸጥምአቶ አርከበ እቂባይ

የኢህአዲግ አገዛዝ ታጣቂዎች 600 በላይ ስላማዊ ዜጎችን መግደላቸውንየአገዛዙ ኮሚሽን አጋለጠ

በኩዌት ውስጥ ኢትዩጵያዊቷ የቤት ስራተኛን ለረሞዳን ጾም በገጸ በረከትነትያቀረበው ድርጅርጅት እርምጃ ተወሰደበት

ሊቢያ ውስጥ የሚገኙስደተኛ ወገኖቻችን በርካሽ ዋጋ እንደሚሸጡ ተነገረ

ከፍተኛ ትኩረት ተጥሎባቸው የነበሩት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ፈይሳ ሌሊሳለንደን ላይ ታሪክ ሳይሰሩ ቀሩ

ኢትዮጵያ በደም ጎርፍ እየታጠበች ነውአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫንካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

The post የህብር ሬዲዮ  ሚያዚያ 15 ቀን 2009 ፕሮግራም appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Hiber Radio Weekly News – April 23, 2017

የፈንጅ ጥቃት በጎንደር ዛሬ ደርሷል – አስናቀው አበበ

$
0
0

ቁጥር 11 የፈንጅ ጥቃት በጎንደር ዛሬ ደርሷል።
ቀበሌ 03 ፊት ሚካኤል አካባቢ በሎጅ ፋሲል አቅራቢያ ነው ፍንዳታ እንደደረሰ መረጃ ያለን።
አካባቢው በፍጥነት በወታደር ተጥለቅልቋል። ወሬው እንዳይሰማ እየጣሩ ነው። ሰው በሰፈሩ እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል። በማሰርም ላይ ናቸው። ወያኔ የከተሞች ቀን ብሎ ጎንደር ውስጥ ለማክበር ማሰቡ ህዝቡን እንዳስቆጣ በተከታታይ ስንዘግብ ቆይተናል።
የህዝብ ጥያቄ በአፈና አይመለስም!
ህዝብ ያሸንፋል©!

The post የፈንጅ ጥቃት በጎንደር ዛሬ ደርሷል – አስናቀው አበበ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Assefa Chabo’s Funeral Assistance

$
0
0

The Ethiopian Community in Dallas is saddened to announce the passing of Mr. Assefa Chabo. Mr. Chabo passed away today, April 23, 2017, at Parkland Hospital in Dallas, TX, where he was receiving treatment.
Mr. Chabo was a prominent author, lawyer, politician, prolific writer, human right advocate and a political prisoner. We ask everyone to support with our fundraising effort to offer Mr. Chabo proper funeral and burial service.

“Lewgen Derash Wegen Newna”.

Thank You
MAAEC, Inc.
Dallas, TX

The post Assefa Chabo’s Funeral Assistance appeared first on Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!.


The sixth Tana High-level Forum on Security in Africa opened today in the Bahir Dar city of Ethiopia

$
0
0

The sixth Tana High-level Forum on Security in Africa opened today in the Bahir Dar city of Ethiopia, where the management of the continent’s natural resources tops the agenda.

Photo: The Observer
Gold mining in Uganda (file photo).

“The Forum has become a platform to nurture open dialogue on the continent’s peace. Unless we manage our natural resources properly, they will become a source of contention,” said Ethiopia’s Prime Minister Hailemariam Desalegn.

He added: “If natural resources have to contribute to human development, they ought to be used productively. Natural resources need to be transformed to manufactured capital and human capital. Specific policies are needed for that to happen.”

A 2016 African Development Bank report notes that over the past 60 years, 40 to 60 per cent of internal armed conflicts on the continent are related to natural resources.

The chairperson of the forum, former Nigerian President Olusegun Obasanjo said that in 2016, Ethiopia, South Africa and Tunisia were among African countries that witnessed protests related to natural resources management.

The deputy chairperson of the African Union Commission, Thomas Kwesi Quartey said that Africa needs to focus on educating its youth in order to solve its major development challenges including natural resources governance.

Reports show that Africa is rich in natural resources, including 12 per cent of global oil reserves, 40 per cent of gold deposit and hundreds of precious minerals.

The continent also possesses 60 per cent of the world’s arable but uncultivated land.

The forum will reflect on what is hampering the continent from better managing its natural resources and come up with recommendations on the way forward.

The two-day forum will also address issues related to the management of agricultural land, inland water, sea water, forests and biodiversity of Africa.

Also on the agenda is the growing demand by some African countries for the renegotiation of concessions with multinational companies, responsible revenue management and resource sovereignty

Among the attendees of the forum are President Yoweri Meseveni of Uganda and former South Africa President Thabo Mbeki.

Named after Ethiopia’s biggest lake and the origin of Blue Nile (Lake Tana), the forum was started in 2012 by the Addis Ababa University’s Institute for Peace and Security Studies following the August 2009 African Union Tripoli Declaration on the need for centred solutions for the continent’s challenges.

The post The sixth Tana High-level Forum on Security in Africa opened today in the Bahir Dar city of Ethiopia appeared first on Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!.

Uganda’s President Museveni in Ethiopia says “Ethiopia’s Adwa is holy place, it removed shame from Africa”

$
0
0

Hundreds gathered in Ethiopia’s Northern town of Adwa, to commemorate the defeat of the Italian troops by Ethiopian forces in 1896 and the establishment of a Pan African University in Africa at the historic town in a ceremony attended by various African distinguished leaders including President Yoweri Museveni.

African leaders and several delegates, who had just attended the 6th Tana High Level Forum on Security in Africa, flew to Adwa to cement African Unity with the establishment of the Pan African University in Africa.

President Yoweri Museveni and his host Ethiopia Prime Minister, Hailemariam Desalegn laid the foundation stone for the construction of the University.

Museveni blamed African chiefs for not fighting and consolidating the sovereignty of the African continent. He thanked the people of Ethiopia for putting up a spirited resistance to colonialism, which couldn’t be done by many African chiefs.

“I am honored along with my colleagues to be in Ethiopia. I am honored to be invited here at Adwa. I would have removed my shoes because this is a holy place, it is the holy land of Africa. It removed the shame from Africa. The African Chiefs should be ashamed of their ancestors who looked on as Africa was being invaded and colonized by the foreigners,” he said.

Museveni said the colonization of African was an indictment of the Africans. “Here in Ethiopia, your ancestors redeemed the honour of Africa and that is why we are here. Adwa is a remarkable inspiration in Africa,” he said.

About the Pan African University, President Museveni said, “I am glad you are establishing a University here at Adwa which will redeem Africa with a combined action of carriage, knowledge and new technology to benefit all Africans for development.”

Adwa is a market town and separate district in northern Ethiopia specifically in the Tigray region. It is best known as the community closest to the decisive Battle of Adwa fought in 1896 with Italian troops. In the age of relentless European expansion into Africa, Ethiopia, led by Emperor Menelik II, defeated one of Europe’s major powers, Italy.

Prime Minister, Hailemariam Desalegn said “Our ancestors have made huge sacrifices to safeguard the sovereignty of the country and pass it on to existing generations.” The battle according to him, was a victory for all black people. He tasked young Ethiopians to involve themselves in the development of the country.

“It is my strong conviction that a generation that remembers the history of its forefathers can also make its own history. In order to pass this history on to the next generation we have to build a war museum and a Pan African University and make Adwa a tourist destination,” he said.

The event saw marches by members of the Ethiopian security forces and displays by horse riders draped in the colours of the country, cheered by hundreds of people from the mountainous Devrch villages 25km from Axum Yohannes Airport.

Former Burundi President Pierre Buyoya, Former Malawi, President, Joyce Hilda Banda, Former South African President Thabo Mbeki, Botswana Vice President, Mokgweetst Masisi and Former Nigeria President, Olugesun Obasanjo attended.

http://www.statehouse.go.ug/media/news/2017/04/24/ethiopia%E2%80%99s-adwa-holy-place-it-removed-shame-africa-%E2%80%93-museveni

The post Uganda’s President Museveni in Ethiopia says “Ethiopia’s Adwa is holy place, it removed shame from Africa” appeared first on Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!.

የደህንነቱ ሰው በህብር ራዲዮ – በ ታመነ በአምላኩ

$
0
0

አቶ አያሌው መንገሻ በወያኔ በበአለ ፋሲካ ሰሞን ከህብር ራዲዮ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩት፡፡ አቶ አያሌው የደህንነት ሰው መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በተለያዩ መምሪያዎች ውስጥ በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ ሀያ አመት ያህል የሰሩ መሆናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህም በመሆኑ በዘመነ ወያኔ የተሰሩ ብዙዎቹን ነገሮች በበቂ መረጃ ሊነግሩን ይችሉ ነበር፡፡ነገር ግን እንደተከታተልኩዋቸው ኀገሩን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተል ማናቸውም ዜጋ ከሚያውቀው የተለየ አዲስ ነገር አልሰጡንም፡፡ ስለሆነም ከዚህ በመነሳት መሞገት ቢቻልም ፋይዳው ሚዛን አይደፋም በማለት ማለፉን መርጬ ነበር፡፡

አቶ አያሌው አብዛኛው ገለጻቸው ማስረጃ አልባ በመሆኑ ከደህንነት ሰው ይልቅ ፖለቲከኛ ያስመስላቸዋል፡፡ ፖለቲካኛ ነገሮችን በጥቅል ይገልጻል፣ የመረጃ ሰው ግን ድርጊትን በግዜ በቦታ እያመሰካረ የአድራጊውን ማንነት በማስረጃ እያሳየ ይናገራል፡፡ ፖለቲከኛ አነጋገር ያሳምራል ብዙም ያወራል፣ የደህንት ሰው ብዙ ማውራት ለስህተት ይዳርጋል ይላል፡፡ ሌላም ሌላም፡፡

አቶ አያሌው ከህብር ራዲዮ ጋር ባደረጉት አንድ ሰአት በፈጀ ቃለ ምልልስ ስም ጠቅሰው ቦታና ግዜ አጣቅሰው የገለጹት የረባ ነገር የለም፡፡ ለምሳሌ ተማሪዎችን ለድርጅት አባልነትም ሆነ ለሰላይነት መመልመል፤የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባላትን ማጥመድ በማእከላዊ ምርመራ አረመናዊ ድርጊት እንደሚፈጸም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው የደህንነት ባለሙያ ገለጻም ትንተናም የማያሻው ጉዳይ ነው፡

ስለሆነም አቶ አያሌው በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ያውም ለሀያ አመት የሰሩ እንደመሆናቸው እርሳቸው በቀጥታ ወይንም በርሳቸው ትእዛዝ ሌሎች የፈጸሙትን ሊነግሩን ባይፈቅዱ በደህንነቱ መስሪያ ቤት የተፈጸሙ ድርጊቶችን ቀን ቦታና አድራጊዎችን በመግለጽ ቢነግሩን ይመረጣል፡ፕ/ር ዓሥራት በከርቸሌ ተመርዘው ነው የሞቱት፡፡ በአዲስ አበባ የኒቨርስቲ የአራተኛ አመት የህግ ተማሪ የነበረው ተሸመ ቢምረው ከጎጃም ከመጡ አርሶ አደሮች ጋር ታስሮ ከተለቀ በኋላ ታፍኖ ተወስዶ የደረሰበት አልታወቅም፤አቶ አሰፋ ማሩ በጠራራ ጸሀይ በአደባባይ ነው የተገደሉት፤ የሰኔ 1/97 ግድያ፤የህዳር 98 እልቂት ብለን የደህንነት ክፍሉ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸው ድርጊቶች መጥቀስ እንችላለን፡፡ አንድ ትልቅ የደህንት ሹም እነዚህንና መሰል ጉዳዮችን ስቴየትና ማብራሪያ ሳያበዛ በመረጃ እያስደገፈ በማስረጃ እያረጋገጠ ቢናገረ ነው ለመማማሪያም ለመተራረሚያም ለመጠያየቂያም የሚበጀው፡፡

ነገርን ነገር ያነሳዋል ሆኖብን እንጂ ለዚህ ጽሁፍ መነሻ ምክንያቴ ግን ይህ ከላይ የገለጽኩት አይደለም፤ የመረጃው ሰው ማስረጃ ሳያቀርቡ ግለሰብና ፓርቲ ሲወነጅሉ መስማቴ እንጂ፡፡ በተግባር የምናውቀውና የሂደቱ አካል የነበርንበት ጉዳይ ተጭምሮ ተቀንሶ ወይንም ሙሉ በሙሉ ተለውጦ በተለይ ደግሞ በመረጃ ሰው ሲገገርም ሆነ ሲጻፍ በዝምታ ማለፍ ከአድራጊው የበለጠ ጥፋተኛ ያደርጋል፡፡ ነገርግን የነበሩበትን ነገር ሙሉ ለሙሉ አውቃለሁ ማለት አይቻልምና በመረጃ ተደግፎ በማስረጃ ተረጋግጦ ቢቀርብ እንዴት ከውስጥ ሆኜ ይህን ሳላውቅ ብሎ ራስን ለመጠይቅ መለስ ብሎም ያሳለፉትን ሂደት ለመፈተሸ ያግዛል፣ ለመማሪያነትም ይጠቅማል፡፡ እንኳን የመረጃ ሰው የፕሮፓጋንዳ ሰራተኛ እንኳን አያሌ ሰዎች በሚያዳምጡት ራዲዮ ቀርቦ ሲናገር መረጃ እየጠቀሰ በማስረጃ እያረጋገጠ ቢሆን ነው ተአማኒነት ሊያገኝ የሚችለው፡፡

ይህን ካላሟላው የአቶ አያሌው ንግግር ጥቂት አብነቶችን በመጥቀስ ትክክል አለመሆናቸውን በማስረጃ ላሳይ፤ ጥያቄም ልጠይቃቸው፡፡ ስለ እውነት ለመነጋገር የግለሰቦች ወይንም የድርጅቶች ጠበቃ መሆን ሳያስፈልግ ነው፡፡ በመሆኑም አቶ አያሌው ስለ ልደቱ ስለተናገሩት ማስረጃ ስጠይቅ ልደቱን ንጹህ በማድረግ ወይንም ለእርሱ ለመከራከር እየዳዳኝ አይደለም፡ራሱን ለገደለ ሰው ምንኑ ይከራከሩለታል፡፡ ዓላማየ ትልቁ የደህንነት ሰው ስለሚነግሩን ነገር መረጃና ማስረጃ ማቅረብ የሙያቸው ግዴታ መሆኑን ለማስታወስ ነው፡፡ እንደውም የመስኩ ባለሙያዎች የደህንነት ሰው ንግግር አምስቱን ወርቃማ ጥቄዎች የሚመለስ መሆን አለበት ይላሉ፡፡

1-ኢዴፓን ያቋቋመው ወያኔ ነው፣ አቶ አያሌው ይህን ሲናገሩ እንዴት፣ በምን ሁኔታና፣ በእነማን እየታገዘ ወያኔ ኢዴፓን እንዳቋቋመው አልገለጹም፣ የደህንነት ሰው እንጂ የአሉባልታ ሰፈር ሰው ባለመሆናቸው መግለጽ የሙያቸው ግዴታ ነበር፡፡ ኢዴፓ በ1988 ዓ.ም ከመአህድ በተባረሩ ወጣቶች በ1992 ዓም የተመሰረተ በ1993 ዓም አንደኛ ጉባኤውን አካሂዶ አንቱ የተባሉ ኢትዮጵያውያንን ለማቀፍ የቻለ እስከ ምርጫ 97 በቁጥር አንድ ከሚጠቀሱ ፓርቲዎች አንዱ የነበረ ነው፡፡ በስድስት አመት ከሰራቸው ተግባራት አንድም በወያኔነት የሚያስፈርጅ ቀርቶ የሚያስጠረጥረው ነገር የለም፣ካስፈለገ አንዚህን በዝርዝር ማቅርብ ይቻላል፣መለስ ብሎ ጽሁፎችን በማገላበጥም መረዳት ይቻላል፡፡

አንድ ዌንም ሁለት ግለሰቦችን ወያኔ ማለትና ድርጅትን ወያኔ ማለት በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው፣ ጭራሽ ወያኔ የመሰረተው ማለት ደገሞ ከሁለቱም የባሰና የከፋ ነው፡፡ ማስረጃ ሳይቀርብ ያውም በደህንነት ባለስልጣን ሲነገር ደግሞ…፤

2-ዶ/ር ኃይሉን በወያኔነት መፈረጅ፤ ከአንድ የመረጃ ሰው ያውም በወያኔ መዋቅር ውስጥ ሀያ አመታት በሀላፊነት ከሰራ ሰው ይህን ስሰማ በእጅጉ አዘንኩ፡፡አቶ አያሌው ከመረጃ ሰውነት ወደ ፕረፓጋዲስትነት የተቀየሩ ሆነውም ታዩኝ፡፡ ለመሆኑ አቶ አያሌው ለዚህ አባባልዎ ማስረጃ ይቅር መረጃ ማቅረብ ይችሉ ይሆን! አዘንኩብዎት፡፡

ስለ ዶ/ር ኃይሉ ከሚታወቀው ትንሽ እንባቢን ላስታውስ፤በደርግ የመጨረሻው ሰአት በብሔራዊ ሸንጎ ሰብሰባ ላይ ፕሬዝዳንት መንግስቱን “እርስዎም ክኒኗን ይዋጧት” ያሉ ሰው ናቸው፡፡ በዚህ ንግግራቸው አቸፍቻፊው ሁሉ ዘመዶቹ አምቦ መድረሳቸውን አይቶ ተማምኖ ነው እንዲህ የተናገረው ሲላቸው፣ ፕሬዝዳንቱም ሊያስሯቸው አስበው በበጎ መካሪ ሰዎች እንደተዋቸው ብዙዎች ተናግረዋል ጽፈዋል፣ (የኮ/ል ፍስኃ ደስታን መጽኃፍ በማስረጃነት መጥቀስ ይቻላል፡፡) እንዲሁም ራሳቸው ፕሬዝዳንት መንግሥቱ፣ “ሀይሉ ደፈረኝ” ብለው ለጋዜጠኛ ገነት ነግረዋት ጽፋዋለች፡፡

በምርጫ 97 ማግስት ዶ/ር ኃይሉ በቅንጅት በታሰሩበት ግዜ ከትንሽ እስከ ትልቅ ወያኔዎች ከሀዲ እያሉ እንዴት ያደርጉዋቸው እንደነበረ አብረዋቸው በእስር የቆዩ ሰዎች ይመሰክራሉ፡፡ ነገርግን ይህ ሳይበግራቸው፣ የእድሜ መግፋት ሳያግዳቸው አንድነት እስከ ፈረሰበት ግዜ ድረስ በተቃውሞው ጎራ ነበሩ፡፡ ታዲያ እኚህ ሰው ዛሬ የወያኔ የደህንነት ባለሥልጣን ሆኖ ለሀያ አመት በሰራ ሰው አንደበት ያውም በራዲዮ ወያኔ ሲባሉ መስማት አያሳዝንም! በዘረኝነት በሽታ ያልተለከፈን፣ በጭፍን ድጋፍና ተቃውሞ የማያምንን ዜጋ ሁሉ የሚያበሳጭ ይመስለኛል፡፡ እርሳቸው ወያኔን ሲታገሉ እርሱ የወያኔ ባለሥልጣን ሆኖ ሲገድልና ሲያስር የነበረ ሰው እንዲህ ለመናገር መድፈሩ ለአድማጩ ያለውን ንቀት ነው የሚያሳየው፡፡

3-ሳንጠይቃቸው ራሳቸው እየመጡ መረጃ የሚሠጡን የተቀዋሚ ድርጅት መሪዎች ነበሩ፡፡ይህ አይሆንም ማለት አይቻልም፣ማስረጃ አልቀረበበትምና ነውም ብሎ መቀበል አይቻልም፡፡ ግን አቶ አያሌው ይህን ያሉት ከእውነታቸው ከሆነ የሰዎቹን ስም መግለጽ ለምን ገደዳቸው? መቼም እነዚህ ሰዎች ተቀዋሚ እየተባሉ እንዲኖሮ የሚፈልጉ አይመስለኝም፣ማስረጃ ከሌላቸው ደግሞ አንዲህ አይነት ጉዳይ ወሬ ለማሳመር አይነገርም፣ነበርኩበት ለሚሉት የኃላፊነት ደረጃ አይመጥንም፡፡

4-ከምርጫ 97 በኋላ ምን እንዳርግላችሁ ተብለው አንዳንዶቹ የኢዴፓ አመራሮች ወደ አውሮፓ ለመሄድ ችለዋል፡፡ አቶ አያሌው ይህን ሲናገሩ ልበ ሙሉ ሆነው ነው፡፡ ልበ ሙሉ ያደረጋቸው አሜሪካ መሄዳቸው ሳይሆን ያላቸው መረጃና ማስረጃ ቢሆን አንዴት መልካም ነበር፡፡ እዚህ ላይ ነገር አላበዛም አቶ አያሌው አስቲ አንድ ሰው ይጥቀሱ?

5-ልደቱ የወያኔ የወጣት ፎረም አባል ሆኖ ሲያገለግል የነበረ ነው፡፡ የትኛው ፎረም? በመቼ አመተ ምህረት?ከእነማን ጋር?

6-የትኛው እስረኛ ነው ቀበሌ ጽ/ቤት ታስሮ ስልክ ቀርቦለት የሚነጋገረው፤ ይህን ያሉት ልደቱን ነው፤ ልደቱ የታሰረባቸው ግዚያትና ቦታዎች በወቅቱ የተዘገቡ እሱም ሲፈታ በቃለ ምልልስ የገለጻቸው በመሆኑ ይታወቃሉ፡፡ ምን አልባት አቶ አያሌው የነገሩን ሚዲያውም ያልገለጸው እሱም ያልተናገረው ርሳቸው በሚያቸው የደረሱበት ከሆነ መቼ ? የትኛው ቀበሌ? በምን ምክንያት ? አንደነበረ እባከዎት በመረጃና ማስረጃ ይንገሩን፡፡

አድማጮች፣ ተመልካቾች አንባቢዎችም ዝም ብለን የሚሰጠንን የምንቀበል አንሁን፡፡ትክክለኛው እውነት ነጥሮ የሚወጣው ውሸቱና እውነቱ ሲፋጭ ነውና፡፡የወያኔን የደህንንት ሰዎች በጠኑም ቢሆን አውቃቸዋለሁ ጉልበት እንጂ እውቀት፣እብሪት እንጂ ክህሎት አላይባቸውም፣የመረጃ ስራ የአእምሮ ስራ አንደመሆኑ በአስተሳሰብ በልጦ መገኘት ቢሆንም በወያኔ ደህንነቶች ዘንድ ያለው ግን ለስልጣን ባበቃቸው ጠመንጃቸው ሁሉንም ነገር ማድረግ የመቻል ደካማነት ነው፡፡አቶ አያሌው ለመረጃና ማስረጃ ዋጋ አለመስጠታቸውና እንደ አፈተታቸው መናገራቸው ሀያ አመት የሳለፉት በዚህ መዋቅርና አሰራር ውስጥ በመሆኑ ተጽእኖው አርፎባቸው ይሆን! የመረጃ ሰው አስቦ የሚናገር ብቻ ሳይሆን እየተናገረም የሚያስብ ነው፡፡

The post የደህንነቱ ሰው በህብር ራዲዮ – በ ታመነ በአምላኩ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

“ጋንታይናው” ‹ጋትዬ› አሰፋ ጫቦ

$
0
0

እውቁ ፖለቲከኛና አንጋውፋ ምሁር አቶ አሰፋ ጫቦ አረፉ። አቶ አሰፋ በማራኪ ተናጋሪነታቸው እና አንደበተ ርቱዕነታቸው የሚታወሱ የሕግ ምሁር ነበሩ። ብዙውን እድሜያቸውን የጨረሱት በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና በእስር ቤት ውስጥ ነው። አሜሪካ ከገቡ በኋላ በ20 ግዛቶች  እየተዘዋወሩ ኖረዋል። በቅርቡ ባሳተሙት የ”ትዝታ ፈለግ” መጽሃፋቸው ለረጅም ግዜ በአንድ ቤት የተቀመጥቁት እስር ቤት ውስጥ ብቻ ነው ሲሉ አስነብበውናል። በአንድ ቤት የተቀመጥቁት እስር ቤት ውስጥ ብቻ ነው ሲሉ አስነብበውናል።

እኚህ ምሁር በደረሰባቸው ህመም ዳላስ-ቴክሳስ በሚገኝ ሆስፒታል ህክምና ሲክታተሉ ቆይተው በዛሬው እለት (እሁድ) ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

ጣይቱ የባህልና የትምህርት ማህከል አሰፋ ጫቦን እረፍት አስመልክቶ የሚከተለውን የሃዘን መግለጫ አውጥቷል።

አቶ አሰፋ ጫቦ ከአባቱ ከጫቦ ሣዴ ሃማ ያሬና ከእናቱ ከማቱኬ አጀን ከተራራ አናት ላይ ከሚገኝ ሜዳማ ቦታ ላይ ጨንቻ ከተማ ነው የተወለደው።ከጋሞ ሰንሰለት ተራራዋች አንዱ ጫፍ ላይ የሚገኝ ጠረጴዛ ነው ይላታል ጨንቻን ሲገልጣት ከ2-6ኛ ክፍል እዚያው ጨንቻ የተማረ ሲሆን በዘጠኝ ዓመቱ የጨንቻ ገብርዔል ዲያቆን በመሆንም አገልግሏል በድቁናው ባገኘው ካፒታልም ጥቂት የዶሮና የበግ ግልገል ገዝቶበታል ሐሙስ ሐሙስን እየጠበቀ ኤዞ ገበያ ዶሮና እንቁላል አየነገደ ይውል ነበር ከእነሱም ውስጥ ት/ቤት ድረስ እየተከተሉ ያስቸግሩት የዶሮና የበግ ግልገልም ነበረው እንደፈረንጆቹ pet መሆናቸው ነው። የ8ኛ ክፍል ትምህርቱን በሻሸመኔ በኃላ ታሪኩን ሲያውቅ ስሙን ካላስቀየርኩ ብሎ ከታገለበት ከአጼ ናኦድ ት/ቤት ከ39 ተማሪዎች አንዱ በመሆን ነበር የተከታተለው።

የተዋቀረበትን ዋልታና ካስማ ያየበት ቆይታው በጋሞ ውስጥ ካሉ 40 ከሚሆኑ ‹ካዎ›ች አንዱ በሆኑት በዘመዱ በቀኛዝማች ኢሌታሞ ኢቻ ቤት በኖረበት ወቅት ነበር።

ሲገልጻቸውም ‹በኢሌታሞና በሰዋች መሀከል የግንኙነት አጥር የለም።ወግ ሳያበዙ ለህዝብ አሳቢና ተቆርቋሪ ናቸው ነው› የሚላቸው የጋሞ ካዎ የሚፈራ ሳይሆን የሚከበር ነው ይለናል። ገና በልጅነቱ ለህዝብ በመስራት እርካታ ማግኘት እንደሚቻልም የተገነዘበው በጉሌታ-አንዱሮ ግብር ተቀባይ ተደርጎ በቀኛዝማች ኤሌታሞ ሲመደብ ነው ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከአዲስ አበባ ከኮከበ ጽባህ አቋርጦ ሲቪል አቪዬሺን ተቀጥሮ ባህር ዳር ሄደ። ‹ሀ› ብሎ የመጀመሪያውን ስራውንና የመጀመሪያ ልጁንም ያገኘው ጎጃም ነበር። ‹ጎጃሜ ተነቀለ› ብሎ ፖሊስና እርምጃው ላይ ጽፎ ጠፍቶ እስከወጣ ድረስ እዚው ነበር። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሕግ ት/ቤት LLB አግኝቶ የተመረቀ ሲሆን በዓለም አቀፍ የህግ ተማሪዋች ውድድር ከውጭ የምስክር ወረቀት ከንጉሱም የወርቅ ኦሜጋ ሰዓት ተሸልሟል። በ 1960 የህግ ተማሪ ሆኖ በአፍሪካ አዳራሽ የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር ስብሰባ ላይ ከመጮህ ጀምሮ ይህው እስከእልፈተ ሞቱ ድረስ ለአገርና ለወገን ዋይታውን አላቋረጠም ነበር ። በአጠቃላይ የአጥቢያ ፍ/ቤት ጸሐፊ፤የበጅሮንድ ጽ/ቤት ተላላኪና ጸሐፊ የአየር መርማሪ (meteorology) የህግ አማካሪ ሆኖ ሰርቷል።በፖለቲካው መስክ ከተማሪዎች ንቅናቄ ባሻገር የሁለት ድርጅቶች መስራችና መሪ ሲሆን ከ 1966-1967 የልጅ እንዳልካቸው አዲሱ ካቢኔና የደርግ አውራጃ አስተዳዳሪ ሆኖ ጋርዱላ ሄዶ ነበር። በጄኔራል መብራቱ ፍስሃ ታስሮ እስከተባረረ ድረስ የፖለቲካ ድርጅት መስራችና መሪ፤የአውራጃ አስተዳዳሪ የመንግሰትና የባለስልጣን አማካሪ፤የህዝብ ተከራካሪ በመሆን በለውጡ ውስጥ ሰርቶእል።

በኃላም በራሱ ከግቢ የመራቅ ጥያቄ አነሳሽነት ‹‹በችሎታው መጠን ሥራ ይሰጠው›› የሚለውን ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ የፈረመበትን ደብዳቤ ይዞ መገናኛ ሚኒስቴር ወረደ። ከዚያ ነው እንግዲህ በየካቲት 1971 ዓ.ም መጀመሪያ ወደ ደርግ ጽ/ቤት ታፍኖ ተወስዶ ከዚያም በማዕከላዊ ታስሮ ከ 10 ዓመት ከ 6 ወራት ከ 6 ቀናት በኃላ የተፈታው፤ ማዕከላዊ እስር ቤት የሰው ገበያ ነበር ብሎ ሲገልፀው በ10 ዓመት የእስር ዘመኔ ውስጥ ከ100ሺ በላይ ሰው አይቼበታለው ይለናል ካያቸውም ውስጥ በባህርይ፣ በቁመና፣ በአለባበስና በስነምግባራቸው ጥሩ አድርጎ በመጻህፉ ውስጥ ይገልጻቸዋል።እንደተፈታም የአስኮ ጫማ ሱቅ የነበረበት ፎቅ ላይ የጥብቅናና የንግድ አማካሪ ቢሮ በመክፈት ሙግቱን አስረዝሞ ገንዘብና ጊዜ ከማባከን ይልቅ አስቀድሞ በድርድርና ከፍ/ቤት ውጭ ለመጨረስ ያደረገው ጥረትም ከዚሁ ከራሱ ማንነት የመነጨ ነው። በሽግግር መንግስቱ የምክር ቤት አባል በመሆንም በ 1983 አርባ ምንጭ ሄዶ ነበር ሁሉም አልሆን ሲለው ያለውዴታ በግድ አሜሪካ በስደተኝነት መጥቶ መኖሩን ጀመረ።

በተፈጥሮው ሰው መጥላት የማይፈልገው አንጋፋው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ቀጥተኛው፣ብዕረኛው አቶ አሰፋ ጫቦ የ 73 ዓመት ባለዕድሜው የአራት ልጆች አባትና የዘጠኝ ልጆች አያት ነበር።

‹የትዝታ ፈለግ› በሚል ርዕስ ለንባብ ያበቃውን መጽሐፉን በምናነብበት ወቅት ብዙ ወደማናቃቸው ጊዜያትና ግለሰቦች ከመውሰዱም ሌላ የአጻጻፍ ውበቱ እጅግ ያስደንቃል የባህሪይ አቀራረፅ ችሎታውና የአካባቢ ስዕላዊ መግለጫው ያረካል

‹‹ነፍጠኛ›› ማለት አማራ ብቻ ነው ማለት እምነት እንጂ እውነት አንዳልሆነና ‹‹ነፍጠኛ›› በሚል የሚበጠብጠንን ጥያቄ ለመመለስ ናችሁ የተባልነውን ሳይሆን ውስጣችን ገብተን ሆነን ያለነውን እንድናስተውል ይጎተጉተናል።

ዋታካዳ እንደሚጠሩት ‹‹ጋንታይናው›› ‹ጋትዬ› አሰፋ ጫቦ ዛሬ አብዛኛው እየፈራ እየሸሸ ምክንያቱን በሚደረደርበት ወቅት እሱ ምን አቅብጦኝ ከደርግ ጋር ገጠምኩ; ብሎ አያውቅም አምኖ እንጂ ምናምን ፍለጋ ወይም ሰው ገፍቶት እንዳልገባ በግልጽ አስቀምጦልናል እንዲያውም ‹በመሸ በጠባ ቁጥር በጥሼ የምቀጥለው ማተብ› የለኝም ይል ነበር

በንባብ የዳበረ የበሰለ መሆኑን ከማሳየቱም ሌላ ስለ አሜሪካ መምጣትና መኖር ያካፈለው ምክር በቀላሉ የሚታይ አይደልም ስለስደቱ ዓለም ችግርና ውጥንቅጥ ሲጽፍም ስደተኛው በሃብት ድህነትና በአእምሮ ድህነት መሃከል ያለው ልዩነት የጠፋበት መምሰሉን ፍንትው አድርጎ አቅርቧል በአጠቃላይ ጆሮ ጠገብነት ማወቅን አለመተካቱን ያሳውቀናል

ጀግና ፍለጋ ጦር ሜዳ መሪዋች አምባ የፖለቲካ ሰዋች አምባ እንሄዳለን። ሲገኝ አገር ያውቀዋል ፀሃይ ይሞቀዋል ያልታወቁ በየቤቱ የታጨቁ ተራሰው የሆኑ ያልተሰጣቸውን በመፈጸም የጀግኑ አሉ ይላል

ጋሞ ይላል፤ ጋሞ ግብር ገበረ እንጂ ሥርዓቱን አልገበረም በማለት ጥፋቱን ስህተቱን በማመን መቀበልና ባደባባይ ይቅርታ መጠየቅ የጋሞነት ገላጭ አብሮ የተወለደ የውሰጥ ባህርይ መሆኑን በመተንተን ለየት ስላለው የአገርና የህዝብ አስተዳደር ሥርዓት ሲያጫውተን አንዳንዶቻችን በአገራችን ውስጥ ይህ መኖሩን ባለማወቃችን እንቆጫለን ወደዛሬያችን ለማምጣት በምኞት እንጋልባለን

ሌላው የጋሽ አሰፋ ትልቅነቱ እንደአንዳንዶቹ ፀሃፊዋች በራሱ አራት ነጥብ ዘግቶ እመኑልኝ ሳይለን ያየሁትና የኖርኩት እንጂ ያጠናሁት አይደልም ይላል በትዝታዋቹ ውስጥ እየሾለከ የሁላችንንም ትዝታ የቆሰቆሰውን ያህል ዛሬ በአገራችን ስለተንሰራፋው ሥርዓትም በማዘን እየገለጸ ወደተሻለ እንድንጓዝ ይማፀነናል።በእስራት ብዛት የህዝብ ነጻነት ታፍኖ የቀረበት ዘመንም አገርም አለመኖሩን በማስረገጥ የጋራ ቤታችን የሚፈለገውን መጠነኛ ጥገና በማካሄድ ፈንታ መናድ የመረጡትን አውግዞአቸዋል።አገራቸውን ባለማወቅ ወይም ለማወቅ ባለመፈለግ ነቀዝ የበላው ቤት እንድትሆን ስለማድረጋቸው በመውቀስ ወደምትፈለገዋ ከስህተቷ ልምድ የቀሰመች አዲሲቷ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጽያን እንድንገነባ ይጣራል።

አብርሃም ሊንከን እንዳለውና ጋሽ አሰፋም በመጽሃፉ ላይ እንደጠቀሰው ‹‹ማንንም ያለቂም እንድንመለከት፣ ሁሉንም በልግስና እንድናቅፍ፣ በሃቅ ላይ እንድንጸና፣ አምላክም ይህንን ሐቅ እንድናይ እንዲረዳን እንማጸን።

ጋሽ አሰፋ ጫቦ ያመነበትን እንደተናገረና እንደሰራ ሃገርና ወገኑን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንደደከመ አለፈ። ይህን ታላቅ ሰው በህይወቱ እያለ በጣይቱ የትምህርትና የባህል ማህከል ጋብዘን በማስተናገዳችን ክብር ተሰምቶናል ። ብዕረⶉቻችን ጀግኖቻችን ጠበብቶቻችን ሳያልፉ ማክበር ግዴታችን መሆኑን እናምናለን።

(EMF)

የሀገራችን “ልሂቃኖች” ድምፅ  ለምን ጠፋ ? (ኤድመን ተስፋዬ)

$
0
0

 

እውቁ ኢኮኖሚስት ዳግላስ ኖርዝ የአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናም ሆነ ቀውስ ከሀገሪቱ ተቋማዊ ጥንካሬ ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ በመግለፅ አብዛኛዎቹ ደሀ ሀገራት ድህነት መንስኤ ከገነቡት ተቋም ጥንካሬ ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ ይተነትናል፡፡ እንደ ኖርዝ ሁሉ የአሜሪከሳው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጋናን በጎበኙበት ወቅት አፍሪካ የሚያስፈልጋትም ሆነ ያጣችው ጠንካራ ግለሰብ ሳይሆን ጠንካራ ተቋም ስለመሆኑ በመግለፅ ለአፍሪካ  ሀገራት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግር መፍትሄው ጠንካራ ተቋም  መገንባት ስለመሆኑ አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል፡፡ በምንገኝበት የሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የተቋማት ሚና ለሀገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግር መፍትሄ ከመሆናቸው ጋር በቀጥተኛ ሁኔታ ተገናኝ በሆነ ሁኔታ የሚታይ ሲሆን፣ይህ የተቋማት ሚና  ስኬት ደግሞ ተቋሙን በሚመሩት እና በሚያንቀሳቅሱት ግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡   አማርታሲያን ሴን ለምርታማነት ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱ የሆነው የሰው ሀይል ከሌሎቹ በተለየ ለኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ሚና እንዲኖረው ያደረገው ከሰው ልጅ የማሰብ እና ከመራመር ፀጋው ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ ይገልፃል፡፡ ይህ የሴን ንድፈ ሀሳብ ተለጥጦ ሲታይ የሰው ሀይል ለምርታማነት ምክንያት ነው ሲባል ጉልበቱ ብቻ ሳይሆን በዋነኛነት እውቀቱ ነው እንደማለት ነው፡፡

የልሂቃኖችን እውቀት እንደ ግብአት በመጠቀም ህዝባቸውን ከማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በማውጣት ኢኮኖሚያቸውን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት ከቻሉ ሀገራት ውስጥ ጀርመን አንዷ ስትሆን፣ጀርመን በሰው በላው ሂትለር በተማገደችበት ጦርነት ማክተም በሁአል አንድ የነበረው ሉአላዊ ግዛቷ ለሁለት ከመከፈሉም ባለፈ በሂትለር መሪነት በአራቱም የአለም ማእዘን  በተማገደችበት ጦርነት የተነሳ  ለኢኮኖሚያዊ ቀውስ መጋለጧ ከጦርነቱ በህይወት የተረፈውን ዜጋዋን ለከባድ የኑሮ ፈተና እንዲጋለጥ መንስኤ ሆኖታል፡፡ ለ ሁለት የተከፈለው ሉአላዊ ግዛቷ አንድ በመሆን ኢኮኖሚዋን አሁን ላይ ከአውሮፓ ሀገራት ግዙፉ ኢኮኖሚ እንዲሆን ካስቻሉት ውስጥ በዋነኛነት የሚጠቀሱት የሀገሪቷ ልሂቃኖች ስለመሆናቸው በጉዳዩ ዙሪያ ጥናት ያደረጉ ባለሞያዎች የሚገልፁት ጉዳይ ነው፡፡

ፕሮፌሰር በህሩ ዘውዴ የኢትዮጲያ ልሂቃን ታሪክ ጅማሮው ከአድዋው ድል በሁአላ እስከ ዳግማዊው የጣሊያን ወረራ ባሉት አራት አስር አመታት መሆኑን በመጥቀስ በዚህ ወቅት የነበሩትን ልሂቃኖች የመጀመሪያዎቹ የሀገራችን ልሂቃኖች ይሏቸዋል፣ እ.ኤ.አ ከ 1941 እስከ 1971 ድረስ ያሉትን በሀገራችን የልሂቃን ታሪክ ሁለተኛው ትውልድ ስለመሆናቸው በመጥቀስ እ.ኤ.አ  ከ1971 እስከ አሁን ድረስ ያሉትን ሶስተኛው ትውልድ ስለመሆናቸው በጥናቶቻቸው ይገልፃሉ፡፡ ፕሮፌሰር በህሩ ዘውዴ ከአድዋው ድል በሁአላ እስከ ዳግማዊው የጣሊያን ወረራ ባሉት አራት አስር አመታት ግዜ ውስጥ የነበሩትን በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያ የሆኑትን ልሂቃን የነበሩበት ግዜ የአድዋ ድል ከፈጠረው መነቃቃት፣በዛ ያሉ ኢትዮጲያውያን በአውሮፓ ዘመናዊ ትምህርት ተምረው ወደ ሀገራቸው ከመመለሳቸው፣በዛ ያሉት ልሂቃን የጃፓንን እድገት እንደ ሞዴል ከመውሰዳቸው እና ለሀገራቸው እድገት ምን አይነት መንገድ መከተል ይገባናል በሚሉ ክርክሮች የተሞላ መሆኑ ግዜውን የተለየ እንዲሆን ያደረገው ምክንያት ስለመሆኑ ይገልፃሉ፡፡ አቶ አሰፋ ጫቦ በበኩላቸው መሬት ላራሹ በሚል መሪ ቃል ንጉሱን ከስልጣን ያወረደውን እና ስልጣኑን በሚሊተሪው የተነጠቀውን ትውልድ በአንድ በኩል  መሬት ላራሹ የሚለውን መርህ የተገበረውን ደርግ የነበረበትን የልሂቃን እጥረት ቀረብ ብሎ ከሞሙላት ይልቅ የሶሻሊስትም  ወኪል እኔ ነኝ  በሚል እሰጣ ገባ በሌላ በኩል ባልተሰጠው ውክልና እራሱን የአንድ ብሄር ወኪል በማድረግ ወደ አላስፈላጊ እልቂት የገባ ስለመሆኑ ይጠቅሳሉ፡፡ ፕሮፈሰር መሳይ ከበደ በበኩላቸው ፕሮፈሰር ባህሩ ዘውዴ ከጊዜ ቀውደም ተከተል አኩአያ በሁለተኛ ድፍ ላይ ያስቀመጡትን የልሂቃን ትውልድ ለሀገሩ ያለው ፍቅር ምሳሌ የሚሆን ስለመሆኑ በመጥቀስ የትውልዱ ስህተት የኢትዮጲያን ችግር በምእራቡ አስተምህሮት  ብቻ ለመፍታት መሞከሩ ስለመሆኑ ይጠቅሳሉ፡፡ አሁን ላይ የሚገኙት የሀገሪቷ ልሂቃኖች ለሀገራቸው  ምን አይነት የልሂቅነት አስተዋእፆ እያደረጉ ነው  የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ ያለው ምልከታ በአብዛኛው መነሻው የልሂቃኖቹን እና የፖርቲውን ግንኙነት እንዲሁም ፖርቲው በየዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ ነፃነትን በተመለከተ ከወረቀት ባለፈ በነባራዊነት የሚከተለውን ፖሊሲ ማእከል ያደረገ ነው፡፡

በሀገሪቷ በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚገኙ ልሂቃኖች ኢህአዴግ በሀገሪቷ አመጣውት የሚለውን የኢኮኖሚ ለውጥ በተመለከተ እውቀታቸውን ማእከል በማድረግ የመሞገታቸውም ሆነ ማረጋገጫ የመስጠት እና እውቀትን ማእከል ያደረገ የልሂቅ ክርክር የማድረግ የሞያ ሀላፊነታቸውን ከየትኛውም ዘመን በተለየ የተቀዛቀዘበት ዘመን ስለመሆኑ ጉዳዩን ያጠኑ ወገኖች ስምምነት ቢኖራቸው መንስኤውን በተመለከተ ግን  በአንድ በኩል የፖርቲውን አገዛዝ የሚኮንኑ ሲኖሩ በሌላ በኩል ደግሞ የልሂቃኖቹን አድርባይነት በምክንያትነት የሚያቀርቡ አሉ፡፡

 

ገዢው ፖርቲ የሚለፍፈውን  ማረጋገጫ የሚሰጥለትን እና አመጣውት የሚለውን ልማት እንዲያስተጋባለት በአስተማሪነትም ሆነ በአመራርነት በየዩኒቨርስቲው ያስቀመጠውን ልሂቅ ድጋፍ እና እውቅና እየሰጠ ፖርቲውን የሚሞግቱትን መኮነኑ እና ፀረ ልማት አድርጎ መበየኑን እንዲሁም በየዩኒቨርስቲዎቹ የአካሚክ ነፃነት አለመኖሩን በምክንያትነት በማቅረብ እንደ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደን ያሉ  ሙሁራኖች ልሂቁ በሀገሪቷ ጉዳዮች ላይ ያለው ሚና እምብዛም  እንዲሆን ለመሆኑ ተጠያቂው   ገዢው ፖርቲ ስለመሆኑ ይናገራሉ ፡፡  እንደ ፕሮፌሰር አለማየው ያሉ ምሁራን በበኩላቸው ልሂቁ በሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ሚናው ለመቀዝቀዙ   ገዢው ፖርቲን ተጠያቂ ከሚያደርጉት ምክንያቶች እኩል  የልሂቃኖቹ  አድርባይነት በሀገሪቷ ጉዳይ ላይ እውቀትን ማእከል ያደረገ ሚናቸውን እንዳይወጡ እንዳደረጋቸው ይተነትናሉ፡፡

ከላይ በተጠቀሰው የፕሮፌሰር መሳይ ከበደ ሙግት የሚስማሙ ወገኖች በአንጋፋዎቹ እና በአደባባይ ሙሁራኖቹ ዶክተር ዳኛቸው ዘውዴ እና ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ላይ የደረሰውን ሁነት በማስረጃነት በማንሳት የሀገራችን ልሂቃኖች የሀገራቸውን ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሁነት ከአካዳሚካዊ እይታ አኩአያ በነፃነት እና በገለልተኝነት የመፈተሻቸው ነገር ከየትኛውም ጊዜ በላይ አሁን ላይ ለተቀዛቀዘበት ምክንያት ገዢውን ፓርቲ ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡

የልሂቅነት ሃላፊነት እውቀትን ለሀገራዊ ችግር መፍቻ መሳሪያነት ማዋል ስለመሆኑ የጀርመን ልሂቃንን ተሞክሮ በምሳሌነት በመጥቀስ የሚሞግቱት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዢው ፖርቲ ከአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመር ወጣ ያለ ልሂቅ ማየት ያለመፈለጉ ነገር እንዳለ ሆኖ የልሂቅነት እዳው እና ሀላፊነቱ እንደዚህ አይነት ግትር መንንግስታዊ ስርአትን በእውቀት መሞገት ስለመሆኑ በመጥቀስ ከኢህአዴግ ግትርነት እኩል ልሂቁ ከሀገሩ ችግር ይልቅ ለግል ጥቅሙ ቅድሚያ መስጠቱ ባልተለመደ መልኩ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሆን ብሎ እንዲያንቀላፋ እንዳደረገው ሲገልፁ በ2008 የፌደራል ኦዲተር መስሪያ ቤት ከፍተኛ የሆነ ሙስና ተንሰራፍቷል ብሎ ከጠቀሳቸው የሀገሪቷ ተቋሟች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ስለመሆናቸው መግለፁን   በአስረጂነት በመግለፅ ነው፡፡ በእኔ እምነት ሃገራችን እስከመቼ  ድረስ ደፋር ካድሬዎች ፈሪ ልሂቃኖችን የሚያስተዳድሩበት ሃገር ሆና ትቀጥላለች የሚለው ጥያቄ ደግሞ የሀገራችንን ልሂቃኖች የቁም ሞት አመላካች ከመሆን ባለፈ አንገብጋቢው ጥያቄ ይመስለኛል።

 

 

The post የሀገራችን “ልሂቃኖች” ድምፅ  ለምን ጠፋ ? (ኤድመን ተስፋዬ) appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.

Viewing all 3686 articles
Browse latest View live